2023-05-13 21:48:45
« ከጥሩ ባል መገለጫዎች
በጥቂቱ ፡-
➧በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል
➧ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል
➧በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል
➧ለሚስትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል
➧ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም)
➧ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል
➧ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል
➧ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል
➧በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም
➧ትርፍ ቃል ከመናገር በመታቀብ በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል
➧ሚስቱ አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም
➧ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ ስሜቷን ይጋራል
➧ከሚስቱ ጋር በመተባበር ልጆቹን በኢስላማዊ አደብና እውቀት ቀርጾ ያሳድጋል።
➧ሚስቱ ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይህን ያደርጋል የመላ ሰውነቱን ንጽህናም ይጠብቃል
➧ቤቷን ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም አልፎ የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል።
➧ለቤቱ በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ያመሰግናታል ድምበር ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል
➧በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና ትዕግስትን ተላብሶ ይኖራል
➧አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም ሚስቱን እንደ እህቱ በመቁጠርና ለሷ በማዘን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና ቁጣውን ዋጥ በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል::
➲አሏህ ጥሩዎች ያድርገን
ላገቡትም ላላገቡትም መልካምና ስኬታማ ትዳር ይወፍቀን::
@ikhlasstudents
||ikhlas Tube
6.4K viewsMᴜᴀᴢ, 18:48