Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-22 16:28:58
. . .of the day!
1.1K viewsFa, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 19:03:28 አንቺ የሌለሽበት አራተኛው ረመዳን
.
ጊዜው አይታክተው፣መጋለቡን አይተው፤ እኔም በተዛነፈው የሕይወት መንገድ፣ በተስፋ ባንኜ አንድ ስንዝር አልራመድ፤ አለሁ በቆምኩበት፤ አለሽ ባልኖርሽበት!
.
ሰውነቴ ውስጥ ደሜ እስካለ ድረስ በእያንዳንዷ ጠብታ ውስጥ የማያረጅ፣ የጊዜ ኃያል ቁር የማያፈዝዘው፣የማያደበዝዘው ዘላለማዊ ትዝታሽ፣ ጠረንሽ፣ ሣቅሽ፣ ምክርሽ፣ በአቅመ ቢስነት ዘመኔ በጡትሽ በኩል የመጠጥኩት ደግሞም የማጌጥበት የእናትነት ማርዳ አለ። ሰውነቴ ውስጥ ነፍሴ እስካለ ኖረሽ ባየሻቸው የምላቸው ተራ ቀኖች አሉ። ተራ ቀን ውስጥ ከተራነት የሚያወጣኝ የአለኝታ ጎህ፣ ከተርቲበኛነት የሚያላቅቅ ውድ ቅርስ አንቺ ውስጥ አኑሬያለሁና።
.
እንድደርስ የፈለግሺው ቦታ ላይ ልደርስ አንድ ሐሙስ ሲቀርሽ፣ አንድ ረቡዕ የጎደለሽ፣ ሁለገብ ኾነሽ በሕይወቴ እያንዳንዱ ጽንፍ ውስጥ የገባሽ፣ መንገዴን ለማቅለል ከእቶን እሳት የተባሽ፣ እኔን ለማቅናት ዘላለም የሚያጥርሽ፣ ያልጠረጠርሺው ነገር. . ."የትም መድረስ አይከብደኝም፣ ጎኔ ቆመሽ መቻሌን ቀድመሽ ካመንሽ!"
.
የረመዳን ወጋገኖች ያላንቺ ምሉዕ አያደርጉም።ያላንቺ ግን በትዝታ፣ በናፍቆት በፀፀት ያልፋሉ እንደ ጉም።
.
ከመራቅሽ አራራቅሽ! ከዙሪያ-ገቡ ቅኝት የውስጥ ውስጥ ጭርታው! ሰዎች መሐል ያለ ኦናነት! ከጭብጨባው ከአድናቆቱ፣ ስኬት ውስጥ የመሸገ ትርጉም አልባነት ልብ ይሰረስራል። የማይታይ ቀለም አልባ ገመድ አካሔድን ያስራል። እንዲህም ቀን ይቆጠራል፣ እንዲህም ዘመን ይበርራል። የትናንት ሞገደኛ ሣቆቻችን፣ የትናንት ሌሊት የማይበግራቸው ውይይቶቻችን ዛሬ ጥቁር ለምድ ለብሰው ብቅ ብለዋል። ጉልበቴ ልሟል፣ ሕሊናዬ ግን ባጣሽ ቀን. . .ባጣሽ ቦታ ላይ ሐውልት ኾኖ ቆሟል። ዘመን ግን እንዲህም ይቆጠራል፣ ጊዜ ግን ዛሬም ይበርራል። አንድ. . .ሁለት. . . ሦስት. . . እነሆ በሌለሽበት አራተኛው ውድ እንግዳ መጥቷል. . .
.
ረመዳን ሙባረክ ለሁላችንም!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1.7K viewsFa, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 18:11:55 አላውቀውምና. . .
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ከፋኝ፣
አኗኗሩ ጠፋኝ፤
የቆምኩበት ኩርማን፣ከምድሪቱ ሰፋኝ።
.
ሳሳሁ፣
አመጣጤን ረሳሁ፤
ውድቀቴን ለማድመቅ ታድሼ ተነሣሁ።
.
ከዳኝ፣
የጊዜ ቅኔ ጎዳኝ፤
ወዳለፍኩት እሳት፣ለመመ'ለስ ዳዳኝ።
.
ብቻ. . .
ብቻ. . .
እንቅፋቱም፣አፈታቱም
ከእኔው ኾኖ ሳለ፤
በነፍሴ ትከሻ፣ነበልባል ተሳለ!
በገዛ ፍርሃቴ ሕልሜ ተገደለ፤
አላውቀውምና ምኔ እንደጎደለ!
.
@huluezih
@huluezih
964 viewsFa, edited  15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 17:46:28 https://youtube.com/shorts/20FWgz0oGXg?feature=share
997 viewsFa, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 17:26:37
. . .of the day!
939 viewsFa, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 19:39:01 የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
ሳሞግስ ቀልብ የምሰልብ፤
ስተች ነውር የምገልብ፤
ከአባት አያቶቼ ሽለላ የተዋስኩ፤
በሰልፍና እንቅልፍ ዘመኔን የጨረስኩ !
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!)
.
በማሳ መሐል ኾኜ በረሃብ የተቀጣሁ፣
ዓለም ላይ ለመድረስ. . .
ትራንስፖርት ያጣሁ!
በታሪክ መሥሪያ ዕድሜ፣
ታሪክ 'ምተረጉም፤
የማያስኬድ መንገድ
ለሰው የምጠቁም!
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ)
.
ግፍ እና ጡር አምላኬን ያስረሣኝ፤
ፀበል ሙሉ ሐገር፣ልቤን ያላነፃኝ!
አርሼ ዘርቼ መሶቤ የከዳኝ፤
ከአረር ጥይት ይልቅ በጀት የሚጎዳኝ!
(የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!)
.
ቅሬታና ምሬቴን ከእልባት ለማድረስ
በጠረጴዛ ዙሪያ አድፍጬ ምቧቀስ
ጉልበተኛ ሲነካኝ. . .
"ልብ አድርጉልኝ!" እያልኩ ሁሉን የምታገስ!
የዚህ ሐገር ሰው ነኝ!
.
@huluezih
@huluezih
951 viewsFa, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 16:57:16
"ጽሑፍ ምን ያደርጋል?"
.
ከስምንት ዓመታት በላይ ከእኔ ጋር የቆየው ላፕቶፔ እስትንፋሱ ተቋረጠ። የስምንት ዓመታት ታሪኬ ብቻ አይደለም የወደመው። እንደ ሌሎች ደራሲያንና ጸሐፊያን በእስክርቢቶ ለመጻፍ ልምድም ዐውድም ስለሚጎድለኝ የወደፊት ጸሑፊቼም በአግባቡ የሚወለዱ፣ ቢወለዱም ስሜት አልባ ሚኾኑ ይመስለኛል።
.
"ሰው እንዴት በዚህ ልክ ከቁስ ጋር ረቂቅ የኾነ ትስስር ሊኖረው ይችላል?" እላለሁ ከኮምፒዩተሬ ጋር ያለኝን ቁርኝት ሳስተውል። ስለእኔ ከኮምፒዩተሬ በላይ ጠንቅቆ የሚያውቀኝ ያለ አይመስለኝም። ሐዘኔን፣ደስታዬን፣ ግራ መጋባቴን ሁሉ ከትቤበታለሁ። ተዝናንቼበታለሁ፣ ተጽናንቼበታለሁ. . .ደሞ አሻግሬ የሰዎችን ቁስል አክኬበታለሁ። ከቤተሰቤ አንዱን ያጣሁ ያክል ጠዝጥዞኛል።
.
በአምላኬና በኮምፒዩተሬ እገዛ ሁለት መጽሐፎችን ጽፌበት ለህትመት አብቅቻለሁ። መድረኮች ላይ የቀረቡ ሁሉም ጽሑፎቼ በዚህ እስትንፋሱ በተቋረጠው ላፕቶፔ በኩል ያለፉ ናቸው። ሦስተኛ መጽሐፌ 95% (ዘጠና አምስት በመቶው) የሚኾነው አልቆ ነበር. . .ግን ዱኒያ ውስጥ ያሉ ሁሉ የጊዜ ገደብ አላቸውና ላፕቶፔም የጊዜ ገደቡን ጥሶ አልፏል። አሁን ላይ ብዙም በስልክ ዘለግ ያለ ነገር የመጻፍ ልምዱ ስለሌለኝ ከጽሑፍ ራቅ ብያለሁ. . .የዚህም ቅሬታና ልዝብ ተስፋ መቁረጥ "ጽሑፍ ምን ያደርጋል?" እያስባለኝ ነው። ግን ሁሉም ለበጎ አይደል? በጎውን አያዘግየው

R.I.P dear
414 viewsFa, 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 21:05:34

703 viewsFa, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 20:23:27
. . .of the day!
1.0K viewsFa, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 21:47:08
. . .Of the day!
134 viewsFa, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ