Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-10-13 11:45:41 የማለዳ ማስታወሻ #143
.
ሰው ዐይቻለሁ፣ሁሉንም ዓይነት ሰው። ለመልዓክ ከተጠጋ ንፁህ እ ስከ ግብረ-ሰይጣን ድረስ ዐይቻለሁ። ይኼን ሁሉ ዓይነት ሰው ከማየት አንድ ነገር ቀሰምኩ። ጎልተው በአዕምሯችን የሚመጡት፣ ከልሳናችን የማይጠፉት፣ ክፉ ሰዎች ናቸው። ክህደታቸው፣ ውሸታቸው፣ ክፋታቸው፣ ምቀኝነታቸው እና ራስ ወዳድነታቸው ዛሬም ድረስ ስናስበው ቢያልፍም ይጠዘጥዘናል፣ ቁጭት መንፈሳችን ላይ ጠባሳውን ጥሎ ስለሚያልፍ አንረ ሳቸውም። ስለ ጭካኔ፣ ስለ አረመኔነት ሲነሣ ሰርክ ዓይነ-ሕሊናችን ላይ ይውላሉ። ሰዎች ነንና የቱንም ያኽል ይቅርታ አድርገን በምሕረት ብናልፍ እንኳ ከይቅርታ ጋር ከልባችን የሚወነጨፍ የእርግማን ፍላፃ ወደ ሕይወታቸው ይወረወራል።
.
መጥፎ እና አረመኔ ሰዎች ዕድሜያቸው ረዥም ነው። የነኩት የሚበዛ፣ የዳበሱት የሚወዛ መሻታቸውን የሚያገኙ ኾነው እናያለን። ክፋታቸው ወይም መጥፎ ግብራቸው ተረስቶ ሳይኾን ከአወዳደቅ በፊት ለቅጽበት የሚደምቅ አቋቋም ስላለ ነው። ይወፍራሉ፣ ለመገርጠት አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው። ያካብታሉ፣ ለመደኽየት እርምጃ ሲቀርባቸው። ደግሞም ይረጋጋሉ፣ ለመተራመስ አንዲት ንጋት እስክትመጣ።
.
ሰዎችን ዐይተናል። ዙሪያችን ያሉ መልዓክትን ግን የረጋ ቦታ አልሠጠናቸውም። በሚነቃነቅ ድልድይ ላይ እጃቸውን የዘረጉልንን፣ በነዲድ በረሃ ውኃ ያ ስጎነጩንን፣ ነገን ለማየት አቅም አንሶን አንጠራርተው የነገን ጀምበር የጠቆሙንን ብዙ አንልላቸውም። ሲያልፍ ካለፈ ቀን ጋራ ባሉበት ጥለን ወደፊት እንጓዛለን። ሰው ነን።
.
ሁሉንም ዓይነት ሰው ስታዩ፣ ሰው መኾንን አትርሱ። በእኛ ሕይወት ውስጥ የሚዘረጋ እጅን ስንፈልግ በሌላው ሕይወት ውስጥ ግን እጅ የሚዘረጋ መልዓክ ነን። የቀረው ይቅር እንጂ ለቅጽበት ሰይጣንን አትኹኑ። ሰዎቹ ይቅር ቢሉን የጊዜ ሚዛን የፍርድ አረሩን ይዞ ያሳድዳችኋል። ሕይወት ቀላል ነው። እንደገና የመጀመር ብዙ ዙሮች ያሏት አጭር ሻማ ናት። መልዓኮቻችንን እያከበርን፣ ከታደልንም መልዓክ እየኾንን ነገን እንጠብቃለን። በእነዚህ አጭር ዙሮች ሊጥሉን የባተሉ ሰይጣናት እንደ ሾላ ሲረግፉ እያየን ጉዟችን ላይ ትንሽ መረማመጃ እናበጃለን። ብሩህ ቀን ከፊታችን እየጠበቀን ለምን በሰይጣን ሰዎች ምክንያት እንቆማለን?
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
3.8K viewsFa, 08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:29:52 "ግመሎች ይሔዳሉ፣ውሾች ይጮኻሉ!"
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የአጎብዳጅ እውነት. . .
በጩኸት!
የሰርጓጅ እምርታ. . .
በዝምታ!
ግመሎች ይሔዳሉ፣
ውሾች ይጮኻሉ!
ኡኡታም ሲረክስ
በዝንጀሮ ክስ. . .
እስክስ!!!!
ወደ ላይ ሲታገል፣ንፋስን ሲጋፈጥ፣
ወጡን ያባክናል፣ቅመም ለማጣፈጥ!
.
(Inspired by: Ayub Adem)
.
@huluezih
@huluezih
877 viewsFa, 14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 17:12:33
. . .of the day!
772 viewsFa, 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 13:32:23
. . .of the day!
966 viewsFa, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 21:08:20 እንቆቅልሽ መፍቻ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ሲዛነፍ ውላችን፣
ያሳለፍነው ጊዜ ጣዕሙ ተረሳ፣
ፀጋ በረከቱ ከእጃችን ተነሣ።
የሉም የነበሩት. . .
ጊዜዬን የገበሩት!
.
አሁን ላይ. . .
ልሙት ወይም ልኑር?
ልውደቅ ወይም ልቁም?
በፍፁም አያውቁም!
.
አልፈርድም በማንም፣
ጊዜ እና ሰው አላምንም!
.
እንቆቅልሽ መፍቻ፣
መች ታደልኩኝ አቅም?
ልሙት? ወይም ልኑር?
እኔ ራሴም አላውቅም።
.
@huluezih
@huluezih
581 viewsFa, edited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:50:53 ለአዳ'ኝ ሰባሪዎች
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የድባቴ ገደል ሐዘን እንዲበላኝ፤
የድቅድቅ ጎራዴ፣ ስለት እንዲቀላኝ፤
ጥረው ጡብ አቆሙ. . .
አዋጡልኝ ጠጠር፣
የፍካቴን ዕድሜ፣
ዘመን ለማሳጠር ።
መስበር. . .
ማጨለም፣
ማድቀቅ. . .
ማነከት. . .
ፈገግታ ለውሶ፣ተስፋ ለመፈንከት!
እውነቱ ግን ወዲህ፣
እንቅጩ ግን እንዲህ፣
.
.
.
"ምሬትን ተላምዶ፣የሰው ነፍስ ሲለግም፣
የተሰበረ ልብ አይሠበርም ዳግም!"
.
@huluezih
@huluezih
215 viewsFa, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 07:43:51 የማለዳ ማስታወሻ #142
.
ሩቅ ነኝ። ከቆምኩበት መሬት እንደ ሰማይ የራቅኩ ያክል ይሰማኛል። ከግቤ የተሰደድኩ ያክል እየሸሸሁ፣ ከዓላማዬ የተኳረፍኩ ይመስለኛል። ራሴን የሌለሁበት ቦታ ላይ የምፈልግ፣ አሁን የተገኘሁበት ሥፍራ ላይ እንግዳ የኾንኩ ያክል ባይተዋርነት ይወርረ ኛል። ዓለም የጠበበችኝ አልያም የሰፋችኝ ይመስለኛል። አጥር አልባ ሕይወት ውስጥ፣ ድንበር የለሽ ክበብ ውስጥ ራሴን ደጋግሜ አገኘዋለሁ። ሕጎች ስብዕናዬን የማያከብሩ ያክል ይጨቁኑኛል። የኑሮ ዑደቶች እየዞሩ ወደ ነበርኩበት የውዥቀት ዳስ ውስጥ ይመሉሱኛል። ራሴን እስክጠላው፣ ሰው መኾኔን እንደ መቅሰፍት እስክቆጥር ድረስ እወርዳለሁ። ወድቄ ለመነሣት ስል ደጋግሜ እወድቃለሁ። መሞከር ይደክመኛል። እያንዳንዱ ሙከራዎች ሌላ ህመም የሚፈለፍሉ መንገዶች ኾነው ይሰሙኛል። የትም የለሁም፣ የትም እገኛለሁ። ሁለት ዓይነት መንገዶች በትንሿ መቆሚያዬ ላይ ይታዩኛል። ወዴትም ባልሔድ እንኳ የየትኛውም ጎዳና እሳት ወደ እኔ የተረጨ ያክል ያቃጥለኛል። የቱም የእኔ አይደለም። የእኔ ጉዳይ ያልኾኑ ነበልባሎች ግን ወደ እኔ ከመስፈንጠር አይቦዝኑም። ገፈት ቀማሽ ነኝ።
.
ከዚህ ሁሉ ረመጥ ውስጥ የማይለየኝ አንድ ስሜት ብቻ ተስፋ ይሠጠኛል። የኾነ የማይታየኝ መፍትሔ እንዳለ ውስጤ ይነግረኛል። ከዚህ የእኔ ከማልለው ክበብ ውስጥ እንደምወጣ ይሰማኛል። የኖርኳት እፍኝ የማትሞላ ዕድሜ ሕይወት ላይ እና ታች እንዳላት አስተምራኛለች። ይኼ የሕይወት አንዷ የታች ገጽታ እንጂ የማይናውዝ ቋሚ ምስሏ እንዳልኾነ ይገባኛል። አንድ ቀን "የእኔ" የምለውና የሚመጥነኝ የነፍሴን ሥፍራ አገኘዋለሁ። የገፋኝ ሁሉ በጠመደው ወጥመድ ሊስበኝ ይሞክራል። ትናንቴን ረስቶ የጣለኝ ይሸከመኛል። አሁን ሩቅ ነኝ። ቅርበት ግን ሩቅ እንዳልኾነ ልቤ ይነግረኛል። ጊዜ ከአምላክ በታች ያለ ሌላ አምላክ ነው። የታቹን ወደ ላይ፣ የላዩን ወደ ታች የማድረግ ሥልጣን ተሠጥቶታል። የራቅኩትን ያክል ወደ ራሴ የምቀርብበት ጊዜ ይመጣል። ጊዜ ሁሉን ይለውጣል፣ ራሱ ጊዜም ይለወጣል።
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
339 viewsFa, 04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 13:16:10
. . .of the day!
1.3K viewsFa, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 15:34:09 ‹‹ሣቅሽ እና ነገ››

(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1.7K viewsFeYsel Amin, edited  12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 20:55:57
. . .of the day!
3.1K viewsFeYsel Amin, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ