Get Mystery Box with random crypto!

ikhlas Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube I
የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube
የሰርጥ አድራሻ: @ikhlasstudents
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.73K
የሰርጥ መግለጫ

በዱንያም በአሄራም አላህ ስኬታማ ከሚሆኑ ሰዎች ያድርገን
@ikhlasstudents
አስታየት ካላችሁ @muaz_mb ሊያገኙን ይችላሉ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-12 23:28:55 ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሞቱት በሙዕሚኖች እናት በሆኑት ዓኢሻ ክፍል ውስጥ ነበር። ግንባራቸውን ለፈጣሪያቸው ደፍተው መሞት የሚችሉበት ሁናቴ ቢኖርም የርሳቸው ምርጫ የነበረው የመጨረሻ ህቅታቸው በዓኢሻ እቅፍ ውስጥ ሆነው እንዲቋጭ ነበር። ምኞታቸው ሰመረ። በዓኢሻ እቅፍ ውስጥ እስትንፋሳቸው ተቋረጠ። ወገን! «ፍቅር እስከ ትንሳዔ!» ይሏል ይህ ነው!!!

  @ikhlasstudents ||ikhlas Tube
5.9K views Elham , 20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 21:04:18 ~አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ~

እንዴት ናቹ አህባቢ?

ብዙ ቀናት አዘግይተን ለምንለቀው ለፍቅር ፊዳ የተሰኘው ታሪካችን ለናንተ ቶሎ ማድረስ ባለመቻላችን አፉታ እየጠየቅን ከዚ በኃላ ጊዜ ሊመቻችልን ስላልቻለ ጊዜ አመቻችተን በየ ሁለት ቀኑ የምንለቅላቹ መሆኑን እናሳስባለን!

ከተየማቹን አፉወን በኛ ቦታ ብትሆኑ ትረዱን ነበር
5.9K viewsHãyú, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 21:03:32 ‍ ------------ ------------
★ለፍቅር ፊዳ★
----------- -------------

★ክፍል ሀያ አንድ★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…12 እያለች ዲቪ ሞልታ ነበር እንደ እድል ሆኖ ከአንድ አመት ቡሀላ ደረሳትና ለመሄድ ወሰነች አባቴም ከኪሱ ምንም ገንዘብ ስላልነበረው ከጎረቤት ተበድሮ ላካት ከዛ…"አዛን መውጣቱን መስጊዱ ሲያበስር "በቃ ነገ ጨርስልሻለሁ አሁን እንስገድ ብሎ ተነሳ እሷም ታሪኩን ሚያጓጓ ቦታ ላይ ማቆሙ አበሳጭቷታል እንዴት እንዲ አይነት ሰው እንደሆነ በምን እንደተቀየረ ቤተሰቦቹ ከምን እንደደረሱ የሱ ህይወት ውስጥ ፍቅር እንዴት እንደገባ ማወቅ ጓግታለች ብቻ ባጠቃላይ እስኪነጋ ሁላ ምጠብቅ አልመሰላትም እየተበሳጨችም ቢሆን ለመስገድ ገባች ቤቱ ከቅድሙ ሰው አሁን ቀለል ብሉ አክስቶቿ እና አጎቶቿ ብቻ ናቸው የቀሩት ሰላት ሰግዳ እራት ከኻዲማቸው ጋር ተጋግዘው አቀረቡ ለሚፍታህ እንዴት እራት እንደምታደርስለት ግራ ገብቷታል ብትሄድ ስለ ማያ እንደሚጠይቃት ታቃለች አማራጭ ስላልነበራት የመጣው ይምጣ ብላ ሚበላ ና ሚጠጣ ነገር ይዛለት ሄደች ልቧ ከመጠን በላይ እየመታ ነው ልክ የበሩን እጀታ ጠምዝዛ በሩን እንደከፈተች እንቅልፍ ባይወስደውም ተጋድሞ ነበር ልክ እሷ መሆኗን ሲያቅ ፈገግ ብሎ መጣች አላት ሀፍሲ በዚህ ጊዜ መብረቅ እንደመታው ሰው ሆነች ያሰበችውን ስላልጠየቃት ነበር እንዲ በተስፋ መጠበቁና መጓጓቱ ነበር ልቧን ያሸበረው ምትለው ግራ ገብቷት ምግቡን አስቀምጣ ልትመልስለት መንተባተብ ጀመረች
"እ…አ…አ…ይ"
"እና"ተኮሳተረ
"እ…እ…ንትነው አልተመቻትም ማለቴ የፈተና ሰአት ስለሆነ ጥናት በዝቶባት አይመቸኝም"ውሸት እንደሆነ አነጋገሯ ያሳብቅ ነበር
"ሀፍሲ!"ተቆጣ ደነገጠች
"በይ እውነቱን ንገሪኝ ምንድነው እየተፈጠረ ያለው እንዴት መታመሜን እያወቀች እስከዛሬ ዝም አለች ለምንስ አባቷ እንደ ድሮው ይዟት አይመጣም"
"እኔ አላቅም"አሁንም ሚያስታውቅ ውሸት ጨመረች
"ሀፍሲ ከዚ በላይ እንድበሳጭ ባታረጊኝ ጥሩ ነው"
"እሺ በቃ…"ብላ እየተነጫነጨች እየፈራች እውነቱን ነገረችው ይሄን ሲሰማ በጣም ተበሳጨባት
"ሀፍሲ!ወላሂ ስራሽ እኮ አንድ አያምርም አሁን ምን አገባሽ ባትፈልገኝ አሁን እየመጣች አያት ነበር ይሄ ሁሉ ባንቺ ምክኒያት ነው እንደውም ምግቡ ይዘሽ ሂጂ እኔ አልበላም"በቁጣ በጩሀት ድምፅ ነበር የተናገራት አነጋገሩ አናዷት እሷም በቁጣ መለሰችለት
"ምንድነው ያልከው ሚፍታህ ምን አገባሽ ነው ያልከኝ እኔ ላንተ ስል በተሰቃየሁት እንዲ ትለኛለህ ቆይ ይሄ ፍቅር እያሉ ሚጃጃሉበት ነገር ሚጠቅም ነገር ነው ሚመስልህ የምን መጃጃል ነው ፍቅር ከተባለ ትዳር ውስጥ ብቻ ነው ያለው እሷ ደሞ ለመቅበጥ ስትል ምትፈልገው የትዳርን ፍቅር አይደለም የመጃጃሉን ፍቅር ነው ምትፈልገው ደሞ እንቢ ካለችህ እንቢ አለችህ ነው አለቀ ለምንድነው ለሴት ምትርከፈከፈው ጅል አትሁን እሺ ለሴት ፍቅር እንዲ የሆንከው ባባ እንዳሳደገን ለአላህ ፍቅር እንዲህ ብትሆን ይሄን ባላጣሀት ነበር ቢገባህ ግን አትረባም ምን አገባሽ ነው አይደል ላንተ ብዬ ብሰቃይ ምን አገባሽ ሆነ አይደል መልሴ ጥሩ ሁለተኛ አልመጣልህ በላህ ጠጣህ ብላ መታ ትጨነቅልሀለች ቆይ ጠብቅ እሺ ጅል"ብላው ተበሳጭታ ምግቡን ሳታነሳ በሩ አጋጭታ ወጣች እንደ ዛሬ አበሳጭቷት አያቅም…


★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!


Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
6.0K viewsMᴜᴀᴢ, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 21:23:55 ከኔ የበለጠ ወንድ የሚያምር
አለን ?? ብሎ ጠየቃት

ዝም አለችና ... ከዚያ አላውቅም አለች

እሺ ከኔ ሚሻልስ አለ? አላት

አሁንም አላውቅም አለች

እሺ ከኔ የበለጠ ለስለስ ያለስ? አላት

አላውቅም አለኩህኮ ... አለችው

እንዴት አታውቂም? አላት

ከኔ ጋር ሆነህ እንዴት ወደ ሌላ ወንድ ልመልከት? ፍቅርህ እንዲህ አድርጎኝ እንዴት ሌላን  ማየት እችላለሁ?? አለችው

እንዲህ አይነቷን እንዲወፍቃቹህ ዱዓ አድርጉ

#Elu_ነኝ

@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
6.3K views Elham , 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 21:06:38 ሀቢቢ ሚስትህን, ,ፈገግታህን አትንፈጋት
ስሜትህን ግለፅ!! 
እውነተኛ ሁን!!
     እወድሻለሁ፣ አንቺ
ለኔ ልዩ ሰው ነሽ ,,በላት
ፍቅርህን በገለፅክላት ልክ
ፍቅሯ ይጨምራል

ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
@ikhlasstudents
2.2K views Elham , 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:17:00 ‍ ------------ ------------- ★ለፍቅር ፊዳ★ ------------ ------------- ★ ክፍል ሀያ★ «በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ» …"ከሱ ጋር ስለሆንሽ ምን ትሆኛለሽ ውበት ከሆነ ማንኛውም ሴት እንደምትፈልገው አይነት ቁመና አለው ኢማን ፣ገንዘብ፣ የተማረ ምን ጎደለው ንገሪኝ እስቲ"ሳታስበው እየጮሀች ነበር" "ምንም ቢሆን በቃ አልችልም" "ምን አልሽ እንደዛ ነው ማያ አንቺ…
3.3K viewsMᴜᴀᴢ, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 20:28:17 ‍ ------------ -------------
★ለፍቅር ፊዳ★
------------ -------------

★ ክፍል ሀያ★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…"ከሱ ጋር ስለሆንሽ ምን ትሆኛለሽ ውበት ከሆነ ማንኛውም ሴት እንደምትፈልገው አይነት ቁመና አለው ኢማን ፣ገንዘብ፣ የተማረ ምን ጎደለው ንገሪኝ እስቲ"ሳታስበው እየጮሀች ነበር"
"ምንም ቢሆን በቃ አልችልም"
"ምን አልሽ እንደዛ ነው ማያ አንቺ ግንጨካኝ አረመኔ ነሽ ቢገባሽ እና ደደብ ባትሆኚ ኖሮ አንቺ ለካለድ እንደሆንሽው ወዶሽ እንደተሰበረ እያየሽ ትረጂው ከህመሙ ታድኚው ነበር አንቺ ምፈልጊው ፍቅር ከትዳር በፊት ያለውና ጊዜያዊውን ነው ግን እሱ በኢስላም የተጠላ እንደሆነ ታቂያለሽ ፍቅር ያለው ከትዳር ቡሀላ ነው ሚፍታሄ እኮ እንዳቺ አባት ሚረዳው ሰው የለውም በማን ምክኒያት ከህመሙ ይድናል እኔ እንደሆንኩ ስለፍቅር ራሱ ማቀው ነገር ቢኖር መሰበርን ብቻ ነው"በሀሳቧ ሰሚር እየመጣ ስለነበር ንግግሯንለትንሽ ደቂቃ ገታ አድርጋ ትለምናት ጀመር
"እ ማያ በአላህ ተለመኚኝ ቢያንስ እሺ መተሽ አውሪው"
"በቃ አልችልም አልኩሽ እኮ እኔ ልቤ ከካሊድ ሌላ ማሰብ አይችልም በሱ በቅቶኛል የወንድ ነገር ገባሽ ከዚ በላይ ሚበቃን ይመስላል ደህና ሁኚ"ብላት ወደ ቤት ገባች ሀፍሲ ስራው የበለጠ እንድጠላት እያረጋት መጣ ተናዳ ጊቢያቸውን ለቃ ወጣች ቤት ስደርስ አሁንም ድረስ ሰው ብዙ ነው ወደ ሚፍታህ መሄድ ፈለገች ግን ምን ብላ ልትነግረው እንደምትችል ግራ ገብቷታል ከዚ ውጪም የሰሚር በጭንቅላቷ መመላለስ ጭንቀቷ ተደራርቦ ሰው ማያያት ቦታ ጥግ ይዛ አይኗን ጨፍና ግርግዳ ተደግፋ በሀሳብ ላጥ ብላለች ሰሚር ስልክ ሊያናግር ወቶ አውርቶ ሲጨርስ መግሪብ እስኪደርስ ለመዟዟር አስቦ ወደዛ ወደዚ እያለ ድንገት ወደ ጥግ በኩል ሲዞር ሀፍሲን ተመለከታት ትናንት ቀይ የነበረው ፊቷ ዛሬ ከሰል ለብሷል የጨነቃት ነገር እንዳለ ከፊቷ ያስታውቅ ነበር ፍዝዝ ብሎ ከተመለከታት ቡሀላ ነቅቶ ሊረዳት ሄዶ አጠገቧ ተቀመጠ
"እህም…ሀፍሲ ደና አይደለሽም እንዴ"ብሏት ሶስት ሰው ሚያስቀምጥ ቦታ በመሀላቸው አስቀርቶ ተቀመጠ በሀሳቧ እያሰበችው ሲመጣ ደንግጣ
"አ…አ…ረ…ደ…ና… ነኝ"አጠገቧ ሲቀመጥ የልቧ አመታት እንኳን ለሷ ከውጭ ላለ ሰው ሚሰማ ነው በድንጋጤ አይኖቿ እሱላይ እንደ ባትሪ ስታፈጥ ግራ አጋብታው
"እንዴ ምንድነው እንዴት ነው ምታዬኝ ቢስሚላህ ልበይኝ ነው"ብሎ ፈገግ አለ
"ፈገግታህ ያምራል"ሳታስበው ስላመለጣት አፏን ያዘች እሱም የሱ ስሜት እሷ ጋር እንዳለ ተረድቷት ዝም አለ እሷ ግን ስለፍቅር ስሜት ስለማታቅ ፍቅር ነው ብላ አላሰበችም
"እኔ ምለው መጨነቅሽን አይቼ ልረዳሽ ነበር አመጣጤ የውስጥሽን ብነግሪኝና ብረዳሽ ደስየ ይለኛል ደሞም በህይወት መንገድ ብዙ ፈተናዎችን ያለፍኩ ሰው ስለሆንኩ ምናልባት ሊገባኝ ይችላል"
"እሺ ግን እባክህ ከልብህ አዳምጠኝ ከልቡ ሚረዳኝ ሰው ነው ምፈልገው"
"እሺ"…ጭንቀቷን በሙሉ ዘረገፈችለት አንድ ነገር ሲቀር የሱ ጉዳይ ብቻ ነበር እሱም ሁሉንም ካዳመጣት ቡሀላ ፈገግ ብሎ
"ታቂያለሽ ሀፍሲ ይሄ ፍቅር የሚሉት ነገር ማይገባበት ቦታ የለውም የኔን የህይወት ታሪክ ልንገርሽ ና ተማሪበት እኔ የተወለድኩት ሀዋሳ ነበር ቤተሰቦቼ በጣም ዝቅተኛ ሚባል አይነት ኑሮ ነበር ሚኖሩት በዛ ላይ እናቴ እና አባቴ ያላቸው ብቸኛ ልጅ እኔ እና አንድ ታላቅ እህቴ
ነበርን ያን የድህነት ኑሮ መቋቋም ሲያቅተን እናትና አባቴ እየደከሙ ሲመጡ እነሱን ለማገዝ እየተማርን ያገኘነውን ስራ እየሰራን ለለውጥ መነሳት ጀመርን ያኔ ገና 9ኛ ክፍል ነበርኩ እህቴ ደሞ 12 ነበረች የህይወት ፈተና ተደራርቦብን ምግብ ሳንበላ ምንውልበትም ምናድርበትም ጊዜ ነበር ከማጣታችንም በላይ ደሞ የእናቴ መታመም ነበር እያስጨነቀን የመጣው እማዬን ለማትረፍ ሁላችንም መሯሯጥ ጀመር እማዬን ተሻላት ብለን እፎይ ስንል ደሞ ሚላስ የሚቀመስ ከቤት ይጠፋል በቃ ፈተናው እየተደራረበብንም ጊዜው መሮጡን እንደቀጠለ እኛም ለመለወጥ እየተጋን እኔ ከት/ቤቱ አንደኛ በመውጣት ወደ 10 አለፍኩ እህቴ ደሞ 12 ተፈትና የሀገሪቷን ከፍተኛ ውጤት አምጥታ ቤተሰቦቻችንን አስደሰትን እኔ ወደ አስር ባልፍም እህቴ ግን ወደ ዩንቨርሲቲ መሄድ አልፈለገችም 12 እያለች ቪዛ ሞልታ ነበር እንደ እድል ሆኖ ደረሳትና ለመሄድ ወሰነች አባቴም ከሰው ብር ተበድሮ ላካት ከዛ…"አዛን ሲወጣ በቃ ነገ ጨርስልሻለሁ አሁን እንስገድ ብሎ ተነሳ…



★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
3.6K viewsMᴜᴀᴢ, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 07:41:27
"በዓለም ላይ ያለኝ አንድ ወዳጅ ልብስ ሰፊ ነው! " አለ ሰውዬው።

ምነው ሲባል፣ "በትላንቱ አይለካኝም"

     ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
4.5K viewsᗰᑌᗩᘔ, 04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 20:49:18 ----------- -------------
★ለፍቅር ፊዳ★
----------- -------------

★ክፍል አስራ ዘጠኝ★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…እየተመናቀረች ስትሄድ ሁኔታዋ አስቆት እየተመለከታት ነበር ድንገት ፊት ለፊት ያላየችው ውሀ አንሸራቷት ልቶድቅ ስትል ሩጦ ሄዶ ወገቧን ያዛት እሷም ሸሚዙን ጨምድዳ ያዘቸው የህንድ ፊልም ሚሰሩ ይመስል ተቃቅፈው ይፋጠጣሉ ሁለቱም መላቀቅ የፈለጉ አይመስሉም እንደፈራና እንደደነገጠ ሰው አስመስለው ይፋጠጣሉ ሰው ያየናል ብለው ያሰቡም አይመስል ተመሳስጠዋል በመሀል የሀፍሲ እናት ኡዱእ ለማድረግ ሲወጡ ጉዳቸውን ተመልከተው ከመቆጣት ይልቅ ሳቃቸውን ለቀቁት እነሱም የሰሙት ሳቅ አባኗቸው ተላቀቁ ሀፍሲ እናቷን ማየት አፍራ ምንም ሳትል አጎንብሳ ከግቢ ወጣች ልጁም ስራው አሳፍሮት ለሀፍሲ እናት ለማስረዳት ይንተባተባል
"ማ…ማዘር ማለቴ የሚፍታህ እናት ወላህ ሌላ ነገር አይደለም ውሀ አንሸራቷት ልቶድቅ ስትል ነው የያዝኳት"
"አይዞህ ልጄ አትጨነቅበት እንደፈለክ አርገህ ያዘት ግን ወደ ሀላል መንገድ አምጡት ብቻ"አሉ ሳቃቸውን ገታ አድርገው ወደ ፈገግታ ለውጠው ሰሚርም ለስራው ኢስቲግፋር እያደረገ ሊሰግድ ገባ…ሀፍሲ እነ ማያ ቤት እስክትደርስ ድረስ የሰሩት ነገር በሀሳቧ እየተመላለሰ አንዴ ስፈግግ አንዴ ደሞ የእናቷ ማየት እያሸማቀቃት በሀሳብ እንደነጎደች እነ ሀፍሲ ቤት ደረሰች አሁን ግዴታ ሀሳቧን መሰብሰብ ስለነበረባት ሀሳቧን በሙሉወደ ወንድሟ አዞራ በሩን አንኩዋኳች ሰሞኑን የማያ አባት ብቻ ስለነበር እየመጣ ሚፍታህን የሚያየው የማያን መልክ ራሱ ሳትረሳው አትቀርም አሁን ምን እንደምትላት ራሱ አታቅም ሰው ላይ ከተናደደች በንግግር ሰውን እንደምታስቀይም ታቃለች እንደምንም ራሷን አረጋግታ ለማናገር አሰበች ከደቂቃዎች ቡሀላ በሩ ተከፈተ ኻዲማቸው ነበረች የከፈተችው
"እንዴ የጠፋ ሰው አሰላሙ አለይኩም ምንድነው እንደዚ መጥፋት አንቺዬ"አስገብተዋት በሩን ዘግተው ኻዲማቸው ነበረች ሁሌ ቤታቸው ስትመጣ ከርማ የሰሞኑ መጥፋቷ ጨንቋቸው? ነበር
"ወአለይኩም አሰላም ሀቢብቲ ትንሽ ወንድሜ ታሞ መውጣት ስላልቻልኩ ነው የጠፋሁት ደና ናቹ እናንተ"
"እኛስ ደና ነን አላህ ያሽርልሽ በይ ግቢ ውስጥ አሉ እነ ባባ"
"አረ አልገባም ባይሆን ማያን ፈልጌያት ነበር አለች?"
"ካልሽ ኸይር አሷስ አለች ግን…እኔ ምልሽ እንደው የሰሞኑ ፀባዯ ልክ አይደለም ምግብ በስርአት አትበላም ከክፍሏ ብዙም አትወጣም አንቺን ስላጣች ይሁን እንዴ?"
ሀፍሲ የሰማችው ነገር ገርሟት በውስጣ‘ደሞ ምን ሆንኩ ልትል ነው እሷ ምኗ ተነካ ወይስ ፀፀት ይዟት ነው’
"እኔጃ አክስቴ ጥሪያት እስቲ"
"ለምን ገብተሽ አታወሪያትም"
"አረ ቸኩላለው ሰላም ብያት ለመሄድ ብቻ ነው"
"እሺ በቃ"ብላ ልትጠራት ገባች በመሀል የማያ አባት ወተው ሰላም አሏት
"እንድ ሀፍሲዬ አሰላሙ አለይኪ ደና ነሽ"
"ወአለይኩም አሰላም ደና ነኝ ባባ አንተ ደና ነህ"
"እኔስ ደና ነኝ እኔ ምለው ልጄ እንደው ከማያ ጋር እንደተቀያየማቹ ልከርሙ ነው"አሏት እሷም የምፀት ፈገግታ እያሳየች አንገቷን አቀረቀረች
"እኔ ዝምድናን እንቀጥል የአላህ ራህመት እናገኛለን ብል እናነት በትንሽ ነገር ትቀያየማላቹ"
"እሺ ምን ላርግ ባባ ወንድሜ ሞቶ ቢሆንስ በሷ ምክኒያት ሆኖ ሊቀር ያለኝን አንድ ወንድሜን ባጣስ"
"እሺ እንድታገባው ላስማማት እና አፉ ተባባሉ"
"ሳትወደው አግብታው ሰላም ባይኖራቸውስ"
"ተይ እንጂ ልጄ አሁን ከመስመር እያለፍሽ ነው በቀደር እያመንሽ እንዲ ቢሆንስ ይባላል ተይ እንጂ ሀፍሲ"
"እሺ ባባ" ብላ ስትዞር ማያ በአንድ እጇ ሺቲዋን ወደላይ ሰብስባ ይዛ በአንድ እጇ ፀጉሯን እያከከች ወደነሱ እየመጣች ነው ሀፍሲ ስታያት የወንድሟ ነገር ትዝ ብሏት ልትኮሳተር ብላ መልሳ የይምሰል ፈገግታዋን መለሰች ማያም እነሱ ጋር ስደርስ መሬት እያየች በእጇ አንገቷን ይዛ "አቤት"አለቻት በደከመ ድምፅ የማያ አባት ያወሩ ብሎ ትቷቸው ገባ
"ደና ነሽ ማያ"
"ደና ነኝ"አጭር መልስ ሰጠቻት
"አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነበር የመጣሁት"
"ምችለው ከሆነ እሺ"
"እ…ምን መሰለሽ አውቃለው በወንድሜ ምክኒያት እንዳስቀየምኩሽ ነገር ግን አንቺም የራሽን ስሜት ብቻ ማዳመጥ አልነበረብሽም የሱን ስሜት መረዳት ነበረብሽ ማያ ወላሂ እሱ ማንንም ሴት አፍቅሮ አያቅም ደሞ ባትወጂው ራሱ እኮ አብረሽው ሆነሽ ደስተኛ ብታረጊው ራሱ ትልቅ ነገር ነው እሱ ከህመሙ ገና እንደነቃ ራሱ ከኛ ይልቅ አንቺን ፈልጎ ሲያጣሽ ልቡ ሲደማ ማየት ትችይ ነበር ከህመሙ ሳይድንም እሷን ጥሪልኝ ማለት አላቆመም ምግብ ራሱ በስርአት ከበላ ወር ሆኖታል ወላህ ማያ ብታየው ከሰውነት አለም ወቷል ልክ አንቺ ለካሊድ እንደሆንሽው…"አይኖቿ በእንባ ታጥበው መናገር አቃታት ማያም ሳታስበው እያለቀሰች ነበር ሀፍሲም ቀጠለች
"በአላህ ማያ ልለምንሽ ከጎኑ ሁኚለት ቢያንስ ደስታውን ልመልከት"ማያም እንባዋን እየጠረገች ፈገግ እያለች
"ታቂያለሻ ሀፍሲ እኔም ታላቅ እህት ብትኖረኝ እንዲ እንዳቺ ቁማ እንደምትከራከርልኝ እሺ ለሱ ባስብ እኔስ ልቤስ እ…ንገሪኝ እኔስ አላሳዝንሽም"
"ከሱ ጋር ስለሆንሽ ምን ትሆኛልሽ ውበት ከሆነ ማንኛውም ሴት እንደምትፈልገው አይነት ቁመና አለው ኢማን፣ ገንዘብ ፣የተማረ ምን ጎደለው ንገሪኝ እስቲ"ሳታስበው ጮሀች
"ምን ቢሆን አልችልም!"
"ምን አልሽ…


★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
5.9K viewsHãyú, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 22:22:10 ሴት ልጅ እነዚህን ነገሮች ያለውን
ወንድ ትወዳለች

1 ያለሷ የማያይ አይን ያለው
2 ክህደት የማያውቅ ልብ ያለው
3 ሁሌም የሚያሞግሳት
4 ሁሌም የሚታመንላትን
5 እንደ እናቱ የሚያያት (የሚንከባከባትን)

#Ⓔ︎Ⓛ︎Ⓤ︎

@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
5.6K views Elham , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ