Get Mystery Box with random crypto!

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /2/ ገላትያ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁶ በክርስቶስ ጸጋ እናን | ሕያው ቃል

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /2/


ገላትያ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ ⁷ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ⁸ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። ⁹ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን ¹⁰ ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።

ሌላ ወንጌል የለም /1÷6-10/

(ቁ.ር 6-7) ጳውሎ በገላትያ ክርስቲያኖች ባሕርይ እጅግ መደነቁን ያሳያል ። የገላትያ ሰዎች ከቅርብ ጊዜ በፊት የጸጋ ወንጌል ተቀብለው ነበር ፤ አሁን ደግሞ በፍጥነት ከዚህ ወንጌል ፊታቸውን  መመለስ ጀመሩ ። ከኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ አይሁድ ክርስቲያኖች የገላትያ ክርስቲያኖችን ሌላ ወንጌል እንዲከተሉ ጥረት ያደርጉ ነበር ።  ይህ <<ወንጌል>> ድኅነት በጸጋ ሳይሆን በሥራ እንደሚገኝ የሚናገር ሲሆን ፥ የገላትያ ክርስቲያኖችን ግራ አጋብቶአቸዋል ። (በቁ.ር 7) ። ጳውሎስ ግን የእነርሱ <<ወንጌል >> እወነተኛ ወንጌል እንዳልሆነ በመናገር ፥ እውነተኛው ወንጌል ድኅነት በጸጋ  መሆኑን ተናገረ ። እነዚህ የገላትያ ክርስቲያኖች የሚያደርጉት የሚያሳዝንና የሚያሳፍር  ነገር ነው ። በጳውሎስ ስብከት የእግዚአብሔር ነጻና ወሰን የለሽ ጸጋ ተቀብለዋል ። አሁን ግን ጳውሎስንና የጠራቸውን እግዚአብሔርን ዘነጉ ። የእግዚአብሔርን ጸጋ ተቃወሙ ፥ አቃለሉትም ።  ጳውሎስ የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ለሚሞክሩ ሐሰተኛ መምህራን ነው የተቃወመ ደብዳቤ የጻፈው ።  የእነዚህ መምህራን ትምህርት ክርስቶስ ብቻ  አያድንም የሚል ነው ። ሰለዚህ ለመዳን የአይሁድ ሕግ መፈጸም አስፈላጊ ነው ።  እንዲሁም ያለ ትምህርት የክርስቶስን ጸጋ ከንቱ የሚያደርጉ ነው ። ጸጋ ከወንጌል ከተለየ ወንጌል መሆኑ ይቀራል ።  ጳውሎስም ከዚህ የተነሳ  መንፈሳዊ ልጆቹ ከእውነተኛው ወንጌል  እንዲርቁ አይፈልግም ። ልናስትውል ይሚገባን  ጳውሎስ እነዚህ ቦታ የጻፈው የአይሁድ ሕግ በመጠበቅ ለመዳን አስፈላጉ ነው የሚለውን የስሕተት ትምህርት ለሚያስተምሩ አንዳንድ አይሁድ ክርስቲያኖች ነው ። በዚህም ዘመን ቤተክርስቲያናትን ሊያናውጥ የሚችል የስህተት ትምህርት ሊኖር እንደሚችል ይህ መልእክት ምሳሌ ይሆነናል ። በየትኛውም ሐገር ለመዳን አንዳንድ ሕግጋትን ወይም የሃይማኖታዊ ወጎችንና ለማዶችን መፈጸም እንዳለብን የሚያስተምሩ አሉ ። እውነተኛው ግን ሰው የሚድነው በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ነው የሚል ነው   ይህ የክርስቶስ ወንጌል መሰረት ነው ።

(ቁ.ር 8-9) ከዚህ የምንማረው የእግዚአብሔር ስራ የእግዚአብሔር ወንጌል እንዴት ትልቅና አስፈላጊ  እንደሆነ ነው ። የእግዚአብሔር ወንጌል በማንኛውም መንገድ በየትኛውም አቅጣጫ ልንቀይረው አይገባም ።  ሰባኪ ወይም አስተማሪ መልአክ እንኳን ቢሆን የእግዚአብሔር ቃል የመለውጥ ስልጣን የለውም ። የእግዚአብሔር ቃል መስበክና ማስተማር ከባድ ኃላፊነት ነው ። እኛም በታማኝነት ልንሰብከው እና ልናስተምረው ይገባል ። ምክንያቱም ወንጌልን የመጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈበት አላማ  በመጻረን ከሰበክን በእግዚአብሔር የተረገመ እንሆናለን ። ቃሉን የሚሰሙት ከአንዱ እውነተኛ ወንጌል ጋር ሊጣበቁና ከሐሰተኛ መምህራን ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል ።

(ቁ.ር 10) በገላትያ የነበሩ የጳውሎስ ተቃዋሚዎች ጳውሎስ የሚጥረው ሰዎችን ደስ ለማሰኘት  ብቻ ነው ብለው ከሰውታል  ። ጳውሎስ የአይሁድ ሕግን መከተል አያስፈልግም በሎ የሚያስተምረው ከአሕዛብ ወገን የሆኑትን  የገላቲያ ሰዎችን ደስ ለማሰኘትና  ድኅነትን በቀላቁ እንዲያገኙ የሚያደርገው ጥረት ነው ይላሉ ። ጳውሎስ ግን ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እንደማይሞክር ተናግሯል (1ጢ 2÷6) ። በዚህ መልእክት ጳውሎስ የገላትያ ክርስቲያኖችን በብርቱ ገሥፆአቸዋል ። ሰዎችን ደስ እያሰኙ የእግዚአብሔር አገልጋይ  መሆን በጣም የሚያስቸግር ነገር እንደሆነ ጳውሎስ በዚህ ቦታ ተናግሯል ። ሌሎች ሰዎች ምንም ቢያስቡ የክርስቶስ አገልጋይ የሆኑ የሆኑ ወንጌልን በታማኝነት ሊሰብኩ ይገባል ። (1ተሰ 2÷4) ። የሰባኪ ዋንኛው ዓላማ ክርስቶስን ማክበርና ሰዎች ወደ ድኅነት መንገድ መምራት ነው  (1ቆሮ 9÷19 ፣ 22-23) ።

ይቀጥላል ......

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid0GseKmrdMMv5keFkgMdvxSDcEQWpZE5xAXpkapzFS9CAd3WhNr2L6rSLtj9sqi9Zxl/?app=fbl
Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur