Get Mystery Box with random crypto!

ውበቴን _ በፊትህ 'ልጄን አሳዩኝ?' አለች በደከመ ድምፅዋ ከወሊድ ስቃዩዋ ገና እፎይ ሳትል። አም | ISLAM IS UNIVERSITY

ውበቴን _ በፊትህ
"ልጄን አሳዩኝ?" አለች በደከመ ድምፅዋ ከወሊድ ስቃዩዋ ገና እፎይ ሳትል። አምጥተው ክንዶችዋ ላይ አደረጉላት። ህፃኑ የተሸፈነበትን ጨርቅ ገላለጠችው። ክው ብላ ደነገጠች።
ዶክተሩ ሁለት እጆቹን እንዳጣጠፈ ፊቱን ወደ መስኮቱ አዙሮ ከሆስፒታሉ ክፍል ወደ ውጭ ማየት ጀመረ።....ተፈጥሮ ሰሰተች። ህፃኑ ያለ ጆሮ ነበር የተወለደው ። የእናት እንባ ህፃኑ ፊት ላይ ተንጠባጠበ።
ከዓመታት በኋላ ግን ምንም እንኳ ሁለቱ የጆሮዎቹ ቅጠሎች ባይኖሩም የልጁ የመስማት ሁኔታ ጤናማ እንደሆነ ታወቀ። ይሁንና ሁልጊዜ ከትም/ት ቤት መልስ ሮጦ እናቱ ላይ እየተጠመጠመ ያለቅሳል። "አስፈሪው ልጅ! እያሉ ይሰድቡኛል" ይላታል።
ጊዜው ይሮጣል። ......ልጁ አደገ።....ጆሮ ከማጣቱ በስተቀር ፍፁም ውብና ደመ-ግቡ የሆነ ታዳጋ ሆነ።.....እናት ግን ዘወትር በሀዘን ትቆራመዳለች። " ነገ ከሰው ጋር ሲቀላቀል እንዴት ይኖር ይሆን?" እያለች ትተክዛለች።
አባቱ በበኩሉ ዶክተሩን እየተመላለሰ ይወተውተዋል። " በቃ ልጄን ምንም ልትረዱት አትችሉም ማለት ነው?" .....ተስፋ ባለ መቁረጥ ይጠይቃል። " ሁለቱን የጆሮ ቅጠሎች ብናገኝ እኮ ቀላል ነበር" አለው ዶክተሩ።
ፍለጋው ተጀመረ ለዚህ ለጋ ታዳጊ ከሞት በኋላ ጆሮዎቹን ለመለገስ ሊናዘዝ የሚችል ሰው ተፈለገ።
ከሁለት ዓመት በኋላ አባት ልጁን ጠራውና " ነገ ሆስፒታል እንሄዳለን። ሁለት ጆሮ የሚሰጥ ፈቃደኛ ተገኝቷል!..... "አለው።  " ነገር ግን የበጎ አድራጊው ስምና ማንነት ቢያንስ ለተወሰኑ ጊዚያት ሚስጥር ነው! "አለው። በነገታው እናትና አባት ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ።.......የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደረገ፣ አዲስና ይበልጥ ውብ የሆነ ታዳጊ ደግ ተከሰተ። በቃ ዓለምን በድጋሚ ተቀላቀላት። በራስ መተማመኑ ሲጨምር በእውቀትም የተካነ እየሆነ መጣ።
ሀይስኩልና ዩኒቨርሲቲን በጥሩ ሁኔታ አጠናቀቀ።......ትዳር መሰረተ።....ጥሩ ስራ ያዘ።......" አሁን ግን ማወቅ አለብኝ!" ሲል አባቱን ጠየቀው። "ይህን የህይወቴን ታላቅ ስጦታ የቸረኝ ማነው? ምንም በደርግለት ነፍሴ የምትረካ አይመስለኝም!" አለው።
".......አይይ ምንም ልታደርግለት የምትችል አይመስለኝም!" ሲል መለሰለት። "በውላችን መሰረት ደግሞ የለጋሹ ማንነት በሚስጥር መያዝ አለብን!.....ቢያንስ ለጥቂት ዓመታት!" ሲል አግባባው።
...ቀናት ይህን ሚስጥር በሆዳቸው እንደታቀፉ ከነፉ!.....ነጎዱ!.....ሚስጥሩ ይፋ የሚሆንበት ጊዜ ደረሰ።
አንድ ቀን ቤተሰቡ ተሰበሰበ። አባት ሄዶ ከእናት ጎን ቆመ። ....ልጁ በጭንቀት ተዋጠ።....አባት የእናትን ዞማ ፀጉሮች ወደ ላይ ቀስ ብሎ ከፍ አደረጋቸው።......እናት ጆሮ አልባ ነበረች!.......ልጁ ዓይኖቹ በእናቱ ጆሮ አልባ ፊት ላይ እንደተተከሉ እንባ አንጠባጠቡ.... "ልጄ...." አለችው " የኔ ውበት ያንተ ፊት ላይ አለ!" አለችው።
**
ወዳጆቼ እናት  ማለት እንግዲህ እንደዚህ ነች.......
እናት