Get Mystery Box with random crypto!

ይህ ሸይኽ ሙሐመድ አስ-ሳዊ በአንደበታቸው የተናገሩት እውነተኛ ታሪክ ነው። የዙሑር ሰላት ከ | ISLAM IS UNIVERSITY

ይህ ሸይኽ ሙሐመድ አስ-ሳዊ በአንደበታቸው የተናገሩት እውነተኛ ታሪክ ነው።
የዙሑር ሰላት ከተሰገደ ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ወጣት በፍጥነት ሲነጉድ በነበረ ባቡሩ ተገጭቶ የሲቃ ድምፅን ሲያሰማ ለአደጋው ቅርብ የነበሩ ሰዎች በዙሪያው ተሰበሰቡ። ባቡሩ ሰውነቱን ደፍጥጦታል። አጥንቱ ተሰባብሮ አካባቢው በደም ተጨማልቋል። ሮጠው ሲደርሱ እስትንፋሱ አለች። ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ ልቡ በኃይል ይመታል። ደረቱ ተቀዶ ሳንባው ሲተነፍስ ይታያል። በህይወት አለ። አንድ አዛውንት ላኢላሃ ኢለላህ በል በማለት ወደ ጆሮው ተጠግተው ሹክ አሉት።

"ከአላህ በስተቀር የሚገዙት ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ" እያለ እስትንፋሱ ተቋረጠ። በሸሃዳ ሞተ። አድራሻውን ለማግኘት ኪሱን መፈተሽ ጀመሩ። ቀኝ እጁ ላይ የመስቀል ምልክትን አዩ። መታወቂያውን ሲገልጡ ክርስቲያን መሆኑን አወቁ።
ግራ ተጋቡ "ሸሃዳ ይዞ እንዴት ሞተ?!" ተባባሉ

በዝምታም በዝግታም ጀናዛውን ተሸክመው ወደ አባቱ መንደር ይዘውት አቀኑ። የተፈጠረውን ዘርዝረው አስረዱ። አባት አንገቱን ዝቅ አድርጎ እያለቀሰ እንዲህ አለ፡-
"ልጄ ክርስቲያን ነው ቁርኣንን መስማት ግን አብዝቶ ይወድ ነበር። ወደ ክፍሉ ስገባ ሁል ጊዜ ሄርፎን በጆሮው ላይ ሰክቶ አገኘዋለሁ። ምንድነው የምትሰማው ብዬ ስጠይቀው ደስ የሚል ዘፈን ይለኛል። ወደ ጆሮ ማዳመጫው ጠጋ ብዬ ስሰማ ቁርኣን መሆኑን አስተውላለሁ" አሉና ተንሰቅስቀው አነቡ

"ልጅዎ ነፍሱ ልትወጣ እስትንፋሱ ልትቋረጥ በሞት አፋፍ ላይ እየተሰቃየ የአላህን ብቸኛ አምላክነት መስክሮ ሞቷል" አልናቸው።
ሀዘንተኛው አባት "ልጄ የመሰከረውን እኔም እመሰክራለሁ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ" በማለት ሸሃዳን ይዘው ሰለሙ።