Get Mystery Box with random crypto!

ikhlas Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube I
የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube
የሰርጥ አድራሻ: @ikhlasstudents
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.73K
የሰርጥ መግለጫ

በዱንያም በአሄራም አላህ ስኬታማ ከሚሆኑ ሰዎች ያድርገን
@ikhlasstudents
አስታየት ካላችሁ @muaz_mb ሊያገኙን ይችላሉ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-06-10 20:53:44 ‍ ---------- ----------
★ለፍቅር ፊዳ★
---------- ----------

★ክፍል ሀያ ስድስት★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…"ፍቅር ያዘኝ ሚፍቱ"የሰማው ቃል ከሀፍሲ መሆኑ እያጠራጠረው በድንጋጤ አፉ ተሳሰረ
"ም…ም…ን?"
"አው ሚፍቱ ከኔ ማይጠበቅ ነገር እንደሆነ አቃለው ግን አላቅም ብቻ እንዴት እንደሆነ በናንተ ስፈርድ በኔ ደርሶ ስቃያቹን አይቼዋለው ስለፈረድኩባቹ ይቅርታ ግን ከብዶኛል ወንድሜ ምን ላርግ" ማልቀሷ እየበረታመጣ ለትንሽ ነገር ምታለቅስ ሳይሆን ቤተሰቧን ያጣች ህፃን ነው ምትመስለው ሚፍታህ ሁኔታዋ አንጀቱን በልቶት እንደ ህፃን ልጅ አቅፎ ያባብላት ይዟል ትንሽ ቆይቶ ሳታስበው እንቅልፍ ይዟት ሄደ በሚፍታህ እና በሰሚር ምክኒያት ለሳምንት ያልተኛችውን እንቅልፍ አሁን እያጣጣመች ነው ሚፍታህም እሷን እንዳቀፋት እንደሷው እንቅልፍ ወሰደው ሁለቱም የነቁት ከአቅራቢያቸው ካለው መስጂድ አዛን ሲሰማ ነበር ሀፍሲ እንደተከፋች ተነስታ ሰግዳ ክፍሏ ቁጭ ብላ ትንሰቀሰቃለች ለምን ትላለች እራሷን ትጠይቃለች "ፍቅር ይሄ ነው በቃ መዋደድ ልብን መሰባበር ነው በቃ ጌታዬ አንተ ያስቀመጥከው ፍቅር ይሄ ነው ኢላሂ ንገረኝ እንጂ መፋቀር የሚሉት መጃጃል እህህ…አሁንማ ኘጃጃል ብዬ መስደብ ሁላ እኮ ፈራው ጌታዬ መጃጃል ብዬው አጃጅሎኝ አረፈው አሁን እኮ ኢላሂ ተስፋ ማድረግን ሁላ ክፋት አርጌዋለው ከዚ ቡሀላ መጨረሻዬ እንዲ ሊሆን ነው እንዴ በቃ ጌታዬ በዚው ሊያበቃልኝ ነው ኡፍ…"ማልቀሷን አቁማ በረጅሙ ተንፍሳ ቁርአን መቅራት ያዘች እሱም ቢሆን ከበዳት ገና የአላህን ቃል ስታወጣው አይኖቿ የቋጠረውን ይዘረግፋ ድሮን ናፈቀች ያኔ ቁርአን ስትቀራ የአላህን ቁጣ ፈርታ ስታለቅስ ነበር ዛሬ ለወንድ የተፈጠረባትን ስሜት ጠልታ እያለቀሰች መሆኑ ራሱ ቀፈፋት ከማስጠላትም በላይ ዘጋት እሷነቷን እስክትንቀው ድረስ በመሀል ኻዲማቸው ሀፍሲን እየተጣራች በራን ስታንኳኳ ቁርአኑን አስቀምጣ ፊቷን ጠራርጋ በሩን ከፈተችላት
"አቤት አሙዬ"ሀፍሲ
"ሚፍታህ ነይ እያለሽ ነው ሂጂ"
"እሺ መጣው" ብላ በሩን ዘግታ አየር ስባ ፊቷን ታጥባ ራሷን አረጋግታ ወደ ወንድሟ ሄደች…
"ወዬ አሂሻ ጠራኸኝ እንዴ"በግዷ ፈገግ ለማለት እየሞከረች
"አው ሀቢ ነይ እስቲ ምጠይቅሽ ነገር አለ"ቅድም አልቅሳ አሁን ፈገግ ማለቷ አስደስቶት ፈገግ እያለ
"እሺ ምንድነው ምጠይቀኝ"
"እም…ሀፍሲ ወላሂ እኔ ቅድም ያልሽው ነገር አስፈርቶኛል ሀቢበቲ እስቲ ማነው ልጁ ምንድነው እንዴትስ ለሱ ይሄ ነገር ተሰማሽ በምንስ አወቅሽ ምንስ ለዚ አበቃሽ ሁሉንም ንገሪኝ እስቲ"አንዴ እንባ እየተናነቃት አንዴ ፈገግ እያለች የተፈጠረው ያሳለፈችውን ሁሉ አስረዳችው
"ውይ የኔ ምስኪን ምናልባት እኮ ከዛች ሴት ገር አሁን መገናኘት አይፈልግም ይሆናል ደሞ የፈለገ ቢሆን ሀፍሲዬ ከኔ ተማሪ ደስታን መግኘት ከፈለግሽ የኔውድ ሁሉንም ለአላህ ተይለት አንድን ነገር ለአላህ ስተይው እሱ የተሻለውን ይሰጥሻል ሀፍሲዬ ትናንት እኔን መክረሽኝ ዛሬ እንዲ ስትሆኚ ይከብደኛል አሁን እኔ ማያ ላይ ተስፋ ቆርጫለው ፍቅሬን ረግጣ ከሄደች ትሂድ ከመጣች ትምጣ ብዬ ለዚ አንቺም እንደዚው ብለሽ ተይው እሺ የኔ እህት"
"እሽ የኔ ወንድም"
"ደሞ አንድ ነገር ላሳይሽ ቆይማ" ብሎ ተነሳ ያየችውን ማመን አቃታት አይኖቿ እንባ አቅርረው ፈገግ እንዳለች ፈዛ ቀረች…


★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
2.3K viewsMᴜᴀᴢ, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 19:45:58 እስከ ምሽት 10,000 ኢንሻአላህ እንገባለን
2.5K viewsᗰᑌᗩᘔ, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 17:35:10 ሁላችንም አድ እናድርግ የዛሬው ለሽልማት ያቀረብነው ለፍቅር ፊዳ ክፍል 26  እና 27 ን ነው 10,000እንደገባን እንለቃለን አድ ለማድረግ https://t.me/ikhlasTubeGroup
2.7K viewsᗰᑌᗩᘔ, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 14:33:25 ሁላችንም አድ እናድርግ

የዛሬው ለሽልማት ያቀረብነው ለፍቅር ፊዳ ክፍል 26  እና 27 ን ነው

10,000እንደገባን እንለቃለን

አድ ለማድረግ

https://t.me/ikhlasTubeGroup
3.1K viewsᗰᑌᗩᘔ, 11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 10:18:02
ሁላችንም አድ እናድርግ

አድ ለማድረግ

https://t.me/ikhlasTubeGroup
https://t.me/ikhlasTubeGroup
3.4K viewsᗰᑌᗩᘔ, 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 09:12:42 «መስጂዴ ለምን ተፈረሰብኝ?» በማለታቸው ብቻ ከአንዋር መስጅድና ከሌሎች አካባቢዎች በግፍ ታስረው የነበሩ 174 ገደማ የሚጠጉ ወንድምና እህቶች ተፈተዋል። አል-ሐምዱ ሊላህ!
ምናልባት ሌሎች ያልተፈቱ ታሳሪዎች ካሉ ጠቁሙ ተብሏል።

አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል አለሚን

ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
3.3K viewsᗰᑌᗩᘔ, 06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 22:36:11 ሁላችንም አድ እናድርግ

የዛሬው ለሽልማት ያቀረብነው ለፍቅር ፊዳ ክፍል 26 እና 27 ን ነው

አድ ለማድረግ https://t.me/ikhlasTubeGroup
3.8K viewsᗰᑌᗩᘔ, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 20:55:05 ‍ ----------- -----------
★ለፍቅር ፊዳ★
----------- -----------

★ክፍል ሀያ አምስት★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…በዛ በተንጣለለ ቤት እየኖርን እኔም 11 ኛ ክፍል የሀብታሞች ት/ቤት ተመዝግቤ መማር ጀመርኩ ያን ሁላ ፈተናዎች አልፈን ዛሬ ህይወት በአዲስ መልኩ ጀመርናት እህቴም አረገዘች ብቻ ዱኒያ የወደደችን ነበር የመሰለኝ ይሄን ደስታችንን ማማ እና ባባ ባዩልን ብለን ተመኝተን ብዙ ቀን አልቅሰናል የእህቴ ባል በጣም ደግ ሰው ነበር ለሚስቱ የሚሰጣት እንክብካቤ እኔን በትምርት እድጠነክር ያልሆነ ቦታ እንዳልወድቅ ሁሌ ይመክረኛል እኔም እንደ ድሮዬ በኢማኔ አልሰነፍኩም ነበር ግን የአደም ልጅ ሲባል ሲያጣ አላህን ሚያስታውስ ሲያጣ ደሞ የሚረሳ አይደል እኔም የገባሁበት ት/ቤት ትምርቱ ጥራት ቢኖረውም ተማሪዎቹ ግን ጥሩ አልነበሩም የሆኑ ልጆች ከክላስ ጓደኛ እንሁን ብለው ተዋወቁኝ እኔም የዋህ ልቤ ይለውጡኛል ብዬ ሳላስብ ተቀላቀልኳቸው በትምርት ደካሞች ነበሩ እኔ ደሞ ስለምችል የፈተና ጊዜ እኔ ነበርኩ ማሰራቸው የነሱ ስራ ሴት እየቀያየሩ ማሳደድ በኳስ መወዳደር ብች ሁሉም ነገራቸው የዱኒያ ነበር ሙስሊሞቹ ራሱ ሰላት ቁርአን ምንም ሚያቁት ነገር አልነበረም እኔንም እያዳከሙኝ መጡ ጌም እየተጫወትኩ ሶሻል ሚዲያ እየተጠቀምኩ ሰላት አሳልፋለው ቁርአን ደሞ እስከነ ጭራሹን ተውኩት ታዲያ አንድ ቀን ቁጭ ብለው ሴት እየለከፉ አንዲት ጠይም ሴት በኛ በኩል እያለፈች ሳለ አታምርም እያሉ ሲያወሩ ድሮ አንገት ደፊ የነበርኩት ልጅ ቀና ብዬ ተመለከትኳት የመጀመሪያው የልቤን አላርም ሰማሁት ከአይኔ እስክትሰወር ነበር የተመለከትኳት ለመጀመሪያ ጊዜ ለሴት ልጅ ልዩ ስሜት ፈጠረብኝ ማለትም ፍቅር ያዘኝ ልበለው እኔጃ ብቻ" ብሎ እንደጨረሰ ኻዲማቸው
"ዙሁር ደርሷል ሀፍሲ ምሳም ብሉ" አለቻት በብስጭት "እሺ" አለቻት ኻዲሟም በሁኔታዋ ፈገግ እያለች ገባች
"በቃ ሌላ ጊዜ ስመጣ ጨርስልሻለው አሁን ሰግጄ ልሂድ ዩሚ ናፍቃኛለች"
"መቼ ነው ምትመጣው እሺ ቢያንስ ታሪክህን ለማያ አጫውታትና ሚፍቱን ትረዳው የኔስ ይቅር እሺ"ባዘነ ፊት አይን አይኑን እያየችወንድን እንዲ አፍጥጣ ያየችበት ቀን ለራሷም ትዝ አይላትም ከምንም በላይ ሳይነግራት መሄዱ ሳይሆን ሚወዳት ሴት እንዳለች ስለነገራት ነበር የተከፋችው አይኖቿም ጭምር እንባ አቅርረው ነበር ጥሏት መሄዱም ጭምር አስከፍቷታል አንድ ልቧ ሚሰማው ስሜት የፍቅር መሆኑም አበሳጭቷታል እሱም መከፋቷን አይቶ
"እሺ በቃ ነገ ከዙሁር በፊት መጥቼ ጨርስልሽና ትነግሪያታለሽ በቃ"
"እሺ በቃ እንስገድና ምሳ በልተህ ትሄዳለህ"ፈገግ ለማለት ሞከረች ምን እንደሆነች ለራሷ እንኳን ሳይገባት ውስጧ ተከፍቷል ውዱእ ሊያረጉ ከተቀመጡበት ሲነሱ ወደሷ ዙሮ
"በነገራችን ላይ ይቺ ማያ ምትያት ልጅ ማቃት ይመስለኛል 11 እያለው የጓደኛዬ ፍቅረኛ ስም እንደዚ ነበር ታሪካቸውም ይመሳሰላል"
"ይሆናል ነገ እናያለን"ውስጧ ጥሩ ስሜት እየተሰማት ስላልሆነ ልታስከፋው ስላልፈለገች ቶሎ ከፊቱ ተሰወረች ውዱእ አርገው ሊሰግዱ ሲገቡ የሀፍሲ እናት እየሳቁ
" እናንተ ወረኞች ትናንት ተዋውቃቹ የአመት ጓደኞች መሰላቹ እኮ"ሲያወሩ በመስኮት እያዩዋቸው እነሱን ላለማቋረጥእስከ ዙሁር ድረስ ዝም ያሉዋቸው ዙሁር ሰግደው ምሳ በልተው ሰሚርን ሸኝተው ሲመለሱ ሚፍታህ ሀፍሲን እድትመጣ በእናቷ ያስጠራታል መጣላታቸውን ረስታ እንዳኮረፈች ዝም ብላ ክፍሉ ገባች ሀፍሲ እዚ ትሁን እንጂ ሀሳቧ ሁሉ ሌላ ቦታ ነው ሚፍታህ ሲያያት ፈገግ ብሎ
"ሀፍሲዬ እንደተከፋሽብኝ አውቃለው እንደበደልኩሽም ታውቆኛል አፉ በይኝ የኔ ውድ እህት አንቺ እንደምትፈልጊው እሆንልሻለው"
"እሺ"በመልሷ ግራ እየተጋባ ተመለከታት ፊቷ ሌላ ያስከፋት ነገር እንዳለ ያስታውቃል
"ሀፍሲ ያስከፋሽ ሰው አለ እንዴ"
"የለም"
"ምን ሆነሽ ነው ታዲያ እንዲ ፊትሽን የጣልሽው ነይ እስቲ ወደኔ"ብሎ በተኛበት ወደ ደረቱ አስጠግቶ አስተኝቶ አቀፋት የዚ ጊዜ ታምቆ የነበረው ሀዘኗ ሁሉ ወጣ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ሚፍታህ ደንግጦ ዝም ብሎ እያዳመጣት ነው ትንሽ ቆይቶ
"ሀፍሲ ምን ሆነሽብኝ ነው የኔ ውድ በአላህ አታስጨንቂኝ ንገሪኝ"
"ሚፍቱ አንተን እያልኩ እኮ እኔም ልጨመር ነው"
"ማለት?"ግራ ተጋብቶ
"ፍቅር ያዘኝ ሚፍቱ"የሰማው ቃል ከሀፍሲ መሆኑ እያጠራጠረው በድንጋጤ አፉ እየተሳሰረ
"ም…ም…ን?"……


★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
4.2K viewsᗰᑌᗩᘔ, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 21:36:00
በግሌ ቅር ያሰኘኝ ሀሳብ

መስጅዶች የከተማ ውበትና ድምቀቶች እንጂ ለከተማ ልማትና ውበት የማይመጥኑ አይደሉም።

እንደዛ ከሆነ ለከተማ ውበት የሚመጥነው መጠጥ ቤት ሲስፋፋ ነው

በወርቅም ይሰራ በጭቃ መስጊድ አላህ ጋር አንድ ነው ዋጋቸው

    ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
5.1K viewsMᴜᴀᴢ, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 20:07:27 ለፍቅር ፊዳ ክፍል 25 ዛሬ ይለቀቅ??


@ikhlaastudents
4.7K viewsᗰᑌᗩᘔ, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ