Get Mystery Box with random crypto!

በየመን የዘካተል ፊጥር ሶደቃን ለመቀበል በተፈጠረ ግፊና ትርምስ ቢያንስ የ 78 ሰዎች ህይወት አለ | ISLAM IS UNIVERSITY

በየመን የዘካተል ፊጥር ሶደቃን ለመቀበል በተፈጠረ ግፊና ትርምስ ቢያንስ የ 78 ሰዎች ህይወት አለፈ !

ነገሩ እጅግ አሳዛኝ ነው !
በአሳዛኝ ረሀብና ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የመን ከ 17 ሚሊዮን በላይ ረሀብተኞችን የያዘች ሀገር ናት ። ሳኡዲና አጋሮቿ ከላይ በቦንብ ያነዷታል ከሁቲዎች ጋር እየተፋለሙ ። ከስር የረሀብ አለን ህዝቧን እየገረፈ የመናዊያን ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው መኖር ከጀመሩ አመታት ተቆጠሩ ።

በዛሬው የተሻሉ የሚባሉት የየመን ነጋዴዎች ለችግረኞች ዘካተል ፊጥር ለማከፋፈል በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ሰብስበው የነበረ ቢሆንም እርዳታውን ለመቀበል በተፈፀ ግፊ ከ 78 በላይ ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶቹ ቆስለዋል ።

የሚገርመው የሚከፋፈለው እርዳታ ለአንድ ሰው 10 ዶላር ብቻ የነበረ ቢሆን እርሷን ለማግኘት ሲጋፉ ህይወታቸውን አጥተዋል ። በበርካታ የአረብ ሙስሊም ሀብታም ሀገራት የተከበበቺው የመን እርሷ ግን የረሀብና ጠኔ ምሳሌ ናት ።

ረሀብ እያሰቃየ ከሚገድለን ተጋፍተን በቶሎ እንሙት ብለው ይሆን

አላህ የሞቱትን ይማራቸው ! የመንንም ከመከራዋ ያውጣት !