Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-07-06 18:27:29
. . .of the day!
5.4K viewsFa, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 14:35:21 Channel photo updated
11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 15:05:20 ለእንባሽ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ይገርመኛል እንባሽ፣
ከዓይንሽ የሚፈሰው፤
"ይኼን ያህል ጅረት...
እንዴት ያፈልቃል ሰው?"
(ያስብለኛል...)
.
ደሞ ቁስልሽን ሳይ. . .
("አቤት የአምላክ ሲሳይ!")
መኖርን ያህል ደም፣
በገፍ ተቀብቶ፤
እንዴት ይተዋል ሰው. . .
ይኽቺን ብቻ አንብቶ?
(ያስብለኛል)
.
(ቢኾንም. . .)
ከሕይወትሽ ትይዩ፣
ከእንባሽ ተዋስኜ፤
ለጽልመትሽ ሻማ፣
ለእንባሽ መሐረም ኾኜ . . .
ፀሐይሽ እስክትመጣ፣
ብርሃን እያዋስኩሽ፤
ሻማ አስጨብጬ፣
በንጋት ልክ እየሳልኩሽ።
(አለሁ!)
.
(ምናልባትም. . .)
ነፍስሽን አላውቃትም፤
የሚያበራሽ ሻማ አይገኝም የትም።
(ይልቅ. . .)
ሻማውንም እርሺው፣
ወደ ውስጥሽ ግቢ፣ብርሃኑን አምርቺ፤
ቃሌ ይገባሻል፣
የተቋጠረውን ሰንሰለት ስትፈቺ፤
ጽልመት ምታደምቂ. . .
ጨረቃ ነሽ አንቺ!
.
@huluezih
@huluezih
5.1K viewsFa, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 20:19:19
. . .of the day!
4.7K viewsFa, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 09:37:55
. . .of the day!
5.1K viewsFa, 06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 17:33:19
. . .of the day!
5.7K viewsFa, 14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 20:42:00
. . .of the day!
6.2K viewsFa, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 09:32:08 የማለዳ ማስታወሻ #137
.
ሰው መኾን ያስጠቃል። ሰውነትን የሚጋርድ የምትተማመንበት ግርዶ ከሌለህ። አጥቂህ ፈርቶ የሚተውበት መከታ ከፊትህ ካልቆመ ሰው መኾንህ ያስጠቀሃል።
.
እንደ ወጉ አምላኬን ነበር መከታ አድርጌ ራሴን የሸሸግሁት። እሱን ከተጠጋሁ ጠላት ይሸሸኛል ብዬ የተሰፈረልኝን ዕድሜ እየተጓዝኩት ነበር። ጊዜ ግን ጉድ አመጣ። አምላክን ፈርቶ የሚተወኝ ሰይጣን ብቻ ኾኖ ቀረ። ከሰይጣን የሚልቁ መምሕረ-ሰይጣናት የተደገፍኩትን የአምላክ አጥር ንቀው፣ ምክንያት ሳያሻቸው ጦራቸውን ሰበቁብኝ፤እሳታቸውን ጫሩብኝ። አምላኬ ዝም አለ። ደማሁ፣ተቃጠልኩ። እንደ ቅንጣት ተቆጠርኩ፣የደሜ ዋጋ ከጠል አነሰ። ቀለልኩ።
.
ከእኔ ቁስል የአምላኬን ዝምታ ፈራሁ። አደጋገፍ ስቼ የተደገፍኩት መስሎኝ ይኾን? ወይስ አምላክም እንደ ሰው ጨካኝ ነው? ከሞቴ ወዲያ ሊክሰኝ? ወይስ እኔንም ገዳዬንም ከምድረ ገጽ አጥፍቶ አዲስ ፍጡር ምድር ላይ ሊያሰፍር ነው? በዚህች ኪራይ ዓለም....ገልቱ ተከራይ ሲያጠፋ የዋህ አከራይም አብሮ መባረሩ አይቀር ይኾናል። አላውቅም።ነገን ፈራሁ። ሞቴን ሳይኾን አሟሟቴን፣ አመጣጡን አይደለም ዱካውን።
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
5.7K viewsFa, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:46:33 እቆማለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ሐዘን ሰርስሮ ኝ፣
መንፈሴ ሥር ቢገባ፤
አላባክንም እንባ!
እቆማለሁ. . .
በዘመመው ልቤ፣በቆሰለው ሀሞት፤
እንደ ወንዝ ዳር በለስ. . .
በቁሜ እስክሞት።
.
@huluezih
@huluezih
5.2K viewsFa, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 20:09:25
. . .of the day!
5.3K viewsFeysel Amin, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ