Get Mystery Box with random crypto!

ikhlas Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube I
የቴሌግራም ቻናል አርማ ikhlasstudents — ikhlas Tube
የሰርጥ አድራሻ: @ikhlasstudents
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.73K
የሰርጥ መግለጫ

በዱንያም በአሄራም አላህ ስኬታማ ከሚሆኑ ሰዎች ያድርገን
@ikhlasstudents
አስታየት ካላችሁ @muaz_mb ሊያገኙን ይችላሉ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-15 03:53:38 ለይለተል ቀደርና ምልክቶቿ
=================
ክፍል:-③
①) ፀሀይ ትወጣለች ምንም ጨረር የሌላት ሆና ብትመለከታት እንኳን አይንህን አትወጋህም ምክንየቱም…
||
እስኪ አንድ ጥያቄ ላንሳ የለይለተል ቀደር ለሊት ቀን መላኢካዎች እንዲሁም ጅብሪልም ሳይቀር ይወርዳሉ የሚወርዱት ለምን ይመስላችሁል?

መላኢካዎች ወደምድር የሚወርዱት አንተ/ቺ ዱዓ ስታደርግ/ጊ «አሚን» ይላሉ አስባችሁታል ዱዓ አድርጋችሁ መላኢካዎች "አሚን" ተቀባይነት ያግኝ ሲሉ አላህ ይወፍቀን።
ወደዎናው ሐሳቤ ስመለስላችሁ…ምን ላይ ነበርኩ አስታውሱኛ¡
*
ፀሀይ ስትወጣ ጨረሯ ይደክማል ላይ ነበርኩኣ! ለምን ይመስላችሁል የሚደከው?

እንዲሚታወቀው ፀሀይዎ መውጣት ስትጀምር፣ ሲፈጅር ወደ መሬት የወረዱት በጣም ብዙ መላኢካዎች ወደ ሰማይ ይወጣሉ፣ ሲወጡ ፀሀይ የምትለቃቸውን ብርሃን ይጋርዱታል በዚይም ምክንያት ፀሀይ ብርሃኗ ደካማ ሆና ትወጣለች።
*
«በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች»፡፡
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ሙስሊም ዘግበውታል

②) ለሊቱ የተረጋጋ ሰላም ያላት ሌሊት ሞቃታማም ብርዳማም የማትባል ነፋሳማ ለሊት ናት።

③) ቀለል ያለ ዝናባማ ለሊትም ልትሆን ትችላለች ተብሏል።

④) ጨረቃዎ የሰሀን ግማሽ ሆና በደንብ ትታያለች።
||
አላህ ይወፍቀን
#ወሰላሙዓለይኩም

#ሼር_አድርጉት

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
3.6K viewsMᴜᴀᴢ, 00:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 05:06:56
የእስልምና ውበት በተግባር

ሼይክ Ebit Lew ይባሉ ማሌዥያዊ ሼይክ ሲሆኑ ስለነዚህ ሴቶች እንዲህ ይላሉ።
" ማታ ከተራዊህ ሶላት በኋላ በጃካርታ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ለደዓዋ ወጣሁ። እነዚህንም ሴቶች አገኘውሃቸው። ሴቶቹ በጃካርታ ጎዳናዎች ላይ በሴትኛ አዳሪነት የሚተዳደሩ ወጣቶች ናቸው።

ጠጋ ብዬ አናገርኳቸው በዚህ ስራ ላይ ለምን እነደተሰማሩም አስረዱኝ። አብዛኛዎቹ የዕለት ኑሮዎቻቸውን ለመግፋት ገቢ በማጣታቸው፣ ሌሎቹ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ገሚሶቹ ደግሞ በቤተሰብ እጦት እና ሌላም ሌላም ነገሩኝ ። ባጠቃላይ ለዚህ መጥፎ ስራ ያበቃቸው ችግር መሆኑን ነገሩኝ። ውስጤ በጣም አዘነ ። እኔም ከዚህ ስራ መውጣት እንዳለባቸውና አላህ የተሻለ ነገር እንደሚለግሳቸው። ነገርኳቸው። እጅግ አዘኑ በነገርኳቸው ነገር አለቀሱ ።ብዙ ነገር አወራን ስህተት ላይ መሆናቸውንና ከዚህ ስራ እንደሚወጡ አረጋገጡልኝ። በመጨረሻም የአላህን ከንድነት በመመስከር ወደ ኢስላም ብርሃን ተመለሱ። "" ይሉናል።

እንዴት ያለ ስብዕና ! እንዴት ያለ ተሰጥዖ ነው? ሰዎች በሚሰሩት መጥፎ ስራ ሰውን ማንቋሸሽና እነሱን እንደ መጥፎ ምሳሌ ከመጠቀም በቀር እንደዚህ አይነት ቦታ ላይ ወርዶ የሰው ችግር አዳምጦ የሰውን ችግር ቀርፎ ወደ ዲን መጣራት !! አጂብ ነው!!!!!


በሀገራችንም መሰል ተግባር ላይ የተሰማሩ እህቶቻችንን ችግሮቻቸውን አዳምጦ ወደ ትክክለኛ መንገድና ህይወት የሚጠራቸውን መሰል ጀግና አላህ ይስጠን
#አሚን
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
4.0K views𝕞𝕠𝕙𝕒𝕞𝕞𝕖𝕕 𝕪𝕚𝕞𝕒𝕞 , 02:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 03:47:04 ለይለቱል ቀድር
==========
ክፍል:-②
ለይለቱል ቀድርን መቼ እንፈልጋት?
ለይለተል ቀድር እጅግ የምትገመተዋ ለሊት 27ኛዋ ለሊት ናት፣ ለዚህም ነብዩ
(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ማስረጃ መሆን ይችላል፡-
«ለይለተልቀድርን በ27ኛው ለሊት ውስጥ ፈልጓት»፡፡
ሙሐዲሱ ሸይኽ ሶሒሕ ብለውታል
*
ላሂቅ ቢን ሐሚድ እና ዐክረማ እንዲህ ብለዋል፣ ዑመር (ረድየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ብለው ጠየቁን፣ «ከናንተ ማነው ለይለቱል ቀድር መች እንደሆነ የሚያውቅ?»

እነሱም መልሰው እንዲህ አሉ፣
«ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምተናል "እሷ ለይለቱል ቀድር
በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ናት፣ ሰባት ሲያልፍ፣ አልያም ሰባት ሲቀር" አሉ።

«ይህም 23ኛው ለሊት ወይም 27ኛው ለሊት»።
ምንጭ:- ሙስነድ አህመድ ቁ(2543)

«አንድ ሰው ወደ ነብያችን በረመዳን
መጥቶ እንዲህ አላቸው የ አላህ ነብይ ሆይ! እኔ ታማሚ ሽማግሌ ነኝ አላህ እንዲወፍቀኝ በ አንዷ ለሊት እዘዘኝ አሉ።
ነብያችንም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «27ኛዎን ለሊት ያዝ» አሉት።
ምንጭ:- ሙስነድ አህመድ ቁ(2149)

በሌላ ሐዲስ ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስርት ቀናቶች ፈልጓት በተለይ በጎደሎ በውትር ቀናት ማለትም በ21,23,25,27 እና በ29 ፈልጓት ብለውናል።

«ለይለተልቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ ለሊቶች በዊትሮቹ
ፈልጓት»፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ይህ ማለት ግን ከናካቴው በሸፍዕ (Even) ለሊቶችም ማለትም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ለማለት አይደለም፡፡

ይህንንም ከሚያስረዱን ማስረጃዎች አንዱ ነብዩ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ለይለተል ቀድርን በረመዳን የመጨረሻዋ ለሊት ላይ ፈልጓት» ማለታቸው ነው፡፡

ስለ ለይለተል ቀድር በጣም ብዙ ዘገባዎችና በቀላሉ ወደ 40 የሚጠጉ አቅዎሎች አሉ ነገር ግን የእኔ የመጀመረያ ምክሬ የመጨረሻዎቹን 10 ቀናቶች ሳትዘናጉ መፈለጉ በላጭ ነው ባይ ነኝ።

ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል» ብለዎልና አስሮቹን ቀን አደራ እንበርታ ያጀማዓ።


ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
||
ክፍል:-③ ይቀጥላል
√ የለይለተል ቀደር ምልክቶች…
#ሼር_አድርጉት
#ወሰለሙ ዓለይኩም

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
1.2K viewsMᴜᴀᴢ, 00:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 03:55:16 ለይለቱል ቀድር
==========
ክፍል:-①
#ሼር_አድርጉት
ለይለቱ-ልቀድር ማለት ምን ማለት ነው?
«ለይለተል ቀድር ማለት በአጭሩ የመወሰኛይቱ ሌሊት ማለት ነው፣ ይች ለሊት ትልቅ ቀድር ወይም ደረጃ ያላት ለሊት ናት በተጨማሪም ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ናት።
||
የለይለቱል-ቀድር ደረጃዎች:-
①) ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرٌِ۝
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (1)

②) በርሷ ላይ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች በተለየና ምንዳው የበለጠ ነው።
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-

لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٌٍ۝
መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (3)

③) በርሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ይላል፡-

تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٌٍ۝
በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (4)

④) ለሊቷ ዒባዳህ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት፡፡
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرٌِ۝
እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ቀድር (5)

⑤) የተባረከች ለሊት ናት።
አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ إِنَّا كُنَّا مُنذِرِينٌَ۝
እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ሌሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ እኛ አስፈራሪዎች ነበርንና፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (3)

⑥) በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜ እና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል፡፡
አላህም እንዲህ ብሏል፡-

فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٌٍ۝
በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አድዱኻን (4)

⑦) በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው፡፡

⑨) ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት
ነች፡፡
ነብዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
«ለይለተልቀድር አምኖ እና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል»፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል፡፡
ኢብኑልቀይም (ረሒመሁላህ) ይችን ንግግር ተናገሩ:-
«ለይለተልቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እርሷን
ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር፡፡ #በረመዳን አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? እንዴት እዘናጋለሁ?!» አሉ።

ለይለቱልቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?
ለይለተልቀድር የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው፣ ከረመዳንም ደግሞ በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ነው፡፡ ይህንንም የሚያስረዳን ነብዩ (ሰለላሁ
ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸው ነው፡-

«ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ፣ ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ "እሷ በርግጥም
የመጨረሻው አስር ላይ ናት" ተባለኝ» ማለታቸው ነው፡፡
*
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡-
«በሱ (በረመዳን) ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች፣ የርሷን ኸይር
የተነፈገ በእርግጥም "ትልቅ ነገር" ተነፍጓል»፡፡
አስ-ሶሒሕ

ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጥር ይገባል፡፡
ፁሁፍ ሲንዛዛ አልወድም እንዳላበዛባችሁ
ክፍል:-② ነገ ይቀጥላል…
④) ለይለቱል ቀድርና ምልክቶቹ?
⑤) ለይለተልቀድር በአይን ትታያለች?
⑥) የዚያች ምሽት ተወዳጅ ዱዓእ ምንድነው?
||
ሼር አድርጉት

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
2.9K viewsMᴜᴀᴢ, 00:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:13:12 የረመዷን ወርቃማ 10 ቀናቶች


የወራቶች ሁሉ አለቃ የሆነው ረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶቹ ደግሞ የወሩ ቀናቶች ቁንጮ ናቸው፡፡በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የምትገኘዋ ለይለቱልቀድር ደግሞ የቁንጮዎች ቁንጮ ናት፡፡

አስሩን ቀኖች (ሌሊቶች) በሙሉ ለይለተል-ቀድርን በማሰብ በዒባዳ ያሳለፈ ያለምንም ጥርጥር ለይለተል-ቀድርን ያገኛል።

ቡኻሪይና ሙስሊም ከእናታችን ዓኢሻ
እንደዘገቡት ነቢዩ ﷺ"የረመዷን 10 ቀኖች ሲገቡ መቀነታቸውን ያጠብቁ ነበር፣ ለሊቱንም በሙሉ በዒባዳ (በሰላት) ያሳልፉ ነበር፣ ባለቤቶቻቸውንም (ለዒባዳ) ይቀሰቅሱ ነበር" ብለዋል፡፡

ጅምርና መነሻ ላይ ሁሉም እኩል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮች የሚለኩት ግን በፍጻሜያቸው ነው፡፡ እስከመጨረሻው ታግሶ ስራውን አሳምሮ ያጠናቀቀ ይሸለማል፡፡ መጨረሻ ላይ የተሳነፈና ያበላሸ ግን ሽልማቱን በማጣት ወይም ከዛም በከፋ ነገር ሊቀጣ ይችላል፡፡

የረመዷን የመጨረሻ 10 ቀናት ላይ ይበልጥ ኸይር ስራ ላይ ልንተጋና መጨረሻችን ያማረ እንዲሆን ጥረት ልናደርግ እንጂ ልንዘናጋና ልንሰላች በጭራሽ አይገባንም፡፡

ኢብኑል-ጀውዚይ እንደሚሉት"ፈረስ እንኳ የእሽቅድድም ሜዳ ላይ የመጨረሻው ዙር ላይ ሲደርስ ኀይሉን አሟጦ ተጠቅሞ ሌሎች ፈረሶችን በመቅደም ከግቡ ላይ ቀድሞ ለመድረስ ይጥራል" ፣እነሆ ከፈረስ በላይ እንጂ በታች ልንሆን ፈፅሞ አይገባምና እኛም ወደ ጀነት በሮች በመልካም ስራ ልንሽቀዳደም ይገባናል፡፡

የረመዷን የመጀመሪያ አስርቶች ላይ ከነበረን የተሻለ ንቃትና ትጋት ሊኖረን ይገባል።

ሰራተኛ ስራውን ሲያጠናቅቅ የሚያገኘውን ደመወዝ በማሰብ የስራውን ድካም ተቋቁሞ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርገው ሁሉ እኛም የአላህን ውዴታና ጀነትን በማሰብ ነፍሲያችንን በማሸነፍ መልካም ስራ ላይ ልንበረታ ይገባናል፡፡ ሁኔታዎች ለመልካም ስራ የማያግዙበት ወቅትና ቦታዎች ላይ ሁሉንም ተቋቁሞ ከእኛ የሚጠበቀውን ማድረግና አላህ እንደሚፈልገው ሆኖ መገኘት ደረጃው ለዲን ብሎ ወደ ነቢዩﷺ የመሰደድ ያክል ነው፡፡

ኢዕቲካፍ በመግባት ከዓለማዊ ጉዳዮች ርቆ፣ ከዱንያ ግርግርና ወሬዎቿ ተነጥሎ፣ ዒባዳ ታስቦ፣ የተለያዩ የአምልኮ ተግባራትን መፈፀም እዚያው ለመዋልና ለማደር ጠቅሎ መስጊድ መግባት ማለት ነው፡፡ የቻለ አሥርቱን ቀናት ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላል፤ ያልቻለ የተመቸዉን ቀን መርጦ ኢዕቲካፍ ማድረግ ይችላል፡፡ ኢዕቲካፍ ነፍስን ያጠራል፣ ዉስጥን ያፀዳል፡፡ አሥርቱን ቀናት ኢዕቲካፍ ማድረግ የፈለገ ሰው ረመዷን 20 ቀን (ምሽቱ 21) ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መስጊድ ይገባና ነገ ዒድ ሲባል ከፀሐይ መጥለቅ በኋላ ይወጣል፡፡

"የሰው ልጅ ሆይ:- የተወለድከው ብቻህን ነው፣የምትሞተውም ብቻህን ነው፣ ቀብርም የምትገባው ለብቻህ ነው፣ ለምርመራ አላህ ፊት የምትቆመውም ለብቻህ ነው፣ጀነትም ይሁን ጀሀነም የምትገባው ለብቻህ ነው!" ታዲያ ነገ የምትድንበትን ኸይር ስራ ለብቻህ መስራት እንዴት ይከበድሃል?!?

ዛሬ ዱኒያ ላይ መስፈርቱን ያሟላ መልካም ስራ ከሰራን ነገ ኣኺራ ላይ በጀነት ስናርፍ ድካሙን በሙሉ እንረሳዋለን! ከዛም አልፎ የከፈልነውን ዋጋ እንንቃለን!

በወርቃማ አስርቱ ቀናት፣

1/ ኢዕቲካፍ በመግባት

2/ ቁርኣን

3/ ለራሳችንም ለሌሎችም የተለያዩ ዱዓዎችን በማድረግ በተለይም (አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ) የሚለውን ዱዓ ማብዛት

4/ ዚክር በማብዛት

5/ ሰደቃ

6/ ለሊቱን ሙሉውን -እስከ ሱሑር- በሰላት ብቻ ማሳለፍ የቻለ ይህን በማድረግ ይህን ያልቻለ ደግሞ ለሊቱን ከፋፍሎ በዚክር፣በዱዓእና በኢስቲግፋር እንዲሁም የቻልነውን ያክል ረዘም ያሉ 2/2 ረክዓ ሱንና ሰላቶችን በመስገድ ልናሳልፍ ይገባናል፡፡

አላህ ያግዘን ለይለቱል-ቀድርንም ይወፍቀን "ኣሚን"
ኡስታዝ አሕመድ አደም

@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
3.4K viewsMᴜᴀᴢ, 09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 05:37:01
ከላይ የምታየዋቸውን ፀዴ ፀዴ ልብሶች ነፆ በሚባል ዋጋ የምታገኙበትን አማራጭ ከ kemuti turkish fashion trend ይዘንላቹ መተናል። ለወንዶች የሚሆኑ quality ያላቸው ልብሶችን መርጠው Order ያድርጉ።

ለተከበሩ ደንበኞቻችን ለኢድ የሚሕሆን ልብስ ኦርደር መቀበል ጀምረናል ምትፈልጉትን ቶሎ አሳዉቁን for more ቻናላችንን ይቀላቀሉን
https://t.me/uhjkkg
https://t.me/uhjkkg
42 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 02:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 23:43:56
993 viewsМαнι ×͜×, 20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 19:36:07
#በመቐለ

ኑር የቁርኣን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ከትግራይ መጅሊስና ከኡሙ አይመን የልማትና ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር ረመዳን 26 በመቐለ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር አዘጋጅቷል።

በዚህ ታሪካዊ ክስተት ላይ ለመሳተፍ የሚከተሉትን አድራሻዎች ይጠቀሙ

0929501670
0913373697
0911285537

የኢፍጣሩ ፕሮግራም ላይ የበኩልዎን አስተዋፅኦ ለማድረግ ከፈለጉ
በንግድ ባንክ አካውንት ገቢ ማድረግ ይችላሉ
1000538765458

የአንድ ሰው የማስፈጠርያ ሙሉ ፓኬጅ
ዋጋ 250 ብር ።
Ali Amin
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
1.7K views𝕞𝕠𝕙𝕒𝕞𝕞𝕖𝕕 𝕪𝕚𝕞𝕒𝕞 , 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 06:03:59 #አሏህን_ምን_ልጠይቀው......???

=>አንድ ባለ ሀጃ( ባለ ጉዳይ) ዱአ
    ሲያረግ ምን ብል ይሻለኛል ብሎ
    አንድን ትልቅ የሀገራችንን አሊም
    ይጠይቃል
° ሀጅ ሙሳን እሳቸውም የየትኛውም
   ሠው ሀጃ በ ➎ ( አምስት ) ጥያቄዎች
   ይጠቃለላሉ።
☞ እነዚህ ከጠየክ ሀጃህን በሙሉ
    ያጠቃልልላሀል አሉት።

              ... እነሡም ...

➊ ማንኛውም ሠው አሁን
    ያለበት ሁኔታ አያረካውም።
    መድረስ ሚፈልግበት ቦታ አልደረሠ
☞ ለዚህ ውድቀቱ መንስኤዉ
=> ወንጀሉ • ነውና ከሁሉም በፊት
     ወንጀሌን ማረኝ ይበል።
=> ምህረት ይጠይቅ።

➋ ከተማረ በሆላ ሊሠጠው ስለሆነ
   የሚሠጠውን በደንብ እንዲጠቀምበት
   አፍያ( ጤና) ለግሠኝ ይበል።
=> የቀልብ በሽታቹህን፣ የአካል
በሽታቹህን ፣ የአስተሳሰብ በሽታቹህን፣ የስንፍና በሽታቹህን......
☞ በአጠቃላይ ሁሉንም አይነት በሽታ
    የምትፈውስ አፍያን ለምኑ አሉ።

➌ ሶስተኛ የምጠይቅህን
    አሳውቀኝ በሉ።
=> ይህ የተሠጣቹህን ፀጋ ባለማወቅ
     ከመጠየቅ ይጠብቃቹሀል።
☞ የማይጠቅማቹህን ከመጠየቅም
     ይገላግላቹሀል አሉ ሀጅ ሙሳ።

➍ አራተኛ በማላገኘው ነገር
     አታድክመኝ በሉ አሉ።
=> ይህ ጊዜንና ድካምን በከንቱ
     እንዳይባክን ይጠቅማል።

➎ በመጨረሻምየተብቃቃ ዱንያን
    ለግሠኝ በሉ አሉን።
=> ይህን የትልቅ ሠው ዱአ
    ለራሳቹህም ለእኔም ለወዳጆቻቹህም

 #ሌሎችም_ይወቁ_እስኪ_share_አድርጉ

@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
609 viewsMᴜᴀᴢ, 03:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 12:04:46 بسم الله الرحمن الرحيم، الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على رسول الأمين، وعلى آله واصحابه اجمعين.
اما بعد:-
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته!

በጥያቄ ልጀምር… ረመዳን እንዴት ነዉ ወንድሜ? ወይኔ ምንም ሳልጠቀምበት ሊያልቅብኝ ነዉ እያልክ ነዉ ወይስ ምነዉ ቶሎ አያልቅም እንዴ ብለህ ተሰላችተሀል?
ኢባዳ ፈፅመህ ፈፅመህ ከበደህ እንዴ? ቁርዓን መቅራት፣ ዚክር ማለት፣ ዱዓ ማድረግ ደከመህ?

ይሀዉ ልብህን ላፅናናዉ መጥቻለሁ።

ምንም ያህል ቢደክምህም፣ ብርታትህ ቢዝልም እሷ ራሷ ዉስን ቀናት ናትና አትድከም ሀቢቢ!

ምኞቱ ጀነት የሆነ ሙእሚን ሰዉ ድካሙን ተቋቁሞ እንደበረታ ነዉ መቀጠል ያለበት። ሀሳቡና ግቡ ጀነት የሆነ ሰዉ በጭራሽ ሊደክም አይገባዉም።

ሀቢቢ! ነፍስህን ኢባዳ ሲከባዳት ልብህን መታ አድርግና ‘ጀነትን አትፈልግም እንዴ?’ በላት። ‘ያቺ ነቢይህ ያሉባት ሀገር አትናፍቅህም እንዴ?’ በላት። ‘የነቢያት፣ የእዉነተኞች፣ የሰማእታት፣ የደጋግ ሰዎች ጎረቤት መሆን አያምርህም እንዴ?’ በላት።

ሀቢቢ! ነፍስህን  ኢባዳ ሲከብዳት ልብህን መታ አድርግና ‘ያን ዉቡን የአላህን ፊት ማየት አይናፍቅህም እንዴ?’ በላት።
‘አይዞህ ጥቂት ቀናት ነዉ ከዚያም አላህ ካለ ኺታሙ ጀነት ነዉ።’ በላት።

ሀቢቢ! ያለፈዉ አልፏል። በኢባዳ ጠነከርክም ተሳነፍክም የፈፀምከዉን ይዞ ሂዷል። አሁን የቀረዉ ደግሞ ካለፉት በሙሉ የሚበልጥና በብዙ እጥፍ የሚሻል ነዉ። እናም ከየትኛዉም ጊዜ በላይ መበርታት አለብህ።

የመጨረሻዎቹ አስርቱ ቀናት ዉስጥ አላህ ለኛ ያስቀመጠለን እጅግ ምርጥ አጋጣሚ አለ። አላህ በአንዲት ሌሊት ዉስጥ ምትፈፀምን ኢባዳ ለ1000 ወር ከሚፈፀም ኢባዳ በላጭ አድርጓታል። አላህ ብሎ ያቺን ቀን የተወፈቀ ሰዉ በርግጥም መልካም ነገርን ተወፍቋል።

በምሳሌ ላስረዳህ…
እንበልና በዚያች ሌሊት ዉስጥ 1ጁዝ ቁርኣን ከቀራህ ለ1000 ወር 1ጁዝ ከመቅራት በላይ ኸይር ይፃፍልሃል። ከጨመርክ ይጨመርልሃል።

እንበልና በዚያች ሌሊት ዉስጥ ሁለት ረከዓ ከሰገድክ ለ1000 ወር ከሰገድከዉ ሁለት ረከዓ በላይ አጅር ታገኛለህ። ከጨመርክ ይጨመርልሃል።

እንበልና በዚያች ሌሊት ዉስጥ ዚክር ካደረግክ ለ1000 ወር ዚክር ከምታረገዉ በላይ ምንዳ ይፃፍልሃል።

እንበልና በዚያች ሌሊት 1ፆመኛን ካስፈጠርክ ለ1000 ወር ፆመኛን ካስፈጠርከዉ በላይ ምንዳ ታገኛያለህ። ከጨመርክ ይጨመርልሃል።

ባጭሩ ወንድሜ በነዚያ አስርቱ ቀናት ዉስጥ ነፍስያችንን አሸንፈን ከየትኛዉም ጊዜ በላይ በኢባዳ መጠንከር አለብን። አላህ እኔንም፣ አንተንም፣ አባቶቻችንንም፣ እናቶቻችንንም፣ መላዉ ወዳጆቻችንንም በዚህ ወር ከእሳት ነፃ የተባሉ ሰዎች ያድርገን!

በፆሙ ስላስረዘምኩኝ አፉ በሉኝ!!


@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
@ikhlasstudents ||ikhlas Tube
1.9K viewsMᴜᴀᴢ, 09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ