Get Mystery Box with random crypto!

ሕያው ቃል

የቴሌግራም ቻናል አርማ hiyaw_qal — ሕያው ቃል
የቴሌግራም ቻናል አርማ hiyaw_qal — ሕያው ቃል
የሰርጥ አድራሻ: @hiyaw_qal
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.89K
የሰርጥ መግለጫ

''ነዋ ወንጌል መንግሠተ ሰማያት "፦ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ ወንጌል እንሆ። "

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 11:07:36
1.2K viewsⒷaⒷa, 08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:50:37 (ቁር,22-24) በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል በይሁዳ ያሉት አብያተክርስቲያናት ጳውሎስ ወይም ሳኦልን የሚያስታውሱት በአሳዳጅነቱ ነው ። ሰለ ክፉ ስራው በሙሉ ሰምተው ነበር ። ጳውሎስ በይሁዳ ወንጌልን ስላልሰበከ የይሁዳ ክርስቲያኖች የተለወጠውንና የክርስቶስን ሐዋርያ የሆነውን የጳውሎስን አዲስ ሕይወት የማየት እድል አልገጠማቸውም ቢሆንም ጳውሎስ በሶርያና በኪልቅያ የሰበከውን ሰለስምሙ ሰለ እርሱ እግዚአብሔርን የመሰግን ነበር ። ነገር ግን ጳውሎስ እንዲያውም ያሰደዳቸው የገላትያ ክርስቲያኖችን ክእርሱ ራቁ ከመጀመሪያው አንስቶ እንደ አባት ይወዳቸው የነበሩት የገላትያ ሰዎች እርሱን ተቃወሙ ።

አንዳንድ ገለጻዎች

➮መንፈስ ቅዱስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሁል ጊዜ ይሰማማል ። ምክንያቱም መጸሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በመንፈስ ቅዱስ ሰለ ሆነ ነው ።
➮ ይሁዲት የአይሁድ ሕዝብ የሚከተለው ሃይማኖትና የኑሮ ዘይቤ ነው ።
➮ ክርስቶስ ከመምጣቱ ሁለት ሺ ዓመታት ገደማ እግዚአብሔር አብርሃምን የአይሁድ ሕዝብ አባት እንዲሆን መረጠው ። እግዚአብሔር አይሁድን የተለየ ሕዝቦች እንዲሆኑ መረጠ ። የአይሁድ ሕግ የሚባለውን የራሳቸውን ሕግ ሰጣቸው ። በብሉይ ኪዳን የአይሁድ ታሪክ ይዘገባል ። የአይሁድ ሕግና የአይሁድ ነበያትን መጸሐፍ ይዟል ።
➮ በእኔ የሚለው ቃል ምትክ ሌሎች ትርጉሞች ለእኔ በማለት ጸፏል ።
➮ ደማስቆ የመካከለኛ ምስራቅ ሶሪያ ዋና ከተማ ነች ።
➮ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ደቡባዊ ክፍል አገር የነበረች የአይሁድ ዋና ከተማ ነበረች ። ኢየሩሳሌም ለአይሁድ ዋና ከተማ ፣ቅዱስ ከተማ ፣ እንዲሁም ለሃይማኖታዊ (ለመንፈሳዊ) ሕይወታቸው ማእከል ነበረች ። ዛሬም ኢየሩሳሌም በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ዋና ከተማ ነች።

ይቀጥላል ......

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid035mrCdvJhbekf2HguvxTX8L1MgXrHBPACkJVoxsc4wgayHqWiyjbz4ARLxjSnRfYjl/?app=fbl :Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur
1.3K viewsⒷaⒷa, edited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:50:37 የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /3/

የጳውሎስ በእግዚአብሔር መጠራት (1÷11-24)

11-12 በእነዚህ በቁጥሮች ጳውሎስ እወነተኛ ሐዋርያ እንደ ሆነ ለገላትያ ሰዎች ይናገራል ። የሚሰብከው እወነተኛ ወንጌል ሲሆን ይሄንንም የተቀበለው በቀጥታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በራዕይ ነው (ቁ 12)። ጳውሎስ ይህንን ራዕይ በመጀመሪያ ከሞት የተነሣው ኢየሱስ በደማስቆ ሲገልጥለት ነው ። (የሐዋ 9÷3-5) ። የክርስቶስ ወንጌል በሰዎች የተፈጠረ ልብ ወለድ አይደለም ። ከአይሁድ እምትና ከክርስትና እምነት በስተቀር በዓለም ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሃይማኖት ከሰዎች ፍልስፍናና ሀሳብ የተወለዱ ናቸው ። የክርስቶስ ወንጌል ግን እግዚአብሔር ራሱ ያደረገው የምስራች ነው ። ሰለጠኑ እግዚአብሔርና ድህነት ሰለሚገኝበት መንገድ በቂና የመጨረሻው ፍጹም እውነት ነው ። ክርስቲያኖች በመጀመሪያ ወንጌል የተቀበል መንፈስ ቅዱስ ገልጦልን ወይም መጸሐፍ ቅዱስ አንብበን ነው ። አንዳንድ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በቀጥታ ከክርስቶስ በሆነው ትምህርት ወንጌል እንቀበላለን ። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በቀጥታ ትምህርትን ስንቀበል ከቅዱስ ቃሉ የተለየ ወይም አዲስ መልእክት አይመጣም ፥ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚስማማ መልእክት ነው ያለው ። ጳውሎስ ግን ወንጌል የተቀበለው አዲስ ኪዳን ከመጻፉ በፊት በቀጥታ ከክርስቶስ ነው ። ጳውሎስ ወንጌል ከሌላ ሰው የተቀበለ ቢሆን ኖሮ ከዚያ ሰው « ያነሰ » ይሆን ነበር ማለትም « ተማሪ ሐዋርያ » ይሆን ነበር ። እርሱ እውነተኛ ሐዋርያና የሚሰብከውም ወንጌል እውነተኛ ወንጌል ነው ። ስለዚህም የገላትያ ክርስቲያኖች ይህን ሊጠራጠሩ አይገባም ። የጳውሎስ መልእክት የምናጠና እኛም አንጠራጠርም ። የክርስቶስ ወንጌል እወነተኛ ወንጌል ነው ።

(ቁ .ር 13-14) ጳውሎስ በህይወቱ የተከናወነውን ታላቅ ለውጥ ለገላትያ ክርስቲያኖች ያስታውሳቸዋል ። በመጀመሪያ እጅግ በክፉ ሁኔታ የክርስቶስን ቤተክርስቲያን ያሳድድ ነበር ። ( የሐዋ 8÷3 ፣ 9÷1-2 ) የአይሁድ ሃይማኖት ይሆነውን ይሁዲነት በጥብቅና ለሃይማኖቱ በመቅናት ይከተል ነበር ። (የሐው 22÷3 ፣ ፊል 3÷4-6) በአይሁድ እምነት አንድ ሰው ሊድን የሚችለው የአይሁድ ሕግን ሲፈጸም ብቻ እንደሆነ ያስተምራል ። ጳውሎስ እንዲ ያምን ነበር ። “ አሁን ግን የጳውሎስ ዋና መልእክት ሰው በጸጋ በክርስቶስ በማመን ብቻ ይድናል የሚል ነው”። እጅግ በክፉ ሁኔታ ያስድዳቸው የነበሩት ሰዎችም የክርስቶስ ተከታይ ናቸው ። በጳውሎስ ሕይወት እንዲህ ያለውን ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው ።

(15), ጳውሎስ ከመወለዱ በፊት ሐዋርያው እንዲሆንለት እግዚአብሔር መርጦት ነበር ።እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ከመወለዳችን በፊት መርጦናል ። (መዝ 139÷-13-16) ። ይለቁን አለም ከመፈጠሩ በፊት አሰቀድሞ እግዚአብሔር መርጦናል ። (ኤፌ 1÷4 ) ። እግዚአብሔር እኛን የመረጠበት በጸጋው እንጂ እንደ ስራችን አይደለም ። በዚህ ስፍራ ጳውሎስ በጸጋው የጠራኝ (1ቆር 15÷9-10) ። እግዚአብሔር የጠራን ለምን ጉዳይ ነው ? በመጀመሪያ ለድህነት ጠራን ። ሁለተኛ ከመዳናችን ጋር የእርሱ ልጆች እንድንሆን ጠራን ። (ኤፌ 1÷5) ማለትም ከክርስቶስ ጋር አብረን እንወርስ ዘንድ ጠራን (ሮሜ 8÷17)። ሦስተኛው እግዚአብሔር ለእኛ ያዘጋጀልን ሥራ ወይም ተግባር እንድንፈጽም ጠራን ። (ኤፌ 2÷10) ። የጳውሎስ የተለየ አገልግሎት ለአሕዛብ ወንጌል መስበክ ነበር ።

ቁ(ር 16) እግዚአብሔር ልጁን በእኔ ለመግለጥ ወደደ ሲል ፦ ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ጽፏል ። ክርስቶስ «ለእኛ »መገለጡ ብቻ በቂ አይደለም ። «በእኛም »መገለጥ አለበት ። የክርስቶስ መንፈስ በውስጣችን ማደር አለበት ። አለዚያ እምነታችን ደካማ ሕይወታችን መንፈሳዊ ኃይል የሌለው ይሆናል ።

(17) ጳውሎስ የሕይወቱ ለውጥ ካገኘ በኋላ ለሦስት ዓመታት እንደ ጴጥሮስና የጌታ ወንድም ከሆነው ያዕቆብ ካሉት ሐዋርያት ጋር አልተገናኘም ። ከሌላ ሰው ምንሞ ትምህርት አልተቀበለም ። እርሱ በቀጥታ ከእግዚአብሔር የተቀበለ ነው ። ከሕይወቱ ለውጥ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ወደ ዓረብ አገር ሄዶ ነበር ። ነገር ግን እዛ ምንም ያደረገው እንደነበር የሚታወቅ ነገር የለም ። ምናልባት እግዚአብሔር ለጠራው ሥራ የሚያዘጋጀው ጸሎትና የብሉይ ኪዳን መጸሐፍት በማጥናት ጊዜውን ያሳልፍ ይሆናል ። የሕይወት ለውጥ አግኝቶ በዓረብ አገር ካደረገው ቆይታ በኋላ በመጀመሪያ ደማስቆ ተመለሰ ። ከዚያም ሶስት ዓመት በደማስቆ ከቆየ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ በቁ.ር 18 ። ከዚህ የምንመለከተው ጳውሎስ የሚዘጋጅበት ጊዜ አስፈልጎት እንደ ነበር ነው ። ይህም ሁላችን የሚያስፈልግ ነው ። በአንድ ጊዜ የበሰሉ ክርስቲያኖች አንሆንም ። እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ሊያዘጋጀን ይፈልጋል ። ይህም ደግሞ ጊዜን የሚጠይቅ ነው ። በብሉይ ኪዳን የአይሁድ ታላቅ መሪ የነበረው ሙሴ ለማዘጋጀት ዓርባ ዓመታት ወስዷል ። ሰለዚህም በቅጽበት ለአገልግሎት እንበቃለን ብለን አናስብ ። የተጠራነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነው ። ለአገልግሎት የምንዘጋጀውም በእግዚአብሔር ጸጋ ነው ። እያንዳዳችን በእየለቱ ሳያቋርጠ እንዘጋጃለን ። ሁሉ በጸጋ ነው ። በእግዚአብሔር ጸጋ ከዋክብትና ዓለማትን በምህዋራቸው ይጠበቃሉ ።

በሙቀት ብዛት እንዳንቀልጥ ወይሞ በቅዝቃዜ መክንያት በረዶ እዳንሆን በመሬትና በፀሐይ መካከል ያለው ርቀት በእግዚአብሔር ጸጋ የተጠበቀ ነው ። በእግዚአብሔር ጸጋ እንተነፍሳልን ፣ እንበላለን ፤እንጠጣልን ደግሞም እንኖራልን ። እግዚአብሔር አላማውን ለመፈጸም የሰው ድካም አያስፍልገውም ። እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅሩን ለእርሱ በምናደርገው በእኛ ሥራላይ የተመሰረተ አይደለም ። ይህም የእርሱ ልጆቾ በመሆናችን ነው ። የእርሱ ልጆች የሆነው በጸጋ በኩል ነው ። ስለዚህም ወዳጆቼ ሕይወታችንን በሙሉ ክብር ለሆነው ጸጋ ለመኖር እንፈልግ ኤፌ 1÷6

(ቁር ,18) ጳውሎስ የሕይወቱ ለውጥ ካገኘ ከሶስ አመት በኋላ ከጴጥሮስ ጋር ተገናኘ ። ጳውሎስና ጴጥሮስ በሐዋርያነት ስልጣን እኩልነትን ናቸው ። ታዲያ ጳውሎስ ይህን መጻፍ ለምን አስፈለገ ? ምክንያት በገላትያ የነበሩት የጳውሎስ ተቃዋሚዎች ጴጥሮስ እወነተኛ ጳውሎስ ግን ሐሰተኛ ሐዋርያ አድርገው ይናገሩ ሰለ ነበር ነው ። ጳውሎስ ከጴጥሮስ ጋር ለመገናኘት ያደረገው ጉዞ በሐዋርያት ሥራ 9÷26-30 ላይ ተገልጧል ።( 19-20 ) በዚህ ቦታ የተጠቀሱት ሌሎች ሐዋርያት (የአስቆሮቱ ይሁዳን ሳይጨምር ) አስራ ሁለቱ የኢየሱስ ደቀመዝሙር ናቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ በተጨማሪ ሌሎች ሐዋርያት ነበሩ ከእነሱም የኢየሱስ ወንድም ያዕቆብ ይገኝበታል (1ቆሮ 15÷7) ። ጳውሎስ ይህን መልእክት ለገላትያ ክርስቲያኖች በሚጽፍበት ጊዜ ያዕቆብ በኢየሩሳሌም የነበረ «እናት ቤተ ክርስቲያን » ዋና መሪ ነበር ። (የሐዋ 21÷18 ፤ ገላ 2÷9) ። በዚህ ስፍራ ጳውሎስ እንደሚለው በዚህ የጉበኝት ጊዜ ከያዕቆብ በስተቀር ከማንም ሐዋርያ ጋር አልተገናኘም

(21) ጳውሎስ በኢየሩሳሌም የቆየው ለአስራ አምስት ቀናት ብቻ ነበር ።(በቁ.18) በይሁዳ ባልት ስፍራዎች ዙሪያ አልሰበከም ። ነገር ግን ይህንንም አከባቢ ትቶ ከአይሁድ ወገን ውጪ ለሆኑት ወንጌልን ለመስበክ ወደ ሶሪያ ኪልቅያና ሂዷል ።
1.2K viewsⒷaⒷa, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:14:06 የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /2/


ገላትያ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ ⁷ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ⁸ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። ⁹ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን ¹⁰ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።

ሌላ ወንጌል የለም /1÷6-10/

(ቁ.ር 6-7) ጳውሎ በገላትያ ክርስቲያኖች ባሕርይ እጅግ መደነቁን ያሳያል ። የገላትያ ሰዎች ከቅርብ ጊዜ በፊት የጸጋ ወንጌል ተቀብለው ነበር ፤ አሁን ደግሞ በፍጥነት ከዚህ ወንጌል ፊታቸውን  መመለስ ጀመሩ ። ከኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ አይሁድ ክርስቲያኖች የገላትያ ክርስቲያኖችን ሌላ ወንጌል እንዲከተሉ ጥረት ያደርጉ ነበር ።  ይህ <<ወንጌል>> ድኅነት በጸጋ ሳይሆን በሥራ እንደሚገኝ የሚናገር ሲሆን ፥ የገላትያ ክርስቲያኖችን ግራ አጋብቶአቸዋል ። (በቁ.ር 7) ። ጳውሎስ ግን የእነርሱ <<ወንጌል >> እወነተኛ ወንጌል እንዳልሆነ በመናገር ፥ እውነተኛው ወንጌል ድኅነት በጸጋ  መሆኑን ተናገረ ። እነዚህ የገላትያ ክርስቲያኖች የሚያደርጉት የሚያሳዝንና የሚያሳፍር  ነገር ነው ። በጳውሎስ ስብከት የእግዚአብሔር ነጻና ወሰን የለሽ ጸጋ ተቀብለዋል ። አሁን ግን ጳውሎስንና የጠራቸውን እግዚአብሔርን ዘነጉ ። የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቃወሙ ፥ አቃለሉትም ።  ጳውሎስ የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ለሚሞክሩ ሐሰተኛ መምህራን ነው የተቃወመ ደብዳቤ የጻፈው ።  የእነዚህ መምህራን ትምህርት ክርስቶስ ብቻ  አያድንም የሚል ነው ። ሰለዚህ ለመዳን የአይሁድ ሕግ መፈጸም አስፈላጊ ነው ።  እንዲሁም ያለ ትምህርት የክርስቶስን ጸጋ ከንቱ የሚያደርጉ ነው ። ጸጋ ከወንጌል ከተለየ ወንጌል መሆኑ ይቀራል ።  ጳውሎስም ከዚህ የተነሳ  መንፈሳዊ ልጆቹ ከእውነተኛው ወንጌል  እንዲርቁ አይፈልግም ። ልናስትውል ይሚገባን  ጳውሎስ እነዚህ ቦታ የጻፈው የአይሁድ ሕግ በመጠበቅ ለመዳን አስፈላጉ ነው የሚለውን የስሕተት ትምህርት ለሚያስተምሩ አንዳንድ አይሁድ ክርስቲያኖች ነው ። በዚህም ዘመን ቤተክርስቲያናትን ሊያናውጥ የሚችል የስህተት ትምህርት ሊኖር እንደሚችል ይህ መልእክት ምሳሌ ይሆነናል ። በየትኛውም ሐገር ለመዳን አንዳንድ ሕግጋትን ወይም የሃይማኖታዊ ወጎችንና ለማዶችን መፈጸም እንዳለብን የሚያስተምሩ አሉ ። እውነተኛው ግን ሰው የሚድነው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው የሚል ነው   ይህ የክርስቶስ ወንጌል መሰረት ነው ።

(ቁ.ር 8-9) ከዚህ የምንማረው የእግዚአብሔር ስራ የእግዚአብሔር ወንጌል እንዴት ትልቅና አስፈላጊ  እንደሆነ ነው ። የእግዚአብሔር ወንጌል በማንኛውም መንገድ በየትኛውም አቅጣጫ ልንቀይረው አይገባም ።  ሰባኪ ወይም አስተማሪ መልአክ እንኳን ቢሆን የእግዚአብሔር ቃል የመለውጥ ስልጣን የለውም ። የእግዚአብሔር ቃል መስበክና ማስተማር ከባድ ኃላፊነት ነው ። እኛም በታማኝነት ልንሰብከው እና ልናስተምረው ይገባል ። ምክንያቱም ወንጌልን የመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት አላማ  በመጻረን ከሰበክን በእግዚአብሔር የተረገመ እንሆናለን ። ቃሉን የሚሰሙት ከአንዱ እውነተኛ ወንጌል ጋር ሊጣበቁና ከሐሰተኛ መምህራን ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል ።

(ቁ.ር 10) በገላትያ የነበሩ የጳውሎስ ተቃዋሚዎች ጳውሎስ የሚጥረው ሰዎችን ደስ ለማሰኘት  ብቻ ነው ብለው ከሰውታል  ። ጳውሎስ የአይሁድ ሕግን መከተል አያስፈልግም በሎ የሚያስተምረው ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን  የገላቲያ ሰዎችን ደስ ለማሰኘትና  ድኅነትን በቀላቁ እንዲያገኙ የሚያደርገው ጥረት ነው ይላሉ ። ጳውሎስ ግን ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እንደማይሞክር ተናግሯል (1ጢ 2÷6) ። በዚህ መልእክት ጳውሎስ የገላትያ ክርስቲያኖችን በብርቱ ገሥፆአቸዋል ። ሰዎችን ደስ እያሰኙ የእግዚአብሔር አገልጋይ  መሆን በጣም የሚያስቸግር ነገር እንደሆነ ጳውሎስ በዚህ ቦታ ተናግሯል ። ሌሎች ሰዎች ምንም ቢያስቡ የክርስቶስ አገልጋይ የሆኑ የሆኑ ወንጌልን በታማኝነት ሊሰብኩ ይገባል ። (1ተሰ 2÷4) ። የሰባኪ ዋንኛው ዓላማ ክርስቶስን ማክበርና ሰዎች ወደ ድኅነት መንገድ መምራት ነው  (1ቆሮ 9÷19 ፣ 22-23) ።

ይቀጥላል ......

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid0GseKmrdMMv5keFkgMdvxSDcEQWpZE5xAXpkapzFS9CAd3WhNr2L6rSLtj9sqi9Zxl/?app=fbl
Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur
1.5K viewsⒷaⒷa, edited  06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:12:24 የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /1/
       
     መግቢያ

ገላትያ አሁን ቱርክ ተብላ በምትጠራዋ አገር ማዕከላዊ ስፍራ የምትገኝ የቀድሞው የሮም መንግስት አንዷ ክፍለ ሐገር ነበረች ። ጳውሎስ ለገላቲያ ቤተክርስቲያኖች የጻፈው ይህ መልእክት ለአንዲት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ለብዙ አብያተክርስቲያናት ነበር። እነዚህም አብያተክርስቲያናት በተለያዩ ዓመታት ቀደም በለው ጳውሎስ ራሱ የመሰረታቸው ናቸው ። በዚህ መልእክቱ ላይ ስማቸውን በዝርዝር ስላልጠቀሰ ለየትኛው እንደጻፈ አይታወቅም ። በተጨማሪም ይህን መልእክት የተጻፈበት ትክክለኛ ዓመት ባይታወቅም አንዳንድ ሊቃውንት በ54_56 ዓ.ም ወስጥ ተጽፏል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በ48-49 ዓ.ም እንደተጻፈ ይናገራሉ ። ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ የጻፈበት ምክንያት በመልእክቱ በግልጥ ተጠቅሶ ይገኛል ።እነዚህን የአሕዛብ አብያተክርስቲያናት እንደመሰረተ አንዳንድ አይሁድ ክርስቲያኖች መጥተው የጳውሎስን ትምህርት መቃወም ጀመሩ ። ጳውሎስ ያስተምር የነበረው ፣ ሰው በእግዚአብሔር ፀጋና በእምነት አማካኝነት እንደሚድን ነበር  (ኤፌ 2÷8)። እነዚህ አይሁድ ክርስቲያኖች ግን አንድ ሰው ለመዳን የአይሁድ ሕግ በተጨማሪ መፈጸም እንደሚገባው አስተማሩ ። የእነዚህ አይሁድ ክርስቲያኖች ትምህርት ከተስፋፋ የጳውሎስ የፀጋ ወንጌል ከንቱ ሆነ ማለት ነው ። ስለዚህ ገና ሕፃን የሆኑትን የገላትያ ክርስቲያኖች በአይሁድ ክርስቲያኖች ትምህርት ምክንያት ከእውነተኛው የመዳን መንገድ እንዳይስቱ ለማድረግ የስህተት ትምህርት የሚቃወም መልእክት መጻፍ ነበረበት ። የገላትያ ሰዎች ድህነትን በሕግ ስራዎች ለማግኘት ጥረት ማድረግ ከጀመሩ የተቀበሉትን ጸጋ በማጣት አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚታወቀው ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች የጻፈው መልእክቱ የላቀ ዋጋ ሲስጠው ቆይቷል።አንዳንድሰዎች ድህነትን በራሳቸው ሥራና ጥረት ለማግኘት ይፈልጋሉ ። ሰለዚህም በሐይማኖታዊ ወጎችንና ሥርዓቶችን በመፈጸም እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ይሞክራሉ ። በገዛ ብርታታቸው ጻድቅ ለመባይል ይጥራሉ ። ነገር ግን ይሄ ሁሉ ድካም ከንቱ ነው ። ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚያገነው በጸጋ ብቻ ነው ። እግዚአብሔር ከታላቅ ፍቅሩና ከብዙ ምሕረቱ የተነሳ ለኃጢአተኞች ሰዎች የሰማይን በር ከፍቶላቸዋል ። በክርስቶስ በማመን በዚህ በር ማለፍ ይቻላል ።ይህ ለገላትያ ክርስቲያኖች የተጻፈው ዋና መልእክት ነው ።
   
ሰላምታ /1÷1-5/

ጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ እንዲሆን በቀጥታ የተሾመ ሰው ነበር ።ይህን ኃላፊነት በሌሎች ሰዎች አማካኝነት አልተቀበለም ። በአዲስ ኪዳን ሐዋርያ ማለት ወንጌል ለመስበክና ቤተክርስቲያንን ለመመስረት  ከክርስቶስ ልዩ የሆነውን ስልጣን የተቀበለ ሰው ነው ። በአዲስ ኪዳን የነበሩት በዙዎቹ ሐዋርያት የክርስቶስን ትንሣኤ በአይናቸው የተመለከቱ ናቸው ። ጳውሎስ በደማስቆ የነበሩትን ክርስቲያኖች በማሳደድ ስጓዝ ኢየሱስ አገኘው (ሐዋ 9÷3-6) ። ሐዋርያ እንዲሆን ከኢየሱስ ሐዋርያነትን ሹመት ተቀበለ (ሐዋ 9÷15 ፣  26÷16 ) ።ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ለእኛም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ሙሉ ስልጣን ይህን መልእክት ጽፏል ። ሰለዚህም የገላትያ ሰዎች የጳውሎስን ደብዳቤ ልብ ሊሉ ይገባቸዋል እኛም እንዲሁ (ሮሜ 1÷1 ፣ ኤፌ 1÷1 ማብራሪያውን ይመልከቱ )። ጳውሎስ የተጠራው በእግዚአብሔር አብና በኢየሱስ ክርስቶስ  እንደ ሆነ አስተውሏል ። ኢየሱስና አብ አንድ አምላክ ናቸው ። ሁልጊዜ በአንድነት ይሰራሉ ። ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች  እንደ ጳውሎስ ክርስቶስን ለማገልገል ተጠርተናል ። እንደ ጳውሎስ የተለየ ስልጣን ባይኖረንም ደቀ መዛሙርት እንድንሆንና  ከክርስቶስ ጋር እንድንወርስ ተመርጠናል ። የተለዩ ሐዋርያት ብቻ የእግዚአብሔር ስራ እንደ ሚሰሩ አንጠብቅ ። እግዚአብሔር ለያንዳንዳችን የምንሰራለትን ሥራ ተሰጥቶናል ። ይሄንን ስራ እንድንሰራም በመንፈስ ቅዱስ የሚያስፈልገንን ጸጋና ኃይል ሰጥቶናል ።
ኢየሱስ እራሱ .. “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥”( ዮሐንስ 14፥12)

(ቁ.ር ,2) በዚህ ቁጥር ለየትኛው ለገላትያ አብያተክርስቲያናት እንደ ጻፈ አይታወቅም ፣ አያሌ የመጻሕፍት ቅዱስ ሙሁራን ጳውሎስ የጻፈው በደቡብ ገላትያ  ወደሚገኘው የጲስዲያ  ፣አንጾኪያ  ፣ኢቆንዮን ፣ ልስጥራን ፣ ደርቤን የሚባል ከተሞች እንደሆነ ይናገራል ። (የሐ 13÷14 ፣ 14÷1 ፣16÷1-2 ገለጻውን ይመለክቷል) ። ጳውሎስ እነዚህ ከተሞች ሁሉ በመጀመሪያውና  በሁለተኛው ተልእኮ የጎበኛቸው ናቸው ።

(ቁ.ር ,3) ጳውሎስ መልእክቱን የሚያነቡ ሰዎች ጸጋንና ሰላምን እንዲያገኙ የጸልያል ። ጸጋና ሰላም ዋና ዋና የሆኑ የወንጌል አዕማድ ናቸው ። በመጀመሪያ ጸጋ ከዛም ሰላም ጸጋ ሁልጊዜ የመጀመሪያ ነው ። ማንኛውም ነገር ምንጩ ጸጋ ነው ። የተጠራነው በጸጋ ነው ። በጸጋ ኃጢያታችን ይቅር ተባለ ፣ በጸጋ ዳንን ፣በጸጋ ጸደቅን ፣ ቅድስና አገኘን በጸጋ ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ሰላም አለን ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ክርስቶስ ወደምድር መጣ ፣ ሰለ ኃጢያታችንም ስርየት እራስን ሰጠን። ጸጋ ብድራት አይደለም ውሰን የሌለው የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት ነጻ ስጦታ ነው ። ስለዚህም ጸጋ  ክብርን ለእግዚአብሔር መስጠትና ማመስገን መተው የለብንም (ሮሜ 1÷7 ፣ኤፌ 1÷2 እና ማብራሪያውን ይመልከቱ ) ። እዲሁም ጸጋና ሰላም ከእግዚአብሔር አብና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ  እንደሚመጡ እናስተውል ። እግዚአብሔር እና ክርስቶስ አንድ ናቸው (ዮሐ 10÷30)።

(ቁር ,4-5)  ክርስቶስ ሰለ ኃጢያታችን ራሱን ሰጠን ። የእርሱ መስዋዕትነት ለድኅነታችን ሙሉና በቂ ነው ። ለድኅንነታችን እኛ የምናደርገው ነገር የለም ። ነገር ግን እምነታችን በክርስቶስ ላይ መሆን ይኖርበታል ። ክርስቶስ ከዚህ ክፉ አለም አዳነን ። ይህ ዓለም የሲጣን መንግስት ነው ፣ ሲጣን የዚህ ዓለም ገዢ ነው ፤ (ዮሐ 16÷11)። ክርስቶስ እኛን ከዚህ ዓለም አላወጣንም ነገር ግን ከዚህ ክፉ ዓለም አዳነን (የሐ 17÷15)

ይቀጥላል.
እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉ ።

ወገኖቼ ይህን ትምህርት ትኩረት ሰጥታችሁት እንድትማሩ እለምናለው ። ስትማሩ ወንጌል ከጎናችሁ አድርጋችሁ አንድላይ በታጠኑ ይበልጥ ይገባችኋል ። ትምህርቱን ለሌሎች አጋሩ ።

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid035mrCdvJhbekf2HguvxTX8L1MgXrHBPACkJVoxsc4wgayHqWiyjbz4ARLxjSnRfYjl/?app=fbl
Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur
1.8K viewsⒷaⒷa, edited  06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:17:20 ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
1.7K viewsⒷaⒷa, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:13:28 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
               ዘዳ 33:26

ሁሌ ተበዳይ እርሱ ተበድሎም የሚክስ እርሱ፤
ጀርባ የምንሰጠው እርሱ፥ በፍቅር የሚቀርበን እርሱ፤   
የለም ተብሎ የሚካድ እርሱ እንደ በደላችን ያልከፈለን እርሱ፤
ከህይወት ይልቅ ሞትን መርጠን የራቅነው ከርሱ ለሙት ማንነታችን ህይወት ሰጥቶ ያፈቀረን እርሱ
የረሳነው እኛ ያስታወሰን እርሱ
የገደልነው እኛ ያስነሳን እርሱ
በምርጫችን የጠፋነው እኛ በነፃ የፈለገን እርሱ
የተሸከመን እርሱ የከበደን እኛ

     ኸረ እንዳንተስ ያለ የለም። ተመስገን

ይቀላቀሉ ➙ @hiyaw_qal
ይቀላቀሉ ➙ @hiyaw_qal
2.1K viewsⒷaⒷa, edited  06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 22:30:51 ያኔ መዳን [ከክርስቶስ በቀር] በሌላ በማንም የለም /የሐ4:12/ የሚለውን ሕያው እውነት የተቃወሙት የአይሁድ ካህናት አለቆች ናቸው። ዛሬም በዚህ ቃል የማያምንበት የሚቃወም ካለ የእነሱ አባል ወይም ተባባሪ ነው ማለት ነው ።
2.1K viewsⒷaⒷa, edited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 22:23:48 New Ethiopian Orthodox Afaan Oromoo Mezmur Kaleessa Naceesifte
2.5K viewsⒷaⒷa, edited  19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:56:53
ሕያው ቃል:
በኢየሱስ ልደት፣ ሞትና ትንሣኤ ለማያምኑ፣ "ጽድቅ" ግለ ጥረት ስለሚመስላቸው "ጸድቄአለሁ" ማለት ያፍራሉ! እኛ ግን አምነን ባጸደቀን ልደቱ፣ ሞትና ትንሣኤው አናፍርም! አዎን፤ እርሱን በመምሰል በጸጋው ለመመላለስ በክርስቶስ ጸድቀናል! አሜን።

ይቀላቀሉ ➙ @hiyaw_qal
ይቀላቀሉ ➙ @hiyaw_qal
2.7K viewsⒷaⒷa, 07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ