Get Mystery Box with random crypto!

(ቁር,22-24) በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል በይሁዳ ያሉት አብያተክርስቲያናት ጳውሎስ ወይም ሳኦልን | ሕያው ቃል

(ቁር,22-24) በእስራኤል ደቡባዊ ክፍል በይሁዳ ያሉት አብያተክርስቲያናት ጳውሎስ ወይም ሳኦልን የሚያስታውሱት በአሳዳጅነቱ ነው ። ሰለ ክፉ ስራው በሙሉ ሰምተው ነበር ። ጳውሎስ በይሁዳ ወንጌልን ስላልሰበከ የይሁዳ ክርስቲያኖች የተለወጠውንና የክርስቶስን ሐዋርያ የሆነውን የጳውሎስን አዲስ ሕይወት የማየት እድል አልገጠማቸውም ቢሆንም ጳውሎስ በሶርያና በኪልቅያ የሰበከውን ሰለስምሙ ሰለ እርሱ እግዚአብሔርን የመሰግን ነበር ። ነገር ግን ጳውሎስ እንዲያውም ያሰደዳቸው የገላትያ ክርስቲያኖችን ክእርሱ ራቁ ከመጀመሪያው አንስቶ እንደ አባት ይወዳቸው የነበሩት የገላትያ ሰዎች እርሱን ተቃወሙ ።

አንዳንድ ገለጻዎች

➮መንፈስ ቅዱስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሁል ጊዜ ይሰማማል ። ምክንያቱም መጸሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በመንፈስ ቅዱስ ሰለ ሆነ ነው ።
➮ ይሁዲት የአይሁድ ሕዝብ የሚከተለው ሃይማኖትና የኑሮ ዘይቤ ነው ።
➮ ክርስቶስ ከመምጣቱ ሁለት ሺ ዓመታት ገደማ እግዚአብሔር አብርሃምን የአይሁድ ሕዝብ አባት እንዲሆን መረጠው ። እግዚአብሔር አይሁድን የተለየ ሕዝቦች እንዲሆኑ መረጠ ። የአይሁድ ሕግ የሚባለውን የራሳቸውን ሕግ ሰጣቸው ። በብሉይ ኪዳን የአይሁድ ታሪክ ይዘገባል ። የአይሁድ ሕግና የአይሁድ ነበያትን መጸሐፍ ይዟል ።
➮ በእኔ የሚለው ቃል ምትክ ሌሎች ትርጉሞች ለእኔ በማለት ጸፏል ።
➮ ደማስቆ የመካከለኛ ምስራቅ ሶሪያ ዋና ከተማ ነች ።
➮ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ደቡባዊ ክፍል አገር የነበረች የአይሁድ ዋና ከተማ ነበረች ። ኢየሩሳሌም ለአይሁድ ዋና ከተማ ፣ቅዱስ ከተማ ፣ እንዲሁም ለሃይማኖታዊ (ለመንፈሳዊ) ሕይወታቸው ማእከል ነበረች ። ዛሬም ኢየሩሳሌም በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ ዋና ከተማ ነች።

ይቀጥላል ......

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid035mrCdvJhbekf2HguvxTX8L1MgXrHBPACkJVoxsc4wgayHqWiyjbz4ARLxjSnRfYjl/?app=fbl :Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur