Get Mystery Box with random crypto!

'ህልም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ፤ ለአሁኑ ጊዜም ኃይል ይሰጠናል። --ጆን ማክስዌል 'በልበሙሉነ | ISLAM IS UNIVERSITY

"ህልም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ፤ ለአሁኑ ጊዜም ኃይል ይሰጠናል።

--ጆን ማክስዌል

"በልበሙሉነት ወደ ሕልምህ አቅጣጫ ሂድ። ያሰብከውን ህይወት ኑር። "

-- ሄንሪ ዴቪድ ቶሬው

ሁላችንም በህይወታችን ልናደርገው የሚገባ ጠቃሚ ነገር እንፈልጋለን።
ህልም ያንን ይሰጠናል!

ህልም የምንጓዝበትን አቅጣጫ ይነግረናል ፤ እንደ ኮምፓስ ያገለግለናል።

ህልም እምቅ አቅማችንን እንድንገነዘብ እና በውስጣችን እና በአካባቢያችን ያሉትን ታላላቅ ሀብቶቻችንን እንድንረዳና እንድንጠቀም ይረዳናል።

በህልም ራሳችንን በአዲስ ብርሃን ማየት እንጀምራለን፣ የበለጠ አቅም እንዳለን እንረዳለን።

የምናገኛቸው አጋጣሚዎች፣ ያገኘናቸው ሀብቶች፣ የምናዳብረው እያንዳንዱ ችሎታ ወደዚያ ህልም የማደግ አቅማችን አካል ይሆናል።

ሕልማችን ትልቅ በሆነ ቁጥር አቅማችን ይጨምራል።

ራዕይህ - ህልምህ - ታላቅ ከሆነ ስኬታማ የመሆን አቅምህም እንዲሁ ነው።

ህልም በህይወታችን ወሳኝ ለሆኑ ነገሮች ቅድሚያ እንድንሰጥ ይረዳናል።

ምርጫዎቻችንን እንድናመዛዝን እና ለእኛ አስፈላጊ በሆነው ላይ በመመስረት ውሳኔ ለመወሰን እንድንችል ይረዳናል።

ህልም በምናደርገው ነገር ሁሉ በህይወታችን ውስጥ ዋጋ ላለው ነገር ቅድሚያ እንድንሰጥ ያስችለናል።

አንድ ህልም ያለው ሰው ወደ ላይ ለመውጣት መተው ያለበትን ያውቃል። የሚያደርገውን ሁሉ የሚለካው ለህልሙ መሳካት የሚያበረክተውን በማሰብ ነው።