Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-02-14 22:30:40 መክረውኝ ነበረ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
መክረውኝ ነበረ. . .
"ምንም እንኳ ቢራቢሮ. . .
በጉራማይሌ ቀለም ልብን ብትሰቅዝም፣
አትረጋም!
አታርፍም!
የእሷ ልብ አይያዝም!"
.
መክረውኝ ነበረ. . .
"የፈጣሪን ያክል የሰውን ልጅ ብትወደው፣
የክፉ ቀን ንፋስ ነው፣
ከጫንቃህ 'ሚያወርደው!
ዐወቅኩት አትበል. . .
ሲሞላህ፣
ሲደላህ፣
ሲተርፍህ ቀርበኸው፤
የሰው ልጅ ድብቅ ነው፤
ጎብጠህ ካላየኸው!
.
"ራስህን ብቻ እመን፣ልብህን አሰናዳ፤
አያያዝ አያውቅም ልቡ ያልተጎዳ!"
ብለው...መክረውኝ ነበረ. . .
ልቤ መጠርጠሩን ከእነሱ ጀመረ!
.
@huluezih
@huluezih
701 viewsFa, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 17:06:18

718 viewsFa, 14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 20:22:48
. . .of the day!
1.0K viewsFa, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 11:58:41

1.9K viewsFa, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 22:12:46
. . .of the day!
3.5K viewsFa, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 11:33:33
. . .of the day!
4.0K viewsFa, 08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 18:51:20 ድሮ እንደ አሁኑ የዴይ ኬር አገልግሎት በከተማው ሳይስፋፋ የዴይ ኬር አገልግሎት እሠጥ እንደነበር ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ አያውቅም። እኔ ራሴ የዴይ ኬር አገልግሎት በሚያስፈልገኝ ዕድሜ ላይ ሕፃናትን በብሔርና በፖለቲካ አቋማቸው ሳልለይ ሽንት ጨርቅ ከመቀየር ሙዳቸውን እስከመቀየር የሚደርስ አገልግሎት በነፃ እሠጥ ነበር።(በጎ ሰው ነበርኩ. . በግ ሰው ሳልኾን በፊት )
.
ይኼ ዐመሌ አብሮኝ አድጎ ዛሬ ከሕፃናት ጋር ሳናወራ በዓይን እንግባባለን። ልጆች የተለየ የፊት ገጽታ ያሣዩኛል። ሕፃናት ገና ሲያዩኝ "He is one of us!" የሚሉ ይመስለኛል። ሰሞኑን ታክሲ ውስጥ አንዲት ወጣት እናት ልጇን ከአሜሪካ በመጣ ማዝያ ደረቷ ላይ ሰቅላው፣ ፊቱ ላይ ደግሞ ለወጉ የሐበሻ ሻርፕ ጣል አድርጋበት አጠገቤ መጥታ ተቀመጠች። ልጁ ጠንቋይ መምሰሉ በእጅጉ አበሳጭቶታል። ዝም ብሎ ያለቅሳል። ልጁን ዝም ለማስባል ያልፈነቀለችው ጡት የለም። ርቦት እንዳልኾነ ሲገባት ምናልባት ዳይፐሩ አቃጥሎት ነው ብላ ከኋላ ያሉትን አራት ትርፍ ሰዎች አስነስታ ዳይፐሩን ቀየረችለት። በርግጥ ልጁ ለደቂቃዎች ለቅሶውን አቆመ። ጠረኑ ግን ሹፌሩን ጨምሮ ሙሉ ተሳፋሪውን አስለቀሰ።
.
ብዙም ሳይቆይ ልጁ ሁለተኛ ዙር ማልቀስ ጀመረ። ይኼ በመንመን ላይ ያለ ክህሎቴን ተጠቅሜ ልጁን ተቀብዬ ማጫወት ጀመርኩ። ወደ እናቱ ዞር ብዬ "ሥሙ ግን ማነው?" አልኳት የልጁ እኔ ላይ መለጠፍ አስግቶኝ።
"አዶናይ በለጠ" ወይ ደሞ "አዶናይ ደረጀ"
"ሁለት አባት ነው ያለው እንዴ?"
"አዎ...መቼም ከሁለቱ አያልፍም!"
"ወራጅ አለ!" ሦስተኛው ተጠርጣሪ ከመኾኔ በፊት ሰላሳ ብር የታክሲ ከፍዬ የሦስት ብር እንደሔድኩ ለመውረድ ተገደድኩ።
.
እና ምን ለማለት ነው . . .ለምን ዴይ ኬር አልከፍትም?
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
968 viewsFa, 15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 22:26:40
. . .of the day!
1.6K viewsFa, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 14:45:31

996 viewsFa, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 18:26:57 @huluezih
@huluezih
948 viewsFa, edited  15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ