Get Mystery Box with random crypto!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ huluezih — ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)
የሰርጥ አድራሻ: @huluezih
ምድቦች: ብሎጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.06K
የሰርጥ መግለጫ

ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-01 19:14:52 እነሆ አዲሱ ላፕቶፔን ተዋወቁት!
.
የተጠነሰሰ ነገር ኹሉ ጉዞው ወደ ማክተሚያው ነው። የተጀመረ ነገር ሁሉ የማይመለስ ማብቂያ አለው። ሕይወትም ማለት በጅምሯ እና በፍጻሜዋ መሐል ጉራማይሌ ቀለም ያላት አጭር መንገድ ነው።
.
ከአንድ ወር ገደማ በፊት የእኔና የላፕቶፔ ታሪክ ተፈፀመ። የእሱ ስብራት የእኔም ኾነ። ግን ብዙ ሰዎች አፅናኑኝ። መልካም ተመኙልኝ። ማድረግ ቢችሉ የሚያደርጉ ሰዎችን ዐየሁ። ግድ የማይሠጣቸውንም ሰዎች ለየሁ። ሕይወት ያለ "Apitite" ቀጠለ። (ቀና አስተያየትና መልካም ምኞታችሁን ያሰማችሁኝን ኹሉ እዚህ ጋር አመሥግኜ አልፋለሁ! )
.
በመሐል አንድ ወዳጄ ለዓመታት ከተጠፋፋን በኋላ ደውሎ ከሐገር እንደወጣ ነገረኝ። ክፉ ደጉን አብረን አሳልፈን ከዓመት በላይ ለሚኾኑ ጊዜያት ድምጹን አልሰማሁም።ያለበትን ጥግ አላውቅም ነበር፣ እሱም ያለሁበትን ሁኔታ ለማወቅ የሚያመች ሁኔታ ውስጥ አልነበረም።
.
በቃላት ልውውጣችን መሐል "ምንም እንኳ ገና በሰው ሐገር ኾኜ በሁለት እግሬ ባልቆምም ወይ ስልክ ወይ ላፕቶፕ ልግዛልህ!" ብሎ አጥብቆ ጠየቀኝ። የላፕቶፔን መሰበር አያውቅም። መናገርም አልፈለግኩም። ግን ለችግሩ ጊዜ የነበረኝን ሌላ ላፕቶፕ መሸጤንና ለእሱ ብዬ ብዙ መበደሬን ያውቃል። ለእሱ ውለታ መመለሱ ነበር። ልቤን የነካ ታሪክ ነው። ልበ-ቀና እና ከሚመኝልኝ ስኬት በላይ አብዝቼ የምመኝለት ፈርጀ ብዙ ሰው ነው! (አላህ ሂዳያ እንዲሠጣቸው ከምለምንላቸው ወዳጆቼ አንዱ ነው)
.
በጽሑፎቼ ይተማመንብኛል።"ብዙ መሥራት ትችላለህ" ብለው ከሚያምኑብኝ በጣት ከሚቆጠሩ ሰዎች ጎራ ነው። በመጨረሻም "ተቸግረንም ቢኾን ደህና ነገር እንግዛ!" ብሎ ትንሽ ብር ተበድሮ እና ጨምሮበት አዲስ እና ቀልጣፋ ላፕቶፕ ላከልኝ። አሁን ሥራዎቼ ካቆሙበት ይቀጥላሉ። የዛለ መንፈስ የሚያድስ ወዳጅ ኾኖ ብቅ አለ።
.
በዚህ ታሪክ ውስጥ ዋናው ትምህርት "አምላክህ የማይተካልህን ነገር አይነፍግህም!" የሚል ነው። የሚደግፉህን፣ ግድ የማይሠጣቸውን ጠጋኝ ቃል ከማቃበል ጀምሮ ለአንተ ያላቸውን ምልከታ በደንብ ተረድተህ ስታበቃ አምላክህ የነጠቀህን በተሻለ ይተካልሃል።
.
@huluezih
3.6K viewsFa, 16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 17:08:23 ልቤ ያምናል!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የቆለፈኝ ችንካር፣
ያለሁበት ስካር፣
ያይላል. . .
ይፈላል. . .ለአፍታ አይቀንስም!
እንኳን ወደ ህልሜ. . .
ወደ አልጋ አያደርስም!
ግን ልቤ ያምናል. . .
የጠለፈው አዚም እያንገዳገደው፤
"መነሣት ይችላል፣መውደቅ ያልከበደው!"
.
@huluezih
@huluezih
738 viewsFa, 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 22:41:13
ሰው ኹሉ ተነክቶ. . .
በመላ-ቢስ ብይን፣
በ"ዕድሜ ይፍታህ" ግዞት፤
"ምን አለው? ምን አላት?"
የሚል ልክፍት ይዞት. . .
አትራፊ ኾነና፣የጥቅም ባለሟል፤
ወልዶ መሳም ከብዶ፣
ገዝቶ ማቀፍ ቀሏል!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
1.7K viewsFa, 19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 22:11:10 እቀያየራለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
መቼም ሰው አይደለሁ?
ጊዜ ይጫነኛል፣ያሰክራል መንገዴን፣
ዘመን ያዘመዋል:
ያጥፋል አካሔዴን. . .
አቅሜን አሳንሶት፣ሰው የመኾን አህዋል፤
የንጋት እንቡጤን፣ምሽት ይቀጥፈዋል።
ደርሼ ስከለስ፣
አርጅቼ ስታደስ፣
በትናንቱ ሥርፋ፣ዛሬ ላይ የለሁም፣
እቀያየራለሁ፣ቁርኣን አይደለሁም።
.
@huluezih
@huluezih
923 viewsFa, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:02:24
. . .of the day!
776 viewsFa, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 23:34:54
. . .of the day!
1.1K viewsFa, 20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 23:13:58
. . .of the day!
903 viewsFa, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 06:13:51 የማለዳ ማስታወሻ #149
.
እጅ ለእጅ ተያይዘን ቁልቁለት የወረድነው፣ ልብ አሙቅ ቃላት እየተለዋወጥን ጋራ የወጣነው፤ አንዳችን ለአንዳችን በክፉ ቀን መደበቂያ፣ በብሩህ ቀን መድመቂያ የኾንነው. . . እዚህ ደርሰን እንደ ባዕዳ፣ እንደ ባይተዋር የሩቅ ሰው ለመኾን አልነበረም። ግን የማይጠበቀው ይኾናል፣ የማይታሰበው ይከሰታል። ማሸነፍ በማንችለው ድብቅ ራስ ወዳድነት ያሳለፍነው ሁሉ ልቦለድ፣ ያቀድነው ሁሉ ተረት ይኾናል።
.
አሁን እንዴት ካንቺ ጋር ሰላምታ መለዋወጥ እንደምችል አላውቅም። የሚመጥነኝን መልስ አላገኝም ብዬ እፈራለሁ። ሁሉም አብቅቷል ብዬ መንገድ እጀምርና ነገ የሚጠብቀኝን ፀፀት ፈርቼ እመለሳለሁ። ልቤ ስሔድ ቁም፣ ስመለስት ተው ይለኛል። ልቤ ላይ የታተመው ጠረንሽ ተቀይሮብኛል። ዓይንሽ እንደፊቱ እርጋታ የለውም። ንግግርሽ ውስጥ ተስፋ ጎድሎብኛል። ድልድዩን ተሻግረን ያለምናቸው ነገዎች ጭጋግ አደብዝዟቸዋል። እጄ ላይ የቀሩ የልፋቴን እንቁላሎች ሁሉ ባንቺ ቅርጫት ውስጥ ለማስቀመጥ የልቤ ላይ እምነት አቅም ያንሰዋል።
.
ማጠናከሪያ ትምህርት ሲባል ሰምተሽ ታውቂያለሽ? ዋናው ትምህርታችን ላይ እንድንጎብዝ ባለን ትርፍ ሰዓት የሚሠጥ ትምህርት ነው። ምናልባት አንዳችን ለአንዳችን ማጠናከሪያ ትምህርት ነበርን። ዋናው ሕይወታችን ላይ እንዳንሰንፍ ለመጠነካከር የተገናኘን!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih
870 viewsFa, 03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 19:39:14 ላብ እና በቀቀን
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
አትጠራጠር!
ተራራ አይኖርም፣ጠጠር ባይፈጠር!
ዓለምም እንዲያ ነች!
ከመልኳ ይጎድላል አንተ ባትቆጠር!
ያልከውን አስልቶ፣
የሥራህን ቆጥሮ፤
መልሶ ይሠጣል፣ላብና በቀቀን፤
በቃ ታገስ!
ቀን ያይኻል አንድ ቀን!
.
@huluezih
@huluezih
1.2K viewsFa, 16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 22:10:27
. . .of the day!
855 viewsFa, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ