Get Mystery Box with random crypto!

ሀላል ትዳር👫💍

የቴሌግራም ቻናል አርማ hayu_abdi — ሀላል ትዳር👫💍
የቴሌግራም ቻናል አርማ hayu_abdi — ሀላል ትዳር👫💍
የሰርጥ አድራሻ: @hayu_abdi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.54K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-08-17 12:57:18 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

ደብረዘይት እየተጓዝን ነዉ ሁለታችንም ተፈራራን እሱ ሂኩ አለኝ
እኔም አቤት
መኪና መንዳት ትችያለሽ አለኝ
...እኔም አልችልም መንጃ ፍቃድ የለኝም አልኩት
......እሱም ኢንሻ አላህ እኔ ነኝ የማወጣልሽ...እኔስ ያለመኪና መንቀሳቀስ አይሆንልኝም ይሄን መኪና አባቴ ነዉ ገዝቶ የሰጠኝ አላህ እድሜዉን ይጨምርለት አለኝ፡፡

........እኔም አዎ ትክክል ነህ የታክሲዉም ወጭ አለ ታክሲ በፈለክበት ሰአት አይገኝም ብታገኝም በየቦታዉ ስለሚቆም አላህ እርዚቅ ለሰጠዉ ሰዉ መኪና ገዝቶ መገላገል ይሻላል አልኩት፡፡
..
ደብረዘይት ደርሰን ወደ የት ነዉ የምንሄደዉ አልኩት
.....እሱም ባቡጋያ ሪዞርት ነዉ አለኝ፡፡ ባቡጋያ ሪዞርት የአዲስ አበባ ባለሀብቶች እሁድ ከቤተሰቦቻቸዉ የሚዝናኑበት ሁሉንም ያካተተ መዝናኛ ነዉ በጣም የሚያምር የደስ ደስ ያለዉ ብዙ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተማሪዉ የመንግስት ሰራተኛዉ የሚመርጠዉ መዝናኛ ነዉ፡፡
.... ደብረዘይት ደረስን ወደ ባቡጋያ ሪዞርት መኪናዉ ጉዞ ጀመረ፡፡
ባቡጋያ ሪዞርት ገብተን መኪናዉን አቆመ ፡፡ የሚያምር መዝናኛ ነበር ፡፡ እየዞርን አብረን ሰልፊ ፎቶ እየተነሳን እስከ አስር አንድ ሰአት ቆየን....

አስራ አንድ ሰአት አካባቢ ሂኩ አይንሽን ጨፍኚ አለኝ እሺ ብየ ጨፈንኩኝ...... በስጦታ እቃ የተጠቀለለ ሰጠኝ.....ክፈችዉ አለኝ እሺ ብየ ስከፍተዉ የሚያምር የወርቅ የአንገት ሀብል ነበር፡፡
ያየሁትን ማመን አቃተኝ ለእኔ ነዉ ?? አልኩት እሱም አዎ ብሎ አንገቴ ላይ አረገለኝ .......በጣም ደስ አለኝ እሱም የወደፊት የእኔ ነሽ ብሎ ...ከንፈሬን ሳመኝ ሲስመኝ በጣም ደነገጥኩ .... ግን የደስታ ድንጋጤ ሳይሆን አይቀርም እኔም ደስ ብሎኝ በቃ ከምነግራችሁ በላይ ወደድኩት በመሳሳም የእሱን ፍቅር ልገልፀዉ አልቻልኩም.....ከአላህ ህግጋት ዉጭ ጭልም ወዳለዉ በእጅ የማይጨበጠዉ ፍቅር የሚባል የሚባል ነገር ተጃጃልኩ፡፡ የቀራሁት ቁርአን ሀዲስ እኔን ሊያስቆመኝ እኔን ሊከለክለኝ እኔን ከወንጀል ሊታደገኝ ካልቻለ የአላህ ቃል ቁርአን ካልመለሰኝ፡፡ የነብዩ ሀዲስ ለኔ ሂወት መስመር የማያሲዘኝ ከሆነ፡፡ ዲኔ እኔን በሂወት ዉጣ ዉረድ ላይ ባስቀመጠዉ ህግ የማልተዳደር ከሆነ ቁርአን ሀዲስ መቅራቱ እንደኔ ላሉ ሴቶች በቀኝ ጆሮ አዳምጦ በግራ ጆሮ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡

ብቻ ቃል ግባልኝ
እውነቴን ነው ፍቅሬ ምንም አልዋሸሁም
ማስመሰል ማካበድ ፈፅሞ አላስብም
አንድ እውነት አለኝ የልቤን ልንገርህ
ከኔ አስበልጨ ነው እኔ አንተን የምወድህ !
ለምን ያልከኝ እንደሁ ሁሉ ነገሬ ነህ::

አሳ ከውሃ ውስጥ ወጥቶ እንደማይኖረው
እኔም ካንተ ብርቅ ሂወቴ እንደዛው ነው
ድብርቴ ወደር አልባ ፍፁም መራራ ነው::
መብላት መጠጣቴ መሳቅ መቦረቄ
አንተ ጋር ስሆን ነው አውቃለሁ ጠንቅቄ

እና ምን ልልህ ነው አትራቀኝ ውዴ!
እኔ ካንተ ሌላ ሂወት አለኝ እንዴ?
ድጋሜ ልንገርህ የምኖር ላንተ ነው
ያንተን ደስታ ማየት ከስኬት በላይ ነው
ከኔ ከራከኝ ግን የምሞት ያኔ ነው
አደራ እንዳትርቀኝ እስትንፋሴዬ አይንህ ነው::

ግን ፍቅሬ....
ይህን ሁሉ መንገር ለምን አስፈለገሽ
ቆይ አታውቅም እንዴ እኔ እንደምወድሽ?
ብለህ እንደምትለኝ አልጠራጠርም
እንደው ብሰጋት እንጅ ሳላምንህ አይደለም!
ይገርምሀል ውዴ ብዙ እጨነቃለሁ
ቀኑ ይቅር እና ለሊሊት አስባለሁ
እኔ
እስካለም ፍፃሜ ምንግዜም ያንተው ነኝ
ፍቅሬ ይህን ስልህ አትጨነቅብኝ
ከኔ እንደማትርቀኝ ብቻ ቃል ግቢልኝ ??

እሱን ሳየዉ ደስታ ይሰማኛል እሱ ጋር አብሮ መዝናናቱ ፎቶ መነሳቱ በጣም ደስተኛ እያረገኝ ነዉ ፡፡
ሰኞ አስራ አንድ ሰአት ተኩል ሆነ ፡፡
ባቡጋያ ሪዞርት እየተዝናናን ነዉ ጥንድ ጥንድ ሁነዉ የሚዝናኑባቸዉ ለሁለት ሰዉ ብቻ የተሰሩ የሚመስሉ ጎጆዎች አሉ እነሱ ዉስጥ ሁለታችን ብቻ ገብተን ቁጭ አልን ፡፡የሚበላ ነገር አዘን ቁጭ ብለን አይን አይኔን ያየኛል እኔም እያየሁት በቃ የሚያረገኝ ግራ ገባኝ
....ሳላስበዉ አንድ ድንገተኛ ጥያቄ ከሀይደር አፍ ወጣ ግን ሂኩ ለምን ዛሬ አብረን አናድርም አለኝ...ጥያቄዉ አስደነገጠኝ ዝም ብየ አይን አይኑን ማየት ጀመርኩ....ዛሬ በጣም ደስ ብሎኛል ወደ አዲስ አበባ ከምንመለስ እዚሁ ደብረዘይት አድረን ነገ እንመለሳለን፡፡ አንድ ላይ እንደር እመኚኝ ለወደፊት የትዳር አጋሬ አንቺ ነሽ..ይህን የአንገት ሀብል የገዛሁልሽ ስለማከብርሽ ስለምወድሽ ነዉ...
እመኚኝ ሂኩ አለኝ.............
ሀይደር ይቅርብን እኔ ከቤቴ ዉጭ አድሬ አላቅም እናቴም ትቆጣለች ተረዳኝ እባክህ
እሱም እንዴ የአንቺ ደስታ ደስታየ ነዉ መከፋትሽ ሁሌም ያስከፋኛል፡፡ ወላሂ እመኝኝ መቼም አልተዉሽም የመጀመሪያየ ነሽ ..አለኝ

....እኔም እናቴ ትቆጣኛለች ማደር አልችልም..ነገም ትምህርት እገባለሁኝ፡፡ አንተ የማትመልሰኝ ከሆነ እኔዉ እሄዳለሁ በትራንስፓርት መቼም ቢሆን አንተ ጋር ማደር አልችልም ሳንጋባ ኒካህ ሳናስራ አላህን ልንፈራ ይገባል፡፡ አልኩት ቆጣ ብየ
ግን ሀይደር የሚነግረኝ የሚሸመግልብኝ ቃላቶች ከኔ በላይ ሆነ መልስ ምቱን ከሀይደር እኔ ከማወራዉ እሱ የሚመልሰዉ እያመዘነ ይመስለናል፡፡ ሀይደር ጋር ልደር አልደር እናቴስ ምን ትለኛለች እያልኩ በተለያየ ሀሳብ ተምታትቻለሁ፡፡ እመኝኝ የሰዉ ልጅ ካልተማመን ለወደፊት ትዳር አንተማመንም ማለት ነዉ ሂኩ ለኔ አንቺ አመለካከትሽ ምንድን ነዉ ? እኔን አግብተሽ መኖር አፈልጊም እንዴ ንገሪኝ ቁርጤን ልወቀዉ እስከ አሁን እወድሀለሁ የምትይኝ ዉሸትሽን ነዉ ማለት ነዉ ይለኛል ሀይደር በሚያሳዝን አገላለፅ አለማመን ፡፡
እኔም ..ለመወሰን ግራ ተጋባሁ ግን አንድ ዉሳኔ ዛሬ ግድ ነዉ......

ሂክማ እሺ የምትል ይሆን በቀጣዩ ክፍል እናያለን
162 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:08:21 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

ለፊርዶስ ምን ልበላት እንደባለፈዉ በቤተሰብ የመጣ አለ ብዬ ልዋሻት እንዴ ??? ወይስ እዉነቱን ልንገራት እያልኩ ሁለት ልብ ሆንክ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በመጨረሻም አንድ ዉሳኔ ወሰንኩ ነገ....ፊርዶስን ሳገኛት ጓደኛየ ናት ለኔም ለወንድሟም እያሰበች አንድ ከጎኔ ላለችዉ ፊርዶስ የኔን ማንነት ከመጀመሪያዉ እስከመጨረሻዉ ልነግራት ወሰንኩ፡፡
እንደምንመ ብሎ የወፎቸ ጫጫታ ንጋትን ሊያበስር ብቅ አለ ፡፡ እኔም ቁርሴን በልቼ እናቴ የምታቃቸዉ ሰዎች ስለሞቱ ለቅሶ ደርሼ ልምጣ ቤት ጠብቂኝ ብላ ከቤት ወጣች፡፡ እኔም ጊዜ መግደል አልፈለኩም እኔ ለዙበይር እንደማልሆነዉ እራሴን እነደረከሰ ሴት ስለምቆጥር በጊዜ እኔን እንዲረሳ እኔን እንዳያስታዉስ ለእህቱ ፊርዶስ ልነግራት ወሰንኩ፡፡
ስልኬን ማታ እንዳጠፋሁት ነበር ወዳዉ ስልኬን አብርቼ ለፊርዶስ ደወልኩ
....ፊርዶስም ሂኩ ዛሬ አዳሬን ስጨነቅ እንቅልፍ ሳይወስደኝ አደረ ትናንት ለሰራሁት ስራ አዉፍ በይኝ ዙበይር ጋር ለማገናኘት መጀመሪያ አንቺን ማስፈቀድ ነበረብኝ ብላ እንባ እየተናነቃት ጠየቀችኝ
......እኔም ፊርዱ አንቺ ምንም ጥፋት የለብሽም ስታጠፊ ነዉ አዉፍ የምልሽ ...አንድ ነገር ላማክርሽ ነዉ አሁን የደወልኩልሽ የማይሽ እንደእህቴ ነዉ ደስታየንም ሀዘኔንም ልትካፈይኝ በምነግርሽ ነገር ላትርቂኝ በሆዴ አፍኜ የያዝኩትን የሆድ እሳት የሆነብኝ ሚስጥር ልነግርሽ ወስኛለሁ እኔን ልታዳምጪኝ ልትረጂኝ ዝግጁ ነሽ አልኳት
......ፊርዶስም እንደመደንገጥ ብላ እሺ ዝግጁ ነኝ አለችኝ
......አሁን ከተመቸሽ እቤት መምጣት ትችያለሽ አልኳት
......እሷም እሺ ሂኩ አሁን መጣሁ አለችኝ፡፡

ፊርዶስም ጊዜ ሳትፈጅ በፍጥነት እኛ ቤት ከተወሰኑ ደቂቃዎች ቡሀላ መጣች፡፡ ስገባ ሂኩ አሰላሙ አለይኩም ትናንትና አንቺን ሳላስፈቅድ በሰራሁት ስራ አዉፍ በይኝ ጥፋተኛ ነኝ ይቅር በይኝ እያለች እኔን መለመን ጀመረቸ፡፡
...... ወላሂ ከአንቺ ምንም ጥፋት የለም በራሴ ችግር ነዉ እንደዚህ የሆንኩት ዛሬ ኢንሻ አላህ ትረጂኛለሽ ብየ አስባለሁ ....
ፊርዱ በማወራሽ ሚስጥር እኔ እና አላህ ነን የምናቀዉ አሁን አንቺን የዚህ ሚስጥር የምታቂዉ ከአላህ ከእኔ ቀጥሎ አንቺን ላማክርሽ ልነግርሽ ነዉ ግን ስነግርሽ ጠንካራ ልትሆኝ ይገባል እንደ አጋጣሚ እንባየ ቢፈስ አንቺም ማልቀስ የለብሽም አደራ አልኳት
ፊርዶስም በመደናገጥ እሺ አለችኝ
እኔም ከረጅም ዝማታ ቡሀላ በፊት ስለትምህርቴ ስለጉብዝናየ .. ስለtelegram profile አርጌ......ሀይደር የሚባል ተዋወቄ......አምኘዉ እስከ ደብረዘይት ያሳለፍነዉን በመንታ እንባ የታጀበ እያወረሆት እንባየ ልብሴን እስከሚያርሰዉ አንድ ባንድ ነገርኳት ቂርአትም የገባሁት በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ሁሉንም እያለቀስኩ ለፊርዶስ ነገርኳት ፊርዶስም አብራኝ ታለቅስ ነበር፡፡
ባለፈዉ ሲሀም ዘመዴ ነዉ ያለችኝ ቁጥሬን የሰጠነዉ ቢክራ ነሽ ወይ ብሎ ሲጠይቀኝ ይሄ በሆዴ ያፈንኩት ሚስጥር ስላለኝ በመዋሸት በቤተሰቦቼ የመጣ ትዳር አለ ብየ መለስኩኝ ..አሁንም ይህን ሁላ የነገርኩሽ ያለምክንያት አይደለም እኔ ለወንድምሽ ለዙበይር የትዳር አጋር መሆን አልችልም የቆሸሸ ማንነት ነዉ ያለኝ ዙበይር ከአሁን ቡሀላ እኔን ይወደኝ እንደሆነ ከአሁን ቡሀላ ከኔ ተስፋ ይቁረጥ ፡፡
እኔ ማለት ይህን ነገር ደብቄ ቤተሰቦቼ ሲጨናነቁ አንዱ ከአንዱ ከአንዱ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር በዚሁ የተነሳ ቁርአን ይቀራብሽ ተብየ ደሴ ከተማ ድረስ እንደሄድኩ ....እናቴ ስታለቅስ ስትዉል አጎቶቼን አስጨንቄ ነዉ የኖርኩት አላህ ይምረኝ ይሆን ?? ደግሞ በሀይደር ተናድጄ ከቅርብ ቀናት በፊት ሚስቱን በFace book አግኝቻት ልነግራት የእሱንም ሂወት ላበላሽበት ወስኜ ስልኳን እስከ መቀበል የደረሰ ተግባብተን ደዉየ ልነግራት ብየ ለወለደቻቸዉ ልጆች እና የወደፊት የእሷ ሂወት አሳዝኖኝ ተዉኩት ፡፡ ፊሮዶስ የኔ ወንጀል ብዙ ነዉ አላህ ይምረኝ ይሆን?? አላህ ይምረኝ ይሆን ??
አላህ ያለልኝን እጠብቃለሁ ግን እኔ ለዙበይር የምገባ ሴት አይደለሁም ለዙበይር ሌላ ፈልጊለት እኔ መፈቀር የሚገባኝ ሰዉ አይደለሁም እኔ ማለት ከአንዱ ወንጀል ወደ አንዱ ስረማመድ አሁን ድረስ እኔ በማንነቴ የማፍር..........ብየ ንግግሬን ለፊርዶስ አስረድቼ እምባየን እየጠረኩ ከፊርዶስ ጎን ተነሳሁ፡፡ ፊርዶስ አብራኝ ተነስታ

#part 17 ይቀጥላል
464 views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 04:25:54 እዉነተኛ ታሪክ

#Part 15
ስልኬን አዉጥቼ ልደዉል አልኩና የኢክራም ቁጥር አዉጥቼ ልነግራት ወስንኩ ግን ጨነቀኝ የኔ ሂወት አንዴ ተበላሽቷል ግን የሶስት ሰዉ ሒወት ላበላሽ እንደሆነ ተሰማኝ ሁለት ልጆቿ እና ኢክራም ..ደግሞ ወደ ፍች ከሄዱ ልጁቹ ካለቤተሰብ ፍቅር ተለያይተዉ ኢክራም ወደ ቤተሰቦቻ ትሄዳለች ሌላም ችግር ፈጠርኩ ማለት ነዉ ..የቤተሰቦች ቀዉስ ስልኬን ይዤ ይሄንን አሰብኩ ግን ሀይደር የሰራኝ ስራ መልሶ አእምሮየ ጋር ብልጭ ይልብኛል፡፡ ሁሉንም ነገር ለአላህ ሰጠሁኝ ስልኬን አቅፌ እንደ ወራጅ ወንዝ ማልቀስ ሆነ ያረቢ እርዳኝ ያረቢ እርዳኝ እያልኩ
........የኢክራምን ስልክ ከContact አጠፋሁ Facebook ላልጠቀም ከአሁን ቡሀላ የሀይደርን ሚስት ኢክራምን ላላወራ ብየ ለራሴ ቃል ገባሁ በአላህ ተወከልኩ እስከአሁንም የሰራሁትን ስራ አላህ ይማረኝ..በሀይደር ከነቤተሰቦቹ እሱን ልጎዳዉ ነበር ይቅርብኝ አላህ እሱንም ያስተካክለዉ እኔንም አላህ የተሻለ ይስጠኝ ብየ ዱአየን አርጌ ለመጨረሻ ጊዜ ከሀይደር ለመበቀል ያሰብኩት ሀሳብ ሰረዝኩኝ፡፡

Face book መጠቀም አቆምኩ ግን ሀይደር የሰራኝ ጉድ ለማን ሰዉ እንደምተነፍሰዉ አላቅም አዳሬን ብቻ ማልቀስ ሁኗል ስራየ ፡፡ ከዛ የማይነጋ የለም ነጋ......ወደ ቂርአት ሄድኩ ፊርዶስን አገኘሇት ዛሬ ሂደሽ እናትሽን አስተዋዉቂኝ ብላኝ ከቂርአት መልስ እናቴን አስተዋወኳት ፊርዶስ በረፍት ሰአቷ እኛ ቤት እየመጣች ቤተሰባዊ ጓደኛም ሆነች አላህ የሰጠኝ የዲን እህቴ ፊርዶስ.....እሁድ እንደምጋብዘኝ ነገረችኝ .......ወበሪ ሆቴል....ከአሱር ቡሀላ እንሄዳለን አለችኝ፡፡ እኔም እሺ ፊርዱ አልኳት፡፡ ቀናቶች በተቆጠሩ ቁጥር እሁድ ደረሰ ፊርዶስ አሱርን እኛ ቤት መጥታ አብረን ወበሪ ሆቴል ሔድን እዛ ስደርስ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ ወንድም ዙበይር ቀድሞን መጥቶ ቁጭ ብሎ እየጠበቀን ነዉ፡፡ እኔም ዙበይርን በፊርዶስ ስልክ አፎቶ ላይ አንዴ ስላየሁት እሱ እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ ፊርዶስ ግን ዙበይርም ነዉ አይደለምም አላለችኝም...እሷ ሶስት ወንድሞች ስላሏት ሀይደርም ላይሆን ይችላል ብየ ጠረጠርኩ፡፡ የሚጠጣ ነገር አዘን አንዳንድ ወሬ እያነሳን ከተጨዋወትን ቡሀላ የሚበላ የሚጠጣ ከተጠቀምን ቡሀላ እኔን ሸኝተዉኝ ወደ የቤታችን ተመለስን

ግን ማን ይሆን እያልኩ ሳስብ ሳስብ ....ዙበይር ይሆን እያልኩ ብቻየን ባዶ ቤት ቁጭ ብየ ስከራከር ዳኛ ከሌለዉ ክርክር ዉስጥ ስልኬ ጮኸ ስልኬም ከክርክሩ ገላገለኝ...ስልኬን ሳየዉ የደወለችዉ ፊርዶስ ነበረች
,,...አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ አለች
......እኔም ወአለይኩም ሰላም ፊርዱ ደህና ነሽ
.......አልሀምዱሊላህ በሰላም እቤት ገባሽ አለችኝ
.....እኔም አዎ ገብቻለሁ ፊርዱ
ብዙ ተራ ወሬዎች ካወራን ቡሀላ

....ሂኩየ ቅድም አብሮኝ የመጣዉ ማን እነንደሆነ አዉቀሽዋል አለችኝ
.....እኔም መቼም አንቺ ከአጂ ነብይ ጋር እንደማትሄጅ አቃለሁ፡፡ ከሶስት ወንድሞችሽ አንዱ ይሆናል ፊርዱ አልኳት፡፡
.....አዎ አልተሳሳትሽም ዙበይር ነዉ ፡፡ በአካል አገናኚኝ እያለ ረበሸኝ ምን ላርግ ፊርዱ አንቺ ነሽ እኮ አይቴ(የወንድሜ ሚስት ለማለት ነዉ) ዙበይርም ወንድሜ ነዉ ፡፡ ዙበይር ናፈቀችኝ ናፈቀችኝ ሲለኝ ነዉ እስከዛሬ በሩቅ ነበር የሚያይሽ ዛሬ ፊት ለፊት እንዲያይሽ ያረኩት አለችኝ ፊርዱ
.....እሷ ባለችኝ ነገር ደርቄ ቀረሁ የምመልሰዉ አጣሁ መልሴ ዝም ሆነ ...

....ፊርዶስም ሄሎ ሄሎ ሄሎ ሂክማ ምነዉ ዝም አልሽ ...አረ በአላህ አጥፍቼ ከሆነ ይቅርታ እንደዚህ ይከፋሻል አላልኩም ሂክማ ..አረ አናግሪኝ አስጨነቅሽኝ .....ሂክማ አረ ሂክማ እያለች እሰማታለሁ ስልኩን አልዘጋሁትም ነበር፡፡

እኔ ምንም የምመልሰዉ መልስ የለም ብቻ እንባየ ቁልቁል ሲወርድ ይታወሰኛል

ፊርዱም ሄሎ ሄሎዉ ማለቷን አላቆመችም በድንጋጤ ..እኔም ስልኩን ዘጋሁት መልሳ ፊርዶ ደወለች እኔም አላነሳሁኝ.....ፊርዶስ በመደወል ትደጋግም ይዛለች.....እኔም በtext ነገ የማወራሽ ነገር አለ ብየ በmessgae ልኬ..ስልኬን አጠፋሁት፡፡ ለፊርዶስ ምን ልበላት እንደባለፈዉ በቤተሰብ የመጣ አለ ብየ ልዋሻት እንዴ ??? ወይስ እዉነቱን ልንገራት እያልኩ ሁለት ልብ ሆንክ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በመጨረሻም አንድ ዉሳኔ ወሰንኩ ነገ....ፊርዶስን ሳገኛት

ለፊርዶስ በሆዷ ያፈነችዉን ሚስጥር ሂክማ ትነግራት ይሆን ??? ለሂክማ ነገረች ማለት ዙበይር ሊርቃት ይችላል እናንተ ምን ትላላችሁ ??
በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን፡፡

#Part 16 ይቀጥላል
928 views01:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 17:36:00 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

በጣም ተናደድኩ ሀይደር የራሱን ኑሮ እየኖረ የኔን ሂወት አበላሽቶ ጨለማ አድርጎ እኔ በሂወት እያለሁ መኖር አይችልም ብየ ወሰንኩኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ የእሱን ሂወት ማበላሻ ......ሀይደርን ለመበቀል በጣም ቀላል ዘዴ አገኘሁ
Face book ገብቼ የfb ጓደኞች እያየሁ ሚስቱን በprofile ስላየሆት የfb ጓደኛዉ እንደሆነች ብየ መፈለግ ጀመርኩኝ፡፡ ጓደኞችን ስመለከት ብዙዎቹ ጓደኞቼ ሴት ነበሩ ገረመኝ፡፡ Fb ላይ ከ3000 በላይ ጓደኞቼ ነበሩት በስንት ድካም ልፋት ቡሀላ አንድ ፎቶ አየሁ የእሱ እና የእሷ profie የሆነ፡፡ time line ገብቼ ስመለከት የእሷ የብቻ ፎቶም አለ ፡፡ ሲጋቡ የተነሱ ፎቶዉ ላይ መብሩክ በሉኝ ብላ ፅፋለች፡፡

ያሰብኩት ተሳካ አሁን frind አርጌ የእኔን ሂወት እንዳበላሸብኝ የእሱን ላበላሽበት ወሰንኩኝ፡፡ እኔ እያለቀስኩ እሱ ስቆ እንደማይኖር ወሰንኩኝ ...frind request ላኩላት ከአንድ ቀን ቡሀላ ተቀበለችኝ ...በጣም ደስ አለኝ ሀይደር የእኔ ሂወት አበላሽቶታል የእሱንም ሒወት አበላሸዋለሁ እያልኩ ብቻየን እየዛትኩ ነዉ፡፡ face book ላይ online ቀን ቀን አትጠፋም ነበር ፡፡ ነገሮችን ሁሉ ሳስበዉ እሱ ማታ ማታ በስልኩ ይጀናጀናል እሷም ቀን ላይ ብየ አሰብኩ በትዳር በመሀላቸዉ የሆነ ክፍተት እንዳለ ያስታዉቃል፡፡ እኔም እያወረሇት ነዉ በሂደት ተዋወቅን ግን ለክፉም ለደጉም ብየ ትክክለኛ ስሜን አልነገርኳትም ፡፡ ሚስቱ የአዲስ አበባ የመርካቶ ሰፈር ልጅ እንደሆነች ስሟም ኢክራም እንደምትባልና የባሏም ስም ሀይደር እንደሚባል እና የሁለት ልጆች እናት እንደሆነች ..... የባለሀብት ልጅ ሀይደርን በጣም እንደምወደዉና በፊት ሹፌር ነበር ተዋወቅን ተዋደን ተጋባን ....ከዛም አባቴ ሀይደርን ከሹፍርና ስራ አቁም ብሎት አሁን መርካቶ ሱቅ ከፈተልን ከዛም የቤት መኪናም ዶልፊን አባቴ ገዝቶ እንደሰጠዉ አጫወተችኝ፡፡

ኢክራም በጣም ግልፅ ልጅ ናት ሁለ ነገሯ ተመቸችኝ ፡፡
አንቺስ ብላ ጠየቀችኝ እኔ ቂርአት እየቀራሁ እንደሆነ ነገርኳት፡፡ ስለ ሀይደር ምንም አላነሳሁ፡፡ ግን በጣም ገረመኝ ወንድ ልጅ ሴትን ልጅ ለማጥመድ በእጁ አድርጎ የሚፈልገዉን ለመዉሰድ የማይፈነቅለዉ ድንጋይ የለም ዉሸታቸዉ ከባድ እንደሆነ ተረዳሁ ፡፡ ጥፋቱ የኔ ነዉ የነገረኝን ማመኔ ብቻ ወደ ጆሮየ የገባዉ ሁሉ እዉነት ይመስለኝ ነበር ሚስጥሩ እያደር ገባኝ ማታ ማታ ስደዉል አይመችም ስልክ ለማንሳት በtelegram እናወራለን የሚለኝ ሚስቱ ኢክራም ሲያወራ እንዳሰማዉ እንደሆነ ገባኝ፡፡
ግን ለምን አረ ለምን ኢክራም ወዳዉ ከሹፍርና ኑሮ ገላግላዉ በቤተሰቦቿ ጥረት ሱቅ ተከፍቶለት መኪና ተገዝቶለት እሷ ባለዉለታዉ ሁና በመኪናዉ ሴት ሲሸወድ እንደ እኔ ያለዉን የተዘነጋ በማዘናጋት እንደዚህ መሆኑ ለኢክራም አዘንኩ፡፡ ወይ ጎራ ሁን ወይ ጎራ ተጠጋ አይደል የሚባለዉ ሀይደር ጎራ ተጠግቶ ይሄዉ በኢክራም ጥረት እና በቤተሰቦቻ ሀብት ለሌላ ለሀራም አላማ እየተጠቀመበት በመሆኑ ያሳፍራል፡፡ ደግሞ ለኔ የዋሸኝ ዉሸት ፊቴ ላይ ድቅን አለብኝ፡፡ ምነዉ ሀይደር ዉሸታም ነዉ ብየ ንገሪያት ንገሪያት የሚል መንፈስ ከጀርባየ አለ፡፡ ሀይደር ዉሸታም ነዉ ብየ ፅፌዉ ልልከዉ ብየ ቆይ ለሁሉም ሰአት አለዉ አልኩና ባልሽን ትወጅዋለሽ ብየ ጠየኳት
....በጣም ሀይደር ሁለ ነገሬ ነዉ በጣም እወደዋለሁ ያለ እሱ መኖር አልችልም በስራም ጎበዝ ነዉ ዉይ ሲወደኝ እኮ ብላ ታወራኝ ይዛለች በfb
......ግን ስለ እሱ መጥፎ ነገር ብሰሚ..ትጠይዋለሽ አጠይዉም ብየ ጠየኳት

.....እሷም እንዴ ሀይደር መጥፎ ነገር የለዉም የሚሰራዉን የሆነዉን ሁሉን ይነግረኛል እኔን ሳያማክር ፈፅሞ አያቅም ፡፡ በህይወቴ እሱ ነዉ የመጀመሪያየ ወንድ በጣም ነዉ የምወደዉ፡፡ ምንም መጥፎ አይሰራም እተማመንበታለሁ አለችኝ፡፡

...እኔም አይ ግን ሰርቶ ብታገኝዉስ አልኳት
.......ጭራሽ አያረገዉም ጥያቄዉ መልስ የለዉም ሁሌም ቢሆን በሀይደር የምተማመንበት ጨዋ ልጅ ነዉ፡፡አላህ በስንት ዱአ መሰለሽ የሰጠኝ አለችኝ፡፡

በጣም ደስ የምትል ሚስት አለችዉ ግልፅ ናት እኔም ማንነቴን ደብቄ እናወራ ይዘናል ከመግባባት ብዛት ስልክ ቁጥሯን ተቀበልኳት፡፡ ስልክ ቁጥሯም0911....2372 ብላ በfb text አረገችልኝ ፡፡ እቤቴ ሁኜ ማሰብ ጀመርኩኝ ሀይደር የእኔን ሂወት እንዳበላሸ ላበላሽበት ወይስ እኔን አላህ ይክሰኛል ቶብቻለሁ ለሚስቱ እና ለሁለት ልጆቹ ሒወት ብየ ልተወዉ እያልኩ ተወዛገብኩ፡፡ ያሳለፍኳቸዉ የደብረዘይት ጊዚያቶች እና አሁን ትዳር ሲመጣ የምጨነቃቸዉ ጭንቀቶች ፊቴ ላይ ድቅን ይላሉ፡፡
ይህን ጉዳይ ለፊርዶስ አላማከርኳትም ...ፊርዶስ ብሰማ ምን ትለኝ ይሆን ?
ስልኬን አንስቼ ቀጥታ ለኢክራም ልደዉል ቁጥሯን አዉጥቼ የሀይደርን ጉድ ልነግራት ወሰንኩ፡፡ ሀይደር እኔን እንደሸወደ ሚስቱን ሲሸዉድ አይኖርም ...ስልኬን አንስቼ ወደ ሀይደር ሚስት ኢክራም ልደዉል save ያረኩትን አወጣሁ....ከዛም

#part ይቀጥላል
1.1K views14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 21:39:47 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

ግን ለእሱ አንድ ዉሸት ዋሸሁት አላህ ይቅር ይበለኝ ሲደዉልልኝ ምን ወሰንሽ ብሎ ጠየቀኝ እኔም...በዉሸት ወንድሜዋ ቀጥታ እናቴን ጠይቂያት አይህንም እኛ ያዘጋጀነዉ አባትሽ የመረጠልሽ ልጅ አለ አለችኝ ወንድም አላህ ከኔ የተሻለ ይስጥህ ከአሁን ቡሀላ መደዋወል እና በtelegram አናወራም ለምን ብትለኝ የወደፊት የትዳር አጋሬ መሆን ስለማንችል ከቤተሰቦቼ ትእዛዝ ዉጭ መፈፀም አልፈልግም አልኩት፡፡

እሱ ጋር በዚሁ ተለያየን ክፉም ከአፌ ሳይወጣ እሱም ክፉ ሳይናገረኝ ወደድኩህ ወደድኩሽ የለአንቺ መኖር አልችልም ያለ አንተ መኖር አልችልም ሳንባባል በሀላል መንገድ ጀመርን፡፡ በሰላም ተለያየን አላህ ከእኔ የተሻለ የትዳር አጋር ይስጠዉ፡፡
........ምን ላርግ የጠየቀኝ ጥያቄ ላይ ድንግል አይደለሁም ብለዉ አላህ ወንጀሉን ነዉሩን የሸፈነ እኔ እሸፍንነታለሁ ብሏል እኔ ቶብቻለሁ በወንጀሌ ተፀፅቻለሁ ግን የእሱን ሂወት ዋሽቼ ገብቼ ማበላሸት አልፈለኩም፡፡ እኔ ሀይደር ሸወደኝና ማንኛዉንም ወንድ በክፉ አላይም፡፡ ለምን አባቴ ወንድ ልጅ ነዉ፡፡ ወንዶች ገደል ይግቡ ካልኩ እኔን ለማሳደግ ለመንከባከብ ከቤተሰብ ፍቅር ዉጭ ሁኖ የሚኖረዉ አባቴን ተሳደብኩ ማለት ነዉ ፡፡ ይህ ደግሞ የወላጆቼን ሀቅ አልተወጣሁም ማለት ነዉ፡፡ ስለሆነም ጥሩ ወንዶች አሉ በተዘዋዋሪም ጥሩ ያልሆነ ወንዶች አሉ እነሱንም ከመሳደብ አላህ ልቦና ይስጣቸዉ ግን ይህ ጭካኔ በእህቱ በእናቱ ቢሆን የማይወደዉን በሌላ ሴት ልጅ መጨዋት ግን ያሳፍራል፡፡
በየሳምንት ከጁምአ ሶላት ቡሀላ የደአዋ ዝግጅት አለ ሴቶች አሚራችን ፊርዶስ ደአዋ ታረግልን ነበር፡፡ እንደ አጋጣሚ እሷ አሟት ሳትመጣ ቀረች....
ከዛም አንቺ አድርጊ እያሉ አስገደዱኝ ደአዋ አደረኩኝ፡፡ በጣም የሚያምር ደአዋ አደረኩ የደአዋዉ ርዕስ በወንድ ተኩላዎች እንዳትሸወጅ ነበር፡፡ እኔም የተሰማኝን በደአዋዉ እያለቀስኩኝ ሀይደር የሰራኝ ስራ የሸወደኝ ትዝ እያለኝ እልክ በያዘኝ መልኩ ደአዋ አረኩላቸዉ ...የትምህርቱ ጠቃሚነት ብዙዎቹ አብረዉኝ ያለቅሱ ነበር፡፡ ደአዋዉን ሳረግ ለእህቶቼ ቢጠነቀቁ ብየ በኔ ሂወት የደረሰዉን ጠባሳ በተለያዩ ዘዴዎች የደአዋ ሲስተም ነገርኳቸዉ እንዲጠነቀቁ እና የtelegram group ጥቅም እና ጉዳቱን ዘርዝሬ ነገርኳቸዉ ከዛ ደአዋየን ጨርሼ ተቀመኩኝ፡፡

ከዛ ቡሀላ አሚራችን ፊርዶስ አንቺ አድርጊ ባለፈዉ ሳልመጣ ቀርቼ ያደረግሽዉ ደአዋ በጣም እንደሚያምር ነግረዉኛል ....እንደዚህ የደአዋ ብቃት አለሽ ማለት ነዉ ማሻ አላህ ብያለሁ አለችኝ ፊርዶስ ፡፡
እኔም እምቢ አንቺ ስለቀረሽ ነዉ ያረኩት አላረግም ብላት እንዴ አላማችን አንቺ አንቺ ልንባባል ሳይሆን ያወቅነዉን ለማሳወቅ ነዉ ሂኩ ፡፡ እኔ ማረግ በምፈልግ ሰአት አረጋለሁ አንቺ አድርጊ አለችኝ...ፊርዶስ አበረታታችኝ ጁምአ ከሶላት ቡሀላ ተሰብስበን ደአዋ አድራጊዉ እኔ ሆንኩ ...

አላህ የሰራሁትን ወንጀል እንዲምረኝ በምሰግድ ሰአት ብቻየን ስሆን ረከአተይን ከሰገድኩ ቡሀላ አላህንም ማረኝ እያልኩ ባገኘሁት አጋጣሚ እያለቀስኩ ነዉ....
ፊርዶስ አንድ ነገር አማክርሻለሁ ብላ ደወለችልኝ ከአሱር ቡሀላ ልንገናኝ ተቀጣጠርን፡፡
ከአሱር ቡሀላ ከፊርዶስ ጋር ተገናኝተን አንድ ያልጠበኩትን ነገር ነገረችኝ፡፡ ሂክማ ባለፈዉ የነገርሽኝ ነገር ሲሀም ለትዳር የሚፈልግሽ አለ ብላ እንደነገረችሽ እኔ ሳልነግርሽ አረፈድኩና ግን ዛሬ ልነግርሽ ወስኛለሁ፡፡ ወንድሜ አብረን ስንሄድ አይቶናል አንቺ ጓደኛየ እንደሆንሽ ያቃል ለትዳር እንደሚፈልገኝ ነገረችኝ ፡፡ ሂኩ ወንድሜ ዲን አለዉ አላህን ፈሪ አንቺን ከጓደኝነት አልፎ ለወንድሜ ዙበይር ብታገቢዉ ደስ ይለኛል ሂኩ ማስተዳደሪያም አልሀምዱሊላህ አላህ እርዚቅ ሰጥቶታል .... አንቺን እንዲያገባሽ እፈልጋለሁ አለችኝ፡፡ ባለፈዉ የሲሀም ዘመድ ይፈልገኛል ብለሽ ስታማክሪኝ ደነገጥኩ ወንድሜ ዙበይር እሷን ማግባት እፈልጋለሁ እያለ እኔም ወንድሜን እንድታገቢ እየተመኘሁ ያንን ወሬ ስሰማ ለዙበይር ነግሬዉ እንዴት እስከ አሁን ሳነግሪያት ብሎ ተቆጣኝ አለችኝ፡፡
.....እኔም ደነገጥኩኝ እስኪ ቆይ ልሰብበት አልኳት ከዛም
እቤቴ ሂጄ አሰብኩበት ለሚመጣዉ አመት ትምህርት የመማር እቅድ ነበረኝ..... እናቴም ብዙም ትምህርቴን እንድማር አትፈልግም...አባትሽ ተምሮ ለስራ የሚኖረዉ ደብረዘይት, ነዉ፡፡ የእኔን ፍቅር የልጁን ፍቅር ሳይሰጥ ይሄዉ እየኖረ ነዉ፡፡ መማር እንደዚህ ከሆነ ይቅር ትለኝ ነበር፡፡
መኝታ ክፍል ሁኜ ዙበይርስ ቢክራ ነሽ ወይ ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድን ነዉ ??? እያልኩ እያሰብኩ ነዉ፡፡

በጣም ተናደድኩ ሳላስበዉ ሸይጧን ወሰወሰኝ ሀይደር የራሱን ኑሮ እየኖረ የኔን ሂወት አበላሽቶ ጨለማ አድርጎ እኔ በሂወት እያለሁመኖር አይችልም ብየ ወሰንኩኝ ፡፡ በዙ ሀይደርን የምጎዳበት ነገሮች መኝታ ክፍሌ ሁኜ የቤታችንን ኮርኒስ እያየሁ አንድ ሀሳብ መጣልኝ የእሱን ሂወት ማበላሻ ቀላል ዘዴ አገኘሁ ...እኛን የቸገረን ኸይር መስራቱ እንጂ ተንኮል መስራቱ መቼ ያቅተናል ......ሀይደርን ለመበቀል በጣም ቀላል ዘዴ አገኘሁ እስከአሁን ትዝ ሳይለኝ ብየ ተቆጨሁ፡፡ ...የሀይደርን .....

#Part ይቀጥላል
1.3K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 10:43:49 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

አጎቴ እቤት መጥቶ አንድ መፍትሄ አለኝ ሲል ሰማሁት ለምን አታገባም ሲል መኝታ ክፍል ሁኜ ሰማሁት ....... እኔ እኮ ተማሪ ናት እያልኩ ነዉ እጂ ብዙ ሰሞች ጓደኞቼ ለራሱ ለምን አትድረንም አግብቻት እኔ ጋር ሁና አስተምራታለሁ ያሉኝ አሉ፡፡ ግን እኔ ትምህርቷን ትጨርስ ለእናንተም ማዉራት አይሆንም ትላላችሁ ብየ ዝምታን መርጬ ነዉ ብሎ ለእናቴ ሲናገር ሰማሁት ...

እናቴም እኔንም ብዙ ሰዉ ጠይቆኛል ግን ትምህርቷን ትጨርስ ብየ ነዉ፡፡ እሷም አስራሁለተኛ ክፍል ተፈትና ዉጤትም ቢመጣለት ዩኒቨርስቲ አትገባም ተነጋግረን እሺ ብላኝ ነበር፡፡ አላህ ያለዉ ሆነ እንጂ ይሄዉ ልጄ በሽታዋ ሳይታወቅ ታማለች አሁን ዱአየ አላህ እንዲያሽራት ነዉ፡፡ ጤናዋን ካገኘች ቡሃላ ስለ ሂክማ ትዳር አስብበታለሁ ብላ እናቴ እንባ እየተናነቃት ለወንድሟ ነገረችዉ ፡፡ እኔ እነሱ የሚያወሩትን ወሬ ስሰማ እዛዉ መኝታ ክፍሌ አለቀስኩ ለምን ለትዳር ብቁ አይደለሁም...ሀይደር አዋቂ መስሎ ሸዉዶኛል የወደፊት የትዳር አጋሬ ቢክራ ነሽ ወይ ብሎ ቢጠይቀኝ ምን መልስ አለኝ????
ወደ ትምህርት እንዳልመለስ ከወር በላይ አለፈኝ ካቋረጥኩ ፡፡ አንድ የትምህርት ቤት ጓደኛየ እቤት መጥታ ትምህርቱን ዘንድሮ የማቀጥይ ከሆነ ለምን ጃክሮስ ሰፈር አካባቢ ጃክሮስ መስጊድ አለ እዛዉ አካባቢ ሴቶች ተሰባስበዉ ኪታብ የሚቀሩ አሉ እነሱ ጋር ኪታብ አቀሪም ብላ አመላከተችኝ፡፡
ከዛም ቅዳሜ ቀን ወስዳ የሚቀሩበትን ቦታ እና አልፎ አልፎም መስጊድ እንደሚቀራ ነገረችኝ፡፡
እዛ ኪታብ መቅራት ጀመርኩ እንደገና ወደ ዲኔ ለመመለስ ወሰንኩኝ ፡፡
ኪታብ እየቀራሁ አላህን ማረኝ እያልኩ እያለቀስኩኝ ነዉ፡፡ ....የጀመአዉ አሚራችን ፊርዶስ ትባላለች እሷ ጋር በጣም ተግባባን ፊርዶስ ጃክሮስ ሰፈር አለፍ ብሎ ያለዉ ጎሮ የሚባለዉ ሰፈር ነዋሪ እንደሆነች ነገረችኝ፡፡
ፊርዶስ ኪታብም ታቀራን ነበር አሚራችን ናት ፡፡ እኔ ጋር ኢስላም መጀመሪያዉኑ ወንድምህን ዉደድ እና እህትሽንም ተዋደዱ ኢስላም አስተሳስሯችሇል ብሎናል፡፡
ከትምህርት ጓደኞቼ በላይ ፊርዶስን እንደእህቴ ቀረብኳት ለምን እኔ እህት ስለለኝ ፊርዶስን እንደ እህቴ ነዉ የማያት ፊርዶስ ሶስት ትልቅ ወንድሞች አሏት ፡፡ ሁለቱ አግብተዋል አንዱ ወንድሟ ግን አላገባም ፡፡
እዛዉ ኪታብ በመቅራት የተዋወቀነው ሲሀም የምትባል ልጅ አለች ሁሌ ኪታብ ቀርተን በተገናኘን ቁጥር ሂክማ የአንችን ቁጥር ስጭኝ እያለ እያስቸገረኝ ነዉ ዘመዳችን ነዉ አብረን ኪታብ እንደምንቀራ አይቶናል ቁጥሯን ስጭኝ እኔ አላማየ ቀጥታ ወደ ትዳር ብቻ ነዉ እያለ እያስቸገኝ ነዉ ሂክማ እኔ ይተዉሻል ብየ ዝም ብለዉ አኔን መቸካቸኩን አላቆመም ያለአንቺ ፍቃድ ደግሞ ቁጥርሽን መስጠት ከበደኝ እስከ ጠዋት አስበሽ ንገሪኝ አለቸኝ፡፡

ጠዋት ደረሰ ኪታብ የምቀራበት ሄድኩኝ ሲሀምን አገኘሇት ምን አሰብሽ እሱ አይቶሻል በስልክ አላስቀምጠኝ አለ፡፡ ምን ይሻለኛል ወይ ስልክሽን ፍቀጅልኝ እና ልስጠዉ እናንተ አዉሩ አለችኝ፡፡
እሺ ትንሽ ቆይቼ አሳዉቅሻለሁ ሲሀም አልኳት፡፡
ፊርዶስ ኪታብ ስጨርስ ለብቻዋ አማከርኳት፡፡ ፊርዶስም አይታወቅም የአላህ ነገር ለኸይር ይሆናል የሀራም መንገድ ሳጀምሩ ስለማንነቱ አጣርተሽ በስልክ በTelegram ሳይረብሽ ቀጥታ ወደ ሀላሉ ሊገባ ከቻለ አላህ የፃፈልሽ እሱ ጋር ሊሆን ስለሚችል ለሲሀም ቁጥርሽን እንድሰጠዉ ፍቀጅላት አለችኝ ፡፡
ፊርዶስም በመቀጠል እኔም እኮ በጣም ዲነኛ የሆነ ልጅ በቤተሰብ የመጣ በጣም ጥሩ ስነምግባር ያለዉ ነዉ አይቸዉ ፈትኘዋለሁ ቤተሰቦቼ ጥሩ ባል መርጠዉልኛል እኔም የማመቻቸዉ ነገር ስላለ ነዉ እንጂ ማግባቴ አይቀርም ...ግን አንቺ ቀድመሽኝ ካገባሽ በጣም ደስተኛ ነኝ ሂኩ አላህ ያሳካዉ ዱአ አትርሺኝ እኔም አረሳሽም አለችኝ እየተሳሳቅን፡፡

ወደ ሲሀም ሂጄ እሺ ቁጥሬን ስጭዉ አልኳት፡፡ እሷም ሰጠችዉ ...ደወለልኝ በስነ ስርአት አወራኝ ....በአካል እንደሚያቀኝ ነገረኝ እኔ ግነ አላቅህም አልኩት፡፡ ከአስር ቀን በላይ ሆነን ማዉራት ከጀመርን፡፡ የግድ መገናኘት ስላለብን ተቀጣጥረን ተገናኘን ተያየን ማሻ አላህ ቆንጆ ልጅ ነዉ ፡፡
ስሙን ከተዋወቅን ቡሀላ እኔ አንቺን ለማጀዘብ ሳይሆን ለትዳር ነዉ የምፈልግሽ አለኝ ፡፡
እያወራን የፈራሁት ጥያቄ መጣብኝ ሂክማ ያዉ ለወደፊት የትዳር አጋሬ መርጬሻለሁ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ግን ቢክራ ነሽ አለኝ???
......ምን ብየ ልመልስ ዝም አልኩት,,,,ወንዶች ማግባት የምፈልጉት በቃ እንደዚህ ነዉ አልኩት፡፡ እሱም የሌላዉን አላቅም ግን እኔ በአላህ እምልልሻለሁ እስከ አሁን ተጠብቄ አላማየም ማግባት የምፈልገዉ እንደ እኔዉ የሆነችዉን ነዉ አለኝ፡፡
እኔም እሺ በስልክ አሳዉቅሀለሁ ብየ ተለያየን፡፡

ሀይደር የኔን ሂወት አበላሽቶብኛል አለቀስኩ ድንግል ነኝ ብየ ባገባዉ ድንግልናየን ሳያገኝብኝ ቢቀር መፋታቴ ወይም ሲሰድበኝ ሲያንቋሽሸኝ ወይም የእሱ ሞራሉ እንደተጎዳ ይኖራል፡፡የሴት ልጅ ህይወት ግድ እስከ ክብሯ መገኘቱ ወሳኝ እንደሆነ ተገነዘብኩኝ ፡...ገና ከመጀመሪያዉ የትዳር ፈተና ጀመረኝ፡፡ ስለሆነም ብቻየን መኝታ ክፍሌ አሰብኩኝ ባስበዉ ባስበዉ ምንም መፍትሄ ላገኝ አልቻልኩም ያረቢ ብየ አለቀስኩ ፡፡ ግን ለእሱ አንድ ዉሸት ዋሸሁት አላህ ይቅር ይበለኝ ሲደዉልልኝ ምን ወሰንሽ ብሎ ጠየቀኝ
እኔም............

#Part ይቀጥላል
1.5K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 20:30:37 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

Face book ላይ profile pic ሳይ ደነገጥኩኝ
የምናገረዉ ጠፋብኝ እክፍል ዉስጥ ወድቂያለሁኝ
......ሀኪም ቤት እራሴን ስቼ ማን እንደወሰደኝ እንኳ የማቀዉ ነገር የለም ......የወደፊት ባሌ ብየ የሴትነት ክብሬን የወሰደዉ ሀይደር ባለ ትዳር ነዉ፡፡

...,..,fb profile እና time line ብዙ ፎቶዉች አሉ ለሰርጋቸዉ ጊዜ አብረዉ የተነሱት ....ምን ልበል ያዉ የምናገረዉ የለኝም ብቻ በማለቀዉ ድንጋጤ እራሴን ስቼ ሀኪም ቤት ገብቻለሁ፡፡
..... የተኛሁበትም ሆስፒታል እኛ ሰፈር ገርጂ አቅራቢያ የሚገኘዉ ኮርያ ሆስፒታል ነዉ፡፡ ሆስፒታል ሁኜ ልረጋጋ አልቻልኩም፡፡ አባቴም ሸዋሮቢት ሀገር የመንግት ሰራተኛ አይደል መታመሜን ሲሰማ ጊዜ ሳይፈጅ መጣ ፡፡ አልናገር ምግብ ለራሱ ብዙም አልበላም ግልኮስ ተተክሎልኛል፡፡ ብቻ በሁለቱም ጉንጬ እንባየ ሲረግፍ ነዉ የሚዉለዉ፡፡ እናቴም በእኔ ሁኔታ ተደናግጣለች የምትዉለዉ የምታድረዉ እኔዉ ጋር ነዉ...እኔ እያለቀስኩ የእናት ሆድ አያስችል አብራ ታለቅስ ነበር፡፡
....እኔስ መናገር ያልቻልኩት የዋጥኩት እሳት ነዉ የሚያስለቅሰኝ.....እናቴ ግን ልጇ ስለሆንኩ መናገር ስለማልችል ሳለቅስ ብቻ ታለቅሳለች፡፡
........ኮርያ ሆስፒታል አምስት ቀን ተኝቼ ህክምና ወስጄ ወደ ቤቴ ተመስኩ፡፡ ግን ምን እንደሆንኩ አላቅም አፌ እንደበፊቱ አቀላጥፎ ማዉራት አልቻለም ፡፡ ምን ሁነሽ ነዉ ምንሽን ይሰማሻል ይሉኛል... እኔ የሆንኩት ሌላ መልስ የሌለዉ ጥያቄ ነዉ፡፡
......አባቴም የያዛት ጅን ነዉ ተብሎ የሰፈራችን ጀመአዎች አሉ፡፡ ማታ ላይ ሳልሰማ መጥተዉ እስከ 4 ሰአት ቁርአን ቀሩብኝ፡፡ እነሱ የሆንኩትን አያቁም ...ቁርአን ቀርተዉ ምንም የጅን ምልክት ስላላገኙ ....አንዱ ቁርአን ከሚቀሩት አረ ይሄ ጅን አይደለም እናቁም ብለዉ አቁመዉ ሄዱ፡፡
...,.ግን ጅንም ባይሆን ለኔ ቁርአን መቀራቱ ትንሽ ለዉጥ አመጣሁ ማዉራት ትንሽ እየከፈተልኝ ነዉ፡፡

አባቴ አላስቻለዉም እኛ ሰፈር ያለዉ ኢብኑ አባስ መስጊድ ዉስጥ ታዋቂ የጂን የሚቀሩት ልጆች አሉ ተብሎ ተነገረዉ፡፡ ማታ ላይ ከመቅሪብ ቡሀላ እቤት ይዟቸዉ መጣ ፡፡ እኔ ሁሉን በሆዴ ይዠዋለሁ ፡፡ መናገር የማልችለዉ ነገር ነዉ፡፡ ከኢብኑ አባስ መስጊድ የመጡ ጀመአዎች ማታ ላይ ሲቀሩብኝ አመሹ ለዉጥ የለም ያዉ ነዉ፡፡

ግን ቁርአን በተቀራብኝ ቁጥር ልቤ በጭንቀት በሀሳብ አልተረጋጋም ብቻ ግን የተያያዘዉ አፌ እየተፍታታ ነዉ፡፡
እናቴ ደግሞ ሰፈሩ አሉ የሚባሉት ትላልቅ ሴቶችን ጠርታ ቅዳሜ ቀን በግ ታርዶ ምሳቸዉን አብልታ ከምሳ ሰአት የጀመሩ እስከ መቅሪብ ድረስ ዱአ ሲደረግልኝ ዋለ፡፡ ከእኔ በላይ ቤተሰቦቼን አስቸገሪኩ፡፡

ቤተሰቦችን አስጨነኳቸዉ ለነገሩ አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ ምን ያርጉ አባቴም የመንግስት ስራዉን ከሸዋሮቢት አስፈቅዶ መጥቷል፡፡ እናቴም ጭንቀቷ እኔ ሁኛለሁ ስታየኝ በስስት ሳለቅስ የምታለቅሰዉ ከእኔ በላይ ነዉ፡፡ እኔ ተረብሼ ቤተሰቦቼን እረበሽኩኝ በእኔ መቀያር እነሱ ተረበሹ በጣም አዘንኩ፡፡

አላህ የዉመል ቂያማ ሲጠይቀኝ መልሴ ምን ይሆን የወላጆቻችሁ ሀቅ አደራ
እያለ በቁርአን ነግሮኝ ነብዩ ሙሀመድ ሰ ዐ ወ ጀነት ከእናት እግር ስር ናት ብለዉን ....እኔ ግን ገና ሀይደር ያገባኛል ብየ አምኘዉ እሱ ጋር ወንጀል ሰርቼ ለዛዉም ባለትዳር ሆኖ በራሴ ባለመጠንቀቅ በተጎዳሁ በራሴዉ ጥፋት ቤተሰቦቼን አሰቃይ ይዣለሁ፡፡ አላህ በስንቱ ነዉ የሚቀጣኝ አንድ ዚና በመስራቴ ሁለት ወላጆቼን እነሱ በማያቁት ነገር ማስጨነቄ ማስቸገሬ.... ኡፍ እንኳን እንዳትሉ የተባልኩትን ወላጆች በእኔ መረበሽ ማልቀስ ከጀመሩ አንድ ወር ሆናቸዉ ፡፡ ብቻየን እያሰብኩ መኝታ ክፍሌ ገብቼ አለቅሳለሁ፡፡
አንድ የእናቴ ወንድም አለ ደሴ ከተማ የሚኖር ደሴ ትምጣ እዚህ ጥሩ የጂን የሚቀሩ ቁርአን ቀሪዎች አሉ ብሎ ይደዉልላታል፡፡ እናቴም ምንም ይሁን ምንም እኔ አንድ ፍሬ ልጇ ሳለቅስ ስጨነቅ ማየት አልፈለገችም ፡፡ እኔም ሁሉን በሆዴ ደብቄ እነሱ የሚሉኝን እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አማራጭ የለኝም፡፡ እናቴ ጋር አብረን ከ አዲስ አበባ 401 ኪሎ ሜትር ወደ ምትገኘዉ የወሎእምብርት ደሴ ከተማ ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ጠዋት ተነስተን 8:30 ደሴ ከተማ ገባን፡፡ አጎቴ ተቀብሎን አረፍ አለን፡፡ ጠዋት ላይ ደሴ ከተማ የሚገኘዉ ተቋም አካባቢ የሚገኘዉ ጦለሀ መስጊድ በብዙ ጀመአ በተሰበሰበበት ቁርአን ቀሩልኝ ከአዲስ አበባ ለየት ያለ አቀራር ነበር፡፡ ግን አብረዉ የሚቀራባቸዉ ጅን የያዛቸዉ ነበሩ የእነሱ ብዙም ሳይቆይ ለቀቀ እኔ ግን ሁሌን በሄዴ ይዤ ቤተሰቦቼን ዘመዶቼን እያስቸጠረኩ እያሴጨነከ ነዉ፡፡ በመነገታዉ ማታ ላይ ደግሞ ደሴ ከተማ የሚገኘዉ አሬራ አካባቢ አሬራ መስጊድ ከመቅሪብ ቡሀላ ቁርአን ተቀራልኝ ፡፡ ሁለት ቀን ከተቀራብኝ ቡሀላ አጎቴ ደሴን አሶገበኝኝ አዝናናኝ ፡፡ ደሴ ከተማን አንድ ሳምንት ቆይቼ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩኝ፡፡

አዲስ አበባም እንደተመለስኩኝ ጓደኛቼ የክፍል ተማሪዎችም እየመጡ ይጠይቁኝ አጫዉተዉኝ ይሄዱ ነበር፡፡
ትምህርት ካቆምኩ አንድ ወር ሆነኝ
......አዲስ አበባ የሚኖረዉ አጎቴ አልፎ አልፎ እየመጣ ይጠይቀኝ ነበር ፡፡
ዛሬ ግን እቤት መጥቶ አንድ መፍትሄ አለኝ ሲል ሰማሁት ለምን አታገባም እኔ እኮ ዳረኝ ብለዉ የጠየቁኝ አሉ ሲል መኝታ ክፍል ሁኜ ሰማሁት...እኔም ደነገጥኩኝ....

#part ይቀጥላል
1.7K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 07:55:37 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

እንደምንም ብሎ የሰኞ የሀሳብ ለሊት አልቆ ማክሰኞን ተካ ወደ የምማርበት ቦሌ Priparatoty ጓደኜቼ ጋር ትምህርት ቤት ተገናኘን ደብረዘይት የሰራሁት ወንጀል ያዩኝ ያዩኝ ይመስል ፈራሆቸዉ እንደዚህ ወንጀል መስራት ያሳፍራል ማለት ነዉ፡፡ ሂክማ ትናንት የቀረሽዉ በሰላም ነዉ እያሉ በጥያቄ አፋጠጡኝ ..ጓደኞቼም አይፈረድባቸዉም ከትምህርት ቀርቼ አላቅም ስቀር ተደናግጠዉ ነዉ፡፡
........እኔም አዎ እቤት ስራ ይዤ ነዉ ብየ ሌላ ዉሸት ዋሸሁ፡፡ ዉሸትን ለመደበቅ ግድ ሌላ ዉሸት አይደል የምንሰጠዉ ከጓደኞቼን ሰላም ተባብለን ወደ ክላሳችን ገባን፡፡ መምሆሮቹም እንደ ጓደኞቼ ጠየቁኝ በሰላም እደቀረሁ ነገርኳቸዉ፡፡ ክላስ ሁኜ በሰራሁት ስራ በቃ እየገረመኝ የሆነ የማላቀዉ ነገር የወረረኝ ይመስለኛል፡፡ በጓደኝቼ በመምህሮቼ ተወዳጅ እንደ ሂክማ ሁኑ የምባለዉ ልጅ ከአሁን ቡሀላ አይደለሁም እፍረትም ተሰማኝ፡፡ ከትምህርት ስወጣ ደወልኩለት አንስቶ ትንሽ አዉርተን ወደ ቤቴ ተመለስኩኝ፡፡
ግን እቤቴ ከገባብ ቡሃላ ማታ ተኝቼ ከየት መጣ የማይባል ፍርሀት ወረረኝ ምን ሆኘ ነው ምን ነካኝ ብየ ራሴን ጠየኩ መልስ ባላገኝም
.........ከዚህ በኃላ የኔ ህይወት በሀይደር እጅ እደሆነ ገባኝ አሁንስ ቢተወኝ አልፈልግሽም ቢለኝ ብየ ሳስብ የምሆነውን አጣሁ ይህ ሀሣብ ውስጤ ላይ የፈጠረው ፍርሀት ይሁን ቁጭት ባላውቅም ጩሂ ጩሂ አለን ግን ደግሞ ለመጮህም ምክንያት ያሥፈልጋል ፡፡
ጠዋት ወደ ትምህርት እየሄድኩ ስደዉልለት ስልክ አያነሳም ነበር፡፡ ምን ሆነ እያልኩ አሰብኩኝ እሱም ከትምህርት ስንለቀቅ ደወለልኝ ሂኩ አሁን ለማዉራት የማይመች ቦታ ነኝ መልሼ እደዉላለሁ አለኝ ፡፡ እኔም እሺ ብየ የደስደስ ነገር ተሰማኝ፡፡ ግን አልደወለም፡፡ በመነገታዉም ትምህርት ቤትም ቢሆን ስልኬን ደብቄ ይዤ ነዉ የዋልኩት ግን ሙሉቀን አልደወለልኝም ለምን ይሆን ???

የውስጥ ህመም ሆነብኝ በፊት በእረፍት ሰአት እና ከትምህርት ስንለቀቅ አስቦ የሚደዉልልኝ ሀይደር ይህን ሁለት ሶስት ቀን ግን አልደወለም፡፡ እቤቴ ገባሁ telegram ላይ ስገባ on line ነበረ፡፡ አላህ ይወቅ telegram on line መግባቴን አይቶ እንደሆነ አላቅም ወዳዉ ደወለ ፡፡
......እኔም አነሳሁት ሂኩ በጣም ይቅርታ ስራ ላይ ቢዚ ሁኜ ነበር ያልደወልኩት አሁንም ለማዉራት አይመችም ታቂያለሽ እቤት ቤተሰቦቼ ሶላሉ ማታ ማታ ስልክ እንደማላወራ አለኝ፡፡ እራት በላሽ ብዙ ነገሮችን አዉርቶኝ..... ደግሞ እንዳትረሽ አወድሻለሁ አለኝ እኔም እወድሀለሁ ብየ ሥልኩን ዘጋሁ
.....እወድሻለሁ ስላለኝ ደስ አለኝ

ግን ቀናቶች በሂዱ ቁጥር እንደበፊቱ ሁሌ መደወል ቀዘቀዘብኝ telegram ስገባ አላገኘዉም ፡፡ አንድ ቀን በሂወታችን በጀመርን ቁጥር ይህ ቀን ለመሞታችን እየቀረብን ነዉ፡፡ እኔ ከዛሬ ነገ ይስተካከላል ሁሉም ነገር ቦታ ይይዛል ስል ሀይደር እየራቀኝ ስልክም መደወል እያቆመ መጣ በጣም ግራ ተጋባሁ፡፡ደግሞ ለኔ መርዶ የሆነ profile pictur አየሁት ለጊዜዉ በዚህ acount ስለማልጠቀም በዚህኛዉ ነዉ የምታገኙን ብሎ profie አርጎታል፡፡ በጣም ግራ ገባኝ ሌላወን ቁጥሩን አላቀዉም፡፡ ...

በጣም ከምነግራችሁ በላይ ተጨነኩኝ ተወዛገብኩኝ፡፡
......በመጥፋቱ ብናደድም ቢያንገበግበኝም ግን ስራ ስላልተመቻቸለት ነው ይደውላል እወድሻለሁ ብሎኛል እያልኩ ራሴን ለማሳመን ከራሴጋር ሙግት ገጠምኩ ያለፈውን የፍቅር ወሬ በህሊናየ እያዎጠነጠንኩ እፅናናለሁ በtelegram ያወራናቸዉን message እያየሁ እገረማለሁ መልሼ እንደ መፅሀፍ ከላይ ጀምሬ ማታ ማታ አነባቸዋለሁ፡፡በዚህ መልኩ ቀን ቀንን እየተካ 20 ቀን ሆነን በዚህ ቀናት ውሥጥ ሶስት ቀን ብቻ ደውሎልኛል በፊት በቀን ሁለቴ ሶስት ጊዜ ይደውል ነበር እኔ ስጋት ውስጥ ነኝልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡
...... በአንድ በኩል ቢተወኝ ምንድነው ምሆነው እላለሁ መልሽ ደግሞ ቃል ገብቶልኛል ሙስሊም ነው ለዛዉም አላህን ፈሪ ነዉ ፡፡እንደዚህ አያደርግም እላለሁ ሀሳቤ ተበታትኗል፡፡
አሁን መደወል አቆመ ግራ ገባኝ አላስችለኝ አለ፡፡ ስደዉልለት ስልክ አያነሳም .......
........በሌላ ሰዉ ስደዉልበት ያነሳዉና...የእኔ ድምፅ መሆኑን ሲያዉቅ ይዘገዋል፡፡ በጣም ተጨነኩ ግን ይተወኛል ብየየየየየየየየየየ አስቤ አላቅም ፡፡ ሀይደር ምን ሆነብኝ ሀይደር ምን ሆነብኝ ሀይደር ምንሆነብኝ ሁኗል አሳቤ ፡፡ ስልክ እየቀያየርኩ መደወል አልተዉኩም፡፡ የእኔ ድምፅ መሆኑን ካወቀ አንስቶ ይዘገዋል፡፡ telegram የሚጠቀምበትንም ቁጥር ቀይሯል በምን ላግኘዉ ፡፡ ተጨነኩኝ ወይኔ
ሂክማ የምሆነውን አጣሁ በሀሣብ ታመምኩ

ክላስ ቁጭ ብየ የሂሳብ መምህራችን ታሞ አልመጣም ነበር ...እስኪ ሀይደርን facebook ላይ ልፈልገዉ ብየ... በስሙ ፈለኩት ላገኘው አልቻልኩም ፡፡ ግን እሱ ለራሱ ያወጣም ስም አለ ነግሮኝ ነበር በስሜ ከምጠሪኝ ሱደይስ ብለሽ ጥሪኝ የመጀመሪያ ልጄ ስም ሱደይስ ነዉ የምንለዉ ይለኝ ነበር ስሙንም እወደዋለሁ በእሱ ጥሪኝ ይለኝ ነበር ፡፡ ትዝ አለኝ.. ከዛ fb ላይ ሱደይስ እና የአባቱን ስም አንድ ላይ ፅፌ search አረኩት ፡፡ ብዙ ሱደይስ ቢኖሩም የአላህ ነገር የfb....profile pictur ፎቶ ነበር ይገርማል ፎቶ profile ማረግ ወንጀሉ ለሴቱ ብቻ ነዉ እያልኩ ተገራረምኩ እኔን ፎቶ አታርጊ ብሎ የመከረኝ ሀይደር እሱ ፎቶ አርጎ አገኘሁት ..አሁን ይሄን የማስብበት ጊዜ አይደለም ብቻ እሱን fb ላይ ማግኘቴ በጣም ደስ አለኝ በface book እናወራለን አልኩኝ ብቻየን አወራለሁ የዋህ ነኝ እኮ፡፡

face book ላይ time line እና profile pictur ማየት ጀመርኩ፡፡ profile pictur ሳይ ያየሁትን ማየት አቃተኝ ድርቅ ብየ ቀረሁ፡፡ ልቤ ምቱን ያቆመ መሰለኝ እንባየ ይፈሳል አፌ ቃል ማውጣት ተሳነኝ ከጎኔ ያሉት የክፍሌ ልጆች ሂክማ ማን ሆንሽ ሂክማ ምን ሆንሽ ሲሉኝ እሰማለሁ፡፡ ዉሀ እምጡ እያሉ ተማሪዉ ሲጮህም እሰማለሁ ትንሽ ትንሽ ..ከዛ ቡሀላ ግን ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም..... ወደ ሀኪም ቤት ሄድኩኝ.....ሲወስዱኝ ለራሱ አላስታዉስም ....ብቻ ማታ 4 ሰአት ነዉ የነቃሁት ስባንን እኔን ያገኘሁት ኮሪያ ሆስፒታል ነበር እራሴን ስቼ ተኝቼ ከጎኔ እናቴ እና የክፍል ጓደኛቼ ሶስት ልጆች አሉ፡፡

ሂክማ ምን ሁና ነዉ እራሷን የሳተችዉ ...ምን አይታ ነዉ በfb time line ላይ የሀይደር profile pic ሀኪም ቤት እስከምትገባ ድረስ የሚለዉን ?????
በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን፡፡
1.7K views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 01:38:22
አላህ ሆይ ፍላጎታችንን ወደ አንተ እናነሳለን በአንተም እንታመናለን።
አላህ ሆይ ችግራችንን አቅልልን
ምክንያቶቻችንን አቅልልን፤ ዱኣችንን ተቀበይነት ከለቻው መካከል አድርገን።
አሏህ ሆይ ከሚያሰቃየን ጭቆና፣ ከሚያሳዝንም ሀዛን በአንተ እንጠበቃለን።
@hayu_abdi
261 views22:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 00:22:08 ዱሀ አድርጉልኝ
338 views21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ