Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-12-06 10:34:17 የማለዳ ማስታወሻ #147
.
ገና ነን. . .ሕይወትን ለመፈረጅ፣ መንገዳችንን ለመተርጎም፣ ኖርን ለማለት።ገና ገና ነን!
.
ምድርን ዐይተን መቼ ጨረስን? የምሥራቋን ፀሐይ፣ የምዕራቧን ጀምበር ውቅያኖስ ጠርዝ ላይ መቼ ተመለከትን? ተራራዎችን መቼ ወጣን? ሸለቆዎችን መቼ አቋረጥን?
.
ነገሩ ስላለማቆም ነው። ባሰብነው ልክ ባይኾን እንኳ በቻልነው መጠን ስለ መንቀራፈፍ! የሚያሰጥም በሚመስል ግዙፍ ውኃ ላይ በትዕግሥት ስለ መንሳፈፍ! የምንመኘውን ያክል ብርቱ ባንኾንም ወደ ነገ እጅን ለመስደድ ስላለመስነፍ። ይኼው ነው የሕይወት ውል። ዘወትር በሙከራ ውስጥ ራስን መዝፈቅ።
.
ብዙ ሞክሮ ያልተሳካለት የለም። ያልተሳካለትም አልከሰረም። በብዙ ሙከራ ውስጥ ተዓምር አለና ከሞከረው የበለጠ ጣዕም ያለው በለስ ይገጥመው ይኾናል።
.
ገና ነው። ፈርጀ ብዙ መንገድ ይጠብቀናል። የደከምንለት ገና መቼ ካሠን? የወደቅንለት መቼ አስከበረን? ከራሳችን አልፈን ለምንወዳቸው መቼ ተረፍን? ሕይወትን መቼ ዐየን? "ዓለም ዘጠኝ ናት" ሲባል አልሰማህም? ዘጠኙም ዓለም በሕይወትህ እስካልመጣ ኖርኩኝ አትበል። ገና መጀመራችን ነው. . .ያንተን ታሪክ ለመስማት ጆሮዎች እስኪጓጉ ድረስ አትቦዝን. . .ብዙዎች አንቺን ለመኾን እስኪመኙ ድረስ መሞከር አታቁሚ። ሌላው ካሰበበት ከደረሰ እኛን ማን ይከለክለናል? ገና ነው!!!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
742 viewsFa, 07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 16:36:25
. . .of the day!
847 viewsFa, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 18:35:34 ስለ እኔ. . .እኔው ላውራ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
937 viewsFa, 15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 20:36:48
. . .of the day!
1.3K viewsFa, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 08:22:13 የማለዳ ማስታወሻ #146
.
"ዝናብ እንወዳለን" ያሉት ሲዘንብ ዣንጥላ ዘርግተው ዐይቻለሁ። ፀሐይ የሚወዱት ከፀሐይ ሸሽተው መጠለያ ሥር ሲውሉ አስተውያለሁ። "የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ!" ያሉኝ የተፈጥሮ ጸጋቸውን በዘመን አመጣሽ ብልሃት ሲጋርዱ ታዝቤያለሁ።
.
"እውነት ለሰው ልጅ መሠረታዊ ነገር ነው!" ብለው ሰይጣን ሚያስቀና ውሸት ይዋሻሉ። ግልፅነትን ከልሳናቸው ዘርተው ሁለመናቸውን ይደብቃሉ። ብዙ የኖረ ትልቅ ሰውነት ይዘው የጨቅላ ጣት በምታክል አዕምሮ የሚኖሩ ሰዎች ገጥመውኛል። ሰይጣንን አጥላልተው የሚኮንኑ ግን ከሰይጣን የከፉ ሰዎች በሕይወት መንገዴ ላይ ቆመው ያወቃሉ።
.
ምላስ ያለው፣ልሳን የታደለ ሁሉ ቃላትን እንደዋዛ ይተፋል። ቃል የማንነት ማሣያ ሽንቁር መኾኑን ዘንግቶ። በብዙ ስብራት፣ በእልፍ ትዝብት፣ በአይቆጠሬ ክህደት ውስጥ አልፌ ከሰው የሚወጣ ቃል ባላምን ትፈርጂብኛለሽ?
.
"እወድሃለሁ!" ስትይኝ ጠባሳዬን አልፎ ልቤ ጋር ባይደርስ ጥፋቴ ምንድነው? ይኼን እያወቅሽ ንፁሕ የፍቅር ቃላት የወረወርሺው አንቺስ ምን አጠፋሽ? አንዳንዴ. . .አልፈን የመጣነው ገሃነም የገነትን መግቢያ ይጋርድብናል!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
360 viewsFa, 05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 17:41:41 መልዓኳ አንቺ፣ሰይጣኑ እኔ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
እንኳን የቁም ፀሎት፣
አይሰምርም ተዓምሩ፣
ተቃርኖ ነበርንና ፊትም ከጅምሩ።
ልብሽ የጠቆረ፣
ክፋት የቋጠረ፣
መልዓክ ነበርሽ አንቺ፣
ቅድስና ይዘሽ፣ጽድቅን የምታጪ!
.
ሰይጣን ነበርኩ እኔ፣
በመልኬ ሳቢያ ግብሬ እንዳይጠወልግ
በእሳት ገሃነም ውስጥ ሰላም የምፈልግ!
.
@huluezih
@huluezih
1.2K viewsFa, 14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 08:28:42
. . .of the day!
438 viewsFa, 05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 21:12:34 ዘ ፍጥረተ ጥም
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ብታይል. . .ብትፈረጥም፣
ኑሮህ እንደ ወይን እያደረ ቢጥም፤
ከጊዜ አትበልጥም!
ምንጭ ዳር ተኝተህ ትሞታለህ በጥም።
ዕጣ ፈንታዬ ኾኖ. . .
በጥም የሞተን ገላ፣
በእጆቼ ገነዝኩኝ፣
እኔ ከጥም ጋራ ስለተፈጠርኩኝ።
.
@huluezih
@huluezih
1.3K viewsFa, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 18:37:57
. . .of the day!
978 viewsFa, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 08:54:34 የማለዳ ማስታወሻ #145
.
ሕልም የሌላትን ሴት እፈራለሁ። ሕልሟ አግብቶ መውለድ ብቻ የኾነች ሴት ሳይ ደግሞ እሸማቀቃለሁ። አግብቶ መውለድ በተፈጥሮ የተሠጠ መንገድ እንጂ ሕልም መኾን አይችልም። ድመትም ፍየልም ሳያልሙ በተሠጣቸው አጭር ዕድሜ ውስጥ ወልደው ያልፋሉ። መጠለያ የሌላቸው የጎዳና ተዳዳሪ ሴቶችም ይወልዳሉ። ምክንያቱም መውለድ የተፈጥሮ ሕግ እንጂ ሕልም ስላለኾነ።
.
የማሕበረሰብ ቀውስ መድኃኒትም መርዝም ሴት ልጅ ናት። ሴት ቁሳዊ ስትኾን፣ እናት ለልጇ ዋጋ ስትተምን ቀሪው ማሕበረሰብ ቁስ አዳኝ ይኾናል። ተምራ፣ሠርታ እና ለፍታ መኪናም ኾነ ቤት መግዛት እንደምትችል ያልተነገራት ሴት ደስተኛ ቤተሰብ መመሥረት አይቻላትም። ደስተኛ ካልኾነ ቤተሰብ የወጣ ልጅስ ለማሕበረሰቡ ብሎም ለሐገሩ ምን መሥጠት ይችላል?(ከጨለምተኝነት ውጪ?)
.
አንጋፋው የራሺያ ደራሲ ማክሲም ጎርኪ "ሴት ልጅ ሁለተኛ ነፍስህ ናት!" በሚለው አምናለሁ። ከማመንም አልፎ ሴት ልጅ ከወንድ አንድ ደረጃ ከፍ ብላ የተቀመጠች ባለማዕረግ መኾኗን እቀበላለሁ።
.
ዘመናችን የሴቶችን ማዕረግና ክብር ከራሳቸው ከሴቶቹም የሸሸገ ይመስላል። አግብቶ ለመውለድ የተፈጠሩ እስኪመስል ድረስ ሕልም አልባ አድርጓቸዋል። ሴትነታቸው ፈተና እንጂ ፀጋ እንዳልኾነ ሁሉ በትዳር ውስጥ ከትግል ለመራቅ ሲጥሩ ይታያል።ይመስላቸው ይኾናል እንጂ ትዳር ውስጥ ያለው ፈተና ቢከፋ እንጂ አያንስም። ትዳር ውስጥ ያለውን ፈተና የሚቋቋም ትከሻቸው ሕልማቸውን ለመኖር ለሚጎሽማቸው የውጪው ዓለም ፈተናም ብቁ ስለመኾኑ ይጠራጠራሉ።
.
ትዳር በትክክለኛው ጊዜ፣ ከትክክለኛው የነፍስ አጋር ጋር ሲኾን ቅዱስ እና ብሩክ ነው። ሕልምን የሚሰዉበት ሳይኾን ሕልምን ለማሳካት የኃይል ስንቅ የሚቋጥሩበት ዓለም ነው።
.
ከአጠገባችን ብዙ ሴቶች እንደፈረስ የፊቱን ብቻ እያዩ ከነ ልጓማቸው ተድረዋል። ቤት ንብረት እና ገንዘብ ስላለው ብቻ አግብተው፣ሕልማቸውንና ዕውቀታቸውን ሰውተው በአንድ ጎጆ ውስጥ ይኖራሉ። ቤት እንደሚፈርስ፣ ንብረት እንደሚወድም፣ ገንዘብ እንደሚጠፋ አለማሰባቸው ውስጥ የማሕበረሰቤን ውደቀት አስተውለላሁ። ሐገር ለማቆም፣ መንገድ ለማቅናት መፍትሔ መኾን የሚችሉ እንስቶች "አልችልም" በሚል መረብ ራሳቸውን አጥምደው ሳይ አዝናለሁ። የሴት ልጅ የመጀመሪያው መስፈርት "ምን ታበላኛለህ?" የኾነ ጊዜ ነበር እንደማሕበረሰብ የከሸፍነው። ወንድ ልጅም የትዳር ጥያቄውን ተንበርክኮ በክብር ጥያቄ ሊያቀርብላት ለሚገባው ሴት " ከገንዘብ፣ ከመኪና፣ ከቤት ውጪ ምን ትፈልጊያለሽ?" ሲላት መውደቂያችን ላይ ተደላድለናል ማለት ነው።
.
ሴት ልጅ ሕልም ይኑራት፣ ለዓለም የሚተርፍ ሕልም። ሴት ልጅ ልብ ይኑራት፣ ለሐገር የሚበቃ። ሴት ልጅ ምንም ማድረግ እንደምትችል ስታምን የሚያገባት ወንድ ሳይኾን የምታገባውን ወንድ በልቧ ፈልጋ ታገኛለች።
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
486 viewsFa, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ