Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.95K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-06-26 13:33:20 Psychologist says:
የሥነ ልቦና ባለሙያ እንዲህ ይላል:


  1. When a person sleeps for a long time, sometimes their sadness is deep. He thinks a lot. There's a lot of things bothering this person so he prefer to just put everything to sleep.
አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ ሲተኛ አንዳንድ ጊዜ ሀዘኑ ጥልቅ ነው.  ብዙ ያስባል።  ይህን ሰው የሚያስጨንቀው ብዙ ነገር ስላለ ሁሉንም ነገር ብቻ መተኛት ይመርጣል።

  2. When he eats a lot of food, sometimes, it means he is stressed. Sometimes it's a lot of fun. You can see the way he eats But in his eyes he is stressed, sad or happy. When he invites you to join him on a food trip, go with him.
ብዙ ምግብ ሲመገብ, አንዳንድ ጊዜ, እሱ ውጥረት አለበት ማለት ነው.  አንዳንድ ጊዜ በጣም አስደሳች ነው.  የሚበላበትን መንገድ ማየት ትችላለህ ነገር ግን በዓይኑ ውስጥ ውጥረት, ሀዘን ወይም ደስተኛ ነው.  በምግብ ጉዞ ላይ እንድትቀላቀል ሲጋብዝህ አብረህ ሂድ።


  3. When he gets angry even for small things, it means he wants to be nurtured, give him attention, understand and he wants people to love him.
ለትንንሽ ነገሮች እንኳን ሲናደድ, ለመንከባከብ, ትኩረት ይስጡት, መረዳት እና ሰዎች እንዲወዱት ይፈልጋል ማለት ነው.


  4. When he laughs loudly, sometimes it means that he is deeply sad. He just passes the sadness with laughter.

  "Be observant of the people you talk to or socialize with. Always say hello to your loved ones."
ጮክ ብሎ ሲስቅ, አንዳንድ ጊዜ በጣም አዝኗል ማለት ነው በቃ ሀዘኑን በሳቅ ያልፋል።

  "የምትወያያቸው ወይም የምታውቃቸውን ሰዎች ታዛቢ ሁን። ሁልጊዜ ለሚወዷቸው ሰዎች ሰላም ይበሉ።"

አሚር ሰይድ
2.7K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 15:35:19
ከግብፅ ዋጋ ከተማ ከካይሮ ዘጠና ሶስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በታንታ ከተማ የቁርኣን ሒፍዝ ማዕከል ውስጥ የሚማሩ ሁለት ወጣቶች ናቸው። አንደኛው ዓይነ ስውር ሌላኛው ደግሞ እግሮቹ ሰውነቱን መሸከም ያቃታቸው መራመድ የተሳነው ሽባ ወጣት ነው።

ዓይኑን የታወረው መራመድ የማይችለውን ወንድም ከቤቱ አንስቶ በትከሻው አቅፎ በአንድ እጁ ግርግዳ እየተደገፈ ሒፍዝ ማዕከሉ አድርሶ ደረጃውን እየረገጠ ሶስተኛ ፎቅ ወዳለው ክፍሉ ያስገባዋል።

"ለምን እንደዚህ ታደርጋለህ" ብለው ሲጠይቁት
"እርሱ የምመለከትበት ዓይኖቼ፣ እኔም የእሱ መራመጃ እግሮቹ ነኝ" በማለት ይመልስላቸዋል።

ጌታዬ ሆይ!
     የምንደገፍባቸው መልካም ወንድሞችን ወፍቀን
2.7K views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 15:34:29
በመኪና የተገጨችው ላም ከመሬት ወድቃ ታቃስታለች። ሰውነቷ ተልጧል። እግሯም ተሰብሯል። መነሳት አቅቷት ተዘርራለች።

መኪናው የደረሰበትን ጉዳት ለማየት ሰዎቹ ዙርያውን ከበው ቆመዋል። ላሟ ብቻዋን ናት። ማንም ወደ እሷ ዞሮ ያያት፣ ጉዳቷንም ከቁብ የቆጠረ አልነበረም። እሷ የተሰማትን ህመምና ስቃይ መኪናው አልተሰማውም። ሰዎቹ የከበቡት ግን መኪናውን ነበር።

ላሟ የሰው ልጅን ጭካኔ በገፅታዋ በኩል ትነግረናለች።
የማወራችሁ ስለ ህሊና ነው
2.1K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-24 15:31:55 ባል ወደ ቤት ሲገባ ሚስቱ የአልጋውን ጫፍ ተደግፋ ተንሰቅስቃ እያነባች አገኛት። ደነገጠ ስታለቅስ ሲያያት ሆዱ ተላወሰ። ያፈቅራት ነበርና ሐዘኗ አሳዘነው። አቅፎ ደግፎ ግንባሯን እየሳመ ለምን እንደምታለቅስ ጠየቀ።
"ከቤታችን ፊት ለፊት የሚገኘው ዛፍ ላይ ያሉት ወፎች ዘወትር ልብሴን ስቀይር ፀጉሬን ያዩብኛል። ይህም አላህን ማመፅ እንዳይሆንብኝ ብዬ እፈራለሁ ለዚህ ነው የማለቅሰው" ብላ መለሰችለት።



   ባል በንጽሕናዋና አላህን በመፍራቷ ተደንቆ በዓይኖቿ መካከል ሳማትና መጥረቢያውን አውጥቶ ከቤታቸው ደጃፍ ላይ የበቀለውን ዛፍ ቆረጠ።

ከሳምንቱ መጨረሻ በአንደኛው ቀን ስራ አድክሞት ያለ ወትሮው ወደቤቱ አቀና። ሌላ ጊዜ ከሚገባበት ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ቤት ተመለሰ። በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሚስቱ በሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ተኝታ አገኛት። አልጋው ላይ እሱ የገዛውን አንሶላ ከሌላ ወንድ ጋር ለብሳ መርፌና ክር ሆና ተመለከታት።

የሚያስፈልገውን እቃ ሻንጣው ውስጥ ሸክፎ ምንም ሳይናገር የትውልድ ቀየውን ለቆ ወጣ።

   ራቅ ወዳለ ሥፍራ ተጓዘ። መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳለ ከአንድ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከተ። ለምን እንደተሰበሰቡ ሲጠይቃቸው የንጉሱ ግምጃ ቤት ተዘርፎ ሌባው አለመገኘቱን ነገሩት።

በዚህ መሐል በእግሮቹ ጣት ጫፍ በቀስታ የሚራመድ ሰው ተመለከተ። ስለማንነቱም ጠየቀ "የከተማው ሸይኽ ነው ጉንዳን ረግጦ አላህ ዘንድ እንዳይጠየቅ በዝግታ ይጓዛል ከአላህ ፍራቻ ብዛት የጉንዳኖችን ህይወት ላለመቅጠፍ በመስጋት በቀስታ ይራመዳል" ብለው መለሱለት።

ወደ ንጉሡ ውሰዱኝ አለ። ወሰዱት። ለንጉሱም የአንተን ግምጃ ቤት የዘረፈው በጣቶቹ የሚራመደው ሸይኽ ነው። እሱ ሆኖ ካልተገኘ ፍርዴ ሞት ይሁን አለ። ንጉሱ ተገረመ በተቅዋው የሚታወቀው ሸይኽ እንዴት ሊዘርፈኝ ይችላል ሲል ራሱን ጠየቀ።

ወታደሮቹ ሸይኹን አምጥተው ከንጉሱ ፊት አቀረቡት። ምርመራው ተጀመረ ሸይኹ መስረቁን አምኖ ተቀበለ። መዝረፉም ተረጋገጠ።

ንጉሱም ወደ ሰውየው ዞሮ ሌባው እሱ መሆኑን እንዴት አወቅክ ሲል ጠየቀው
ሰውየውም፡-
    "አላህን እንፈራለን ብለው ራሳቸውን የሚያጋንኑ ሰዎችን ከተመለከትክ ወንጀላቸውን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን እወቁ" ሲል መለሰለትና በሩን ከፍቶ ከቤተ መንግስቱ ግቢ ወጣ።

የአመለካከት ሊቅ ነን የሚሉ የተቅዋቸውን ጥግ ለማሳየት የሚሮጡ ሼኾችን ማክበር ብቻም ሳይሆን መጠንቀቁ አይከፋም በጠላት ተጠልፈው ኢስላምን ለማጥፋት የሚኳትኑ መኖራቸውንም እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ።

ዲነኛነን አላህን ፈሪ ነን ካሉት ለብሰዉ ካየናቸዉ  ይልቅ እነሱን መመዘን በልብሳቸዉ ሳይሆን በአመለካከታቸዉ በቤት ባህሪያቸዉ ሳይሆን በትምህርት ቤት ባህሪያቸዉ ቢታዩ ባይ ነኝ፡፡
2.1K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 15:31:18 የጁሙአ ስጦታ 2


#ቢስሚከ_ነህያ_አል_ወዱድ



በ #ዉድ እና #ሁብ  ያለው ልዪነት ምንድነው
ምን ያክልስ ከአሏህ ስሞች ጋር እየኖርን ነው??!!!
وَذِكۡرَىٰ لِلۡمُؤۡمِنِینَ

https://t.me/+-zHkXQeSZdc4MjY0
2.4K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-22 15:31:13 የጁሙአ ስጦታ

#ቢስሚከ_ነህያ አልገፉር


በ #ገፋር #ገፊር #ጋፊር ያለው ልዪነት ምንድነው
ምን ያክልስ ከአሏህ ስሞች ጋር እየኖርን ነው??!!!
https://t.me/+-zHkXQeSZdc4MjY0
2.3K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-14 13:33:43
" ገንዘብ በመሞቻዬ ሰአት ላይ አንድ ቀን ወይም አንድ ሰአት መግዛት መጨመር አቅም እንደሌለው ስረዳ ገንዘብ ሐብት ማለት ምንም እንዳልሆነ ለመረዳት ችያለሁ"

ማይክ ታይሰን አለም አቀፍ ከባድ ሚዛን ተዋቂ ቦክሰኛ ከተናገረው
612 views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 06:23:52 ለአንዲት ሴት በተለይ “ቆንጆ ሴት” ነን ብለን ለምናስብ ሴቶች ፣ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤት የሚሆንብን የራሳችን ቁንጅና ነው፡፡ የራሳችን ቆዳ የራሳችን እስር ቤት ነው፡፡
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  ‘ሴትነት እና ቁንጅና’ የሚባል እስር ቤት ፍርግርጋችንን እያስዋብን ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል፡፡ ሁሉም እስር ሰንሰለቱ ፈጦ አይታይም….. እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ለራሱ ጭምር አይታይም፡፡ ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት “የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም፡፡ ስለዚህ የእነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሯዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከሕፃንነቷ  ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል ”
”እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነጽሑፉ፣ በፊለሙ አእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል፡፡ ከመራመዷ በላይ የአረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኖራልች፡፡ ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኙአት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው፣ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት፡፡ እግራቸውን ከለሰለሰ በኃላ፣ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡
እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መሥራት ነው፡፡ ብዙ የፋሽን እና ዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ ’ዘመናዊ’ ሴቶች፣ እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽ እና እጃቸው እንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡ በልስላሴ ሳይሆን በንጽሕናና ራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማን ናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?! ለብዙኃኑ ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ ሀገርን ያቆመ ሳይሆን፣ ሴትነትን የገፋ መስሎ ነው የሚታያቸው፡፡ ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ ገጣሚውም መግጠመ የማይወደው፡፡ ድንጋይ ፈልፍሎ እና እምነበረድ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት ሴት ሐውልት የሚያቆመውን ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው፣ በሥራ የጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሴት በሆነበት አገር፣ ሴቶች እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀምጡ በማድረግ፣ ለውጥ ጠብ አይልም፤ እንዲሰሩ….. ማደፋፈር….እጅ ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት፡፡
                                                                                                                                                                                            
ከእለታት ግማሽ ቀን; ገጽ 182-183
1.7K views03:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 14:52:03 በፈረንጆቹ በ1950ዎቹና በ1960ዎቹ አካባቢ የሴት ፍላጎት፣ መብትና ነፃነት አይደለም ሊከበር ቀርቶ አልታሰበም ነበር፡፡ ሴት ልጅ ያገባች ከሆነ የባሏ አገልጋይ፤ ለትዳር ካልደረሰች ደግሞ የእናቷ ረዳት፤  ወግ ሳይደርሳትና ዕድል ሳይገጥማት ሳታገባ ከቆየች ወይም ፈት ከሆነች ደግሞ በማህበረሰቡ የስድብ ናዳ ይወርድባታል፣ ትናቃለች፣ ትገለላች፡፡ ሴት ሆኖ መፈጠር ምን ያህል ከባድ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡ በአሜሪካ እንኳን እ.ኤ.አ. በ1950 ዓ.ም. የነበረው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀውን የኑሮ በዘዴ መማሪያ መፅሐፍ (Home Economics text book) ብናይ ያገባች ሴት የባሏን ፍላጎት እንዴት ማሟላት እንዳለባት የሚያስተምርና የሚተነትን ነበር፡፡ ሴት ግዴታዋና ሃላፊነቷ የበዛ ነገር ግን መብትና ነጻነቷ ያነሰ፤ ምንም ምርጫ ያልነበራት እንደነበረች እናቶቻችንን ማየት በቂ ነው፡፡

ያም ሆነ ይህ በዘመናችን ያለችው ሴት በእናቶቻችን ዘመን ከነበሩት ሴት በብዙ መልኩ ትለያለች፡፡ ትናንት ፍላጎቷ የማይከበርላት፤ ዛሬ በአንድም በሌላም መንገድ ፍላጎቷ ይከበርላት ዘንድ አቅምና ጊዜ አግኝታለች፡፡ የዘመናችን አንገብጋቢውና አሳሳቢው ጉዳይ ግን ሴቶቹ ራሳችን የምንፈልገውን ነገር አለማወቃችን ነው፡፡ ራሳችንን አለማወቃችን የወንዶች ብያኔ ተጠቂ እንድንሆን አድርጎናል፡፡ ለጉብዝናችን ወይም ለቁንጅናችን የምስክር ወረቀት የምናገኘው ከወንዶቹ ነው፡፡ በዛም አለ በዚህ የወንዶች ስነልቦና ተጠቂ ሆነናል፡፡ በኢኮኖሚ ራሳችንን እየቻልን ብንመጣም በአስተሳሰብ ግን አሁንም የወንዶች ጥገኛ ነን፡፡ ራሳችንን በምግብ ብቻ ሳይሆን በሃሳብም ካልቻልን ከወንዶች ጭቆና አንተርፍም፡፡

መቼስ ሴትን እንደ እንደስነልቦና ምሁሩ ሲግመንድ ፍሮይድ ያጠናት የለም፡፡ ሰውየው ሴት ልጅ ገና ከልጅነቷ ጀምሮ ምን ዓይነት አስተሳሰብና ባህሪ ሊኖራት እንደሚችል፤ እንዲሁም ትክክለኛ ፍላጎቷ ምን እንደሆነ ለማወቅ የተመራመረ ነው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹ሴት የምትፈልገው ምንድነው? What do women want›› በሚለው ጥያቄው የሚታወቀው፡፡

ሴት በሴት መቀናናት ያለ ነው፡፡ የማታስቀናም የማትቀናም ሴት የለችም፡፡ ሴት በወንድ ስትቀና ግን ሊያስገርም ይችላል፡፡ ፍሮይድ ይሄን በተመለከተ አንድ ጥናት ነበረዉ፡፡ ይሄ ጥናት ሴት ገና ከአፍላ እድሜዋ ጀምሮ አጎጠጎጤዎች ስታወጣ፣ የመራቢያ አካሏ እየዳበረ ሲመጣ፣ ለአቅመ ሔዋን ስትደርስና እንደ ወንድ አለመሆኗን ስታውቅ በወንዱ መቅናት ትጀምራለች ይለናል፡፡ መቅናት ከሴት ተፈጥሮ ጋር የተዋሃደ ይመስላል፡፡ ይሄ የስነልቦና ተመራማሪ ስለሴቶች ባህሪ ለማወቅ ብዙ ጥናቶችን ቢያከናውንም ሴቶች ግን እንቆቅልሽ እንደሆኑበት ነው ህይወቱ ያለፈው፡፡ የሚገርመው ሴት ልጅ አይደለም ለወንዱ ለገዛ ራሷ ግራ አጋቢ ፍጥረት መሆኗ ነው፡፡ ኤቭሊን ሌት (Evelyn Leite) የተባለች ታዋቂ የስነልቦና አማካሪ “Women” በተባለ መፅሐፏ ‹‹ፍሮይድ -- ሴት ምንድነው የምትፈልገው? -- የሚለው ጥያቄው ወንዱን ብቻ ሳይሆን ሴቷ ራሷ መልስ ያጣችለት ነው፡፡ (Freud’s question – What do women want – frustrates men, It also frustrates women)›› በማለት ትገልጻለች፡፡

ብዙዎቻችን ሴቶች ባላችን ምን እንዲያደርግልን ከመፈለጋችን በፊት እኛ የምንፈልገውን ቀድመን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ ሚስቶች ከባሎቻችን የምንፈልገው ነገር ብዙ ነው፡፡ ነገር ግን የምንፈልገውን ነገር በግልጽ አናውቀውም፡፡ ባሎችም ሚስቶቻቸው ምን እንደሚፈልጉ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን የሚስቶቻቸው ፍላጎት በየጊዜው የሚለዋወጥ በመሆኑ ግራ ተጋብተዋል፡፡ ሴት የራሷን አካላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ስሜታዊ እና ሌላም ፍላጎቷን ለይታ ካላወቀች እንዴት ብሎ ነው ባሏ ፍላጎቷን ሊያሟላ የሚችለው? ብዙዎቻችን ሴቶች ለይተን ባላወቅነው ፍላጎታችን ወንዶችን ተጠያቂ እናደርጋለን፡፡

ግራ የሚያጋባ ነዉ.....
1.2K viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 21:09:25

2.2K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ