Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-09 22:11:18 ትንሽ ነው የቀረኝ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በሰው ያለኝ ተስፋ፣
ከምድር ሊጠፋ፣
የመኖር ጉጉቴ ባዶ እጄን ሊያስቀረኝ፤
ትንሽ ነው የቀረኝ!
.
ሁሉን ውጦ መቻል፣
ሁሌም ይሰለቻል፣
የሞት ሞት ትግሌ፣"በቃ"ን ሊያስጀምረኝ፤
ትንሽ ነው የቀረኝ!
.
ክቦ ክቦ ማፍረስ፣
አፍርሶ መቀለስ፣
በልቤ መጫወት፣ከኮሶ መረረኝ፤
ትንሽ ነው የቀረኝ!
.
ሔጄ ሔጄ ጨቅላ፣
ዞሬ እምቦቀቅላ፣
ሳልኖረው ያለቀው፣ልጅነት አማረኝ፤
ትንሽ ነው የቀረኝ!
.
መብሰክሰክ. . .
መብሰልሰል. . .
ቀመርና ስሌት፣ሳስበው ቀለለኝ፤
"ትንሽ ነው" ያልኩትም. . .
ብዙ ነው መሰለኝ!
.
@huluezih
@huluezih
6.1K viewsFa, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 19:23:50
. . .of the day!
5.8K viewsFa, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 19:43:51
12.4K viewsFa, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 19:18:25 እመን!
አትፍራ. . .ፀልይ!
ግን ካላመንክ አትፀልይ፤
የሚኾነውን ያውቃል ልብህ እንደ ወልይ!
ፀለይን ክፉኛ፤
ለሰማዩ ዳኛ!
በስብራት ታገልን፣በታጠቅነው እንባ፣
ሰይጣን ለኾኑብን፣"እሳትህን" ጀባ!!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1.4K viewsFa, 16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:02:34
እናትነት የወለዱትን ማሳደግ ብቻ አይደለም!
.
አሳም በተባለ የሕንድ ቀበሌ ውስጥ አንድ ሰው ከአንድ ወዳጁ ላም ይገዛል።ላሟ ከተገዛች በኋላ ግን በአካባቢው ያልተለመደ እና የበረከተ የውሻ ጩኸት ገዢውን ሰውዬ አላስተኛ አለው። ምክንያቱን ማጣራት አለብኝ በማለት ሰውዬ ላሟ ያለችበት ሥፍራ ላይ ካሜራ ገጠመ። ከካሜራው ያገኘው ምስል ግን የማይታመን ነበር።
.
ዘወትር በሌሊቱ አጋማሽ አንድ ነብር ወደ ላሟ ይመጣና ሰላምታ ሠጥቶ፣ግንባሯን ልሶ ሥሯ ይወሸቃል። ላሟም ሥሯ አስቀምጣው ፀጉሩን ትልሳለች። ሌሊቱ ሊያልቅ ጥቂት ሲቀረው፣ ሰዎች የእንቅልፋቸው ማገባደጃ ላይ ሲደርሱ ነብሩ ላሟን በስስት ተሰናብቶ ወደ ጫካው ገብቶ ይሰወራል።
.
በዚህ የተገረመው የላሟ ገዢ ላሟን የሸጠለት ሰው ጋር ሔዶ ነገሩን ይነግረዋል። ሻጩ የነገረው ታሪክ አስደናቂ ነው።
.
የነብሩ እናት በሰዎች ስትገደል ይኽ ነብር ገና የ20 ቀን ዕድሜ ያለው ጨቅላ ነበር።ታዲያ ይኽች የእናት አንጀት የታደለች ላም የጡቷን ወተት እየሠጠች ሕይወቱን እንዲተርፍ ሰበብ ኾነችው።እናት ላጣ ነብር እናት ኾና ክፉ ቀኑን አሳለፈችለት። ዛሬ አድጎ፣ ጡንቻውን አፈርጥሞ ጫካ ቢገባም በእያንዳንዷ ሌሊት የላሟን ጠረን ተከትሎ እየመጣ ባለውለታውን ያመሠግናል። ዐየህ! እናት መኾን ማለት የወለዱትን ብቻ ማሳደግ አይደለም። እናት ለሚፈልግ ኹሉ እናት መኾን ማለትም ጭምር ነው!
.
@huluezih
@huluezih
1.6K viewsFa, 16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 07:40:26 የማለዳ ማስታወሻ #150
.
በልብ እና በአዕምሮ ጦርነት መሐል ነው የምንኖረው። ልባችን የከጀለው ነገር፣ አዕምሯችን ከሚያውቀው እውነታ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር የውስጣችን ሰላም ይደፈርሳል። አዕምሮ የመረጠው መንገድ የልባችንን መሻት እና ምኞት ስለሚሸርፍ የሚያቅበዘብዝ የልብ ምታት ውስጣችንን ያውካል። እንዲህ ነው የምንኖረው። እንዲህ ኾኖ መኖር ታዲያ ራስን አያስመሠግንም? ራስን አያስከብርም? "አሻም" አያስብልም? እኔ ራሴን "አሻም" እላለሁ!
.
ልቤ ተቀብሎት፣ ነፍስያዬ ከጅሎት ሩቅ እንደማያስኬደኝ ዐውቄ ልቤን ተጭኜ አዕምሮዬን ስለሰማሁት፣ ሰምቼም ቅር እየተሠኘሁ አቅጫዬን ስለለወጥኩ፣ በዛሬ ምቾትና ተድላ ነገዬን ስላልቀየርኩ. . "አሻም!" ለራሴ!
.
እንባዎች ቢረብሹኝም መንገድ ስላላሳቱኝ፣ ከራሴም አሻግሬ ለሰዎች ነገ ስል ራሴን ስለገደብኩ፤ ባላየሁት ቃል ላይ፣ ባልጣመኝ መስክ ላይ ጎጆ ስላልቀለስኩ፣ ልቤን ተጭኜ በአዕምሮዬ ስሌት ያለ እረፍት ጉዞዬን ስለቀጠልኩ. . ."አሻም!" ለራሴ!
.
ልቤን ያቆሰሉኝን እግሬ ሥር አግኝቼ ስላልተበቀልኩ፣ በገረፉኝ ጅራፍ ጎትቼ ከገደል ስላወጣኋቸው፣ የዋሹኝን ስላልዋሸሁ፣ የወጉኝን ስላከምኩ፣ ልቤን ሰምቼ ሒሳብ አወራራጅ አዕምሮዬን ተጭኜ የራቁኝን ባሉበት ደግ ስለተመኘሁላቸው፣ የጣሉኝን ስላነሣሁ . . "አሻም!" ለራሴ!
.
ግን አንዳንዴ. . . ሁሉም በጊዜው ቢኾንም... ያንን ትክክለኛ ጊዜ ሳላውቅ. . . "ልቤን? ወይስ አዕምሮዬን?" የቱን መከተል እንዳለብኝ ሳልወስን ለደፈርኩት አጥር፣ ለነካሁት ቁስል፣ ላስመሸሁት ትልም፣ ላደፈረስኩት እውነት፣ ላረፈድኩት ጥሪ፣ ላከሰምኩት ተስፋ፣ ላላላሁት ውጥን አዕምራችሁን ተጭናችሁ በልባችሁ፣ከልባችሁ ለሠጣችሁኝ "ይቅርታ" "አሻም!" ለእናንተ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1.2K viewsFa, 04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 17:48:41
. . .of the day!
1.2K viewsFa, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 19:36:08 የአምላክ ዝምታ እና ሹመት ከታደለ፤
የሰው ልጅ በጭፍን አያደርገው የለ!
አምላክ ቤትህ ፈርሶ. . .
ቂም ቋጥረህ እንደኾን፣
ታውቅ እንደሁ በቀል፤
መዘዙ ብዙ ነው አንተን ማፈናቀል!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
2.6K viewsFa, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 17:31:46
. . .of the day!
3.8K viewsFa, 14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 19:15:08
4.0K viewsFa, 16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ