Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-11-08 19:29:02
. . .of the day!
2.6K viewsFa, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-04 09:06:58
. . .of the day!
346 viewsFa, 06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 22:54:04
. . .of the day!
2.1K viewsFa, 19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 18:45:34
. . .of the day!
3.4K viewsFa, 15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-28 19:09:09 ድንገተኛ ማስታወሻ!
.
ትናንት አንድ ትልቅ ትምህርት አገኘሁ። "ምትክ" የሚባል ትምህርት።
.
ትናንት የተወለድኩበት ቀን ነበር። " እና ስለተወለድኩ ምን ይጠበስ?" የምል ዓይነት ሰው ነኝ። በቃ ተወለድኩ፣ በቃ አለቀ። የተለየ ነገር አላደረግኩም፣ ለማድረግም ጥረት አላደረግኩም። የሥራ ገበታዬ ላይ ተገኘሁ። የአዘቦት እንቅስቃሴዬን ማድረግ ጀመርኩ። በሶሻል ሚድያ ልደቴ መኾኑን ያወቁ ጥቂት ሰዎች መልካም ምኞታቸውን ገለፁልኝ።
.
በልባቸው ውስጥ ለእኔ የተለየ ቦታ ያላቸው ሰዎች ግን በዚህ ምኞት ማለፍን አልመረጡም ። ከሥራ ገበታዬ አፈናቅለው ጥሩ ጊዜ እንዳሳልፍ፣ የተወለድኩበት ቀን በመኾኑ እንድቀብጥባቸው ዕድሉን ሠጡኝ። ጥሩ ጊዜ አሳለፍኩ። እንዲህ ዓይነት ሰዎች ጥቂትም ቢኾኑ ዙሪያዬ ስላሉ አምላኬን አመሠገንኩ።
.
ትምህርቱ የመጣው ውሎዬን ስገመግም ነው ። እነዚህ ለእኔ የተለየ ሥፍራ ያላቸው ሰዎች የዛሬ ዓመት ልክ በዚህ ቀን ሕይወቴ ውስጥ አልነበሩም። የዛሬ ዓመት ሕይወቴ ውስጥ የነበሩ ሰዎች አሁን የት እንዳሉ እንኳ አላውቅም። በዚህ ዓመት ሕይወቴ ውስጥ ባይኖሩም እንኳ አንዳችም የጎደለኝ ነገር የለም ። አንዳንዴ ጤነኝነቴን እጠራጠራለሁ...እንዴት ያን ግዙፍ ቦታ የሠጣኋቸው ሰዎች ከሕይወቴ ወጥተው ደስተኛ ልኾን ቻልኩ? ከልሳናቸው ሲዘንብልኝ የነበሩት ብዙ ዘመን የሚንደረደር የሚመስሉ ቃላቸውስ ዛሬ የት ሔደ ? እንዴት የጎደለ ነገር እንዳለ አልተ ሰማኝም?
.
ለመማር ዝግጁ ከኾንን ሕይወታችን በትምህርት የተሞላ ነው። ወደ እኛ የሚመጡ ነገሮች ሁሉ ሁለት ዓይነት ናቸው ። አንደኛው አስተምሮ ለማለፍ የሚመጣ ሲኾን ሌላኛው እያስተማረ ለመቅረት ይመጣል ። በዚህ ዕድለኛ ነኝ ። ከእያንዳንዱ ሁኔታ ለመማር ጉጉ ስለኾንኩ ያልተማርኩበት ህመም የለም ። ለዘመናት አብረውኝ ያሉ እና የሚኖሩ ባለ ቀና ልቦችም ዙሪያዬ እንደ ሐረግ ተጠምጥመዋል ። ለእነሱ ደግሞ አመሥጋኝ ነኝ ። ትናንት ያገኘሁት ትልቁ ትምህርት ግን ማንም ቢሔድ የሕይወት ደንብ ነውና የሔደውን የሚተካ በትክክል ይመጣል ። ካስተዋልን ሔዶ ያልተካነው አንድም የለም። እናትህን ወይ አባትህን ብቻ ላትተካ ትችል ይኾናል እንጂ ሌላው ምንም ህመም ቢኖረውም ምትክ አለው። ይኼን በፍፁም አትርሱ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
2.0K viewsFa, 16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-26 17:02:30
. . .of the day!
2.7K viewsFa, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 18:41:00
. . .of the day!
8.1K viewsFa, 15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-20 20:23:36 አዲስ ጣዕም
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ዐውቀው ነበር ያንቺን ዓይን፣
አዲስ ጣዕም ሠጠኝ፤
ሲከርም እንደ ወይን!
አንገት ስትደፊ፣አንገቴን አሰገግኩ፤
ከስባሪው ልብሽ፣ የእኔን ግጣም ፈለግኩ።
ምቾቴን ስትሠጪኝ፣ምኞቴ ጠበበኝ፤
ከመንገድሽ ይልቅ፣አካሔድሽ ሳበኝ።
.
@huluezih
@huluezih
11.0K viewsFa, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 17:46:21 ተጋበዙልኝ



4.1K viewsFa, edited  14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 21:50:34 ግዴ-የለሽ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ወደ ቀኝ ብጋረድ፣
ወደ ግራ ብጠመድ፣
(ግዴየለኝም!)
ብቀር ተጋርጄ፣በሐገሬው ልጓም፣
ወደ ተሸፈነው ለመሔድ አልጓጓም !
.
ለማይተወኝ ሕመም፣
ለማይዘልቀኝ ዓለም፣
(ግድ የለኝም!)
የሚያቃጥል እንባ አፍስሼ ዐውቃለሁ፣
አሁን. . .
በእንባዬ ደንድኜ በደሜ እሥቃለሁ።
.
አምላክ ለመመ'ለክ. . .
ፈጠረ ኝ በባሪያ መልክ።
(መልስ የለኝም!)
መልኬን እንደ ሰው፣ልኬን እንደጠጠር፣
እንደ የት? እንደ ማን?
በምን ሥም ልቆጠር?
በሰው እሾህ ስታጠር?
ከእንባና ከበድኔ. . .
ምን አምልኮ ልፍጠር?
.
እንቅልፍ ያጣሁ ጊዜ፣
እንደገና ተኛሁ፣ወዲያ ጥዬ ትራስ፣
ሕልሜን ሳጣስ?
የማንን ሕግ ልጣስ?
.
እርግጥ ነው ባምንም፣
"ሞት አይቀር ለማንም!"
ሲሉኝ. . . በፍርስራሽ ቃል፣
አንጀቴ ይሥቃል!
ነፍስ ተሸክመን ስለ ሞት ስናስል፣
አኗኗሩ ጠፋን የመሰንበት ምስል፣
"መኖር ለማንም" የሚቀር ይመስል!
(ብኖር ግድየለኝም!)

@huluezih
@huluezih
3.7K viewsFa, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ