Get Mystery Box with random crypto!

History of islamic

የቴሌግራም ቻናል አርማ historyofislam2 — History of islamic H
የቴሌግራም ቻናል አርማ historyofislam2 — History of islamic
የሰርጥ አድራሻ: @historyofislam2
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.21K
የሰርጥ መግለጫ

👉ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)
👉 ቁርአንና የቁርአን ተፍሲር እንድሁም ነብያዊ ሀድሶች
👉ኢስላማዊ ታሪኮች የነብያት የሱሀቦች የሰለፎች የሀገራት የታላላቅ ዳኢዎች ቃሪወች ሌሎችም ታሪኮች ይቀርባሉ ። 👉 እንድሁም ኪታቦች ይቀርባሉ አስተያየት (Comment)በ @Abureyaan ፃፉልን #channel_crate_june20_2018

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 22:26:24 ቁርዓን ተፍሲር



#سورة_الكهف
ሱረቱ Al-kahf
#ክፍል_07 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
374 viewsمصباح, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:55:57 #የነብያት_ታሪክ

#ኢሳ_እየሱስ_ዐለይሂ_ሰላም
                

ይህ ወሬ አይሁዳውያን ዘንድ ሲደርስ አይሁዳውያኑ እጅጉን ተቆጡ....እሱ ዘንድም ተሰብስበው ሊፈትኑት፦"የኑህ ልጅ የሆነውን ሳምን ከሞት ቀስቅሰቅልን" አሉት።
ዒሳም ለጌታው በመተናነስ ህዝቡ ያምን ዘንድ ዱዓ በማድረግ የኑህ ልጅ የሆነውን ሳምን ከሙታን መንደር ቀስቅሶ ከፊታቸው አቆመላቸው።አይሁዳውያንም ስለ ኑህ ዘመን ስለተከሰተው ጠየቁት...ሳምም ሁሉንም ነገራቸው'ና ተመልሶ ሞተ።
በዚህ ሁኔታ ለኢስራኢላውያን የተለያዩ ተዐምራትን ባሳያቸው ቁጥር ጥሜታቸው ይልቅ ይጨምር ነበር።
ዒሳ ለኢስራኢላውያን ከጭቃ የወፍን ቅርፅ ሰርቶ ትንፋሹን ሲነፋበት በአላህ ፍቃድ ወፍ ይሆን ነበር።በዘመኑ መድሀኒት የሌለውን የለምጥ በሽታን በአላህ ፍቃድ ይፈውስ ነበር። ማየት የተሳናቸውንም በአላህ ፍቃድ ይፈውስ ነበር።ነገር ግን አብዝሀኛዎች የጥሜትን መንገድ አሟሙቀው ይዘውት ነበር።
ይህ ሊሆን የቻለውም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ አንድን ነብይ ወደ ህዝቡ ሲልከው ያ ህዝብ የተካነበትን የጥበብ ዘርፍ ለዝያ ነብይ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይሰጠው ነበር።
ለምሳሌ፦ በሙሳ ዘመን የድግምተኞች መራቀቅ የድግምትን ጫፍ ደርሶ ነበር። አላህም ድግምትን የሚያስንቅ ግሩም ተዐምር ለሙሳ ሰጠው።
በዒሳ ዘመንም አይሁዳውያን የህክምናን የጥበብ ጫፍ ደርሰው ነበር።አላህም የነሱን ጥበብ በሚያስንቅ ሁኔታ ለዒሳ ሰጠው።
በረሱላችንﷺ ዘመንም ቁረይሾች የንግግር እና የስነፅሁፍ ጥበብን ከየትኛውም ትውልድ በላይ ተክነውበት ነበር። አላህም የሁሉንም የንግግር ስልት በሚያስንቅ ሁኔታ የቁርአንን ተዐምር አወረደላቸው።
በዚህ ሁኔታ በዒሳ ዘመንም የነበሩ ህዝቦች ከፊሉ በዒሳ ነብይነት ሲያምን አብዝሀኛው ደግሞ ኩፍርን በመምረጥ የዒሳ ጠላት ሆኑ።
ከእለታት አንድ ቀን ዒሳ አላህን፦"ጡባ ምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።
አላህም፦"አንድ ተክል ናት...። እኔ ነኝ በእጄስ የተከልኳት..።ለጀነቶችም ሁሉ አድርግያታለሁ...። ስሯ ከሪድዋን ነው...።ውሀዋም ከተስኒም ነው...።ቅዝቃዜዋም እንደ ካፉር ነው...። ጣዕሟም የዘንጀቢል ነው...። ሽታዋም የሚስክ ነው...። አንድ ግዜ ከሷ የተጎነጨ እስከዘለአለም ጥም አያገኘውም" አለው።
ዒሳም፦" ያ ረብ...እስቲ ከሷ ለኔም አጠጣኝ" አለው።
አላህም፦"ያ የሚጠበቀው ነብይ ከመጠጣቱ በፊት የትኛውም ነብይ እንዲጠጣ አልተፈቀደለትም።የዚያ ነብይ ኡመቶችም ከሷ ከመጠጣታቸው በፊት ለየትኛውም ኡመት መጠጣት አልተፈቀደለትም" ብሎ መለሰለት።
አላህም ቀጠል አድርጎ፦"ዒሳ ሆይ!!! ወደ እኔ(ወደ ሰማይ) ከፍ አደርግሀለሁ"አለው።
ዒሳም፦" ለምን ያ ረብ...?" አለ።
አላህም፦"አሁን ወደ ሰማይ የምሰቅልህ በመጨረሻው ዘመን የዚያን ነቢይ ኡመቶች አጃዒብ ልትመለከት እና የተረገመውን ደጃልንም ልትገድልላቸው አወርድሀለሁ።በሰላት ሰዐት ላይ ሳሉ አወርድሀለሁ ከዚያም አንተ ኢማም ሆነህ አታሰግደቸውም...ምክንያቱም የታዘነላቸው ኡመቶች ስለሆኑ" አለው።
ዒሳም፦" ያ አላህ...ስለኒዝያ ስለታዘነላቸው ኡመቶች ንገረኝ" አለው።
አላህም፦"ዒሳ ሆይ! የአህመድ ኡመቶች እኮ በጥበብ የመጠቁ ዑላማኦች ሲሆኑ ልክ ነቢያትን ይመስላሉ(ኡለማኦቹ)።
እኔ ትንሽ በሰጣኋቸቅ ፀጋ ይደሰታሉ፤ እነሱም ትንሽ በሰሩት ዒባዳ እደሰትባቸዋለሁ። ላ ኢላሀ ኢለላህ በምትለዋም ቃል ጀነትን አስገባቸዋለሁ።
ዒሳ ሆይ!!!! እነሱ እኮ አብላጫው የጀነት ነዋሪያን ናቸው። ምክንያቱም የነሱ ምላሶች ለ(ላኢላሀ ኢለላህ) የተናነሱትን ያህል የማንም ኡመት አልተናነሰም።የነሱ ትከሻዎች ለኔ ሱጁድ በማድረግ የተናነሱትን ያህልም የማንም ኡመት ትከሻም ለኔ ሱጁድ በማድረግ አልተናነሰም" አለው።
በሌላ ቀንም ዒሳ አንድ ትልቅ ተራራ ላይ አላህን እያመለከ ሳለ ኢብሊስ መጣ።ወደ ዒሳም ጠጋ ብሎ፦"አንተ አይደለህ እንዴ ሁሉ ነገር በቀዳ እና በቀደር ነው እያልክ የምትሰብከው" አለው።
ዒሳም፦"አዎና" አለው።
ኢብሊስም፦"እስቲ ከዚህ ተራራ ዝለል'ና ቀደር ነው በል" አለው።
ዒሳም፦" አንተ እርጉም..! አላህ ባሪያዎቹን ይፈትናል እንጂ ባሪያዎች አላህን አይፈትኑም" አለው።
ኢብሊስም፦"የመርየም ልጅ ሆይ!!! አንተ የአምላክነትህ ልቅና በልጅነትህ እንድትናገር አድርጎሀል" አለው።
ዒሳም፦"ልቅናም ሆነ አምላክነት ያ በልጅነቴ ላናገረኝ እና አኑሮ ለሚገድለኝ አላህ ብቻ ነው" አለው።
ኢብሊስም፦"የመርየም ልጅ ሆይ!!! አንተ በአምላክነትህ ልቅና ሙታንን ህያው አድርገሀል" አለው።
ዒሳም፦"ልቅናም ሆነ አምላክነት ያ የፈለገውን ህያው ለሚያደርግ አላህ እና እኔ በሱ ፍቃድ ህያው ያደረግኩትን ለሚገድለው አላህ ነው" አለው።
ኢብሊስም፦ወላሂ አንተ እኮ በሰማያትም በምድርም ጌታ ነህ" አለው። ይህን ግዜ ጂብሪል በክንፉ ኢብሊስን በከፍተኛ ሁኔታ ሲመታው ኢብሊስ በአንዴው የፀሀይ መውጫ ላይ ደረሰ።
ዳግም ሲመታው...ወደ ምዕራብ መጨረሻ አደረሰው።አሁንም ዳግም ክፉኛ ሲመታው በጭቃ እስኪላወስ ድረስ ሰባተኛ ባህር ውስጥ ዘፈቀው።
ከዚያም ይህ ቀልበ ደረቅ ከዛ ባህር ውስጥ በመውጣት ዒሳ ዘንድ ሄደ'ና፦"ወላሂ አንተ የመርየም ልጅ ባንተ ሰበብ የተሰቃየሁትን በማንም ሰበብ አልተሰቃየሁም" አለው።
በመጨረሻም የኢብሊሱ ተከታዮች፦"አለቃችን ሆይ!! ዛሬ በጣም ተሰቃየህ እኮ" አሉት።
ኢብሊሱም፦"አይ ይህ እንኳን የተጠበቀ ባሪያ ነው። እሱን ማጥመም ስለማይቻለኝ በሱ ሰበብ ግን ቁጥር ስፍር የሌለውን ህዝብ አጠማለሁ።እሱንም እናቱንም(መርየምን) ከአላህ ጋር አድርገው እንዲያመልኳቸው ሰዎችን እመራለሁ" አላቻው።
ዒሳ ላይ የሰዎች እና የሰይጣናት ፈተናዎች እጅጉን በዝቶበታል።አሁን የነገሩም መገባደጃ እየተቃረበ መጥቷል....።
ዒሳ አንድ ቀን ሀዋሪያቶቹን ሰብስቦ ለ30 ተከታታይ ቀናት እንዲፆሙ አዘዛቸው።ሀዋሪያቱም ሰላሳውን ቀናት ፁመው ካጠናቀቁ በኋላ ዒሳ ዘንድ በመምጣት፦"የመርየም ልጅ ሆይ!! ፆማችንን አጠናቅቀናል። ከሰማይ ማዕድ አውርድልን። አንደኛ እንበላለን...፣ሁለተኛ ፆማችንን አላህ እንደተቀበለን እናረጋግጣለን...፣ሶስተኛ ደግሞ 30 ቀን ለፆምነውም ዒድ ይሆነናል" አሉት።
ዒሳም ይህን ንግግራቸውን ሲሰማ ለአላህ ምስጋና በማሳነስ እንዳይጠፉ ሰግቶ መከራቸው...።እነሱም የሱን ምክር ወደ ጎን ትተው ማዕዱን አሁን ካላወረድክ ብለው ወጥረው ያዙት(አስቡት እስኪ ሙእሚኖቹ እንዲ ካደረጉት ካፊሮቹ እንዴት እንደሚያንገላቱት!!)
ይህን ግዜ ዒሳ ተስተካክሎ ቆመ አንገቱንም ወደ መሬት አቀርቅሮ ከአይኖቹ የክጃሎት እና የፍራቻ እንባ እያዘነበ እላህን ማዕድ እንዲያወርድ ለመነው።
አላህም፦"እኔ (ማእድዋን) በናንተ ላይ አውራጅዋ ነኝ፡፡ በኋላም ከእናንተ የሚክድ ሰው እኔ ከዓለማት አንድንም የማልቀጣውን ቅጣት እቀጣዋለሁ" አለ።
ከዚያም በኋላ በሁለት ዳመናዎች የተጫነ ማዕድ ከሰማይ በከፍተኛ እርጋታ መውረድ ጀመረ።ዒሳ ማዕዷ ወደ ምድር በተቃረበች ቁጥር፦"ያ አላህ የፀጋ ማዕድ እንጂ የመቅሰፍት ማዕድ አታድርግብን" እያለ ይደጋግም ነበር።
ከዚያም ቀስ በቀስ ማዕዱን የተሸከሙት ሁለቱ ዳመናዎች ወደ ምድር በመቃርብ በእርጋታ የተሸከሙትን ማዕድ በዒሳ ፊት ለፊት አስቀመጡት።
ዒሳም ብድግ ብሎ የማዕዱን ሽፋን፦"በአላህ ስም መልካም ለጋሽ በሆነው"

#የዒሳ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ_የመጨረሻዉ ክፍል

ኢንሽዓሏህ
ይ.....ቀ.......ጥ.......ላ......ል፡፡
860 viewsمصباح, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:35:37 ቁርዓን ተፍሲር



#سورة_الكهف
ሱረቱ Al-kahf
#ክፍል_4 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
1.0K viewsمصباح, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:49:40 #ኢሳ_እየሱስ ዐለይሂ_ሰላም




ያ ነብይ...የሚስክ ሽታ አይነትም ያውዳል...።ከሱ በፊትም ሆነ ከሱ በኋላ እንደሱ አይነት ውብ አልታየም...(እህ!!!እባክህ እንባዬ ትንሽ ታገሰኝ።አይኔን አትጋርደኝ.. ፅሁፌን ልጨርስ)
ዒሳ ሆይ !!! የዛን ነብይ ሀላፊነት ውሰድ..።የእናትህን ሀላፊነት ዘከሪያ ወስዶ እንደተንከባከባት ሁላ...።
ዒሳ ሆይ!!! ያ ነብይ እኔ ዘንድ ለማንም ፍጥረት ካለው ቦታ በላይ ቦታ አለው። ንግግሩ ቁርአን ነው...። ሀይማኖቱም ኢስላም ነው...። እኔም ደግሞ (ሰላም) ነኝ።
የዚያን ነብይ ዘመን ደርሶ የኖረ ሰው ምንኛ ታደለ...!!!በዚያ ዘመንም ያን ነብይ ቀርሶ ንግግሩን የሰማ ሰውስ ምንኛ እድለኛ ነው ..!!!"
አላህ ይህን ካለው በኋላ ሙሀመድ ዐሰ በሱ ዘመን ከመጣ ሙሀመድን ዐሰ እንዲከተል ቃል አስገብቶ መፀሀፉን አወረደለት።

በዚህ በታዘዘው ሁኔታ ዒሳ አላህን በመተናነስ እየተገዛ የጌታውንም ተልዕኮ ማድረስ ጀመረ።ከእለታት አንድ ቀንም ዒሳ መንገድ ላይ ሳለ አንዲት ሴትዮ በአንድ ቀብር ተደፍታ ስትንሰቀሰቅ ተመለከታት።
ዒሳም ጠጋ ብሎ፦"አንች ሴት ምን ሆነሻል!?" ብሎ ጠየቃት።
ሴትዮዋም፦"አንዲት ብቸኛ ልጄ ሞታ ነው።ከሷ ሌላ ምንም ልጅ የለኝም...።እኔም ለጌታዬ እሷን ያቀመሳትን ሞት እስኪያቀምሰኝ ወይም ልጄን አንድ ግዜ ቀስቅሷት እስኪያሳያኝ ይህን ቦታ አልለቅም ብዬ ቃል ገብቻለሁ" አለችው።

ዒሳም፦"አንድ ግዜ ካ

የሻት ግን ይህን ቦታ ለቅቀሽ ትሄጃለሽን?" ብሎ ጠየቃት።
ሴትዮዋም፦"አዎን" አለች።
ዒሳም እዛው ቦታ ላይ ሁለት ረክዐ ሰግዶ ወደ ቀብሩ ጠጋ በማለት፦"አንች ኤኬሌ! በአላህ ትዕዛዝ ቁሚ" ብሎ ጠራት።
ያን ግዜ ቀብሩ ተንቀሳቀሰ። ሁለተኛም ሲጣራ ቀብሩ መከፈት ጀመረ...። ሶስተኛም ሲጣራ ከዒሳም እዛው ቦታ ላይ ሁለት ረክዐ ሰግዶ ወደ ቀብሩ ጠጋ በማለት፦"አንች ኤኬሌ! በአላህ ትዕዛዝ ቁሚ" ብሎ ጠራት።
ያን ግዜ ቀብሩ ተንቀሳቀሰ። ሁለተኛም ሲጣራ ቀብሩ መከፈት ጀመረ...። ሶስተኛም ሲጣራ ከፀጉሯ አፈር እየጠረገች ከቀብር ውስጥ ወጣች።
ዒሳም ከቀብር የወጠችውን ልጅ፦"ስጠራሽ ለምን ዘገየሽ?" ብሎ ሲጠይቃት።
እሷም፦"መጀመሪያ ስትጠራኝ አንድ መልዐክ መጣና ቆመብኝ...ሁለተኛ ስትጠራኝ ነፍሴ በገላዬ ገባችልኝ...። ሶስተኛ ስትጠራኝ ቂያማ የቆመ መስሎኝ ፀጉሬ ቅንድቤ ሀሉ ሸበተ" አለችው።
ከዚያም ልጅቱ ወደ እናቷ ዞራ፦" እናቴ ሆይ..!! ምነው የሞትን መራራ ፅዋ ሁለቴ እንድቀምስ ፈልገሽ ነው ወይ ያስቀሰቀሽኝ...!!! እናቴ ታገሺ የትዕግስትሽንም ምንዳ ከጌታሽ ጠብቂ...። እኔ አሁን ከዱንያ ጉዳይ የለኝም...።አንተ የመርየም ልጅ ሆይ!!! ጌታህ ወደ አኪራ እንዲመልሰኝ ጠይቀው። የሞትንም ጣር እንዳያቀምሰኝ..." አለች ዒሳም ዱዓ አድርጎ ወደነበረችበት የሙታን መንደር በአላህ ፍቃድ መልሶ ቀላቀላት።
ይህ ወሬ አይሁዳውያን ዘንድ ሲደርስ አይሁዳውያኑ እጅጉን ተቆጡ....እሱ ዘንድም ተሰብስበው ሊፈትኑት፦"የኑህ ልጅ የሆነውን ሳምን ከሞት ቀስቅሰቅልን" አሉት........

ኢንሽአሏህ
ይ.......ቀ......ጥ.......ላ......ል፡፡



@historyofislam2
@historyofislam2
970 viewsمصباح, 09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:01:31 ቁርዓን ተፍሲር



#سورة_الكهف
ሱረቱ kahf
#ክፍል_1 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
1.0K viewsمصباح, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 20:55:14 #የነብያት_ታሪክ

#ኢሳ_እየሱስ ዐለይሂ_ሰላም

                

ዳኞቹም፦"የዚህስ ልጅ ስሙ ማን ይባላል" ሲሉት፦"ዒሳ" ብሎ መለሰላቸው።
አስክሬኑም ይህን እንደተናገረም ተመልሶ ሞተ።የዒሳም ንፁህነቱ ተረጋግጦለት ተለቀቀ።
ዒሳም በህፃን አንደበቱ እንዲህ ሲል አላህን ያወድስ ነበር፦"አላህ ሆይ! አንተ ከከፍታህም ጋር ቅርብ ነህ።
ከመቅረብህም ጋር የላቅህ ነህ።
ከፍጥረታትህ ሁሉም የበላይ ነህ
ዒሳም በህፃን አንደበቱ እንዲህ ሲል አላህን ያወድስ ነበር፦"አላህ ሆይ! አንተ ከከፍታህም ጋር ቅርብ ነህ።
ከመቅረብህም ጋር የላቅህ ነህ።
ከፍጥረታትህ ሁሉም የበላይ ነህ።
አንተ ያ... ሰባት ሰማያትን በሀዋእ ላይ የፈጠርክ ነህ።በቃልህም ሰማያት በሀዋእ ረግተው ይኖራሉ።
በሀዋእ ላይ በተንጣለለው ሰማይህም አንተን የሚያወድሱ እና የሚያጠሩህ መላዕክት አሉህ።
በጥቁር ፅልመት በተሞላው ሰማያትም ብርሀንን አድርገሀል።
በፀሀይ ብርሀንም ምድርን አስውበሀታል።
ከምስጋና ጋር የሚያጥራራህ የሆነንም የመብረቅ ነጎድጓድ ፈጥረሃል።
በልቅናህም ፅልመትን በብርሀን ትቀይራለህ።
ያ አላህ !!! በሰማይ አፈጣጠርህ የተባረክህ ነህ።በመሬት አነጣጠፍህም....፤ምድርን ውሀ ላይ ዘርግተኻት በአስፈሪ ማዕበላትም ከበብካት። ግልፅ መተናነስንም አስተናነስካት።
ጥንካሬዋ ለትዕዛዝህ ተናነሰ....።ጉዳይዋም ለትዕዛዝህ እጅ ነሳ...። ለልቅናህም ማዕበላቷ አጎበደደ...። ከባህሮች በኋላም ሀይቆችን አደርግክ...። ከሀይቆችም በኋላ ወንዞችን አደርግክ...።ከወንዞችም በኋላ ወራጅ ጅረቶችንም አፈሰስክ...። ከወራጅ ጅረቶችም በኋላ የምንጭ ውሀዎችንም አመነጨህ ...።ከነዚህም ዛፎችን እና ፍራፍሬዎችን አበቀልክ(ጥራት ይገባህ)
ከዚያም በምድር ጀርባ ላይ ተራራዎችን አደረግክ...።በውሀ ላይም (ተራራዎችን)መሰካትን ሰካህ...።ቋጥኞች እና አሸዋዎችም ላንተ ታዛዥ ሆኖ...።ያ አላህ !!! አንተ ጥራት ይገባህ..። አንተን ማን አሞግሶ ይችላል!!!? ማንስ ያንተን ባህሪ ይመሳሰላል!!!?
ዳመናን ትበትናለህ...፣ እስርን ትፈታለህ...፣ እውነትን ትፈርዳለህ።አንተ ከፈራጆች ሁሉ የተሻልክ ነህ...።ካንተ ሌላ አምላክ የለም..ጥራት ይገባህ ከመላው ሀፅያቶቻችን እንድንመለስ አዘኸናል...። ካንተ ሌላ አምላክ የለም..ጥራት ይገባህ ሰማያትን ከሰዎች አይን ጋርደሀል...። ካንተ ሌላ አምላክ የለም..ጥራት ይገባህ...ከባሪያዎችህ አንተን ሚያገኙህ ብልጦች ብቻ ናቸው...።
እኛ ዝም ብለን ያስገኘንህ ጌታ ላለመሆንህ እንመሰክራለን...። ስምህም የሚዝ-ዘነጋ ጌታ አለመሆንህን እንመሰክራለን...። ካንተ ሌላ የምናመልከው አጋርም የለህም...።ስላንተ እንዳንጠራጠር እኛን ስትፈጥር ማንም ያገዘህ አጋዥ የለህም...። አንተም አንድ እና ብቸኛ መጠጊያ ነህ...። አልወለድክም፤ አልተወለድክምም፡፡
ላንተም አንድም ብጤ የለህም....፡፡"እንዲህ ነበር እንግዲህ ዒሳ ለአላህ በመተናነስ ውዳሴ የሚያደርገው።
ዒሳ በህፃንነቱ ነበር ተአምር ማሳየት የጀመረው።ብዙ ግዜ ከ አከባቢህ ህፃናት ሲጫወት ለህፃናቶቹ፦"ዛሬ እናትህ እንዲ እንዲ...አይነት ምግብ ደብቃልሀለች" ይላቸዋል።
ህፃናቱም ዒሳ በነገራቸቅ መሰረት እናቶቻቸው ዘንድ በመሄድ፦" የደበቅሽልኝን ምግብ ስጭኝ" ይላሉ።
እናቶቻቸውም፦"እንደደበቅኩልህ ማን ነገረህ" ይላሉ።
ህፃናቱም፦"ዒሳ ነው" ብለው ይመልሳሉ።
ከእለታት አንድ ቀን የእየሩሳሌም ነዋሪያን፦"ልጆቻችንን ዒሳ እየበከለብን ስለሆነ ከዒሳ ጋር መዋል የለባቸውም" ብለው በመወሰን ሁሉም በየልጆቹ ላይ በሩን ዘግቶ ማዋል ጀመሩ....
ዒሳም የሚጫወታቸውን ጓደኞቹን ሲያጣ በየቤታቸው እየዞረ፦ኤኬሌ...የለም?!!!" ብሎ ይጠይቃል።
ወላጆቻቸውም፦"የሉም" ይሉታል።
ዒሳም፦"አረ ድምፃቸውን እየሰማሁ እኮ ነው" ሲላቸው
ወላጆቻቸውም፦"አይ ይህ የምትሰማው የዝንጀሮዎች ድምፅ ነው" ይሉታል።
ያን ግዜ አላህም ልጆቻቸውን ዝንጀሮዎች ያደርግባቸው ነበር።
በዚህ በሁኔታ ዒሳ እና እናቱ መርየም በርካታ እንቅፋቶችን በማሳለፍ ረጅም አመታትን ኑረው ዒሳም የተውራትን ትምህርት ከተለያዩ ካህናት እየቀሰመ ጎረመሰ።
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ዒሳ ላይ ኢንጂልን ከማውረዱ በፊት ለዒሳ፦" ዒሳ ሆይ! በማዝህ ነገር ጠንከር በል፣ አዳምጥ ፣ታዘዝም...። አንተ የንፁዋ፣የድንግሏ፣የዓቢዷ...ልጅ ሆይ!!! አንተን ያለ ወንድ እና ሴት ንክኪ ፈጥሬሀለሁ። ለአለማትም ተዐምር ትሆን ዘንድም ፈጥሬሀለሁ....።
እኔን ብቻ አምልክ...፣በኔም ብቻ ተመካ...፣ የምሰጥህንም መፅሀፍ በርትተህ ያዘው። ይህንንም መፅሀፍ ይዘህ ሲርያንኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዘንድ ሂደህ አላህ እውነተኛው፣ህያው የተብቃቃ እና ዘውታሪ ጌታ ነው በላቸው።
ዒሳ ሆይ!!! ያን ማንበብም ሆነ መፃፍ የማይችለውን አረባዊ ነብይም መምጣቱን አበስር።
ያ..ነብይ የውበትን ዘውድ ተላብሷል...።ጎላ ባለ ሁኔታ ረጅም አይደለም...፣አጭርም አይደለም መካከለኛ ነው። መልኩም ነጭም አይደለም... ጥቁርም አይደለም...ግን ውበት ያለው ቅላት አለው።
ያ ነብይ...የሰውነቱም አቀማመጥ ለእይታ ማራኪ ነው። ሁለቱ ትከሻዎቹ የተራራቁ ናቸው...ትከሻው ሰፊ ነው።እስከ ትከሻው የሚደርስ ረዥም ፀጉርም አለው...። ፂሙ ብዛት ያለው እና ጠቅጠቅ ያለ ነው ...።
ጣቶቹም ወፋፍራም ናቸው... ጉልበትን
የመሳሰሉ የአጥንት መገጣጠሚያዎቹ እንደዚሁ ሰፋ ያሉና ወፈር ያሉ ናቸው...።
ፊቱ ክብ ነው፡፡ አይኑም ጥቁር ነው፡፡ የአይኑ
ሽፋሽፍቶችም ረዣዥም ናቸው፡፡ የአይኑ ዙርያ ቀይ ነበር፡፡ ከደረቱ ጀምሮ እስከ እንብርቱ ድረስ የሚወርድ የሰውነት ፀጉር አለው፡፡
በሚራመድ ወቅት ልክ ወደ ቁልቁለት እንደሚወርድ ሰው ፈጠን
ብሎ እግሩን በኃይል እያነሳ ነው ሚራመደው፡፡ ፊቱ
ልክ ጨረቃ በየወሩ 15ኛው ቀን እንደምታብረቀርቀው ያብረቀርቃል። ፊቱ ጨረቃን የሚመስል ያህል የፈካ ነው፡፡ ድምፁ
ያማረ ነው...፡፡ ጉንጩ ቀለል ያለ ነው...፡፡ አፉ ተለቅ ያለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የወንዳወንድነት የተሟላ ባህሪ ነው፡፡ ሆዱ እና
ደረቱ ቀጥ ያለና የተስተካከለ ነው፡፡


@historyofislam2
@historyofislam2
1.2K viewsمصباح, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 21:18:32 《الصحيح المصفى من سيرة النبي المصطفى 65
የነብዩ ሙሀመድ ﷺ ታሪክ /ሲራ/
ክፍል 65
በሼህ አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ አብደላህ

ነስር መስጂድ /ዳንዲ ቦሩ ሰፈር/ በመቀራት ላይ ያለ

@historyofislam2
1.2K viewsمصباح, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:17:00 #የነብያት_ታሪክ

#ኢሳ_ዐለይሂ_ሰላም






መርየምም የመውለጃ ሰዐቷ በተቃረበ ግዜ የቤተ አምልኮውን ግቢ ለቃ ወጣች።ብቻዋን #በረሀ ላይ ሳለች ምጡ ጀመራት በጣምም አመማት አሁን ያለችበትን እንግልት እና ከመውለዷ በኋላ የሚከተላትን እንግልት ስታስብ፦"ዋ! ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ" ብላ ተመኘች።
በመጨረሻም ወደ አንድ የደረቀ #የተምር_ዛፍ ዘንድ በመጠጋት ልጇን ዒሳን ተገላገለች።ልክ ልጁን እንደተገላገለች ጂብሪል መጣ'ና፦" አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡
የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም" አላት።
በልታ ስታበቃም ጂብሪል፦"ማንም ሰው ሊያናግርሽ ቢፈልግ እኔ ለአር ረህማን(ለአላህ) ማንንም ሰው ላላናግር ፆሚያለሁ በይ" አላት።
ኢብሊስም መርየም ልጇን ከተገላገለች በኋላ ወደ ኢስራኢላውያኑ ካህናት በመሄድ የመርየምን መውለድ ነገራቸው።ካህናቱም በጣም በመቆጣት ይዝቱባትም ጀመሩ።
ከዚያም መርየም ልጇን ተሸክማ ወደ ቤተ አምልኮው መጣች። ሁሉም ተሰብስቧል....ገና ፊትለፊታቸው ብቅ ስትል፦"የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም" አሏት።(የሀሩን እህት ያሏት ሳሊህ ሰዎችን በሀሩን ስለሚመስሉ ነው።)
እሷም ምንም መልስ ሳትሰጥ ህፃኑን እንዲያናግሩ ወደ ልጇ አመላከተቻቸው።ሁሉም በሁኔታዋ በመገረም ዚና ያደረገችው እንሷት እኛ ላይ ታሾፋለች እንዴ እያሉ ከተነጋገሩ በኋላ፦"በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን" አሏት።
ያን ግዜ ህፃኑ ዒሳ ቀና በማለት፦"እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል።
በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል፡፡
ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)፡፡ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም።
ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን" ብሎ ተናገረ።
ይህን የህፃኑን ንግግር በሰሙ ግዜ ሊወግሯት ተሸክመው የመጡትን ድንጋይ ይዘው ተመለሱ።
የአላህ ፍቃድ ሆኖ #ዒሳ አድጎ ከህፃናት ጋር በመንገድ ላይም ለመጫወት በቃ።
ከእለታት አንድ ቀን ዒሳ ከአከባቢው እኮዮቹ ጋር በመጫወት ላይ ሳለ አንድ ህፃን ሌላኛውን ህፃን በእግሩ ገፍትሮ ሲጥለው ህፃኑም የዒሳ እግር ስር ወድቆ ሞተ።
ሰዉ ሲሰበሰብ ሟች ህፃኑን በዒሳ እግር ስር ወድቆ ተመለከቱ።
የህፃኑ ገዳይ ዒሳ ነው በማለትም ዒሳን በጨቅላ እድሜው ለፍርድ አቀረቡት።
ዳኛውም፦"ህፃኑን ገድለሀልን?" ብሎ ሲጠይቀው
#ዒሳም፦"አልገደኩትም" አላቸው።ከዚያም ዒሳን ለቅጣት ዚያዘጋጁት ዒሳም ለዳኛው፦"እሺ የሞተውን ህፃን አምጡልኝ" አለ።
ዳኛውም በዒሳ ሁኔያ በመገረም የህፃኑ አስክሬን እንዲቀርብ አዘዘ'ና #ዒሳ ፊትለፊት ላይ ቀረበለት።
ዒሳም ዱዓ ሲያደርግ አስክሬኑ በአላህ ፍቃድ ህያው ሆነ።ከዚያም አስክሬኑን፦"ማን ገድሎህ ነው?" ብለው ሲጠይቁት፦"ኤኬሌ...ነው" ብሎ የገዳዩን ልጅ ስም ጠራላቸው።
#ዳኞቹም፦"የዚህስ ልጅ ስሙ ማን ይባላል" ሲሉት፦"ዒሳ" ብሎ መለሰላቸው።
አስክሬኑም ........


ለወዳጅ ዘመድዎ ሸር ያድርጉ


ኢንሻአላህ ይቀጥላል

@historyofislam2
@historyofislam2
1.1K viewsمصباح, 18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:41:31 ቁርዓን ተፍሲር


#سورة_الإسراء 11

በሼህ: አቡ ኒብራስ ሙስጦፋ አብደላህ حفظه الله
https://t.me/tefsser/497
904 viewsمصباح, 17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 07:22:46 ምክር ከሸህ ፈውዛን حفظه الله

ፍቺ በዝቷል። የፍቹ መንስኤ ደግሞ ሴቶች ናቸው። ስነምግባራቸው ተበላሽቷል። ከባለቤታቸው ጋር ያላቸው መስተጋብር ተሰባብሯል። ኩሩ ሆነዋል። በወንዶች ላይ የበላይ መሆንን ሽተዋል። በአንድ ቤት ሁለት ወንድ ሆኗል ነገሩ። በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ ባል መታገስን አይችልም። ባል ትእዛዙን የምታከብርለትን ሴት ነው የሚሻው። በቤቱ የምትኖርን እና እሱ አስተዳዳሪ የሆነበትን ትዳር ነው የሚፈልገው። አሁን ላይ ግን ሚስቶች ባል ሆነዋል። ወንዳወንድ ሴቶች።
1.2K viewsمصباح, 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ