Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-06-22 18:53:01 ያለምነው አልቀረም፤ ‹ጥበብ› ተሞሸረች

‹የጥበብ ቤት› ዳግም ወደ መድረክ ተመልሳ በአፊቃሪዎቿ ታጅባ ትሞሸር ዘንድ መሰናክሎች ጥቂት አልነበሩም፡፡ ዓለም አቀፍ የቁርዓን ውድድሩን ጨምሮ በርካታ የቀጠሮ ማራዘሚያ ሰበቦች፤ ሰኔ 12 የመንገድ መዘጋጋት ያጀበው እክል በአላህ መልካም ፈቃድ ፉርሽ ሆነው ድግሱ እውን ሆኗል፡፡ መሳቅ፤ ማልቀስ፤ መዝናናት፤ መማር፤ መደንገጥ፤ ማኩረፍ፤ መባነን፤ መጫዎት፤ ማሰላሰል፤ መገረም፤ መጨነቅና ሌሎች አያሌ ስሜቶች በግጥሞች፤ ወጎች፤ እንጉርጉሮ፤ ዳዕዋ፤ ተውኔት፤መነባነብ፤ ነሺዳ፤ አነቃቂ ንግግር፤ ካሊዮግራፊና በድንቅ ታዳሚውን ያሳተፉ ፈጠራዎች ተኮርኩረዋል፡፡ ለአዘጋጆች ጭምር እንግዳ የሆኑ አስደናቂ የመድረክ ትሩፋቶች በአዕምሯችን የሳልነው ሁሉ ስጋ ለብሶ እንዲታይ መሆኑ ይህንን የፈቀደው የነገሮች ሁሉ አስተናባሪ የተመሰገ ነው፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ እሁድ ዕለት የተሞሸረችው ‹ጥበብ› የቀጣይ ወር ጫጉላዋን ታስናፍቀናለች፡፡ አክብራችሁን የተገኛችሁ ሁሉ አላህ ያክብራችሁ፡፡ የዕለቱ ድግስ ያለፋችሁ በቀጣይ እንገናኛለን፡፡ ኢንሻአላህ!

የጥበብ ቤትን ድግስ በአካል ተገኝታችሁ መቋደስ ላልቻላችሁ፣

የጥበብ ቤት ዩ ቲዩብ ቻናል:–https://youtube.com/channel/UCCCWT7rEvbkTjFe8IceV2-w
የጥበብ ቤት ቴሌግራም ቻናል:– https://t.me/yehulubet
የጥበብ ቤት የፌስቡክ ገፅ : https://www.facebook.com/የጥበብ-ቤት-Yetebeb-Bet-106187998793025/

ለወዳጆቻችሁ ብታጋሩ ሁላችሁም ታተርፋላችሁ!
4.7K viewsFeysel Amin, 15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 19:18:29 እፈራለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
"ምን ያስፈራሃል?"
ብለሽ ስትጠይቂኝ. . .
"የእኩለ-ሌት ጽልመት፣
ድንግዝግዝ ጨለማ፣ወገግታ የሌለው"
አንቺን የማይበት. . .
ሽንቁር የጎደለው!"
ብዬ መልሼልሽ. . .
ዋሽቼሽ ዐውቃለሁ።
.
አዎ ዋሽቻለሁ. . .
ከፍታ አልፈራም፣ ስበት የራቀበት፣
አዎ ቀጥፌያለሁ. . .
ትግልን አልሰጋም፣የኑሮን አቀበት፤
ውሸት ከስሞ አያውቅም. . .
ከአፍቃሪ አንደበት።
.
ይልቅስ ፍርሃቴ. . .
ከሕልም ዓለም ፍቅርሽ፣
አንድ ቀን ስትነቂ. . .
ወደ ልቤ አድማስ. . .
ዘልቀሽ ስታበቂ. . .
ስለ እኔ 'ማውቀውን. . .
አንቺም እንዳታውቂ።
(እፈራለሁ!)
.
@huluezih
@huluezih
5.1K viewsFeysel Amin, edited  16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 16:06:52
. . .of the day!
5.4K viewsFeysel Amin, 13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ