Get Mystery Box with random crypto!

ሀላል ትዳር👫💍

የቴሌግራም ቻናል አርማ hayu_abdi — ሀላል ትዳር👫💍
የቴሌግራም ቻናል አርማ hayu_abdi — ሀላል ትዳር👫💍
የሰርጥ አድራሻ: @hayu_abdi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.54K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-08-20 20:48:27 ከተራራው ላይ
ክፍል ሶስት
(ፉአድ ሙና)
.
‹‹በሰው ቁስል እንጨት መስደድ፣ ጊዜ አይቶ፣
መጥፎነትን መከናነብ፣ ጥሩው ቀርቶ፣
ለምን ከቶ?››
***
ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ከእንቅልፋችን ተነሳን፡፡ ኢንቱ ወደ ስራ ለመሄድ እንደቀድሞው አልፈጠነችም፡፡ መኝታችን ላይ እንደተቀመጠች ማስታወሻ ደብተሯን ከፍታ መፃፍ ጀመረች፡፡
‹‹ዛሬ ስራ የለም እንዴ?››
‹‹አለ …… ትንሽ አርፍጄ ለመግባት ፈልጌ ነው!››
ሻይ አፍልቼና ዳቦ ገዝቼ ቁርስ አቀራረብኩ፡፡ ቁርስ እንዳቀረብኩ አብዱኬ መጣ፡፡ ሁሌም ጠዋት ወደ ስራ የሚወጣው ከእኔና ከኢንቱ ጋር ነው፡፡ እስከ አለምባንክ ድረስ አብረን እንሄዳለን፡፡ እማዬን ሰላም ካለ በኋላ ቁርስ ለመብላት ተመቻችቶ ተቀመጠ፡፡ ከማታው ፓስቲ ሁለት ይዞ መጥቷል፡፡
‹‹ኢንቲሳር ከባድ ሰው …… ምንድነው የምትፅፊው?›› ማስታወሻ ደብተሩን ቀማት፡፡
‹‹አብዱኬ ወላሂ እንደዚህ አይነት ቀልድ አልወድም አምጣው!›› ሌላ ኢንቲሳር ሆነችበት፡፡ ደንግጦ መለሰላት፡፡ በአይኑ ምን እንደሆነች ጠየቀኝ፡፡ እንደማላውቅ ነገርኩት፡፡
እማዬ የህክምና ካርዷን እየሰጠችኝ ‹‹እስኪ እየው መች ይላል ቀጠሮው?›› አለችኝ፡፡ የእግሯ ህመም በጣም ስለባሰባት ክትትል ጀምራ ነበር፡፡
‹‹ገና እኮ ነው …… ምነው እማ አመመሽ እንዴ?››
‹‹አይ እንዳያልፈኝ ብዬ ነው!›› ፈገግ ለማለት ሞከረች፡፡
ቁርሳችንን በልተን እንደጨረስን ከአብዱኬ ጋር ወጣን፡፡ የኢንቱን ማስታወሻ ደብተር ለማንበብ የነበረኝ እቅድ መክሸፉ አበሳጨኝ፡፡ ባጃጅ ተራ ስንደርስ አብዱኬ ‹‹ስማማ ኢቦ ግን ኢንቱ ለምንድነው የማታገባው? …… አሁን እኮ ወሳኝ እድሜዋ ነው! ገባሻ! እንኳን እሷን የመሰለች ቀሽት ይቅርና ግንብ ራሶቹ እነነቢላ ራሱ አግብተው የለ እንዴ!?›› አለኝ፡፡ ነቢላ የሰፈራችን ልጅ ናት፡፡ አብዱኬ ደግሞ እንዲሁ ትደብረዋለች፡፡ ለሰርጓ ግን አንደኛው አሽቃባጭ እሱ ነበር፡፡ ያው የሰፈራችን ህግ ነው፡፡ ብትወደውም ቢደብርህም ለደስታውና ለችግሩ ቀን አለኝታ የመሆን ግዴታ! ኢንቱ ግን የሌላ ሰው ሚስት እንደምትሆን አንድም ቀን አስቤ አላውቅም፡፡ እሷ የኔ እህት ብቻ ናት፡፡ አዎ ውስጤ የሚያምነው እንደዛ ነበር፡፡ የአብዱኬ ጥያቄ አስበረገገኝ፡፡
‹‹ተናገራ ለምንድነው የማታገባው? ከኛ ሰፈር እንኳን እኮ ስንት ሰው እናትህ ጋር አስልኳል፡፡ ሊጋተቷት ሲሞክሩ ፊት ስለማትገጫቸው እሷን አይደፍሯትም እንጂ እኛ ሰፈር እሷን የማይፎነቅቅ የለም፡፡ ወይስ ቅባት ምናምን ካልሆነ አይሞዳትም?››
‹‹ቅባት ራስ! የምናባህ ቅባት ነው?! ……… ማግባት ከፈለገች እሷ የፈለገችው ሰው ሲመጣ ታገባለች! ምን ያጣድፍሀል? ገና አይደል እንዴ እድሜዋ!›› አብዱኬ በግርምት አይን ሲያየኝ እንደጮህኩበት ገባኝ፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ራስህ ልታገባት ነው የምትመስለው! እኔ ልንገርህ ለምን እንደማታገባ? ባንተ ምክንያት ነው! እሱን አስተምሬ ቦታ ሳላስይዝ ምናምን ብላ ማለት ነው! አንተ ደግሞ ምንም አትረዳም እንዴ? እሷ ላንተ ትጋጋጣለች አንተ እንደ ዲታ ልጅ ከቤት ትምሮ ቤት ትመላለሳለህ! አይደብርህም?››
‹‹እና እኔ ምን ላድርግ? …… የምማረው ለማን ብዬ ይመስልሀል?››
‹‹አላውቅልህም! …… ለማንኛውም እሷንም ተረዳት!››
አለምባንክ ደርሰን ከአብዱኬ ጋር ተለያየን፡፡ ከአለምባንክ በእግሬ ወደ ትምህርት ቤት እየሄድኩ የማስበው የአብዱኬን ንግግር ነበር፡፡ በቁስሌ ላይ እንጨት የሰደደብኝ መሰለኝ፡፡ኢንቱ ትምህርት እንዳቋርጥ አትፈቅድም፡፡ ያለኝ አማራጭ ድካሟን ፍሬ አልባ ላለማድረግ ህልሟን ማሳካት ነበር፡፡ እሱን ደግሞ እያደረግኩት ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የቀረኝ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ብቻ ነው፡፡
በአብዱኬ ንግግር ቀኔ ተበጥብጦ ከትምህርት በኋላ ወደ ቤተ-መፅሀፍት የመሄድ እቅዴን ሰርዤ ወደ ቤት ሄድኩ፡፡ ማንም አልነበረም፡፡ የኢንቱን ማስታወሻ ደብተር ሁሌም ከምታስቀምጥበት ትንሿ ሳጥን ላይ ከመፅሀፍትና ደብተሮች መሀከል ተሸጉጦ አገኘሁት፡፡ ደብተሩ በቁልፍ የሚከፈት ነበር፡፡ መርፌ ቁልፍ ፈልጌ ትንሽ ስጎረጉረው ተከፈተ፡፡ የመጀመሪያው ገፅ ላይ በቀይ እስክሪፕቶ የእንባ ዘለላዎች ተስለዋል፡፡ በእንባ ዝናቡ መሀል ላይ በሰማያዊ እስክሪፕቶ በተሳለ አራት ማዕዘን ሳጥን ውስጥ ‹‹ኢቦዬ›› የሚል ፅሁፍ አለ፡፡ ገለጥኩት፡፡ ቀን እየተጠቀሰ ገጠመኟ ተዘርዝሯል፡፡ ስትፅፍ ኢቦዬ እያለች ነው፡፡ ለማስታወሻ ደብተሯ የእኔን ስም መዋሷን ተረዳሁ፡፡ የመጀመሪያውን ገፅ ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ የተጠቀሰው ቀን አባዬ ከመታመሙ በፊት ነው፡፡
‹‹ኢቦዬ …… ጠፋሁ አይደል? የቀድሞው ደብተሬ ስለጠፋ አዲስ ደብተር ለመግዛት ሳማርጥ እኮ ነው፡፡ ይቅርታ አድርግልኝ፡፡ ስማኝማ ብታይ ዛሬ የክላስ ልጆች አንዷ ጓደኛችን ቤት ደይ ፓሪ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ቤታቸው በጣም ሰፊ ነው፡፡ ቤተሰቦቿ ወደ ውጪ ስለሄዱ ከወንድሟና ከከዝኗ ጋር ብቻቸውን ነበሩ፡፡ እንግሊዘኛ ነሽ …… አፍሪካ ነሽ …… በቃ ያልተጨፈረበት ሙዚቃ አልነበረም፡፡ እኔ ደግሞ ታውቃለህ እብድ ነኝ፡፡ ከብዙ ወንዶች ጋር ጨፈርኩ፡፡ የመጡት ወንዶች ሁሉ እኔ ላይ ሲያፈጡ ነበር፡፡ ትንሽ ወይን ጠጣሁ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለነበር ሞቅ ብሎኝ ነበር፡፡ ፓሪው ሲያልቅ የጓደኛዬ ከዝን ወደ በረንዳው ጋር ወሰደኝና ሊስመኝ ሞከረ፡፡ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር አይመቸኝም፡፡ ትቼው ልሄድ ስል መንገድ ዘጋብኝና ሊነካካኝ ሞከረ፡፡ በሁለት እጄ ጉንጮቹን እንደከበሮ ሳጮህለት ሁሉም ግር ብሎ መጣ፡፡ ጓደኛዬ ምንችግር አለው ምናምን ብላ ለሱ ተደረበች፡፡ ስላናደደችኝ ሳልሰናበታቸው ወደ ቤት መጣሁ፡፡ ቤት ስደርስ ይቅርታ ብላ ቴክስት ላከችልኝ፡፡ እንኳንም መታሁት አይደል? ሀሀሀሀ ዛሬ በራስ መተማመኔ በጣም ጨምሯል፡፡››
ገለጥ ገለጥ እያደረግኩ ተመለከትኩት፡፡ ብዙዎቹ ከክላስ በኋላ ከጓደኞቿ ጋር ስለሚሄዱበት መዝናኛ ቦታ ምናምን ነው፡፡ ጠቃሚ ነገር እንደሌለው ስለገባኝ አለፍ አለፍ ብዬ አባዬ ከታመመ በኋላ የፃፈችውን አገኘሁ፡፡
‹‹ኢቦዬ …. የአባ ኩላሊት ፌል ካደረገ በኋላ ቤት ገንዘብ በጣም ተቸግረናል፡፡ ትምህርቴን አቋርጬ ስራ ለመጀመር ወስኛለሁ፡፡ የትምህርት ቤት ክፍያ የምከፍልበት ብርም የለኝም፡፡ ምን እንደምሰራ ግን አላወቅኩም፡፡ ሰው እያጠያየቅኩ ነው፡፡ ብር ከሌለን አባዬን ማሳከም አንችልም፡፡ ዶክተሮቹ ደግሞ ገንዘብ ለሌለው ሰው ግድ አይሰጣቸውም፡፡ ለማሳጠብ እንኳን ብር አልቆብን ስንለምናቸው አያገባንም አሉን፡፡ ታውቃለህ እስከዛሬ በትምህርቴ ላይ ጎበዝ አለመሆኔ ቆጨኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ጎበዝ ሆኜ ደግ ሀኪም መሆን ተመኘሁ፡፡ የተቸገሩ ሰዎችን በነፃ የማክምበት ሆስፒታል ቢኖረኝ ብዬ አሰብኩ፡፡ ብችል …… ብሆን ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን ትምህርቴን ማቋረጥ አለብኝ፡፡ ወደፊት አንተ ዶክተር ሆነህ የተቸገሩትን በነፃ ታክማቸዋለህ አይደል? ደግሞ እተማመንብሀለሁ፡፡ ጎበዝ ነህ!›› እንባ እይታዬን ጋረደኝ፡፡ኢንቱ ትናንትና የነበረችበትን የመዝናናት ህይወትና አሁን ያለችበትን የመከራ ጊዜ ሳነፃፅር በጣም አሳዘነችኝ፡፡ እንባዬን ጠርጌ ቀጣዩ ገፅ ላይ ያለውን ማንበብ ጀመርኩ፡፡
‹‹ኢቦዬ ….. ዛሬ ከፍቶኛል፡፡ እያለቀስኩ ነው፡፡ ቤት ማንም እንዲያውቅብኝ ስላልፈለግኩ እስካሁን አልገባሁም፡፡ አባዬ ኩላሊቱን ከታጠበ ስለቆየ በጣም እየታመመ ነው፡፡ የመጨረሻ እድሌን ለመሞከር ብዬ የአባዬ ጓደኛ ቢሮ ሄጄ ነበር፡፡ ቢያንስ የአንድ ቀን ትጥበቱን ወጪ እንዲሸፍንልን ተንበርክኬ ለመንኩት፡፡ ኢቦዬ
1.1K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 15:08:50 ከተራራው ላይ
ክፍል አንድ
(ፉአድ ሙና)
.
‹‹በበዳዮቹ ላይ፣ ወይ ፍረድ ወይ ውረድ፣ ብለን ስናነባ፣
ምነው የፍርድህ ክንድ፣ የእነሱን ቤት ትቶ ከጎጇችን ገባ?
ለምን ዛቱብኝ ነው?››
***
ምሽቱ ዝናባማ ነው፡፡ የመብረቅ ድምፅ እየተደጋገመ ይሰማል፡፡ ተራራውን ተደግፋ እንደነገሩ በተቀለሰችው ጠባቧ የጭቃ ቤታችን በር በኩል ከላይ እየተንደረደረ የሚመጣው ጎርፍ ለመግባት ይታገላል፡፡ ታላቅ እህቴ በበሩ ስር ለመግባት የሚታገለውን ጎርፍ ሁሌም ለዚህ ተግባር በምንጠቀምበት ያደፈ ብርድ ልብስ አፍና ውጪ ለማስቀረት ትሞክራለች፡፡ ብርድ ልብሱን አልፎ የሚገባውን በመወልወያው ታደራርቃለች፡፡ እኔ በጣራ በኩል እየተንጠባጠበ ከህመምተኛው አባቴ ፍራሽ ትይዩ የሚወርደውን ውሀ ከአባቴ ለመከላከል መዘፍዘፊያ ይዤ ቆሜያለሁ፡፡
እናታችን ምድጃው ላይ ለእራታችን በቆሎ እየጠበሰች ‹‹የዛሬውስ ልዩ ነው …›› አለች፡፡ ሰውነቷ ተንዘፈዘፈ፡፡
‹‹እንዲህ በቀላሉ የሚቆምም አይመስልም … በቃ ኢንቱ ወትፈሽ ተይው! አንደኛውን ሲገባ ሲገባ መወልወል ይሻላል፡፡››
የያዝኩት መዘፍዘፊያ ወደ መሙላቱ ደርሶ ነበር፡፡ ኢንቲሳር በታዘዘችው መሰረት በሩን ወትፋ፤ መዘፍዘፊያ ልትቀይርልኝ መጣች፡፡ አባቴ ፈገግ ለማለት እየሞከረ አይኑን እኛ ላይ ጥሎ በደከመ ፊት ሁኔታችንን ይታዘባል፡፡
ጥቂት ቆይቶ ዝናቡ ማባራት ጀመረ፡፡ በቆሏችንን እየበላን መጨዋወት ጀመርን፡፡ ትንሽ እንዳወራን እህቴ ነገ በጠዋት ስራ ስለምትገባ ለመተኛት ተመቻቸች፡፡ ከጎኗ ተወሸቅኩኝ፡፡ ሁሌም ከሷ ጋር ካልሆነ መተኛት እፈራለሁ፡፡ ልተኛ ብልም ብርዱን አልችለውም፡፡
ኢንቱ ሀያ አመቷ ነው፡፡ የቤተሰባችን አስተዳዳሪ ናት፡፡ ትምህርቷን ያቋረጠችው አባቴ በኩላሊት ህመም ምክንያት ስራ መስራት ሲያቆም ነበር፡፡ እናቴ እግሯን ስለሚያማት ረዥም ሰዓት ቆማ መስራት አትችልም፡፡ በዚህ ምክንያት በሻጭነት የተቀጠረችባቸው ሱቆች ሁሉ ከወር በላይ አልቆየችም፤ ያባሯታል፡፡ ያላት አማራጭ ቤት ተቀምጣ አባቴን ማስታመም ሆነ፡፡ ኢንቱ ደግሞ የእለት ጉርሳችንን እና የአባቴን የህክምና ወጪ ለመሸፈን ስትል ትምህርቷን አቋርጣ ሀያ ሁለት ማዞሪያ አካባቢ በሚገኝ አንድ ቡቲክ ውስጥ በሻጭነት ተቀጠረች፡፡ ቆንጆ ስለሆነች ስራ ለማግኘት አልተቸገረችም፡፡
የአባቴ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ያስፈልገዋል ቢባልም ወጪው በእኛ አቅም የሚደፈር ስላልሆነ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ፤ አንዳንድ የሚታዘዙለትን መድሀኒቶች ብቻ እየወሰደ ለረዥም ጊዜ ቆይተናል፡፡ አባቴ ለእርሱ በሚገዛ መድሀኒት ሳቢያ እኛ ጾማችንን ማደራችን ከህመሙ በላይ ያንገበግበዋል፡፡ ሁሌም እንባ እየተናነቀው ‹‹አግኝቶ እንደማጣት ያለ ክፉ ቅጣት የለም!›› ይላል፡፡ ሳይታመም በፊት የመኪና ደላላ ነበር፡፡ አየር ጤና ላይ ትልቅ ቤት ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በሂደት የቤት ኪራይ እንኳን የምንከፍለው ስናጣ ከነበርንበት ቤት ለቅቀን፤ አሁን ያለንባትን ደሳሳ ባለ አንድ ክፍል ጎጆ በአነስተኛ ብር ተከራየን፡፡
እኔ ትምህርቴን አቋርጬ ስራ ለመስራት ብፈልግም ኢንቱ አልፈቀደችልኝም፡፡ በራሷ መመልከት ያልቻለችውን ስኬት በኔ ህይወት ውስጥ ለመመልከት ስለምትጓጓ በትምህርቴ በርትቼ ወደ ፊት በደንብ ላግዛቸው እንደምችል ትሰብከኛለች፡፡ እኔ እማራለሁ … ሆዴ ቢጮኽም … ራሴ ቢበጠበጥም … ልብሴ ቢቦጫጨቅም፤ እማራለሁ! በጩኸቱም በማቅለሽለሹም ታጅቤ … ኢንቱ የነገረችኝን ስኬት እያሰብኩ በተስፋ ወደ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ፡፡ እናቴ ድሮ ተከብራ ስትኖር የምታውቃቸው ጓደኞቿ የድግስ ስራ ሲኖርና የልብስ አጠባ ስራ ሲያገኙላት እየሄደች ትሰራለች፡፡ የአንፎ ተራራን ተደግፋ ከተቀለሰችው ጎጇችን የማይወጣው ህመምተኛው አባቴ ብቻ ነው፡፡ አሁን ከህክምናውም ተስፋ ቆርጧል፡፡ በደህናው ጊዜ ኩላሊቱን ለማሳጠብ ሆስፒታል ይመላለስ ነበር፡፡ እጅ ሲያጥረው … አብረውት የበሉ ጓደኞቹ ሲከዱት … ዘመድ ሲሸሸን … ተስፋ ቆረጠ፡፡ ‹‹ከፈለገ ይውሰደኝ እንጂ ከዚህ በላይ ሸክም አልሆንም!›› ብሎ ህክምናውንም ተወ፡፡ ትናንት የነበረበትን ሲያስታውስ ንዴት ንዴት ይለዋል፡፡ ከህመሙ በላይ እሱ ሳይጎዳው አልቀረም፡፡
ከኢንቱ ጎን ተኝቼ እንቅልፍ ሊወስደኝ ሲጀማምር የማቃሰት ድምፅ ሰማሁ፡፡ ኢንቱ ተስፈንጥራ ተነሳች፡፡ እንቅልፌ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ወደ አባቴ ፍራሽ ስዞር እናቴ ስታለቅስ ተመለከትኩ፡፡ አባቴ ነብስ ግቢ ነብስ ውጪ ሆኖበት እግሮቹን ያፋትጋል፡፡
‹‹አባ … አባ … አባይዬ …›› ኢንቱ ከአባቴ ፊትለፊት ተደፍታ ታነባለች፡፡
እኔ ደንዝዣለሁ፡፡ ከጀርባቸው ቆሜ ፍዝዝ ብዬ እመለከታለሁ፡፡ ብዥ ብሎብኛል፡፡ የኢንቱ እና የእናቴ የለቅሶ ድምፅ ጎልቶ ይሰማኛል፡፡ ብዥዥዥዥዥ … ጥርት … ብዥዥዥዥዥ … ጥርት … ብዥዥዥዥዥ … ጥርት፤ የለቅሶ ድምፅ … ‹‹አባዬ አባዬ …›› ‹‹ሰሚሬ ሰሚሬ …›› የሚል የሰቆቃ ዜማ የጆሮዬን ታምቡር ይደበድባል፡፡ በደመ ነፍስ ወደ አባቴ ሄጄ እላዩ ላይ ተኛሁ፡፡ ሰውነቱ በላብ ረጥቦ ነበር፡፡ ቀስ እያለ ቅዝቅዝ ማለት ጀመረ፡፡ ‹‹እህህህህህህ›› የሚል የጣር ድምፁም ጠፋ፡፡ እናቴ እሪታዋን አቀለጠችው፡፡ ኢንቱም ተከትላት እርሪ ማለት ጀመረች፡፡ ነገሩ አልገባኝም፡፡ ሌላ አለም ላይ ያለሁ ይመስል ሁሉ ነገር እንግዳ ሆኖብኛል፡፡ ጎሮቤቶቻችን መጥተው ቤታችንን ቆረቆሩ፡፡ ቀስ በቀስ ቤታችን እየተንሰቀሰቁና እየጮኹ በሚያለቅሱ ሰዎች ተሞላ፡፡ አሁን የአባቴ መሞት ለእኔም ተገለፀልኝ፡፡
አባዬ እኮ ሳይታመም በፊት እኛን መዝናኛ ቦታ ከወሰደን አብሮ የጎረቤት ጓደኞቻችንንም ይዞ ይኼድ ነበር፡፡ የተቸገረ ሰው ከፊቱ መጥቶ በባዶ ተመልሶ አያውቅም፡፡ ዘመድ ቢቸገር ቀድሞ የሚደርሰው እርሱ ነበር፡፡ የእርሱ ተራ ሲሆን ግን የሚደርስለት አጥቶ፤ ኩላሊቱን እንኳ ማሳጠብ ተስኖት እየነደደ ሞተ፡፡ እና ይኼ ፍትህ ነው!? ማንስ ጋ ይከሰሳል!? እና ከዚህ በኋላ አባት የለንም? በድንጋጤ ከገባሁበት ፍዘት ወጥቼ ቤታችን ውስጥ እየሆነ ያለውን ሳይ የአይኔ ቋጠሮ ተፈታ፡፡ እየተንሰቀሰቅኩ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ ጎረቤቶቻችን ህፃን ስለሆንኩ አቅፈው ሊያባብሉኝ ይሞክራሉ፡፡ ለሊቱን ሙሉ ቤቱ በእንባ እስኪረጥብ ሲለቀስ አደረ፡፡ ኢንቱ ደጋግማ በስስት ትመለከተኝና አቅፋኝ እየተንሰቀሰቀች ታለቅሳለች፡፡
‹‹ኢንቱ … አባዬ ሞተ?›› ባለማመን ውስጥ እየዋለልኩ እጠይቃታለሁ፡፡
‹‹ኢቦዬ እኔ አለውልህ እሺ … እማዬ አለችልህ እሺ …›› እንባዋ ከአይኖቿ ቅጥር በቡድን በቡድን እያመለጠ ልታባብለኝ ትሞክራለች፡፡
አባዬ ፊት ላይ ማታ ያየሁት ፈገግታ ፊቴ ላይ ይመላለሳል፡፡ ሞተ ሲባል ምን ማለት ነው? በልጅነት አዕምሮዬ መልሱን አስሳለሁ፡፡
ጠዋቱን አባቴን ለመቅበር የአካባቢው ሰው ተሰበሰበ፡፡ አካባቢያችን ላይ የጀናዛ ትጥበት የሚደረግበት ቦታ ስላልነበረ፤ ጋሽ አብዱረዛቅ ከሁለት የሰፈራችን ወጣት ልጆች ጋር ሆነው ከበሩ ፊት ሊያጥቡ መዘገጃጀት ጀመሩ፡፡ ወዲያው የጓደኛዬ አብዱልከሪም አባት ‹‹ና እስኪ ኢቦዬ›› ብለው ራሴን እያሻሹ ወደ ቤታቸው ወሰዱኝ፡፡ አባቴ ሲታጠብ እንዳላይ ነበር፡፡ ከአብዱልከሪም ጋር እነሱ ቤት ውስጥ ተቀምጬ ስለሆነው ነገር ለማሰብ ሞከርኩ፡፡

አባቴ ደንደን ያለ ሰውነት ነበረው፡፡ እኛም የምንማረው የግል ትምህርት ቤት ነበር፡፡ የምንፈልገውን እንበላ ነበር፡፡ ከቤታችን የማይጠፉ ብዙ ዘመዶች ነበሩን፡፡ አባቴ መኪና ነበረው፡፡ አባዬ በታመመ በሶስት አመት ውስጥ ግን ነገራቶች የተገላቢጦሽ ሆኑ፡፡ የአባቴ ስራ መንቀሳቀስ የሚፈልግ ስለነበር እሱ ሲታመም
602 views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 15:08:28 አዲሱ ጀመረ
431 views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:37 #የመጨረሻዉ #ክፍል

ፊርዶስ ደወለች ስልኩን አነሳሁት ...ምንም አልተፈጠረም ለወሬ አቸኩሉ
.....ፊርዶስ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር አለችኝ
......እኔም ምን ነበር ፊርዱ ??አልኳት
........እሷም ምሳ የጠራችሁን ሁለታችን ነበር ግን አንድ ሰዉ አብሬ እናንተ ጋር ካልሄድኩ አለን ምን ትያለሽ ሂኩ??? አለችኝ
.....እኔም ችግር የለም እሄዳለሁ ያለዉን አብራችሁ ይዛችሁ ኑ አልኳት
....ፊርዱም የዛሬዉ ቀን እኮ ለ ዙበይር
ታላቅ ቀን ነዉ ትናንት ቅዳሜ አዳር እንቅልፍ ሳይወስደዉ ነዉ ያደረዉ በደስታ ተባብለን ተሳስቀን ፊርዶስ አሁን ከቤት እየመጣን ነዉ ብላ ነገረችኝ፡፡ እኛም ተዘጋጅተን ነዉ እየጠበቅናቸዉ ያለነዉ...
ከ30 ደቂቃ ቡሀላ እቤት ደረሱ ፡፡ ወደ ቤት ሲገቡ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ እናት አብረዉ መጥተዋል ቅድም ደዉላ አንድ ሰዉ ይዤ ልምጣ ያለችዉ እናታቸዉን እንደሆነ ተገለፀልኝ ፡፡ የእኔ እናት እና አባት ብድግ ብለዉ ተቀበሉ ፊርዶስ የእኔን እናት ከእሷ እናት አስተዋወቀች አባቴንም ..የፊርዶስ እናት እና የእኔ ቤተሰቦች ሲያወሩ ዛሬ አዲስ የተገናኙ አይመስሉም ነበር በጣም ደስ አለኝ ፡፡
ዙበይር ግን ፈርቶ ዝም ብሏን አባቴ አብሽር ተጨዋት አትፍራ እንጂ እያለዉ ነዉ፡፡
ከዛም ምሳችንን በልተን ጨረስን ቡናዉ ተፈልቶ ተመራርቀዉ ቡናዉን ተጠጥቶ ከጨረሱ ቡሀላ የዙበይር እናት እስኪ የመጀመሪያ ስለሆነ ማስታወሻ ብለዉ የተጠቀለለ ስጦታ ሰጡን ስጦታዉ ለእናቴ የሚያምር ድርኢና ጎጎራ እና የሚያምር ጫማ ሲሆን ለአባቴ ደግሞ ሽቶ የዙበይር እናት አበረክተዉ ለምሳዉ ፕሮግራም አመስግነዉ ተመራርቀዉ ተለያዩ ፡፡ እናቴም አባቴም በጣም ተደስተዉ ከአሁን ቡሀላ ምን ቀረ እንግዲህ ልጄ ያሰብሽዉን አላህ ያሳካልሽ ብለዉ አባቴም እናቴም መረቁኝ፡፡
ማታ ላይ ዙበይር ደወለልኝ ብዙ ነገሮችን አዉርተን ሂኩ መኖሪያ ቤቴን ያከራየሁትን ሰዎቹን ቤት እንዲፈልጉ ደዉየ ነግሪያቸዉ እሺ በቅርብ ቀን ለቀዉ እንደሚወጡ ነግረዉኛል ስለሆነም ተዘጋጂ ብሎ ነገረኝ፡፡
....እኔም እሺ አልኩት
ዙበይርም ሂክማ እወድሻለሁ አላህ ሀላሌ ስላረገኝ የአንቺ በጣም ደስተኛ ነኝ አለኝ፡፡
እኔም እወድሀለሁ ዙበይር አንተ ማለት የሂወቴ ብሩህ ተስፋየ ነህ ጥሩ ልጅ ወልደን በዲነል ኢስላም ገንብተን እንደምናሳድግ ይታየኛል ኢንሻ አላህ አልኩት፡፡ ብዙ ደቂቃዎች አዉርተን ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ፡፡ የእኔ እናት እና የዙበይር እናት በስልክ ማዉራት መቀራረብ ጀምረዋል በጣም ደስተኛ ነኝ

ፊርዶስም እቤት መቼ ሽምግልና እንላክ ??ብላ ጠየቀችኝ ...ቤተሰቦቼን ጠይቄ የሚመችባቸዉን ቀን ቤተሰቦቼን ጠይቄ ለፊርዶስ ነገርኳት
ዙበይርም መኖሪያ ቤቱ አስለቅቆ የቤት እቃ እያሟላ ነዉ ፡፡ በስልክ ቀን በቀን እያወራን ነዉ አልፎ አልፎ በአካል እንገናኛለን ግን ተሳስመን አናቅም የወደፊት መሆን ያለባቸዉን ተወያይተን እንለያያለን....
ሸምግልና የሚልኩበትን ቀን ቤተሰብ የሚመችባቸዉን ጠይቄ ለዙበይር ነገርኩት.....

አስታዉሳለሁ ቅዳሜ ቀን የዙበይር አባትን አብሮ በመምጣት እስከ 10 የሚደርሱ ሽማግሌዎች መጥተዉ ልጅህን ለልጄ ተባብለዉ ለዙበይር ታጨሁ ...በዛዉም የሰርጉን ቀን ተቆርጦ ሽማግሌዎቹ ተመለሱ ....በጣም በሂወቴ ደስተኛ እየሆንኩ ነዉ የዙበይር የሰራዉ የመኖሪያ ቤት ሸጎሌ መንገድ 7 አካባቢ ነዉ፡፡ ምን የራሱ ለወደፊት አብረን ልጅ ወልደን የምናሳድግበት ቤት ነዉ እንጂ


የሰርጉ ቀን ደረሰ ሰርጋችንንም ..
ሁለታችንም ተነጋግረን ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘዉ በኡማ ሆቴል ነበር ፡፡ ፊርዶስ ለኔ የመጀመሪያ ሚዜ ሆነች ሁለቱ ሚዜዎቼ ደሴ ከተማ ካሉት የአጎቴ ልጆች አረኩኝ ..ፊርዶስ ለዙበይር መጀመሪያ የሱን ደስታ ያስቀደመች እህቱ ለእኔ ደግሞ የዲን እህቴም ጓደኛየም ..የወንድሟ ባለቤት(አይቷ) ነኝ፡፡ ሰርጉ በሚያምር ዘመድ ጓደኛቼ በተገኙበት በአማረ ሁኔታ በኡማ ሆቴል ተፈፀመ፡፡ ፊርዶስ ጋር ከበፊቱ በበለጠ ከአገባሁም ቡሀላ ተቀራርበናል ደስ የሚል ሂወት እየመራሁ ነዉ፡፡

አንተን ያወቅኩ ለታ
የዛን እለት ማታ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ያወራሀኝ አንተ የወደድኩህ እኔ
ያን ምገዛውን ፈጣሪዬን ትቼ
ህጉን ተላልፌ ራሴን ሰዉቼ
ትዝ ይልሀል ያኔ
መዉደድህ ሲያሰክረኝ
ፍቅርህ እንዲያ ሲያንገላታኝ
መውደድህ የእውነት
ማፍቀርህ የእውነት
ማውራትህ የእውነት
ሁሉም ነገር እውነት መስሎ ያዘናጋኝ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ከቤት ተደብቄ ምክንያት ፈጥሬ
የውሸት ጋጋታ አውርቼ ደርድሬ
አንተ ጋር ለመምጣት ብዙ ቀባጥሬ
ትዝ ይልሃል ያኔ
አሁን አስብና ያን ሁሉ መሆኔ
ፈገግ እላለሁ አወይ ስልጣኔ
ለካ
ፍቅር የሚሰምረው
ፈክቶ የሚጠነክረው
ከአላህ ጋር ሁኖ የተመሰረተ ነው
በትላንቴ አፍራለሁ በዛኛው ዘመኔ
ግና
መሀሪው ጌታዬ እስኪ ተቀበለኝ ፀፀት ፍራቻዬን
አዲሱን ህይወቴን ካንተ ጋ ልጀምር
አንተ የገባህበት አያውቅም ድንግርግር

ፊርዶስ ከእኛ ሰርግ አራት ወር ቡሀላ ስለታጨች የምታገባበት ቀን ደርሷል ......እኔም ዙበይር ጋር ጥሩ የትዳር ሂወት መኖር ጀመርኩ፡፡ ሁሉም ወንድ አንድ አይደለም ለምን ሁሉም ሴት አንድ ስላላይደል...አንድ ሰዉ የምንቀርበዉ የምንወደዉ ሰዉ ሲሸዉደን መጥፎ ስራ ሲሰራብን ጥሩ ሰዉን ማመን ስለሚያቅተን ሂወታችን ህልማችን ዳግም አይሳካም በሚል እኔ ዙበይርን ላጣዉ ነበር፡፡ የሰዉ ልጅ ነን እና እንሸወዳለን ግን ከተሸወድን ቡሀላ በዛ ነገር ላይ ቋሚ ወንጀለኛ መሆን የለብንም ወደ አላህ መመለስ መቻል አለብን፡፡ ዙበይር ጋር በደስታ በፍቅር እየኖርኩ ነዉ .. በቅርብ ቀን ደግሞ ፊርዶስ ልታገባ ነዉ እኔም የመጀመሪያ ሚዜየ አንቺ ነሽ ተዘጋጂ ብላኝ ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡

ተፈጠመ ከታሪኩ ምን ተማራችሁ?
519 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:21 እዉነተኛ ታሪክ

#Part 22

እኔም እናቴ ጎን ቁጭ ኡልኩኝ...ሁሉንም ልነግራት ጀመርኩ ስለ ዙበይር እናቴ ዙበይር ማለት .......የፊርዶስ ታላቅ ወንድም ስለ ፀባዩ እና እስከሚሰራዉ ስራ መርካቶ ሱቅ እንዳለዉ መኖሪያ ቤትም እንዳለዉ አከራይቶት እሱ ቤተሰብ ጋር እንደሚኖር ነገርኳት፡፡
እናቴም ጥሩ ግን ፊርዶስ በጣም ጥሩ ልጅ ናት ማሻ አላህ የነ እሱ ዘር ጋር አንቺ መጋብትሽ ደስ ይለኛል፡፡ ግን ልጄዋ አለችኝ በስስት እያየችኝ የወደድሽዉ ብር ስላለዉ ሱቅ ስላለዉ መኖሪያ ቤት ስላለዉ ነዉ ወይ ?.. አንቺ በብር አስበሽ ከሆነ አላህ ያይሻል አንቺ በብር የምትገዢ ሸቀጥ አይደለሽም እኔ የምፈልገዉ ኢማን ያለዉ አንቺን ወዶሽ በፍቅር ተሳስራችሁ ልጅ ወልዳችሁ የአንቺን ደስታ ማየት ነዉ እንጂ ገና እሱ ብር አለዉ ብለሽ አስበሽ የትዳር አጋር የመረጥሽዉ ከሆነ ልጄዋ ይቅርብሽ፡፡ እኔ ዲን ያላቸዉ አብራችሁ ማደግ የምትችሉ ሁለት ሰዉ ቅርብ ቀን ልጅሽን ዳሪኝ ያሉኝ አሉ፡፡ ልጄ እኔ የምፈልገዉ የአንቺን ደስታ እንጂ ወንድ ልጅ በብር ሀይል አግብቶሽ የሀብታም እስረኛ እንድትሆኝ አልፈልግም አለችኝ፡፡
.....እኔም እናቴን ምንም አላልኳት ወሬዋን አስጨረስኳት እዉነቷን ነዉ ትዳር ማለት ሁለተኛ ሂወት ማለት ነዉ እንጂ እንደ ሆቴል ገብቶ ተጠቅሞ የሚወጣበት ሂወት አይደለም፡፡ እናቴ ልክ ነሽ ግን ዙበይርን በብዙ ነገር ፈትኘዋለሁ እናቴ ብዙ ለአንቺ መንገሩ ጥሩ መስሎ ያልታዩኝ ሂወቶች ነበሩኝ..... ዙበይር ነዉ የተረዳኝ እሱ በብሩ የማይተማመን እኔ ለራሱ ይሄ ሁሉ እንዳለዉ የሰማሁት ቅርብ ቀን ነዉ ...የቀረበኝ ፍቅሩን ይዞ ትዳርን አስቦ እንጂ ይሄ ቤት አለኝ መርካቶ ሱቅ አለኝ ብሎ አንድ ቀን አዉርቶኝ አያቅም ማሚ በዲኑም ጎበዝ ነዉ ፡፡ የሚገርምሽ እንደ አንዳንድ ወንዶች አይደለም እናቱ ምሳ አዘጋጅተዉ ጠርተዉኝ አስተዋዉቆኛል፡፡ ለእናቱ የወደፊት ሚስቴ ናት ብሎ አሳዉቋል ማሚ እናቱም ወደዉኝ ስጦታ ሰጥተዉኛል ..ዙበይር የሚፈልገዉ እኔን ማጃጃል ሳይሆን ወደ በሀላል ወደ ትዳር ለመግባት ነዉ፡፡ እኔ ወድጀዋለሁ አንቺም ዉደጅልኝ ማሚ አልኳት፡፡

....እናቴም እኔ አንቺን እወድሻለሁ የወደድሽዉንም እወዳለሁ የምጠይዉንም እጠላለሁ ግን አንድ ፍሬ ልጄ ነሽ ጥሩ ትዳር እንዲኖርሽ እፈልጋለሁ ድል ባለ ሰርግ ነዉ የምድርሽ ግን ዙበይርን አምነሽበታል??? አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ ዙበይር ነዉ ምርጫየ ብየ ብዙ ነገሮችን አጫወትኳት ያዉ የሚደበቀዉ ያለ ሁኖ መቼም እናቴ ናት እና ሀይደር ጋር ያሳለፍኩትን እና በዛ ነገር ሀኪም ቤት የተኛሁበትን ሂወት እኔም እናቴም እንድታስታዉሰዉ አልፈልግም........

በመጨረሻም እናቴ እሺ አላህ ያሳካላችሁ አለችኝ
......እኔም ደስ አለኝ ደግሞ ደስታየን እናቴ እንዲህ ብላ ጨመረችልኝ፡፡ ዙበይር አንቺን ለእናቱ ካስተዋወቀሽ በጣም ጎበዝ አስተዋይ ልጅ ነዉ እኔንም እሁድ ምሳ አዘጋጅተን ዙበይርን አስተዋዉቂኝ እሁድ ንገሪዉና ምሳ እንጋብዘዉ እህቱ ፊርዶስም አብረዉ ይምጡ ...እኔም ነገ ጠዋት ደዉየ ለአባትሽ እቤት እንደመጣ እነግረዋለሁ .. አባትሽም ይወቀዉ ነገ ከሰአት መጥቶ ከአባትሽ ጋር እንመካከርበታለን ብላ እናቴ አስደሰተችኝ

እኔም እናቴ ጋር ተቃቅፈን ሁለታችንም በጣም ደስ አለን ፡፡ እሁድ ለመድረስ ገና አራት ቀናቶች አሉ፡፡ እናቴ ለአባቴ ደወለችለት መምጣት የሚመቸዉ ቅዳሜ እንደሆነ ነገራት፡፡ ቅዳሜ አደራ እንዳቀር ለአስቸኳይ ጉዳይ ነዉ የምትፈለገዉ አለችዉ እናቴ...
.....አባቴም ለመስማት ጓጉቶ አሁን በስልክ ንገሪኝ ቢላት አይሆንም በስልክ ተነግሮ አያልቅም በአካል ስንገናኝ ነዉ የምነግርህ አለችዉ...
ወዳዉ መኝታ ቤት በመግባት ለዙበይር ደወልኩለት ሁሉንም ነገር ነገርኩት እና እናቴ እሁድ ምሳ ትዉዉቅ እናድርግ ብላኛለች እሁድ ይመቸሀል ከነእህትህ?? አልኩት
......እሱም በደስታ እንዴት አይመቸኝ ቤተቦችሽን ለመተዋወቅ ዝግጁ ነኝ አለኝ፡፡
.......ከዛ ለፊርዶስ ደወልኩላት ብዙ አዉርተን ...እሁድ ስላት .....ወሬየን አቋርጣ ሂኩ ታዘብኩሽ አለችኝ
ምን ሆንሽ ፊርዱ ??አልኳት
.....እሷም የምሳ ግብዣዉን መጀመሪያ ለኔ ሳትነግሪ ለወንድሜ ነግረሽ ነዋ ከእኔ እና እሱ መጀመሪያ ያወቅሽዉ እኔን አይደል ብላኝ ተሳሳቅን፡፡

የማይደርስ የለም ነገ እሁድ ነዉ ዛሬ ቅዳሜ ላይ ነን ቅዳሜ ሙሉቀን ጀምረን እኔ እና እናቴ ለእሁዱ ባሌን የማስተዋዉቅበት የምሳ ፕሮግራም ደፋ ቀና እያልን ነዉ ..አባቴንም ሸዋ ሮቢት ስለሚኖር እሁድ እቤት ምሳ ተዘጋጅቷል ምክንያቱ ስትመጣ ይነገረሀል ብለን ቅድሚያ ስለነገርነዉ ቅዳሜ ማታ እቤት ገባ፡፡

እቤት እንደገባም ስለ ነገዉ እሁዱ የምሳ ፕሮግራም እናቴ ነገረችዉ ግን አባቴ እና እናቴ በነገዉ ምሳ ላይ የተስማሙ አልመሰለኝም ፡፡ አባቴ ጮክ ብሎ ይሄማ መቼም አይሆንም እኔ ፈቅጄ ልጄን አልሰጥም አንቺ እኔ ሳልፈቅድ ትድሪያት እንደሆነ አያላሁ...እዚህ ቤት ወንዱ ወይ አንቺ ወይ እኔ እንሆናለን አትሰቢዉ እኔን የጠየቁኝ ሰዎች አሉ እንደዉም ለአንዱ ቃል ገብቸለታለሁ ትምህርቷን ስጨርስ ብየ አሁን ከህመሟ ከሻረች እኔም አንቺን አማክርሻለሁ እያልኩ ነበር በስራ ተወጣጥሬ ነዉ እንጂ ዛሬ ላማክርሽም ነበር፡፡ ለአስቸኳይ ስትይኝ ጭራሽ ልጄ ታገባለች ብየ ትዝም አላለኝ፡፡ ወደድሽም ጠላሽም እኔ መቼም አልስማማም እኔ ለመረጥኩት ሰዉ ነዉ ልጄን የምድረዉ ...የነገዉም ምሳ ፕሮግራም እኔ አልኖርም እንደፈለጋችሁ ማረግ ትችላላችሁ...ተስማምቼ እሱን እኔ አልተዋወቅም፡፡ እናተ እሱ እቤት መጥቶ ብትተዋወቁ እኔ እና አንቺ ፍች ነዉ የሚለየን...እኔ ከሀገር ሌላ ሀገር በመንግስት ስራ የቤተሰብ ፍቅር ሳላይ በግዥ በሁቴል ምግብ የምኖረዉ አንቺ እና ልጄ እንድትደሰቱ እንዳትከፉ እንጂ ለራሴ መኖር መች አቃተኝ...ስለሆነም ይሄ የትዳር ነገር መቼም የማይሆን ነዉ ሲል እዉጭ ሁኜ ሰማሁት፡፡

የኔ ፈተና ብዙ ነዉ እኔም ከቤት ዉጭ ሁኜ ደንግጬ ቆምኩኝ...የማወራዉ ጠፋኝ ነገ ምሳ ዙበይርን ጠርቸዋለሁ....ትዳር ቤተሰብ ስቆ መርቆ ሲሰጥ ነዉ አለመግባባት ቢኖር ተመልሰን የምንመጣዉ ወደ ቤተሰብ ነዉ፡፡ ቤተሰብ ለወደደዉ ስቆ ደስተኛ ሁኖ ካልሰጠ ቡሀላ የሆነ ነገር ቢፈጠር ሌላ የቤተሰብ ጫና ይፈጠራል፡፡

....የሂክማ ፈተና በዛ አሁን ደግሞ አባቷ እኔ ያልኩት ካልሆነ አታገባም አለ..ዙበይርም ምሳ ተጠርቷል ምን ይፈጠር ይሆን በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን

#Part 23
325 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:21 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

ወደ አምስት ሰአት አካባቢ ከቤት ልብሴን ቀያይሬ ፊርዶስ ጋር አብረን ጉዟችንን ቀጠልን ..ፊርዶስም ዛሬ ምሳ እኔ ነኝ የምጋብዝሽ ብላኝ መገናኛ አካባቢ የሚገኝ ኢስላም ሬስቶራንት(ምግብ ቤት ) ገባን፡፡ ስንገባ ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ አሁንም ዙበይርን ነበር ያገኘሁት፡፡ ፊርዶስም ዛሬ እስኪ ምሳ አንድ ላይ ሁነን ልጋብዛችሁ ብየ ነዉ አለችን፡፡
...... ምሳችን አዘን በላን....

ከዛም ምሳ በልተን ከምግብ ቤቱ ወጣን ፡፡ ሶስታችን ከመገናኛ ተነስተን እግራችን ወደ አመራን እየተጓዝን ነዉ...ትንሸ እንደሄድን ዙበይርም ፊርዶስን እስኪ ሁለታችን የምናወራዉ ወሬ አለን አየር ትለቂልናለሽ አላት
...ፊርዱም ከእኔ ደብቀህ የምታወራዉ አለ ዙበይር ------እሺ ካልክ እገነጠላለሁ :: ብቻ የህዝብ ተወካዮች የፓርላማ ዉይይት እንዳታረጉት ብላ እየተሳሳቅን ገንጠል አለች
እኔ እና ዙበይር ብቻ ቀረን ሁለታችንም ተፋፈርን በዝምታ ብዙ መንገዶች ተጓዝን ማን ወሬ ይጀምር የተባባልን ይመስል አንዳችን የወሬን መጀመሪያ መክፈቻ ዙበይር ተነፈሰ ..
....... የዛሬዉ ምሳ እንዴት ነበር ???አለኝ
.......እኔም አሪፍ ነዉ አላህ ይስጣት እህትህ ጋበዘችን አልኩት
.....እሱም ግን እኔ መኖሬን ብታቂ ፊርዶስ ብነግርሽ ትመጪ ነበር???? ብሎ ጠየቀኝ
....እኔም እንጃ ግን እህትህ የምትለኝን እሰማለሁ ፊርዶስን የማያት እንደ እህቴ ነዉ፡፡ ስለሆነም ፊርዶስን ያለችን እንቢ የምልበት ድፍረት የለኝም አልኩት፡፡
.......ማሻ አላህ እህቴን እኔም አንቺም እንወዳታለን ፊርዶስ በቤተሰብ የመጣ ትዳር አለ ግን ሁሌ የምትለዉ እኔ ከማግባቴ በፊት ወንድሜን ዙበይርን ደግሼ ድሬዉ ነዉ የማገባዉ ትላለች ፡፡ የእኔ እና እሷ አስተዳደግ የተለየ ነዉ ተከታታይ ስለሆን ተዋደን ነዉ ያደግነዉ ..አሁንም ድረስ ወንድሞቼን ሁሉንም በአንድ አይን ብታይም እሷ ግን እኔ ጋር አስተዳደጋችን የተለየ ስለሆነ በጣም ነዉ የምንዋደደዉ ሚስጥር አደብቀኝም እኔም አልደብቃትም አለኝ፡፡
......እኔም ፊርዶስን እንደ እህቴ ነዉ የማያት የምደብቃት የለኝም አልኩት፡፡
አሁን መፈራራት የለም ሁላችንም ግልፅ ሁነን እያወራን ነዉ፡፡
......ዙበይርም ግን ይሄን ጥሩ ፀባይ ይዘሽ እስከአሁን እንዴት ነዉ እንደ እኔ በፍቅር የወደቀ አላስቸገረሽም??? እንዴ አለኝ እየቀለደ ....
እኔም ለዙበይር ምንም ላልደደብቀዉ ወስኛለሁ፡፡ እኔም የፈነዳ የመኪና ጎማ ይመስል ኡፍፍፍ ብየ #የት_ይደርሳል_የተባለዉን_ዛፍ_ቀበሌ_ቆረጠዉ፡፡ አልኩት፡፡
.....ዙበይርም ማለት አልገባኝም??? አለኝ
.....እስከ አሁን የት እደርስ ነበር ግን በመሀል ዛፍም ያድጋል ብለሀዉ ሲቆረጥ ማደጉ ያቆማል ይደርቃል የኔም ሂወት እንደዛ በለዉ አልኩት
..ዙበይርም እንዴ እንደ እሱ አይደለም ዛፍ ሲቆረጥ ሌላ ያወጣል ያቆጠቁጣል አለኝ
...እኔም የኔ አቆራረጥ እንዳያቆጠቁጥ ነዉ ብቻ በሂደት ያንን ማስረሻ እህትህን ሰጠኝ አልሀምዱሊላህ አልኩት
...እሱም በአላህ ተወኩል ነዉ አላህ ያለዉ ነዉ የሚሆነዉ ደግሞ ያሰብሽበት ግብ ለመድረስ የትናንት ትናንት ነዉ አሁን ያለሽዉ አሁን ላይ ነዉ ያለፈ ትዝታ ትርፉ ቁጭት ነዉ፡፡ የወደፊት ራዐይ ግን ተስፋ ነዉ አለኝ፡፡
.....እኔም ኢንሻ አላህ ግን እስከ አሁን አንተ ለምን አላገባህም ???? ማስተዳደሪያ ብርም አለህ ነጋዴ ነህ መኖሪ ቤትም አለህ አከራይተህ ነዉ የምትኖረዉ ለምን እስከ አሁን አላገባህም??? አልኩት
እሱም እኔ የምመኘዉ ዱአየ አላህ የምወዳትን ልጅ መጀመሪያ የወደድኳትን የትዳር አጋሬ አርግልኝ ነበር የምለዉ .....ግን ብዙ አመታት ማንም ሴት ልቤ ዉስጥ ገብቶ አያቅም ነበር....ግን ከትንሽ ወራት በፊት አንዲት ልጅ ወደድኩኝ ግን ምን ዋጋ አለዉ ፍቅሩ እኔ ጋር ብቻ ሆነ ፡፡ የአንድ ሰዉ መዉደድ ማለት በአንድ እጅ እንደማጨብጨብ ነዉ ዱአ አርጊልኝ ልጅቱ እንደምወዳት እንድትረዳኝ አለኝ፡፡
......እኔም እንደዚህ ሲለኝ እንዴ እኔን ነዉ ወይስ ሌላ ናት ብየ ተወዛገብኩ ለምን እንደሚወደኝ አቃለሁ ደግሞ እኔ ጋር ሁኖ ስለ ሌላ ሴት ያወራኝ መሰለኝ
....እኔም እስከ አሁን ስትወድ የመጀመሪያህ የሆነችዉን ለማግባት ወስነሀል ማለት ነዉ?? አልኩት

እሱም አዎ ወስኛለሁ ልጅቱን እኮ ታቂያታለሽ አለኝ፡፡
...እኔም ማን ናት??? አልኩኝ ፈጠን ብየ
........እሱም ገምች አለኝ
......እኔም መገመት አልችልም አንተዉ ንገረኝ አልኩት
....እሱም ሂኩ አንቺ ነሽ ለምን አትረጂኝም አንቺ በፍልጥ ካልሆነ በፈሊጥ አይገባሽም ማለት ነዉ?? አለኝ ፈገግ እያለ.....
ግን አንተ እኔን የወደድክብኝ ምክንያት መስፈርቱ ምንድን ነዉ ዙበይር እንዴት የትዳር አጋርህ እንድሆን መረከኝ???? አልኩት...
......እሱም ሂኩ እኔ ከሆነሉም የወደድኩሽ ግልፅነትሽ እና ዲን ስላለሽ የዛሬወን ሳይሆን የነገዉን ሂወት የምታስቢ ነሽ ፡፡ ፊርዶስ በጣም ትወድሻለች ታከብርሻለች ፊርዶስ የወደደችዉ ለኔ የወደፊት ትዳሬ ከሆነ ደስተኛ ነኝ ፡፡ ፍቅር መቼ ?የት ?እንዴት ?ከየት? ወደ የት? የማይባል ግዑዝ ነገር ነዉ አላህ ፍቅሬን በሀላሉ አድርጎ የትዳር አጋሬ ብትሆኝ እድለኛ ነኝ ሂኩ አለኝ
......እኔም የደስታም የሀዘንም እንባ ከየት መጣ ሳይባል በአይኔ እንደምንጭ ዉሀ ኩልል እያለ ወረደ .... ሳለቅስ ዙበይር ደነገጠ ምን ሆንሽ ??መናገር የለብኝም ነበር እንዴ?? ምን ላርግ ተቸግሬ ነዉ ሂኩ አለኝ፡፡
ያለቀስኩት በእሱ መወደዴ የደስታ እምባ ሲሆን በተዘዋዋሪም እኔ ደግሞ ለትዳር ብቁ አይደለሁም ዙበይርን እኔም እወደዋለሁ ግን የኔ እንደማይሆን በማሰብ በዉሸት መዉደድ ጉድ የሰራኝ ሀይደር እዉነተኛ እኔን የሚወድ ሳገኝ የተደበላለቀ ሁለት ስሜት ያለዉ እምባ ነዉ፡፡
ግን ዙበይርን ልዋሸዉ አልፈለኩም፡፡ ልነግረዉ ወሰንኩ እሱም አረ በፈጠረሽ አታልቅሺ አታስጨንቂኝ ይለኛል ዙበይር፡፡
.....እኔም እምባየን በክሪሜ አበስ አድርጌ >>>>>> ዙበይር እኔ ለአንተ አልሆንህም ሌላ ፈልግ እኔ አንተን ባገባህ ደስ ይለኝ ነበር ግን ....ብየ ልቀጥል ስል
.......ሂክማ አሁን ያለነዉ ዛሬ ጋር ነዉ ሁሉንም ፊርዱ አስረድታኛለች ......እምባሺን ጥረጊ ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ በእጁ እምባየን ጠረገልኝ......አይን አይኔን እያየ ሂኩ ብቻ ዉደጅኝ አንቺን ማጣት አልፈልግም
ዛሬ ቁርጤን ንገሪኝ ሂክማ እኔ እወድሻለሁ..እኔ እስከማንነትሽ ተቀብየ አንቺ ጋር ጥሩ የፍቅርሽ ተካፋይ የትዳር አጋሪ ልትሆኝ ዝግጁ ነሽ ???...የአንቺን ልብሽ ዉስጥ ያለዉን ስለ እኔ ያለሽን ስሜት ንገሪኝ ...ዛሬ ዉሳኔሽን አሳዉቂኝ አለኝ....

ሂክማ የመጨረሻ ዉሳኔ ትሰጣለች ምን ትወስን ይሆን ?? በሚቀጥለዉ ክፍል እናያለን

#part
232 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:21 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

እኔም ቀጥታ ወደ ቤት ሄድኩኝ.......እቤቴም ደረስኩኝ ዙበይር ሲደዉልልኝ ስልክ አላነሳሁም ነበር....መልሳ ፊርዶስም ደወለች ግን ለእሷም ማንሳት አልፈለኩም መረጋጋት ስላለብኝ እንባየን ጠረኩኝ እና እቤቴ ቁርአኔን ቀርቼ ኢሻን ሰግጄ ተኛሁኝ፡፡ ከሱብሂ ቡሀላ ትንሽ ጋደም እንዳልኩኝ ጠዋት ላይ የፊርዶስ ስልክ ተደወለ ግን ማንሳቱን ፈራሁ ለምን ማታ ወንድሟን አስቀይሜዋለሁ.......ከአሁን ቡሀላ ከእኔ ተስፋ ቁረጥ ብየዋለሁ ግን እኔ ዙበይር ጠልቸዉ አይደለም በፊት የሰራሁት ስራ እኔን የበታች አርጌ ስለማይ እንጂ......
ለፊርዶስ ደግሞ እንደነገራት እርግጠኛ ነኝ ለምን ለእሷ ምንም ነገር አይደብቃትም ....ፊርዶስ ደግማ ስደዉል ...አላስችለኝ አለ ለምን ፊርዶስ የኔ ምርጥ ጓደኛየ ባለዉለታየ ሀሳቤን ያካፈልኳት የሀሳቤ ተካፋየ ነች...ከዛም ስልኩን አነሳሁት ሰላማታ ከተለዋወጥን ቡሀላ
.... ፊርዶስ እየቀለደች አሁን ስልክ አላነሳም ያልሽኝ እቤትሽ አካባቢ መሆኔን አይተሽኝ ነዉ እንዴ ??አለችኝ
እኔም ወላሂ በይ ሰፈራችን መጥተሻል እንዴ?? አልኳት
....እሷም እኔ ግቢያችሁ በር ላይ ነኝ መቆርቆሩ ደብሮኝ ነዉ መጥተሽ ክፈችልኝ አለችኝ
...እኔም ምንም ጊዜ ሳልፈጅ ሂጄ የግቢዉን በር ስከፍተዉ ፊርዶስ ቁማለች ...ከዛ የተራራቁ ዘመዶች ይመስል ተቃቀፍን ወደ ቤት ገባን እናቴ ጋር ሰላም ከተባባሉ ቡሀላ ቁርስ አልበላሁም ነበር እናቴ ቁርስ አዘጋጅታ አብረን በላን...

ቁርስ በልተን ከጨረስን ቡሀላ እናቴ ወደ ዉጭ ስትወጣ ፊርዱም እየቀለደች ትናንት የት ለመድረስ ነዉ ያን ያህል እሩጫ?? እኔ ደግሞ ሂክማ የመቶ ሜትር ሩጫ አለባት እንዴ?? መቼም አንደኛ ወጥተሽ ተሸልመሽ እንደሆነ ሽልማቱን ለማየት ነዉ የመጣሁት አለችኝ እየቀለደች፡፡
ወይ ፊርዶስ ቀልዷ በጣም አሳቀኝ እኔ የጠበኩት ለምን ዙበይርን እንደዛ ጥለሽዉ ተናግረሽዉ ትሄጃለሽ ብላ የምትቆጣኝ መስሎኝ አይኗን ለማየት እየፈራሁ ነበር፡፡ እኔም ሳቅ ብየ ዝም አልኳት ጥሩም ክፉም አልተናገርኩም.....መቼም ዙበይር እንደሚነግራት አልጠራጠርም...

ፊርዶስም ሂክማ አንቺም እህቴ ነሽ ክፉሽን አልወድም ጥሩሽን ነዉ የምወደዉ...ዙበይር ወንድሜ ነዉ የእሱንም ክፉንም አልወድም ስለሆነም ትናንት የተፈጠረዉን ነገር ነግሮኛል ...የአንቺን ጉዳት አቃለሁ እሱ ደግሞ አንቺን ወዶሻል በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ከአንቺ በላይ እንደሚጎዳ ነዉ የሚታየኝ ወንድሜ ደግሞ በፍቅር ሲንገላታ ሲያለቅስ ማየት አልፈልግም ....አንቺን መዉደዱን እንኳን እናቴ ታቃለች ዙበይር በህልሙም ሂክማ ሲል ነዉ የሚያድረዉ፡፡ እናቴ ለምን አታገባም?? ብላ ጠይቀዋለች ..
....መስመር ላይ ነኝ ዱአ አድርጊልኝ ነዉ ሁሌ መልሱ ፡፡ እናቴም ቀን በቀን ስትጠይቀዉ አንቺን እንደሚወድ እና አንቺን ማግባት እንደሚፈልግ ነግሯታል፡፡ የትናንትናዉ የምሳ ግብዣ እናቴ ሂክማን ማወቅ አለብኝ አንቺን ለማወቅ ጓጉታ ሂክማን አስተዋዉቂኝ የወደፊት የልጄን ሚስት ብላኝነዉ..ስለሆነም አንቺም ወንድሜን ተረጂዉ እየወደደሽ አንቺን ቢያጣ አሁን ባለበት ሁኔታ ወንድሜ ሰዉ አይሆንም፡፡ ለወንድሜ እኔ እመሰክርለታለሁ ሴትን ልጅ ቀጥ ብሎ የማያይ ዲን ያለዉ ሰዉ አክባሪ ነዉ ..ስለሆነም ሁለታችሁም ተግባቡ ሂክማ ...አላህ ፅፎላችሁ ይሆናል ስለሆነም ወንድሜ ጋር አብራችሁ ብትኖሩ ደስ ይለኛል አንቺ ለኔ የልብ ጓደኛየ ለወንድሜ ደግሞ የትዳር አጋሩ ስትሆኝ ደስ አይልም እንዴ አለችኝ፡፡

ደግሞ ስለአለፈዉ ማንነትሽ ያቃል ስነግረዉ አዝኖ የብስ ፍቁሩ ጨመረበት ሂክማ አለችኝ.......

ካልደበረሽ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ሂኩ?? አለችኝ..
.....እኔም እሺ ጠይቂኝ አልኳት
...በእስከአሁኑ ቆይታችሁ ዙበይርን ትወጅዋለሽ አትወጅዉም ???አለችኝ
......እኔም የምመልሰዉ አጣሁ በእርግጥ ዙበይርን ወድጀዋለሁ ግን ለወደፊት አብረን የምንሆን ስለማይመስለኝ እሱን ልርቅ ወስኛለሁ ለምን በሀይደር የሴትነቴን ክብር አጥቻለሁ በዙበይር ደግሞ ሁለተኛ ፍቅር በሚባል መጎዳት አልፈልግም ብየ ወስኛለሁ፡፡
.....ፊርዶስም መልሽልኝ እንጂ አለችኝ
........እኔም አዎ እወድዋለሁ ግን....ስል ወሬየን አቋረጠችኝ

ሰባራ ነው ልቤ~

በፍጹም ቅንነት ከልብህ ቀርበኸኝ
የ ሃሳብ ተካፋይ እህትህ አድርገኸኝ
የሆዴን ብሶት በዝርዝር ስነግርህ
ቁስልህ ስለሆነ ቁስሌ አመመህ
ብዙ አይነት ፈተና ቢፈራረቅብኝም
ያን ሁሉ መከራ ችየ አሳልፌም
ግማሹን ታሪኬን በአፌ ስነግርህ
ያለፍኩትን ዘመን ዳስሼ ሳወራህ
ድንገት ሳላስበው ብሶት አስለቀሰኝ
መሆኑ ሳይገባህ በአንተ ህይወት ውስጥ እራሴን አጊቼ
አብሽሪ አልከኝ ማልቀሴ ቢመስልህ ላንተ ተከፍቼ
በጥርሴ ደብቄ የያስኩት ሚስጥር
ታሪኬ ሰፊ ነዉ ገብቶ ሲመዘብር
ያለፍኩትን ህይወት ብነግርህ በዝርዝር
እንዴት እንደሆነ ሰውን አምኖ ማጣት
ቁልጭ ብሎ ታየኝ የልቤ ስብራት
የኔ ነገር ብዙ ነው አንዴ ላጫውትህ
ያንጀቴን የሆዴን ውስጤን ልንገርህ
እናትና እህትህ ባለቤት ልሁንህ
ሰባራውን ልቤን ከሰባራው ልብህ ልገጣጥመውና
አንተም በኔ ድነህ እኔም ልሁን ደህና
ሃሳቤን ዘርዝሬ ልነግርህ አልኩና
ተመልሼ ተውኩት ደግሞ ፈራሁና
ምን አልባት ምን አልባት ህልሜ ይከሽፍና
ማገገሚያ ባጣስ በሰባራው ልቤ ዳግም እጎዳና

.......እኔ የምፈልገዉ እሱን መዉደድሽን ብቻ ነዉ ..ሌላ ምክንያት አልፈልግም አለችኝ...

ከተመቸሽ ዛሬ የምንሄድበት ቦታ አለኝ ፍቃደኛ ከሆንሽ እቤት ስራ ከሌለሽ እንሄድ አለችኝ....እኔም እሺ አልኳት

#part
196 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:21 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

ከፊርዶስ ጓደኛ ከሂክማ የበለጠ ቆንጆ አዲስ አበባ ብፈልግ አታገኝም ብለዉ ሁሉም ሲስቁ ነገሮች ሁሉ እኔን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡

ከዛም ምሳ በልተን ጨረስን ግን ሌሎቹን ሁለቱን የፊርዶስ ወንድሞች እቤት የሉም፡፡ ይሄ program ለኔ እና ለዙበይር በዛዉም እናቲቱ እኔን እንዲያቁኝ የተዘጋጀ ዝግጅት መሰለኝ፡፡
እስከ አሱር ድረስ እነሱ ቤት ፊርዶስ እና እናቷ ጋር እየተጨዋወትን ቆየን፡፡ አሱር እነሱ ቤት ሰግደን ወደ ቤት ልሂድ ተነሳሁ.... ላደረጉልኝ የምሳ ግብዣ አላህ ይስጥልኝ ብየ ከቤት ልወጣ ስል ..... የዙበይር እና ወይዘሮ ዚነት ልጄ እስኪ አንድ ጊዜ ከመኝታ ክፍል እቃ ይዤ ልምጣ ጠብቂኝ ብለዉ ወደ መኝታ ክፍል ገቡ
እኔም እሺ አልኩኝ
.....ማዘር መጡ የሚያምር አበያ ሰጡኝ ልጄ ልበሽዉ የልጄ ፊርዶስ ጓደኛ አይደለሽ በትንሹም ቢሆን ማስታወሻ ይሁን ይሄን አበያ ባየሽ ቁጥር እኔን እያስታወሽ ዱአ እንድታረጊኝ እና መጥተሽ እንድዘይሪኝ እፈልጋለሁ እኔ ከአንቺ ዝምድናዉን እፈልጋለሁ ብለዉ ግንባሬን ሳሙኝ፡፡
እኔም ማዘር አመሰግናለሁ ብየ ተቃቅፈን ተለያየን ፡፡ ፊርዶስ እና ዙበይር እኔን ሊሸኙኝ አብረዉ ከእነሱ ቤት ወጥተን ጉዟችንን ጀመርን ..

እያወራን እየተጠዋወትን እየሄድን ፊርዶስ አንድ የምታቃት ልጅ አግኝታ አሰላሙ አለይኩም ተባብለዉ ተዘያየሩ እዛዉ ቁመዉ ማዉራት ጀመሩ፡፡
ፊርዱ እደርስባችሇለሁ እየሄዴችሁ ጠብቁኝ ከምቆሙ አለችን ፡፡ እኔና ዙበይር ብቻ ሁነን ወደ ፊት ጉዟችንን ቀጠልን ከአሁን አሁን ፊርዱ ትመጣለች ብየ ብዞር እዛዉ ቁማለች እርምጃ በተራመድን ቁጥር ፊርዶስን እየራቅናት መጣን እኔ እና ዙበይር ብቻችንን ሆንን ፡፡ ዙበይርን ወድጀዋለሁ ግን የበፊት ማንነቴ ያስፈራኛል ....እሱም እንደሚወደኝ አዉቃለሁ ግን ዉዴታ ሙሉ የሚሆነዉ አብሮ በትዳር መዝለቅ ሲቻል ነዉ፡፡ ብቻ እኔም ቀጥ ስል አይን ለአይን እንጋጫለን ሁለታችንም አንገታችንን እንደፋለን፡፡

ዙበይር የዝምታዉን ድልድይ ለመስበር እየታገለ ነዉ........ሂክማ ተጨዋቺ ወሬ አምጪ ፊርዶስ እንደሆነች ወሬዋን ከጓደኛዋ ጋር እያወራች ነዉ፡፡ በጣም ከእሷ ርቀት አለን የምመጣ አይመስልም አለኝ፡፡
......እኔም እሺ እጫወታለሁ እልኩት
.........ምሳ እንዴት ነበር??? አለኝ
.............አሪፍ ነበር ጀዛከሏህ አለኩት
አንድ አንድ እያልን በወሬ ተግባባን፡፡ ግን በመጨረሻ ከበድ ያለ ጥያቄ ጠየቀኝ፡፡ ሂክማ ግን ሰለፍቅር ምን ታስቢያለሸ ????አለኝ .....
....ይህን ንግግሩን ስሰማ በጣም ደነገጥኩ የምመልሰዉ ግራ ገባኝ፡፡ ዝም አልኩኝ
.......ሂክማ ምነዉ የማይጠየቅ ጥያቄ ጠየኩሽ እንዴ??? አለኝ
...... አኔም ካላስቸገርኩህ የጠየከኝ መጀመሪያ አንተ ነህ ግን ይህን ጥያቄ አንተ መልስልኝ ስለፍቅር ምን ታስባለህ ???መልስልኝ እና እኔም መልስ እሰጥለሁ አልኩት፡፡
----------------እሱም ፍቅር ሳፈልጊዉ ጊዜ ሰአት ቦታ ሳይል የሚይዝ ነዉ:: ግን ችግሩ ያፈቀረዉ ሰዉ እንዴት እንደሚወድ ለተፈቃሪዉ ግልፅ አለመሆኑ ነዉ; እኔ የወደድኩትን ያፈቀርኩትን የመጀመሪያየ የሆነችዉን ልጅ እስከ ሂወት አጋሬ የልጆቼ እናት ብትሆን ደስ ይለኛል ....አንቺሰ ምን ታስቢያለሽ???? አለኝ
ሀይደር ጋር ያሳለፍኩት ያጠባሳ ጊዜ ትዝ አለኝ፡፡
........ከዛም ዙበይር እኔ ለፍቅር ወንድን የምቀበልበት ልቤ ዉስጥ የማስቀምጥበት ቦታ በጣም ተጎድቷል አልኩት፡፡ አንተንም የቀረብኩህ የፊርዶስ ወንድም ስለሆንክ ነዉ፡፡ አንተ ለኔ የጓደኛየ ወንድም ነህ ከዚህ ዉጭ እኔ ብዙ ያለፉ ሂወቶች የተበላሹ ማንነቶች አሉኝ እኔ ለእንደ አንተ አይነት ጥሩ ወንዶች አልገባም አልኩት፡፡ ምንም አማራጭ የለኝም እየፈለኩት የማጣት አይነት ስሜት ይሰማኛል፡፡
........ዙበይርም እኔ እስከዛሬ ደበኩት ግን መደበቄ ለኔ እንቅልፍ ነሳኝ ዛሬ ለአንቺ ልነግርሽ ዝግጁ ነኝ ሂክማ ይህን ስነግርሽ ከኔ ላትርቂ ላትሸሺ ቃል ግቢልኝ፡፡ ሂክማ እወድሻለሁ አንቺን አጥቼ መኖር አልፈልግም እባክሽ ተረጂኝ እና ቀጥታ ወደ ትዳር እንግባ አግብቼሽ የወደፊት ሚስቴ እንድትሆኝ እፈልጋለሁ ከአንቺ ልጆች መዉለድ እፈልጋለሁ፡፡የዛሬዉ ምሳ እናቴ የወደፊት እጮኛህን አስተዋዉቀኝ እያለች ስረብሸኝ አንቺን ስለመረጥኩ ነዉ ምሳዉ እናቴ ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ ነዉ ......አለኝ አንገቱን ደፍቶ

እኔም ዝም ብየ አንገቴን ደፍቼ የሚለኝን እየሰማሁ ነዉ ዙበይር በእድሜም እኔን ቢበልጠኝ ሶስት አመት ነዉ ከዚህ በላይ አይበልጠኝም በጣም አይናፋር ሲሆን ስራዉም መርካቶ ላይ ደርዘን ልብስ ማከፋፈል ነበር፡፡ ግን እኔ ዙበይርን ማግባት አልችልም ለምን ቢጠይቀኝ መልስ የለኝም፡፡ እኔም አንገቴን እንደ ደፋሁ እንባየ ይወርድ ጀመር
....ዙበይርም ደነገጠ
እንዴ በነገርኩሽ ነገር አስከፋሁሽ እንዴ ???እኔም ተቸግሬ ነዉ ሂክማ እንድታለቅሺ ሳይሆን እንድትረጂኝ ነዉ ፡፡
--------------እኔም ዙበይር ሌላ ፈልግ እኔ ለትዳር አልሆንህም .....እኔ እና አንተ አንድ ላይ መኖር አንችልም ብየ ከእሱ በተቻለኝ አቅም እየሮጥኩ ሄድኩኝ

.....ዙበይርም ሂክማ እያለ ሲከተለኝ፡፡ ዘወር ብየ እንዳትከተለኝ ብየ ተቆጣሁት..ዙበይርም ባለበት እንባዉ እየወረደ ቁሞ ቀረ.....

#እንዲህ #አድርጎኛል
ተፃፈ በ ዘ አዶኒ

ፍቅርሽ እያቃዠ እንቅልፍ ያሳጣኛል
ከእህል ከውሃ ጋር ዘወትር ያጣላኛል
ሆዴን ባርባር እያለ ደርሶ ይጨንቀኛል
በዓለም ለብቻዬ የተተውኩ ይመስለኛል

በውድቅት ሰዓት ከቤት እወጣለው
ፍቅርሽን ፍለጋ ሌሊቱን እሄዳለው
ተጉዤ ሲደክመኝ ኮከብ እቆጥራለው
ለጨረቃ ሳልፈራ የሆዴን እነግራታለው
ጉልበቴን አዝሎ አቅም ነስቶኛል
ቅስሜን ሰባብሮ ወኔ አሳጥቶኛል
የፍቅር ቅጣት ህመሙ መሪር ነው
መጨረሻው ካማረ ሁሉም ለበጎ ነው

ግና እፈራለው ብኩን ሆኜ እንዳልቀር
አይሰምርም ይባላል የአንድ ወገን ፍቅር
ብቻ አለው ዛሬም እኔ እንዳለሁኝ
ህመሜን አይቶ ማንም ሳይጠይቀኝ
የሆንኩትን ሁሉ መግለፅ ቸግሮኛል
ፍቅርሽ በጥቂቱ እንዲህ አድርጎኛል፡፡
#part
184 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:21 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

ስልኩን አነሳሁት የወንድ ድምፅ ነዉ፡፡ ድምፁም የማቀዉ ድምፅ ነዉ፡፡ ስልኩን እንደያዝኩት ደንግጬ ቆምኩ...የደወለልኝ. ዙበይር ነዉ
አሰላሙ አለይኩም
....እኔም ወአለይኩም ሰላም አልኩት
...እንዴትነሽ.... እንዴትነህ ከተባባልን ቡሀላ በሰላም ነዉ መደወሉ?? አልኩት
...መደወል አይቻልም እንዴ ??ስልክሽን ከእህቴ ፊርዶስ ነዉ የተቀበልኩት አለኝ.... አንዳንድ ወሬ አዉርተን ብዙም በስልክ በወሬ ሳንቆይ ቻዉ ተባብለን ስልኩን ዘጋሁት፡፡
ዙበይር በኔ ፍቅር ወድቋል ከንግግሩ ያስታዉቃል በጣም ደንግጧል፡፡
ዙበይር በሂክማ ፍቅር ወድቋል ግን እስከ ማንነቷ ይቀበላት ይሆን ????
#ናፍቆት .
ናፍቀሽኛል ብዬ ቃላት እያወጣሁ
ናፍቆቴን ለመግለፅ ለናፍቆት ቃል አጣሁ
ገና ናፍቀሽኛል ብዬ ሳልጀምረው
ተሰማኝ ናፍቆትሽ ውስጤን ሲያሸብረው
እኔ የፍሬ ናፍቆት ፣ አንቺ የጥበብ ሸማ
ሲመታ አዳምጪው ያን የልቤ ዜማ
በናፍቆት አለንጋ
ደምቶ የማይረጋ
ብዙ ቅኔ ያለው ናፍቆት ሞልቶት ልቤን
ናፈቅሽኝ እላለሁ ላይገልፀው የውስጤን
የመናፈቄን ጥግ የጉጉቴን መጠን
የመውደዴን አቅም የናፍቆት ወሰን
ድንበሩን ለማየት መግለጥ ያሻው ዶሴ
ከምን ደርሶ እንደሆን ይለካ እስትንፋሴ ።

ዙበይር እንዴት ሊደዉልልኝ ቻለ???? ለፊርዶስ ሂወቴን ከላይ እስከታች ነግሪያት እንዴት ስልኬን ሰጠችዉ ????እያልኩ ተወዘገብኩ፡፡ የማይነጋ የለም ነጋ ፊርዶስ ጋር ተገናኘን ከዛ ስለማታዉ ጉዳይ ዙበይር ደዉሎልኛል ብየ ከነገርኳት ቡሀላ .... እንዴት ለወንድምሽ የኔ ቁጥር ትሰጫለሽ??? ሂወቴን አጫዉቸሽ ነግሬሽ ወንድምሽ እኔን እንዲረሳ ማረግ ሲገባሽ ..ይባስ ብለሽ ስልክ ቁጥሬን ሰጠሽዉ ፊርዱ ጥሩ መስሎ አይታየኝም አልኳት፡፡
....ፊርዱም በመቆጣት ከአሁን ቡሀላ ስለ አለፈዉ ሂወትሽ ነግረሽኛል ተረድቸሻለሁ ጨዋና እና ሬድዮ ወሬ አይደጋግምም አይደል የሚባለዉ ..ወደ አላህ ተመልሰሻል ያለፈዉ አልፏል አሁን ያለነዉ ዛሬ ላይ ነን፡፡ አንድ ሰዉ ትናንት ያየዉን ህልም ዛሬ ላይ መድገም አይችልም ፡፡ ሂኩ ከአሁን ቡሀላ ያለፈ ሂወት ብታነሽብኝ የምወድሽን ያህል እጠላሻለሁ፡፡ አንቺ ለኔም ለወንድሜም ለማንም ሰዉ ወንጀለኛ መጥፎ ሰዉ አይደለሽም እንደዉም ጠንካራ ጎበዝ ነሽ ፡፡ ሲደዉልልሽ ፊት አትንሽዉ ዙበይር ወንድሜ አንቺም እንደ እህቴም እንደ ጓደኛየም የማይሽ ነሽ ሁለታችሁም እንድትጎዱ አልፈልግም አለችኝ፡፡
.....እኔም እሺ ከአሁን ቡሀላ ያለፈ ሂወቴን ላነሳ ብየ ፊርዱ አንገት ስር ጥምጥም ብየ አለቀስኩኝ፡፡

ዙበይር ጋር በስልክ ሲደዉልልኝ ማዉራት ጀመረን ዙበይር እንደሚወደኝ አቃለሁ እኔም ትንሽ ለዙበይር ከሌሎቹ ወንዶች ለየት ያለ አመለካከት አለኝ፡፡ ግን ያንን ጥያቄ ቢጠይቀኝ ምን እንደምመልስ አላቅም.... ግን ፊረዱ ያለፈዉ አልፏል አሁን ወደፊት እሰቢ ብላ አስጠንቅቃኛለች፡፡ ዙበይር እንደሀይደር ወደድኩሽ አበድኩልሽ ሳይሆን የጨዋ ወንድ አነጋገር ነበር የምናወራዉ፡፡እያደር ግን ስልክ አዉርተን ስንጨርስ ሂኩ እንደምወድሸ እንዳረሺ ማለት ጀምሯል፡፡ እኔም አረሳም ብየ እጥር ያለ መልስ እመልስለታለሁ፡፡
,
አንድ ቀን ፊርዶስ እሁድ ምሳ እኛ ቤት ጋብዠሻለሁ አንቺ እናትሽን አስተዋወቀሽኛል እናትሽ እኔን የምታየኝ እንደ ልጇ ነዉ ፡፡ እኔ እኮ አላስተዋወኩሽም አለችኝ፡፡
እናም እሁድ ምሳ ጋብዠሻለሁ ቤታችንን ስለማታቂዉ አብረን እንሄዳለን አለችኝ
፡፡ እኔም እሺ ከማለት ዉጭ ምንም አላልኩም፡፡


እሁድ ደረሰ ፊርዶስ እኛ ቤት መጥታ አብረን ወደ እነሱ ቤት ወደ ጎሮ ሰፈር ሔድን ፡፡ ቤታቸዉ ደረስን ቤታቸዉ በጣም ያምራል አባቷ ነጋዴ ነዉ፡፡ ከዟም እናቷ ወይዘሮ ዚነትን አስተዋወቀችኝ ተነስተዉ ጉንጬን ሳሙኝ
... ሂክማ እኔ ልጄን ፊርዶስን በአሳታዋይነቷ በጣም እወደታለሁ ደግሞ ፊርዶስ አንቺን ትወድሻለች ልጄ የወደደችዉን እኔም እወዳለሁ በአካል ዛሬ ስላወኩሽ ደስ ብሎኛል ፡፡ ደግሞም ቆንጅየ ነሽ ማሻ አላህ ብያለሁ አሉኝ ወይዘሮ ዚነት፡፡ እኔም አመሰግናለሁ ማዘር ብየ ግንባሬን ሳሙኝ፡፡ ምሳዉ በጣም ለየት ያለ ዝግጅት ነበር ምሳዉ ቀረበ

--------- ከዉጭ አሰላሙ አይኩም የሚል ድምፅ ሰማሁ ከዛም ወደ ቤት ገባ ፡፡ ወአለይኩም ሰላም ምሳ ላይ ደርሰሀል ና ምሳ ብላ አሉት እናቱ
......እሱም እሺ ብሎ ታጥቦ እኛ ጋር ቀረበ ...እናቱም መቼ ይሆን አንተ ጎጆ መስርተህ ምሳ የምጠራን ዙበይር አሉት
.....ዙበይርም እማየ ዱአ አድርጊ መስመር ላይ ነኝ አላህ ያሳካልህ ብለሽ አላት እናቱን....
ፊርዶስም ከአፉ ቀበል አድርጋ እንዴ ትገርማለህ እኔ የማላቃት ያላስተዋወከኝ ከእህትህ ደብቀህ ያመጠሀት ሚስትማ እኔ አልስማማም አለች ፊርዱ
....ዙበይርም ከአንቺማ ምንም አይደበቅ ፊርዱ እኔ እኮ ታናሽ እህቴም ብትሆኝ አከብርሻለሁ አንቺ የወደድሽዉን ነዉ የምወደዉ አላት ለፊርዶስ፡፡

ወሬዉ እናታቸዉ ዙበይር ፊርዶስ እየተቀባበሉ ስለትዳር ነዉ የሚያወሩት እኔም የሚሉትን ሳዳምጥ ነገሮች ሁሉ ወደ እኔ ያመላከቱ መሰለኝ፡፡ እናቲቱ ማብቂያ ላይ ያሉት ንግግር ገረሞኛል መቼም ከፊርዶስ ጓደኛ ከሂክማ የበለጠ ቆንጆ በሸገር ብትፈልግ አታገኝም ብለዉ ሁሉም ሲስቁ ነገሮች ሁሉ እኔን እንደሆነ ጠረጠርኩ፡፡ዙበይር እና ፊርዶስ እኔ እና ዙበይር ለወደፊት አብረን ለመኖር መስመር እንደጀመርን እናታቸዉ ቅድምያ ነግረዋቸዋል ማለት ነዉ ?? ይሄ ነገር ባይሳካስ?? ለእናታቸዉ ተናግረዉ ይሆን እንዴ ???እያልኩ እዛዉ እነሱ መሀል ቁጭ ብየ በሀሳብ አለም ዉስጥ ተጓዝኩኝ....

#part ይቀጥላል
170 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:57:20 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

እኔ ከተቀመኩበት ስነሳ ፊርዶስ አብራኝ ተነስታ .......
እንባየን ከጉንጬ እየጠረገች ሂኩየ አንቺኮ አሁንም ንፁህ ሰዉ ነሽ ወንጀል ሸይጧን አሳስቶሽ ልሰሪ ትችያለሽ ግን ወደአላህ ተመልሰሽ ማረኝ እያልሽ እያለቀሽ ነዉ፡፡ አላህ መሀሪ ነዉ የወንጀል ጉዳቱ ወንጀል መሆኑን እያወቁ እዛዉ ያለተዉበት በዛዉ ወንጀል ላይ ሁኖ ሳይቶብት መቼ እንደምንሞት ሳናቅ ዛሬ ወይ ነገ እቶብታለሁ እያልን ወይም ሀዲስ ስንሰማ መስጊድ ስንገባ ደአዋ ስናዳምጥ አልቅሰን ወንጀሎኞች ነን ከአሁን ቡሀላ ወደ ወንጀል አልሄድም ብለን እንቶብታለን ግን ወይ ከመስጊድ ስንወጣ ወይ ደአዋዉ ሲያልቅ የቶበትነዉን እንረሳዉና ወደ እዛ ወንጀል እንሄዳለን ይሄ አይነት ደግሞ መቶበት ሳይሆን በራስ ጭንቅላት ላይ ጌም እንደመጨዋት ነዉ...አሁን ብዙ ሰዉ ጋር የሚታየዉ ጥርት ያለ ተዉበት ሳያረጉ መሞታቸው ነዉ፡፡
........ሂኩየ አንቺ ከእነዚህ ሰዎች ትለያለሽ ወንጀል ሰርተሽ ወደ አላህ ነዉ እያለቀሽ ያለሽዉ እንጂ ወንጀል አብራችሁ ወደ ሰራሽዉ ሰዉ አይደለም ስንት እህቶቻችን ይህን ወንጀል ሰርተዉ ወንጀል ከሰሩት ሰዉ ጋር ተጣብቀዉ አንተዉ ቅብረኝ እሞታለሁ መርዝ እጠጣለሁ የሚሉ የፈጠራቸዉን ጌታ የረሱ አሉ አይደል፡፡ አንቺ እኮ የምታለቅሽዉ ወደ ፈጠረሽ ጌታ ወደ አላህ እንጂ ወደ ሀይደር አይደለም ስለሆነም አንቺ ከሌሎቹ ሴቶች ልዩ ነሽ፡፡
ከቦታና ከ አቅጣጫ ጥራት የተገባዉ አላህ ጌታችን እንዲህ ይላል፦ የባሮችን ጉዳይ ተውልኝ እስኪ ከነሱ ወደኔ የተመለሰ (የተፀፀተ) እኔ ወዳጁ ነኝ። እኔኮ እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ ለባሮቼ አዛኝ ነኝ። ብሏል። ሂኩየ ፡፡ ስለሆነም ከአሁን ቡሀላ የአንቺን ለቅሶ ሳይሆን የምፈልገዉ ደስታሽን ነዉ ሂኩየ አንቺ ከአሁን ቡሀላ የረከሽ ወንጀለኛ አይደለሽም ልታለቅሺ ሳይሆን.... የባሰ አለ ብለሽ ልታመሰግኚ ነዉ የሚገባዉ አንቺ ልታለቅሺ አይገባም አላህ መሀሪ አዛኝ የሆነ ጌታ ነዉ ብላ አንገቴ ስር ጥምጥም አለችብኝ፡፡ ከዛም ወደ ቤቴ ልሂድ ብላኝ ሸኝቻት ተመለስኩኝ፡፡

ዉይ ለፊርዶስ ከነገርኳት ቡሀላ ይህ ሚስጥር ተሸክሜዉ እንዳታሳርፊ የተባልኩ ይመስል አፍኘዉ ኑሮ ቅልል አለኝ ፡፡ ዲፕሬሽን ዉስጥ ነበርኩ አንድ ሰዉ ዲፕሬሽን ዉስጥ ከሆነ መፍትሄ ይሰጠኛል ብሎ የሚያማክረዉ ሰዉ ከነገረዉ 50% ከዲፕሬሽን ይላቀቃል፡፡ የሆነ የደስታ ስሜት ተሰማኝ

ማታ ላይ ልተኛ ስል ፊርዶስ ደዉላልኝ በቃ በደስታ አወረሇት ..
.....እሷም ሂኩ ምን ተገኘ ደስተኛ ሁነሻል ??? ስትለኝ
......ምንም አልተገኘ ግን ቅልል ብሎኛል የደስታ ስሜት ተሰማኝ አልኳት ፡፡ ብዙ ነገሮችን አወራን ስንጨርስ በስልክ ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ
ለመጀመሪያ ጊዜ ሳልጨናነቅ ደስተኛ ሁኜ አደርኩ፡፡ የመጀመሪያ የደስታ ሂወት የጀመርኩ ይመስለኛል አልሀምዱሊላህ ተገላገልኩ..... ዙበይር ከአሁን ቡሀላ ተስፋ ይቆርጣል ፊርዶስ እዉነቱን ትነግረዋለች ወደ እኔ በጭራሽ አይደርስም ብየ እራሴን አሳመንኩት፡፡
ሳስበዉ የቸገረን የልባችንን የምነነግረዉ ለአላህ ብለን የምንወደዉ በአላህ መንገድ በዲነል ኢስላም ያገኘነዉ ጓደኛ ነዉ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ አንድ የልብ ጓደኛ ያስፈልገዋል በደስታዉም በሀዘኑም ከጎኑ የሚሆን ሀሳብ ሲያስብ የማያማክረዉ በሀሳቡ ገንቢ አስተያየት መስጠት የሚችለዉ ሰዉ ለሌላ ሰዉ መድሀኒት ነዉ ፡፡ ተማክረዉ የፈሱት ፈስ አይሸትም አይደል የሚባለዉ የልብ ጓደኛ ወሳኝ ነዉ፡፡ ጓደኛ ማለት በክፉም በደስታም በሀዘንም አብሮ መግባባት ሲቻል ነዉ፡፡ መጠንቀቅ ያለብን ሴቶች ማንኛዉም ነገር እስከ ዚና መስራት ወንጀል ድረስ የሴት ጓደኛ ተፅእኖ ግፊት ነዉ ጥሩ ሴቶች እየተበላሹ ያሉት በመጥፎ ሴቶች ጓደኛ ይዘዉ ነዉ፡፡
የአሁን ጓደኝነት ስታማክረዉ ወይ ሚስጥርህን ለሌላ ያሳልፈዋል ወይም በቀኝ ጆሮዉ አዳምጦ በግራ ጆሮዉ ያፈሰዋል፡፡ .የቱርክ ልብስ ማን ልበሺ አለሽ?? ጓደኛየ....የያሽዉ የወንድ ጓደኛ ማን አስተዋወቀሽ?? ጓደኛየ...ሶላት አልሰገድሽም የት ነበርሽ?? ጓደኛየ ቤት....ሜካፕ ሊፒስቲክ ኮስሞቲክስ ማን እንድትቀቢ አስለመደሽ ???ጓደኛየ.......ዚና እንድሰሪ ማን አስተዋወቀሽ ???ጓደኛየ...ነዉ መልሳችን፡፡ አሁን የያሽዉ የሴት ጓደኞችሽ ከስንት አንድ ካልሆነ ከነዚህ ዉጭ ያሉት ብዙዎቹ ሴቶች የሚሸወዱት የሚበላሹት በሚይዙት የሴት ጓደኛ ስበብ እንደሆነ መገንዘብ አለብን፡፡
ሴትን ለሴት እሾህን ለሾህ አይደል የሚባለዉ በጓደኛ አመራረጥ ቢያንስ እንደፊርዶስ አይነት ጓደኛ መያዝ መቻል አለብን፡፡
አሁን ላይ ትዉልዱ ከቤተሰብ ቁጥጥር ዉጭ ሁነናል ጊዜዉ የተራቀቀ ነዉ በፊት ቤተሰብ ይቆጣጠረን ነበር አሁን ግን በስልክ ሁኗል ስራዉ በስልክ ያልቃል ወንጀል ለመፈፀም አንቺ እሱ እና ጌታሽ ብቻ የሚያቃቸዉ ብዙ የዚና መስሪያ ቦታዎች ምን ይሰራ ማን ይግባ ማን ይዉጣ የማይታይበት የወንጀል መስሪያ ቦታዎች በሁላችንም የመኖሪያ ሰፈሮች ቦታዎች እናገኛለን ፡፡ የሂክማ ነገር አላለቀም
#እስኪ #ፈገግ #እንበል
.....አንዷ ሁሌ ላይብረሪ እያለች ትሄዳለች አቧቱ ሲጠይቃት ሁሌ ላይብረሪ እያለች ስታስቸግር ..አንድ ቀን አባቷ ማታ ስትመጣ በብትር ይገርፋታል የት ነዉ የምትሄጅዉ ??ሲሏት ላይብረሪ ስትል...አባቷ አልተማሩም ነበር ላይም ብረሪ ታችም ብረሪ የሄድሽበትን ብቻ ተናገሪ እንዳሉት አባት ትክክለኛ መሆን መቻል አለብን፡፡
መቼም ቀን በቀን ይፈራረቃል አንድ ቀን ባሳለፍን ቁጥር ወደ ሽምግልና እየሄድን እና ወደ ሞት እየተጠጋን መሆኑን እረስተናል፡፡ እኛ ሞትን ብንረሳም ሞት ግን እኛን አይረሳም፡፡
ካልተሳፈሩበት ቶሎ ተሽቀዳድሞ
ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቁሞ
ተብሏል፡፡ ግን አሁን ጊዜ ሰዉ ታክሲ ተሰልፎ ይጠብቃል እንጂ ታክሲ ተሰልፎ ሰዉ መጠበቅ አቁሟል፡፡ ምን ለማለት ነዉ አንተም አንቺም እሱም እሷም ሞት ቁሞ እየጠበቀን ስለሆነ ጥርት ያለ ተዉበት አድርገን ሞትን እንጠብቀዉ፡፡

ነግቶ ፊርዶስ ጋር ተገናኘን ከበፊቱ በበለጠ ፍካቷ እየጨመረ ለኔ ያላት አመለካከት እየጨመረ ሄደ ፡፡ በቃ ምን ልበላችሁ እስከዛሬ በመደበቄ እኔ ስጨናነቅ እንደኖሩኩ አወኩኝ ቢሆንም አልሀምዱሊላህ አሁንም እፎይ ማለቱ በጣም ደስታ ፈጠረልኝ፡፡
ፊርዶስ እኛ ቤት እየመጣች አንድ ላይ እንሆናለን ፡፡

አንድ ቀን እናቴ ለፊርዶስ ምንድን ነዉ አታገቡም እንዴ ፊርዱ??? ሴት ልጅ ትዳር የሚያምረዉ በልጅነት ነዉ፡፡ እኔ ያገባሁት በ19 አመቴ ነዉ ፡፡ ከሁለት አንዳችሁ አግቡ እና በሰርጋችሁ እንልፋ አለቻት፡፡ ለፊርዶስ
..ፊርዱም ኢንሻ አላህ አይቀርም እኔ የማመቻቸዉ ስላለ ነዉ እንጂ በቤተሰብ የመጣልኝ አለ ታጭቻለሁ ሆነም ቀረ የሂክማ ይቀድማል ተዘጋጂ አለች ሳቅ እያለች

#part 18 ይቀጥላል
157 views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ