Get Mystery Box with random crypto!

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /1/              መግቢያ ገላትያ አሁን ቱርክ | ሕያው ቃል

የገላትያ መልእክት ማብራሪያ ክፍል /1/
       
     መግቢያ

ገላትያ አሁን ቱርክ ተብላ በምትጠራዋ አገር ማዕከላዊ ስፍራ የምትገኝ የቀድሞው የሮም መንግስት አንዷ ክፍለ ሐገር ነበረች ። ጳውሎስ ለገላቲያ ቤተክርስቲያኖች የጻፈው ይህ መልእክት ለአንዲት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ለብዙ አብያተክርስቲያናት ነበር። እነዚህም አብያተክርስቲያናት በተለያዩ ዓመታት ቀደም በለው ጳውሎስ ራሱ የመሰረታቸው ናቸው ። በዚህ መልእክቱ ላይ ስማቸውን በዝርዝር ስላልጠቀሰ ለየትኛው እንደጻፈ አይታወቅም ። በተጨማሪም ይህን መልእክት የተጻፈበት ትክክለኛ ዓመት ባይታወቅም አንዳንድ ሊቃውንት በ54_56 ዓ.ም ወስጥ ተጽፏል ሲሉ ሌሎች ደግሞ በ48-49 ዓ.ም እንደተጻፈ ይናገራሉ ። ጳውሎስ ይህን ደብዳቤ የጻፈበት ምክንያት በመልእክቱ በግልጥ ተጠቅሶ ይገኛል ።እነዚህን የአሕዛብ አብያተክርስቲያናት እንደመሰረተ አንዳንድ አይሁድ ክርስቲያኖች መጥተው የጳውሎስን ትምህርት መቃወም ጀመሩ ። ጳውሎስ ያስተምር የነበረው ፣ ሰው በእግዚአብሔር ፀጋና በእምነት አማካኝነት እንደሚድን ነበር  (ኤፌ 2÷8)። እነዚህ አይሁድ ክርስቲያኖች ግን አንድ ሰው ለመዳን የአይሁድ ሕግ በተጨማሪ መፈጸም እንደሚገባው አስተማሩ ። የእነዚህ አይሁድ ክርስቲያኖች ትምህርት ከተስፋፋ የጳውሎስ የፀጋ ወንጌል ከንቱ ሆነ ማለት ነው ። ስለዚህ ገና ሕፃን የሆኑትን የገላትያ ክርስቲያኖች በአይሁድ ክርስቲያኖች ትምህርት ምክንያት ከእውነተኛው የመዳን መንገድ እንዳይስቱ ለማድረግ የስህተት ትምህርት የሚቃወም መልእክት መጻፍ ነበረበት ። የገላትያ ሰዎች ድህነትን በሕግ ስራዎች ለማግኘት ጥረት ማድረግ ከጀመሩ የተቀበሉትን ጸጋ በማጣት አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚታወቀው ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች የጻፈው መልእክቱ የላቀ ዋጋ ሲስጠው ቆይቷል።አንዳንድሰዎች ድህነትን በራሳቸው ሥራና ጥረት ለማግኘት ይፈልጋሉ ። ሰለዚህም በሐይማኖታዊ ወጎችንና ሥርዓቶችን በመፈጸም እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ይሞክራሉ ። በገዛ ብርታታቸው ጻድቅ ለመባይል ይጥራሉ ። ነገር ግን ይሄ ሁሉ ድካም ከንቱ ነው ። ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚያገነው በጸጋ ብቻ ነው ። እግዚአብሔር ከታላቅ ፍቅሩና ከብዙ ምሕረቱ የተነሳ ለኃጢአተኞች ሰዎች የሰማይን በር ከፍቶላቸዋል ። በክርስቶስ በማመን በዚህ በር ማለፍ ይቻላል ።ይህ ለገላትያ ክርስቲያኖች የተጻፈው ዋና መልእክት ነው ።
   
ሰላምታ /1÷1-5/

ጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ እንዲሆን በቀጥታ የተሾመ ሰው ነበር ።ይህን ኃላፊነት በሌሎች ሰዎች አማካኝነት አልተቀበለም ። በአዲስ ኪዳን ሐዋርያ ማለት ወንጌል ለመስበክና ቤተክርስቲያንን ለመመስረት  ከክርስቶስ ልዩ የሆነውን ስልጣን የተቀበለ ሰው ነው ። በአዲስ ኪዳን የነበሩት በዙዎቹ ሐዋርያት የክርስቶስን ትንሣኤ በአይናቸው የተመለከቱ ናቸው ። ጳውሎስ በደማስቆ የነበሩትን ክርስቲያኖች በማሳደድ ስጓዝ ኢየሱስ አገኘው (ሐዋ 9÷3-6) ። ሐዋርያ እንዲሆን ከኢየሱስ ሐዋርያነትን ሹመት ተቀበለ (ሐዋ 9÷15 ፣  26÷16 ) ።ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ለእኛም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ሙሉ ስልጣን ይህን መልእክት ጽፏል ። ሰለዚህም የገላትያ ሰዎች የጳውሎስን ደብዳቤ ልብ ሊሉ ይገባቸዋል እኛም እንዲሁ (ሮሜ 1÷1 ፣ ኤፌ 1÷1 ማብራሪያውን ይመልከቱ )። ጳውሎስ የተጠራው በእግዚአብሔር አብና በኢየሱስ ክርስቶስ  እንደ ሆነ አስተውሏል ። ኢየሱስና አብ አንድ አምላክ ናቸው ። ሁልጊዜ በአንድነት ይሰራሉ ። ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች  እንደ ጳውሎስ ክርስቶስን ለማገልገል ተጠርተናል ። እንደ ጳውሎስ የተለየ ስልጣን ባይኖረንም ደቀ መዛሙርት እንድንሆንና  ከክርስቶስ ጋር እንድንወርስ ተመርጠናል ። የተለዩ ሐዋርያት ብቻ የእግዚአብሔር ስራ እንደ ሚሰሩ አንጠብቅ ። እግዚአብሔር ለያንዳንዳችን የምንሰራለትን ሥራ ተሰጥቶናል ። ይሄንን ስራ እንድንሰራም በመንፈስ ቅዱስ የሚያስፈልገንን ጸጋና ኃይል ሰጥቶናል ።
ኢየሱስ እራሱ .. “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥”( ዮሐንስ 14፥12)

(ቁ.ር ,2) በዚህ ቁጥር ለየትኛው ለገላትያ አብያተክርስቲያናት እንደ ጻፈ አይታወቅም ፣ አያሌ የመጻሕፍት ቅዱስ ሙሁራን ጳውሎስ የጻፈው በደቡብ ገላትያ  ወደሚገኘው የጲስዲያ  ፣አንጾኪያ  ፣ኢቆንዮን ፣ ልስጥራን ፣ ደርቤን የሚባል ከተሞች እንደሆነ ይናገራል ። (የሐ 13÷14 ፣ 14÷1 ፣16÷1-2 ገለጻውን ይመለክቷል) ። ጳውሎስ እነዚህ ከተሞች ሁሉ በመጀመሪያውና  በሁለተኛው ተልእኮ የጎበኛቸው ናቸው ።

(ቁ.ር ,3) ጳውሎስ መልእክቱን የሚያነቡ ሰዎች ጸጋንና ሰላምን እንዲያገኙ የጸልያል ። ጸጋና ሰላም ዋና ዋና የሆኑ የወንጌል አዕማድ ናቸው ። በመጀመሪያ ጸጋ ከዛም ሰላም ጸጋ ሁልጊዜ የመጀመሪያ ነው ። ማንኛውም ነገር ምንጩ ጸጋ ነው ። የተጠራነው በጸጋ ነው ። በጸጋ ኃጢያታችን ይቅር ተባለ ፣ በጸጋ ዳንን ፣በጸጋ ጸደቅን ፣ ቅድስና አገኘን በጸጋ ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ሰላም አለን ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ክርስቶስ ወደምድር መጣ ፣ ሰለ ኃጢያታችንም ስርየት እራስን ሰጠን። ጸጋ ብድራት አይደለም ውሰን የሌለው የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት ነጻ ስጦታ ነው ። ስለዚህም ጸጋ  ክብርን ለእግዚአብሔር መስጠትና ማመስገን መተው የለብንም (ሮሜ 1÷7 ፣ኤፌ 1÷2 እና ማብራሪያውን ይመልከቱ ) ። እዲሁም ጸጋና ሰላም ከእግዚአብሔር አብና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ  እንደሚመጡ እናስተውል ። እግዚአብሔር እና ክርስቶስ አንድ ናቸው (ዮሐ 10÷30)።

(ቁር ,4-5)  ክርስቶስ ሰለ ኃጢያታችን ራሱን ሰጠን ። የእርሱ መስዋዕትነት ለድኅነታችን ሙሉና በቂ ነው ። ለድኅንነታችን እኛ የምናደርገው ነገር የለም ። ነገር ግን እምነታችን በክርስቶስ ላይ መሆን ይኖርበታል ። ክርስቶስ ከዚህ ክፉ አለም አዳነን ። ይህ ዓለም የሲጣን መንግስት ነው ፣ ሲጣን የዚህ ዓለም ገዢ ነው ፤ (ዮሐ 16÷11)። ክርስቶስ እኛን ከዚህ ዓለም አላወጣንም ነገር ግን ከዚህ ክፉ ዓለም አዳነን (የሐ 17÷15)

ይቀጥላል.
እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉ ።

ወገኖቼ ይህን ትምህርት ትኩረት ሰጥታችሁት እንድትማሩ እለምናለው ። ስትማሩ ወንጌል ከጎናችሁ አድርጋችሁ አንድላይ በታጠኑ ይበልጥ ይገባችኋል ። ትምህርቱን ለሌሎች አጋሩ ።

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid035mrCdvJhbekf2HguvxTX8L1MgXrHBPACkJVoxsc4wgayHqWiyjbz4ARLxjSnRfYjl/?app=fbl
Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur