2022-08-23 18:56:50
ከተራራው ላይ
ክፍል ስድስት
(ፉአድ ሙና)
.
‹‹እህህም ሲደላ፣ ሺህ ስቃይ ቢከበኝ ማንባት የት ተገኝቶ፣
የሆዴን ረመጥ፣ መታገስ ነው እንጂ በብሶት ተሞልቶ፣
አይነገር ነገር!››
***
ቅዳሜ ማታውን አብዱኬ ስልኩን ይዞልኝ መጣ፡፡ በጣም የሚያምር አዲስ ስልክ ነው፡፡ ከቤተ-መፅሀፍቱ እየወጣን አብዱኬ ‹‹ስሚ ይኼ አዲስ ሞዴል ነው፡፡ እነሱ አራት ሺህ ብር ካገኙበት በቂያቸው ነው፡፡ አንቺ በደንብ አትርፈሽበት ትሸጪዋለሽ፡፡ ከቤቱ አስራአምስት ምናምን የሚሸጥ ስልክ ነው፡፡›› አለኝ፡፡
ከፍቼ ሳየው ውስጡ ላይ ምንም የለውም፡፡ ‹‹አስፈሮርምተኸው ነው እንዴ?››
‹‹አዎ ፓተርን ምናምን ነበረው፡፡ በቃ አሁን ከቤቱ ሲወጣ እንዳለው ነው! አያስፎግርም!››
‹‹ግን ምን ብዬ ልሸጠው ነው?››
‹‹ከውጪ ተልኮልኝ ነው ምናምን እያልሽ ነዋ! ግን ደግሞ ሰው እየመረጥሽ!››
ስልኬ ጠራ፡፡ የማላውቀው ቁጥር ነበር፡፡ አነሳሁት፡፡
በጣም በተረጋጋ ድምፅ ‹‹አብርሼ ደህና አመሸህ …… ምህረት ነኝ፡፡›› አለች፡፡
‹‹ደህና አመሸሁ! ደህና አመሸሽ?››
‹‹ደህና …… ይቅርታ በዚህ ሰዓት ስለደወልኩ …… ጠዋት ያለንን ቀጠሮ አልረሳኸውም አይደል?››
‹‹አዎ! ለማህሌት እኮ ነግሬያት ነበር፡፡ ውሀውንም ገዝቻለሁ፡፡ እና ደግሞ አቤላ ላይብረሪው ጋር ይጠብቃችኋል! እንዳይጠፋችሁ እሱ ይዟችሁ ይመጣል!››
‹‹እሺ አብርሽዬ በጣም እናመሰግናለን፡፡ በቃ አስራሁለት ሰዓት ሰፈራችሁ ለመድረስ እንሞክራለን!››
ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ፡፡ አብዱኬ ማናት በሚል አይን ተመለከተኝ፡፡ ነገርኩት፡፡
‹‹እና ነፍ ቺኮች ሰፈራችንን ሊያስጨንቁት ነዋ? …… ኧረ ይኼማ አያመልጠኝም! ነገ ስራ ከሰዓት እሄዳለሁ፡፡››
አሳቀኝ፡፡ በቀጣዩ ቀን ጠዋት ላይ እኔና አብዱኬ ታች ወርደን ጠበቅናቸው፡፡ በሶስት የቤት መኪና ተከታትለው መጡ፡፡
‹‹ስሚ ኢቦ ህብረት ምናምን ናቸው አላልሽም እንዴ?›› አብዱኬ ከመኪናቸው የሚወርዱት ልጆች ላይ አይኑን እንደጣለ ጠየቀኝ፡፡
በእርግጥ እኔም የጠበቅኩት ብዙ ሰው ነበር፡፡ አቤል ሳይቆጠር በጥቅሉ ከመኪናዎቹ የወረዱት አስር ብቻ ነበሩ፡፡ ሁለት ወንዶች አሉ በተረፈ ሁሉም ሴቶች ናቸው፡፡ ሴቶቹ ለመንቀሳቀስ የሚመቹ ቀሚሶችን አድርገዋል፡፡ ሰላም ተባብለን ማህሌትና ምህረት እየተቀባበሉ ሌሎቹን አስተዋወቁኝ፡፡ ሁሉም ረጋ ያሉ ናቸው፡፡
‹‹ስሙ ቀሚስ አድርጋችሁ ነው እንዴ የምትወጡት? ወይስ ልትቀይሩ ነው?›› አብዱኬ ከፊት ከፊት እየሄደ ይጠይቃቸዋል፡፡
ምህረት ሰልፊ ስቲኳ ላይ ስልኳን እያሰረች ‹‹እኛ እኮ ሱሪ አንለብስም!›› አለችው፡፡
‹‹ጴንጤ አይደላችሁ እንዴ …… ለምን አትለብሱም?››
‹‹ጴንጤ አይደለንም …… ሐዋሪያት ነን!›› ፈገግ አለች፡፡
አብዱኬ ወደኋላ ዞር አለና በግርምት ‹‹ሐዋርያት የሚባል እምነት አለ?›› አለ፡፡ ፈገግ አለችለት፡፡
‹‹ገባሻ እኔ ፌሎው ምናምን ሲሉ የምሰማው እነሱን ስለሆነ ነው፡፡ ኮንትራት ምናምን ጉዞ እንወስዳቸው ስለነበር እንደዛ ነበር የመሰለኝ!››
‹‹ልክ ነህ ብዙ አይደለንም …… በተለይ ወደዚህ ደግሞ የለንም ማለት ይቻላል፡፡››
የኛ ቤት ቅያስ ጋር ስንደርስ እኔና አቤላ ሮጥ ብለን ውሀውን ይዘን ደረስንባቸው፡፡ አብዱኬ እያሳሳቃቸው እኔና አቤላ ውሀውን እያከፋፈልን ማህሌት የቤቶቹን አቀማመጥ በግርምት ማየት ጀመረች፡፡
‹‹እነዚህ የኤሌክትሪክ ገመዶች የሚሰሩ ናቸው?›› ማህሌት በአጠና የተቀሰቱትን ገመዶች እያየች ጠየቀችኝ፡፡
‹‹የሚሰሩ ናቸው …… ሁሉም ቤት ቆጣሪ የለም ለዛ ነው፡፡ ከአንድ ቦታ ነው ስበን የምንጠቀመው!››
‹‹ዝናብ ሲዘንብ እንዴት ነው የምትንቀሳቀሱት? …… me even አሁን ራሱ በጣም ከብዶኛል!››
‹‹ያው ህይወትሽ ሲሆን ትለምጂዋለሽ! …… ምን አማራጭ አለን?››
‹‹ጎርፍ ምናምን የለም?›› ምህረት ጨዋታችንን ተቀላቀለች!
‹‹አንዳንዴ ይኖራል፡፡ ቤትም ይገባል፡፡ ተኝተሸ ከሆነ ደግሞ ልትበሰብሺም ትችያለሽ፡፡ …… ግን ያው ደግሞ ያልፋል፡፡››
ማህሌት ድክም እያላት ስለነበር በእጇትከሻዬን ተደግፋ መሄድ ጀመረች፡፡ በጣም ዳገታማ ሲሆንና ሲከብዳቸው ቀደም ብለን እየወጣን እጃችንን እንሰጣቸውና እየታገሉ ይወጣሉ፡፡ ወደ ተራራው ከፍ እያልንና ከቤቶቹ እየራቅን ስንመጣ ትንሽ እንድናርፍ ጠየቁን፡፡ አብዱኬ እየዞረ ሁሉንም ያበረታታቸዋል፡፡ ነቃ እንዲሉ እየዞረ ጀርባቸውን አሸት አሸት ያደርጋቸዋል፡፡ ትንሽ አርፈው ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ በመጨረሻም የተራራው ጫፍ ላይ ደረስን፡፡ በጣም ደስ ብሏቸዋል፡፡ትንሽ አረፍ እንዳልን አንዱ ወንድ ከመፅሀፍ ቅዱስ እየጠቀሰ ትንሽ አስተማረ፡፡ ሀሳቤ ሌላ ቦታ ስለነበረ ምን እንዳለ አልሰማሁትም፡፡ ቦታው ስለሚያምር ሁላችንም በአንድነት በምህረት ስልክ ሰልፊ ተነሳን፡፡
ወደ ታች መውረድ ስንጀምር ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ሆኖ ስለነበር ሰፈራችን የተለመደ ግርግሯን ጀምራለች፡፡ የውሀ ወረፋ ለመያዝ ቢጫ ጀሪካን ይዘው ወደ ታች የሚሮጡ ህፃናት …… በየቤቱ በር ላይ በቁምጣ ቆመው ፀሀይ የሚሞቁ ወጣቶች …… ከታች ውሀ ተሸክመው ዳገቱን የሚወጡ ሴቶችና ወንዶች …… ብዙ ትዕይንት ይስተዋላል፡፡
ማህሌት አይኗ በእንባ ሞልቶ ‹‹ሁሌም እንደዚህ ነው …… I mean ውሀም የላችሁም?›› አለችኝ፡፡
‹‹ታች ቦኖ አለ፡፡ ከዛ እንቀዳለን!››
‹‹ሁሌ ይኼን ዳገት መውጣት …… I don’t know ብቻ everything is abnormal!›› እንባዋ ፈሰሰ፡፡ አቅፌ ጠረግኩላት፡፡
‹‹you know what? I wanna see your home. ይቻላል?››
‹‹ቤታችንን …… እሺ!››
አብዱኬ ዳገቱን እስክንወርድ አንድ ጊዜ እንኳን ከእኔ ጋር አልነበረም፡፡ ልጆቹ ጨዋታው ስለተመቻቸው ከበው እየሰሙት እየቀደደላቸው ነው፡፡ እኔ፣ አቤላ፣ ማህሌት እና ምህረት ብቻ ተገንጥለን ወደ ቤት ሄድን፡፡ ወደ ቤታችን የምታስገባዋ ጠባብ ቁልቁለት ለእነማህሌት በጣም ፈተና ሆናባቸው ነበር፡፡
ቤት ስንደርስ ኢንቱዬ ድምፅ ሰምታ ብቅ ብላ አየችን፡፡ ፈገግ ብላ እየተመለከተቻቸው ‹‹እንዴ ጥቁር እንግዳ!›› አለች፡፡
በተራ በተራ እየሳሙ ተዋወቋት፡፡ ባለአንድ ክፍሏ ጎጇችን ውስጥ ገብተው አረፍ ብለው መቃኘት ጀመሩ፡፡ እማዬ ስላመማት ከመኝታዋ አልተነሳችም፡፡ ኢንቱዬ የሚቀመስ ነገር ለማዘጋጀት መንደፋደፍ ጀመረች፡፡ ወዲያው ምህረት ‹‹በቃ …… እንድረስባቸው!›› ብላ ተነሳች፡፡ ኢንቱዬ የሆነ ነገር እንዲቀምሱ ብትለምናቸውም በእጄ አላሉም፡፡ ከቤታችን ወጥተን ዋናውን መንገድ እንደያዝን የጥያቄ ናዳ ያዘንቡብኝ ጀመሩ፡፡
‹‹ኪችን የት ትጠቀማላችሁ?››
‹‹ሻወር የት ትወስዳላችሁ?››
‹‹ያለ አልጋ እንዴት ትተኛላችሁ?
ብዙ ብዙ ለእነሱ ውስብስብ የሆኑባቸውን ጥያቄዎች እየጠየቁኝ መለስኩላቸው፡፡
ከተራራው ወርደን መኪናዎቻቸው ወደቆሙበት ቦታ ስንደርስ ጁስ ከመኪና አውጥተው እየተከፋፈሉ ነበር፡፡ አብዱኬ ቺፕሱንም ጁሱንም እየዞረ ያከፋፍላል፡፡ ተቀላቅለናቸው ጁሳችንን መጠጣት ጀመርን፡፡
‹‹አብዱኬ ግን የሌለ ፈታ ያልክ ሰው ነህ ከምር …… can I get your number …… please?›› አለች ማህሌት ስልኳን እየሰጠችው!
‹‹ስልኬን ማለትሽ ነዋ …… ምን ጣጣ አለው ኧረ ያዥው ……›› ቁጥሩን ፃፈላት፡፡
ትንሽ እረፍት ከወሰዱ በኋላ ለመስተንግዶው ከልብ አመስግነውን ሄዱ፡፡
እኔና አብዱኬ ቦኖው ጋ ሄደን ከወገብ በላይ እና እግራችንን ተጣጥበን ወደ ቤት ተመለስን፡፡ ወደ ቤት ስገባ ኢንቱን መሬት ላይ ስትንከባለል አገኘኋት፡፡ ‹‹ኢንቱ!!!!!!›› እየሮጥኩ ተንበር
777 views15:56