Get Mystery Box with random crypto!

ሀላል ትዳር👫💍

የቴሌግራም ቻናል አርማ hayu_abdi — ሀላል ትዳር👫💍
የቴሌግራም ቻናል አርማ hayu_abdi — ሀላል ትዳር👫💍
የሰርጥ አድራሻ: @hayu_abdi
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.54K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-08-06 20:07:41 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

ደብረ ዘይት ደረስን በመኪና እየዞርን አየናት ከዛ ሰአቱም አሱር ደረሰ ሶላታችንን ሰገድን .... ደብረዘይት የሚገኘዉ ባቡጋያ ሪዞርት ወደ እዛ ሄድን፡፡
ባቡጋያ ሪዞርት ደረስን አንድ ላይ ሁነን ሰልፊ ፎቶ ተነሳን በቃ ሁለታችንም ተቅበጠበጥን እየሄድን መሳሳም ፎቶ መነሳት ሆነ .....ከዛም ሂኩ ይህን ሁለት ቀን በጣም ደስተኛ ነኝ አንቺስ አለኝ እኔም አዎ ብየ መለስኩለት...........
........ተቃቀፍን ሳመኝ.....ነይ የማሳይሽ ነገር አለኝ ብሎ ወደ ባቡጋያ ሪዞርት የሚገኘዉ መኝታ ክፍል ይዞኝ ገባ፡፡
ሀይደር ነገሮቹን አመቻችቶ ጨርሷል ፡፡ እመኝታ ክፍል ኬክ አዘጋጅቶ በሁለታችንም ስም የተፃፈበት ኬክ አብረን ቆረስን ......በኬኩ እየተጎራረስን በቃ መደባደብ ጀመርን ኬኩን ሲቀባኝ እኔም ስቀባዉ የሌለ መነካካት ...ምን ልበላችሁ ሰዉ ከሚሰራዉ ነገር ወጣ ያለ ነገር እየሰራን ነዉ...እሱም ልብሱን አወለቀ ...በመቀጠልም የእኔን ልብስ አወለቀዉ፡፡ እምቢ የምልበት ድፍረቱ የለኝም.......
፡.......ሁለተኛዉ የሀራም የስሜቴን እርካታ ሰኞ ከአሱር ቡሀላ እስከ መቅሪብ ድረስ ለወደፊቱ ባሌ ይሆነኛል ብየ የአሰብኩት ሀይደር ጋር በ ባቡጋያ ሪዞርት መኝታ ክፍል.....በሚያስጠላ እንስሳዊ በሆነ ስሜት ትንቅንቅ አደረግን ፡፡ መቅሪብ ላይ ይበቃናል ....እናቴ ምንም የማስፈቅድበት ምክንያት የለኝም ጊዜዉ መሸ ትናንት ስላደረኩ ዛሬ ማደር አልችልም እንዳትቆጣ ወደ አዲስ አበባ እንመለስ አልኩት.......
......እሱም እሺ አለኝ...እቅፉ ዉስጥ እንዳለሁ ..
ሂኩ ምን እንደናፈቀኝ እንደ ቸኮልኩ ታቂያለሽ አለኝ
.......እኔም አረ አላቅም አልኩት
..........እሱም እናትሽ ጋር እስከ መተዋወቅ በጣም ቸኩያለሁ አለኝ
....እኔም ወላሂ በል አልኩት
.........እሱም ወላሂ አለኝ፡፡ አመንኩት በጣም ከስከዛሬዉ በበለጠ መልኩ ወደድኩት......ግን እሱ ጋር ሀራም መስራቴ የአላህን ትእዛዝ መጣሴ ምንም አልመሰለኝም.......
ከመኝታችን ተነስተን ባቡጋያ ሪዞርት ወጥተን
ወደ አዲስ አበባ እየተመለስን ነዉ.....
አዲስ አበባ ደረሰን እቤቴ ገርጂ ድረስ ሸኘኝ ከንፈር ለከንፈር ተሳስመን ተለያየን....እቤቴ እናቴን እንዴት ዋልሽ ብየ ገብቼ የደስታ ስሜት እየተሰማኝ አልጋየ ጋር ጋደም ብየ ስለ ሀይደር ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በጣም ወድጀዋለሁ ለእሱ የሴትነት ክብሬን ማስረከቤ እንደ ክብር እንጂ ወንጀል መስሎ አልታየኝም......የሰጠኝን የጣት ቀለበት እያየሁ ደስተኛ ሁኛለሁ፡፡

በቃ እወድሀለሁ
——————
ለምን አትበለኝ ምክኒያት የለኝም፣
ፍቅር ስሜት እንጂ ሰበብ አይመስለኝም፣
ብቻ እወድሀለሁ መዉደዴም ጥልቅ ነዉ፣
ፍቅርህ ለእኔነቴ የልቤ ዙፋን ነዉ፣
ህያዉ የምሆነዉ አንተን በማፍቀር ነዉ፣
ሀቁ ቃል ይሄ ነዉ ሰርክ አዲስ የማምነዉ፣
ቂልነት አይደለም ሁሌ አንተን ማለቴ፣
ሞኝነት አይሆንም ለፍቅርህ መክሳቴ፣
ጅልነት አይደለም እራሴን መስጠቴ፣
በቃ አንተን መዉደድ ነዉ ደስታ መደሰቴ፣
ዉለታን ፈልጌ ዉደደኝ አላልኩም፣
ፍቅር ሰጠሁ እንጂ ምላሽ አልፈለኩም፣
እንዴት ለምን ካልከኝ እኔም አላወኩም፣
በቃ እወድሀለሁ ማለቴን አልተዉኩም፣
አዎ እወድሀለሁ፣
አዎ አፈቅርሀለሁ፣
ፍቅርቅር አድርጌህ በፌሽታ እኖራለሁ፣
ዉድድ አድርጌህ አንተን እፎይታ አገኛለሁ፣
ዉዴን እየወደድኩ ሀሴት አደርጋለሁ፣
በፍቅርህ ዉቅያኖስ ስዋኝ እኖራለሁ፣
አንተ ካለህልኝ ለምን እፈራለሁ
ባላገኝህ እንኳ በተስፋላይ ሁኘ ሌላይቱን አለም
እቀላቀላለሁ ሁሌም እወደሀለሁ ።

ሰኞ ማታ ስገላበጥ እሱ ጋር አብረን ያሳለፍነዉን ትዝ እያለኝ እንደ መፀፀት በደስታ ስገላበጥ አደርኩኝ፡፡ ግን በጣም ግራ ተጋብቻለሁ እኔ ነኝ ማለት ነዉ ሂክማ ያ ቆራጥ አመራሬ በትምህርት ቤት ጓደኞቼ መምህሮቼ እንደ ሂክማ ሁኑ ተብሎ በጥሩ ባህሪየ ስነምግባር የምታወቀዉ በሀይደር እንደዚህ እሆናለሁ ብየ መቼም አስቤዉ አላቅም፡፡ ብቻ ሰዉ የሚሸወደዉ በመወሰኑ አይደለም ለምን ኸይር ስራም ቢዝነስም ማንኛዉም ህይወት በዉሳኔ የፀናች ሲሆን ግን ሳናጣራ ግንዛቤዉ ሳይኖረን የምንወስነዉ ዉሳኔ የወደፊት ሂወት ሊያጨልምብን ይበራል ይደምቃል ብለን ያሰብነዉ በተዘዋዋሪ ሊጨለም እና ከጭልመቱም በላይ ብርሀን ቢያገኝ እንኳ አስፈሪ ቁጭት ያለዉ ጨለማ ሊሆን ይችላል፡፡

ጠንቃቃ ነጋዴዌች የሚሉት አሉ ሶስት ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ይላሉ አዉነት ነዉ፡፡ ሀሳብም ቢሆን አንድ ሀሳብ በሶስት መልኩ ማየት መቻል አለብን ፡፡ አንደኛዉ የመጀመሪያዉ መጥፎ ጎኑን ..መጥፎ ጎን ይዞ ቢመጣ በምን ወደነበረበት መመለስ እችላለሁ ወይ ሲሆን....ሁለተኛዉ ጥሩ ጎኑን መሳብ አለብን ...ጥሩ ጎኑ ለኔ ምን ያህል ጠቃሚ ነዉ ብለን ማሰብ መቻል አለብን፡፡ ሶስተኛዉ ዱንያ ስለሚሆን ጥሩ ተስፋ በአእምራችን ላይ ሙሉ በሙሉ መስጠት አያስፈልግም፡፡ የሰዉ ልጅ በጣም የሂወቴ መርህ መለወጫየ ነዉ ብሎ ተስፋ ካረገ ይህ ተስፋ ያረገዉ ነገር ካልተሳካ በጣም የሞራል ዉድቀት እና መልሶ ተስፋ እንዳያደርግ እና በጌታ ላይ ተወኩል ማረግ ሊዘናጋ ይችላል፡፡ ተስፋዎች ማሰብ ባይከፋም ...ግን ኔጌቲቭ ሀሳቦች አብሮ ማሰብ ያሰፈልጋል ዱንያ ነዉ አላህ ከፃፈልን ዉጭ የማይሆን ነገር ነዉ ይህ የአሰብኩት ተስፋ ግብ ካልመታ ወደ በፊቱ ያለበት እስቴፕ ቶሎ መመለስ መቻል አለበት፡፡ ወደ በፊቱ ማንነት ለመመለስ ደግሞ ካሳለፍነዉ የጨለማ ሂወት ያለፉ ታሪኮች ሊከብድ ስለሚችል ያንን በብቃት መወጣት መቻል አለብን፡፡

እኔ ለራሴ የወደፊት ባሌ ሀይደር ነዉ ብየ 100% .እርግጠኛ ነኝ፡፡ ማንም የሚወስድብኝ እሱን የሚያፈቅርብኝ ያለ አይመስለኝም፡፡ እሱም እንደነገረኝ ከእኔ ዉጭ እንደማያገባ የቃልኪዳን ቀለበት እና ሀብል ሰጥቶኛል፡፡ ግን ልቤን ጭንቅ ይለኛል ቢተወኝስ እላለሁ እንደገና አይ ሀይደር በጭራሽ አያረገዉም እላለሁ እንደማያረገዉም እርግጠኛ ነኝ.........

#part 9 ይቀጥላል
1.0K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 15:22:06 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

በእሱ ቁጥጥር ሁኛለሁ የመጀመሪያየ ነበር እሺም እሞቢም የማለቱ ድፍረቱን አጥቻለሁ በስሜት ወድቂያለሁ፡፡ ሀይደር እንደፈለገ ያረገኝ ይዟል ሲፈልግ ይስመኛል ........... በቃ የማላቀዉ አለም ዉስጥ ገባህ እንጃ የዛን ጊዜ የእሁድ ምሽቱን ለመናገር ይቀፈኛል፡......ልብሴን እንኳ እራሴ አላወጣሁም የሚሆነዉ ነገር ማስታወስ አልቻልኩም ስሜት ላይ ነበርኩኝ.......

ፍትጊያዉ ጀምሯል፡፡ የሆነ ሰአት ላይ ካቅሜ በላይ ሁኖ ብቻ ስጮህ አስታዉሳለሁ፡፡
እሱም አይዞሽ ሂኩየ እያለ ወደ ማላቀዉ አለም የትንሽ ሰአታት ደስታ የዘላለም ሂወት ማጨለሚያ የሆነዉን አፀያፊ ስራ እየሰራሁ ነዉ፡፡ ፍትጊያዉ አልቻልኩትም ጮሀኩን የሚሰማኝ የለ....,.,..,,,ከትንሽ ቆይታ ቡሀላ ያ ያማረ ነጭ አንሶላ በቀይ ደም መልኩን ቀየረ፡፡
.....ክብሬን ለሀይደር በሀራም መንገድ አስረከብኩ...ቀይ ደም ሳይ ደነገጥኩኝ.....ወዳዉ እዛዉ መኝታ ክፍል ሻወር ነበር ታጠብኩ ...ከታጠብኩ ቡሀላ ወደ ግድግዳ ዙሬ ተኛሁ እሱም ወደ እኔ ዙሮ ሂኩ ሲለኝ ቆይ ትንሽ ልረፍ ደክሞኛል አልኩት፡፡

...እሱም እሺ ብሎ ተኛ እኔም ተኛሁ፡፡ ግን ተኝቼ መጨነቅ ጀመርኩ ቢተወኝስ እያልኩኝ...እናቴን ለዚና ዋሸሁኝ....,እናቴ ብታየኝ ምን ትለኛለች አምናኝ እናቴን ከደሇት...

ሱብሂ ሶላት ደረሰ ዉዱእ አርጌ ሰገድኩ ግን ዱአየ አላህ ዚና ሰራሁ ማረኝ ሳይሆን....አላህ ሀይደርን የትዳር አጋሬ አርግልኝ ነበር፡፡
...እኔም ሱብሂ ተነስ ስገድ አልኩት እሱም እሺ እሺ እያለ ሳይሰግድ ቀረ፡፡

የማይነጋ የለም ነጋ ቁርስ እዛዉ ኩሪፍቱ ሆቴል
አዘዘ በላን ሂኩየ በጣም ነዉ ያኮራሽኝ ማሻ አላህ ዘልዛላ አይደለሽም ማሻ አላህ ኮራሁብሽ አለኝ፡፡ ቁርስ በልተን ጨረስን ....ከዛ ከደብረ ዘይት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ጉዟችንን ቀጠልን ከደብረዘይት ተመልሰን ገርጂ ደረስ በመኪና ሸኘኝ ከዛም ተሳስመን፡ተለያየን፡፡ አሁን እኔም ወደ እናቴ ጋር እቤቴ ድረስ ሸኘኝ እኔን እቤቴ ካደረሰኝ ቡሀላ እሱም ወደ ቤቱ ተመለሰ.......
......እቤቴ ሄድኩኝ እናቴ እንኳን ደህና መጣሽ ብላ ግንባሬን ሳመችኝ...የእናት ነገር ብርድ ሳይበርድሽ አደረ ልጄ አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ አልኳት
......በይ አረፍ በይ ስራዉን አጠቃለላችሁ ጓደኛሽን አግዥሻት አለችኝ
....እኔም አዎ እናቴ አልኩኝ፡፡
ቁርስ ብይ አለችኝ
እኔም ጓደኛየ ቤት በልቼ ነዉ የመጣሁት አልኳት፡፡
እናቴም እሺ አለችኝ፡፡ መቼም የዛሬዉ ትምህርት ቀርቷል ነገ ድካሙ ሲለቅሽ ትሄጃለሽ አለችኝ፡፡

ዚና ስሰራ እንዳደርኩ የሴትነት ክብሬን እንደተነጠኩ ብሰማ እናቴ ምን ትለኝ ይሆን......
ብየ ብቻየን አለቀስኩኝ ........እንባዬ ዱብ ዱብ ይላል ግን የማለቅሰዉ እኔም ግራ ገብቶኛል፡፡ ሀይደር ይተወኛል ብየ አስቤ ነዉ ??ወይስ ላተቅረቡ ዚና ጌታየ ብሎኝ እኔም የጌታየን ትእዛዝ መጣሴ ነዉ?? ነገ አላህ ፊት ሲጠይቀኝ መልስ ይኖረኝ ይሁን ብቻ እንባየ በሁለቱ ጥያቄ እየጠየኩ ብቻ መልስ በሌለዉ ጥያቄየ እያለቀስኩ ነዉ፡፡

ውስጤ ብሶት አለ
.
እንደ ጥገኛ ትል ከሆድ የማይጠፋ
ውስጤ ችግር አለ ከሀገር የሚሰፋ
ስኖር በዚች አለም ስርክ የገበርኩለት
በዋይታ በዬዬ....እልፍ ያለቀስኩለት
በእንባዬ ብቻ.....በትግስት ያለፍኩት
አካልን አድምቶ .... ሆድ የበጠበጠ
ከጠጠር ጠጥሮ ውስጥ የተቀመጠ
ብሶት አለ ውስጤ
,
ቃላት ማይገልፀው ከሆድ ማይጠፋ
አካሌ ላይ አፎ.....ሁሌም የሚፋፋ
እንባ እየወለደ ...ሀዘን የሚያረግዝ
ደስታዬን በዝብዞ ልብ የሚጠዘጥዝ
እንደ ጥገኛ ትል ከሆድ የማይጠፋ
ውስጤ ችግር አለ ከሀገር የሚሰፋ
ውስጤ ብሶት አለ ፈፅሞ እማይጠፋ

ምሳ ሰአት ላይ ትናንት ዋሽቼ የለ ያደርኩት እጓደኛየ ቤት አቂቃ አለ ብየ ...እናቴን ሄድኩ ብየ ከቤት ወጣሁ በአዲስ አበባ ጎዳና ከገርጂ ተነስቼ እስከ ጎሮ ድረስ በእግሬ እየሄድኩ ብቻየን እያለቀስኩ እንደ መሳቅም እያልኩ ጅል ይመስል የተለያየ የተዘበራረቀ ስሜት እየተሰማኝ እየሄድኩ ነዉ ግን የት እንደምሄድ አላቀዉም...........ብቻ እግሬ ወደ መራኝ ቦታ እየሄድኩ ነዉ፡፡

ሳላስበዉ ድንገት ስልኬ ጠራ የደወለዉ ሀይደር ነበር ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ የት ነሽ ምሳ ልጋብዝሽ አለኝ፡፡ እኔም ያለሁበትን ቦታ ነገርኩት መኪና ስላለዉ ብዙ ደይቃዎች አልፈጁበትም ቶሎ መጥቶ ወደ ወበሪ ሆቴል ሂደን ምሳ ጋበዘኝ፡፡ ምሳ ከበላን ቡሀላ ከሰአት የት ነሽ አለኝ ፡፡ እኔም የምሄድበት የለም አልኩት
..........ሂኩ ለምን ደብረ ዘይት አንሄድም ዛሬ ግን ለመዝናናት ብቻ ነዉ ፡፡ ደብረዘይት ከተማዋን አይተናት ለመመለስ ነዉ እንጂ ለሌላ አይደለም አለኝ አይን አይኔን እያየ... እኔም እምቢ የማለት ድፍረት አጣሁ አንዴ ልቤን ሀይደር ወስዶታል፡፡ እሺ ስለዉ እዛዉ ተሳሳምን አይ ወንጀሌ ...............
ጉዞ ዳግም ወደ ደብረዘይት ለስለስ ያሉ የሱዳን ነሽዳዎች መኪናዉ ላይ ከፍቶት ጉዟችንን ቀጠልን፡፡

የኔ ነገር ገና አላለቀም ዳግም ትናንት ክብረ ንፅህናየን የተነጠኩበት ደብረዘይት እየሄድኩ ነዉ ፡፡ የወደፊቱ ባሌ ሀይደር ጋር ነኝ፡፡ እሁድም ደብረዘይት ሰኞም ደብረዘይት በሚቀጥለዉ part ጋር የሰኞ ከሰአት ጉዴን አጫዉታችሇለሁ

#Part ይቀጥላል
1.1K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:57:37 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

ሂኩ ዝም አልሽ እሳ አለኝ ....እቤት እናቴ ትቆጣለች ከእናቴ ተነጥየ አድሮ አላቅም የት አደርሽ ብትለኝ ምን እላለሁ አልኩት
...እሱም ምክንያት ፍጠሪ አለኝ፡፡
ነገም ሰኞ ነዉ ትምህርት አለኝ እንዴት ብየ እቀራለሁ ብየ የማምለጫ ሀሳብ ባቀርብ የኔ ሀሳብ አንድሱ በሚሰጠኝ መልስ ላስምነዉ አልቻልኩም እምቢ የምልበት ምክንያት አጣሁ፡፡ በዛ በዚህ ብሎ አሳመነኝ ..እምቢ የምልበት ቃል የለኝም......

በመጨረሻም እሺ አልኩኝ....እሱም በደስታ ከንፈር ለከንፈር ጨዋታችንን አጧጧፍነዉ...በቃ የተለየ ስሜት ገባን እኔም ሁኔታዉ ስላላማረኝ ተረጋጋ ሁሌም ፧በሰአቱ ይደርሳል አልኩት፡፡
...እቤት ደዉለሽ አስፈቅጂ አለኝ
......እኔም ለእናቴ ደወልኩኝ
..እናቴም ስልኩን አነሳችዉ
ሀሎ ልጄ ልደዉልልሽ ስል ደወልሽልኝ እንዴት ዋልሽ አለችኝ ጊዜዉ ወደ መቅሪብ ሶላት ደርሷል፡፡
እኔም ደህና ነኝ እናቴ ያዉ እንደነገርኩሽ የጓደኛየ ቤት አቂቃዉ በስራ ዉጥርጥር ብየ ነዉ አልኳት
እናቴም አይዞሽ ጓደኛሽ አይደለች የእሷን ደስታም ሀዘንም አብረሽ መወጣት አለብሽ አለችኝ
....እናቴ .አሁንም እዛ ላድር ነዉ ስራዉ አላለቀም ፡፡ እናዳትሰጊ ልደዉልልሽ ብየ ነዉ አልኳት
.....እናቴም ቅር እያላት ሙሉቀን ሳላይሽ ዋልኩ አሁንም ቀረሽብኝ እሺ ምን አረጋለሁ ልጄ አደራሽን ተጠንቀቂ አለችኝ፡፡ ጭራሽ እኔን ወንድ ጋር ትሄዳለች ብላ አስባዉም አታቅ እናቴ በኔ የምትተማመንብኝ ነኝ ወይኔ ሂክማ ምን አረጋለሁ በሀራም መንገድ ፍቅር ዋሽቼ የማላቀዉን ለወደፊት ተስፋ እና በስጦታ አንበሽብሾ ይሄዉ ለሀይደር ብየ እየዋሸሁ ነዉ፡፡
...እኔም እሺ አልኩኝ
.......እናቴም ግን ሙሉቀን ምግብ ቀምሰሻል አለችኝ
...እኔም አዎ እናቴ አልኩኝ የእናት አንጀት የምታስበዉ አሁንም ለኔ ነዉ፡፡
....እናቴም እሺ ንፋስ እንዳይመታሽ ከምታድሪበት የጓደኛሽ ቤት ሹራብ ደረብ አርገሽ ስሪ ልጄ ...አይዞሽ ደህና እደሪ..ነገ ግን በጠዋት ነይ ዛሬ ሙሉቀን አላየሁሽም ...አንቺዉ ነሽ ያለሽኝ ትናፍቂኛለሽ ነገ አይንሽን እንዳይሽ አለችኝ
...እኔም እሺ እናቴ ደህና እደሪ ብየ ስልኩን ዘጋሁት ፡፡

ሀራም ለመስራት እናቴን ስንቱን ዉሸት ዋሸሁ..እናቴ አምናኝ አልጠረጠረችም ምን ይደረጋል...ሀይደርም ማሻ አላህ በዉሸት ማሳመን ትችያለሽ ማለት ነዉ አለኝ፡፡

እኔም ምን ላርግ ብለህ ነዉ ምንም አማራጭ የለኝ ፡፡
ለአንተ ብየ ነዉ እንጂ እንደዚህ የምዋሸዉ እናቴን ዋሽቼ አላቅም ነበር ምን ይደረጋል አልኩት፡፡
እሱም ነገ እናትሽ የጓደኛሽን ቤት አሳይኝ ብትልሽ እሳ አለኝ
....እኔም እናቴ ታምነኛለች አትለኝም አልኩት፡፡

አንተስ አታስፈቅድም እንዴ አልኩት
..እሱም አስፈቅጃለሁ አለኝ፡፡ አሁን ሰአቱ ከምሽቱ 1:30 አካባቢ ሁኗል የጨረቀዋ ዉበት ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ደስ የሚል ድባብ ነበረዉ፡፡ ግን የሚገርማችሁ አሱር እና መቅሪብ ሶላት አልሰገድንም ነበር፡፡ እሱም እንስገድ አላለኝም....
እዛዉ ባቡጋያ ሪዞርት እራት አዘዝን እሱም ማደሪያ መኝታ ክፍል ያዘ፡፡
እኔም ሀይደር ዛሬ እኮ አሱር እና መቅሪብ አልሰገድንም እኮ አልኩት
...እሱም ሂኩ የሚገርም ነዉ እየቀለደ ሙሳፊር ነን እኮ በዛም ላይ የአንቺ ፍቅር ሶላት አስረሳኝ በይ ዉዱእ እናርግ እና እንስገድ አለኝ፡
ባቡጋያ ሪዞርት በሚገኘዉ እዛዉ መዝናኛዉ ዉስጥ አነስ ባለች ቤት መስገጃ ቦታ በተዘጋጀች ቤት እኔ መጀመሪያ አሱር መቅሪብ ቀዷዉን ኢሻን በወቅቱ ሰገድኩ

እኔ ሰግጄ ስጨርስ እኔ ወጣሁ እሱ ገብቶ ሶላቱን ጀመረ አሱር መቅሪብ ኢሻ ለመስገድ ገባ፡፡....ግን ቶሎ ብሎ ሶስቱን ሶላት ጨርሶ ከመስገጃ ቤቱ ወጣ ፡፡ ...... ሀይደር ሶላት የሰገደ ሳይሆን የህሊና ፃለት አርጎ የመጣ ነዉ የሚመስለዉ፡፡ በጣም ፈጠነብኝ ..እኔም ፈጠንክ ልለዉ አልኩና ዝም አልኩት፡፡
የአዘዝነዉ እራት ደረሰ እየተጎራረስን በላን በቃ የሚምር እራት ግብዣ ነበር፡፡ አንቺ ጋር እራት ስበላ የመጀመሪያየ በጣም ደስተኛ ነኝ ሀዩ አንቺስ አለኝ...
እኔም ደስተኛ ነኝ አልኩት
እሱም ኢንሻ አላህ ዛሬ ሆቴል ብላን ለወደፊት አንድ ላይ ልጆቻችንን ይዘን እቤታችን ነዉ የምንበላዉ ብሎ ጉንጬን ሳመኝ፡፡

በልተን ጨረስን አሁን ሰአቱ ከምሽቱ 2:30 ሁኗል ፡፡ ሂኩ ወደ መኝታ ክፍል እንሂድ አለኝ ፡፡ እኔም ቅር እያለኝ ደስም እያለኝ ተያይዘን መኝታ ክፍል ገባን ......በሩን ሲከፍተዉ የሚያምር ክላስ ነዉ ሻማ የበራበት ነበር፡፡ ሂጄ አልጋዉ ጋር ቁጭ አልኩኝ እሱም በሩን ዘግቶ ከጎኔ መጥቶ ቁጭ አለ፡፡ ጨዋታዉ ጀመረ ...ሀይደር ወደ እኔ ተጠጋ እና ሂኩ አለኝ .....እኔ በእሱ ፍቅር ተሸንፊያለሁ የሚያረገኝን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ...........ወደ እኔ ተጠግቶ ሂኩ እወድሻለሁ ብሎ ..........,

#part 8 ይቀጥል
1.3K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:13:37 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

እኔም ብቻየን የጥመት የራስ አመለካከቴን ማሰብ ብቻየን ማዉራት ጀመርኩኝ፡፡

,,,,,,,ሀይደር አላህን ይፈራል አይጎዳኝም ፎቶ መልቀቅ አረብዙ ነገር ያስተማረኝ ያስረዳኝ እሱ አይደል እያልኩ ደግሞም.... እኔ ፈልጌው ሳይሆን እሱ ነው ወደኔ የመጣው እያልኩ ለሀራም ራሴን እያዘጋጀሁ በሀሣብ ርቄ እሄዳለሁ ፡፡ ትንሽ ያለኝን ኢማን ተፈታተነኝ ዘንድሮ እንደ ማትሪክ ተፈታኝ መሆን አልቻልኩም .ትምህርቴ ላይ ተዳከምኩ ጓደኛቼ የኔን መዳከም ምን ሆንሽ ብለዉ ቢጠይቁኝም እኔ መልስ የለኝም፡፡ በtelegram group የተዋወቅነዉ በሀይደር ፍቅር ላልወጣ ታስሪያለሁ ሀላል የመሰለ አይኑን የጨፈነ የወንጀል መንገድ እየተከተልኩ ነዉ፡፡

........እሱ ባለኝ ነገር ተስማማሁ ግን ጊዜ ስጠኝ ይሄ የመጀመሪያ ነው ለመወሰን ያስፈራል በዛ ላይ በጣም ፈጠነ አልኩት፡፡
...... እሱም እኔን እመኝኝ ምንም ቢሆን እህቶች አሉኝኮ ፡፡ ስለምወድሽ ነዉ አንቺን ማጣት አልፈልግም ፡፡ አሁን ለራሱ ሰዉን ማመን አልቻልኩም ያየሽ ወንድ ሁላ የሚወስድብኝ እየመሰለኝ ሆዴ ይሸበራል፡፡ ባየሽኝ እንዴት በፍቅርሽ ተሰቃየሁ፡፡ ደግሞ ከትንሽ ጊዜ በኃላ አብረን ነው የምንኖረው እያለ አበረታታኝ፡፡

.........እሽ ግን ጊዜ እፈልጋለሁ አልኩት፡፡
....እሱም አንድ ቀን ስጠቸሻለሁ አለኝ፡፡
........እኔም እሺ አልኩት፡፡
ብቻየን ቁጭ ብየ አሰብኩት ....በፍቅር ስለከነፍኩ ምንም እምቢ የምልበት ቅንጣት ምክንያት የለኝም፡፡ እንዳስብበት የተሰጠኝ አንድ ቀን አለቀ፡፡ እሱም ደወለልኝ ምን ወሰንሽ አለኝ እኔም ...አንተን ማጣት አልፈልግም ግን ላተወኝ ቃል ግባልኝ አልኩት እምባ እየተናነቀኝ ፡፡ እሱም ወላሂ ብሎ ቃል ገባልኝ........
........አንድ ቀን ከትምህርትም ቀርቻለሁ ስልክም ሲደዉል ማንሳት አልቻልኩም፡፡
.......ምን ሁነሽ ነዉ አለኝ
እኔም ፔሬድ ላይ ነኝ አልኩት
........እሱም እየአዘነ እህቴ ፔሬድ ስትሆን የሚሰማት ስሜት በጣም ያስለቅሰኝ ነበር ፡፡ አይዞሽ እያለ እሱም በጣም አዘነ ማልቀስ ብቻ ነበር የቀረዉ፡፡
ዛሬ መገናኘት አለብነ አለኝ እኔም እሺ ብየ የት እንገናኝ አልኩት እሱም ከአሱር ቡሀላ ሀሮን ሆቴል እንገናኝ ተባባልን፡፡ከዛ በሰአቷ ተገኘሁ ጋበዘኝ
.......እሁድ ሲደርስ ደግሞ ወበሪ ሆቴል እጋብዝሻለሁ ብሎ ለእሁድ ፕሮግራም ይዘን መቅሪብ አዛን ሊል ሲል በመኪናዉ እቤቴ ድረስ ሸኘኝ፡፡ እሁድ ደረሰ ወበሪ ሆቴል ድረስ አብረን በመኪና ሄድን ፡፡ እዛም ላልተዉሽ ላትተይኝ ዛሬ ቃል የምንገባበት ቀን ነዉ አለኝ፡፡ እኔም አንተን ላልለይ ብየ ቃል ገባሁ እሱም እንደኔዉ ቃል ገባ፡፡ ከዛም በመቀጠል አይሽን ጨፍኚ አለኝ
እኔም አይኔን ጨፈንኩ ከዛም ለመጀመሪያ ጊዜ ሳመኝ እኔም ደግጬ ምንም መልስ የለኝም አይን አይኑን ከማየት ዉጭ ከዛ ሂኩ ምነዉ ደበረሽ እንዴ አለኝ
እኔም አረ ችግር የለም አልኩት፡፡ ችግር የለም ለወደፊት የማይፈታ ችግር ይዞ ይመጣል፡፡
..........ከዛም ደብረ ዘይት ሂደሽ ታቂያለሽ አለኝ
አረ በጭራሽ አላቅም አልኩት
እሺ እኔ ጋር ሂደን አሳይሻለሁ አለኝ፡፡
እምቢ የምልበት አቅም የለኝም እሺ ይበልጣል ከአንዲሺ የተባለ ይመስል መልሴ ሁሉ እሺ እሺ ነዉ፡፡
ፔሬድ ላይ እንዳለሁ እስከምጨርስ ይጠይቀኝ ነበር፡፡ ሲሻለኝ ሲጨርስ ነገርኩት ደስ አለዉ፡፡
የእኔ ፔሬድ መሆኔን መንገሬ ግን ለወደፊት አሁን ድረስ ያለቀቀኝ ችግር ይዞብኝ መጣ፡፡

ሂኩ ለምን እቤት እሁድ ከሰአት አስፈቅደሽ ደብረ ዘይትን አይተናት አንመጣም አለኝ፡፡
እንዴ አናቴን ምን ብየ አስፈቅዳለሁ አልኩት
በሆነ ሲስተም አስቀድሚ መቼም ለወደፊት የሀላል ሚስቴ ነሽ ኢንሻ አላህ አመቻችተሽ አንድ ቀን እናትሽ ጋር ታስተዋዉቂኛለሽ አለኝ፡፡
እኔም ደስ ብሎኝ እሺ አልኩኝ፡፡
እናቴን የትምህርት ቤት ጓደኛየ እናቷ ወልዳ እሁድ አቂቃ አለኝ ብየ ሳይደርስ በወሬ በወሬ ነገርኳት ዉይ ዉሸት ሲያስጠላ፡፡ እናቴም ምን አሸሽ የኔ ልጅ ባታስፈቅጅም የምኮራብሽ የወደፊት ተስፋየ አይኔ አንድ ፍሬ ልጅ ነሽ ይሄ ትምህርት ቶሎ ባለቀቀ ጓጓሁ ሰርግሽን ለመደገስ ተዘጋጅቻለሁ አለችኝ እየቀለደች ዉይ እናት የኛ ደስታ ደስታቸዉ ሀዘናችን ሀዘናቸዉ ነዉ፡፡ ጀነት ከእናት እግር ስር ናት ለእናት ይገባታል፡፡

እሁድ ደረሰ ዙሁርን እቤቴ ሰግጄ እናቴን ቻዉ ብየ ተሰናብቼ ሀይደር መኪናዉን ይዞ መጥቶ ከሰፈሬ ገርጂ አብረን ጉዞ ወደ ደብረዘይት አመራን ፡፡

ደብረ ዘይት ምን ይፈጠር ይሆን????
አብረን በቀጣዩ ክፍል እናየዋለን

#Part ይቀጥላል
@hayu_abdi
1.4K viewsedited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 09:53:45 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

ሂኩ ግን አንድ የደበኩሽ ነገር ግን አለ እባክሽ እንዳትቀየሚ!" አለኝ እንደመደንገጥ ብየ የደበቀኝን ለማወቅ እየጓጓሁ "እእ ምንድነው የደበከኝ!?" አልኩት፡፡
ሂኩ እወድሻለሁ አንቺን ማጣት አልፈልግም እኔ ስትማሪ ጀምሮ እከታተልሽ ነበር ለትዳር ግን በአላህ ፍቃድ በtelegram በተከፈተ ግሩፕ profile አይቼ አላህ አንቺን እንዳላጣ አመቻቸልኝ በሂደት አንቺን ይሄዉ በአካል አገኘሁ ስለሆነም እወድሻለሁ ብሎ ስጦታ የተጠቀለለ ሰጠኝ ፡፡ እቤትሽ ሂደሽ ታይዋለሽ ብሎ ከኪሱ ቀይ አበባ ሰጠኝ ፡፡ እኔም ደስ እያለኝ ተቀበልኩኝ፡፡ ያዘዝነዉ መጥቶ በልተን ጠጥተን ትንሽ ካወራን ቡሀላ ፀሀዯ ወደ መግቢያዋ ስደርስ መቅሪብ ሶላት ሲደርስ ከዞላ ሆቴል ወጥተን ወደ ቤታችን እንሂድ ብለን ተነሳን፡፡ ነይ መኪና ላይ ግቢ ልሸኝሽ ብሎኝ በያዘዉ ዶልፊን መኪና ጋቢና ሁኜ ቤቴ አካባቢ ልደርስ ትንሽ መንገድ እንደቀረኝ እንደአጋጣሚ እናቴ እንዳታየኝ ብየ እቤቴ ሳልደርስ ወረድኩ፡፡ ለሀይደርም መኖሪያ ቤታችንን በሩቅ አሳይየሁት ፡፡
.. ..ከዛም ቻዉ ደህና እደር ተባብለን ያለምንም መነካካት መጨባበጥ ተለያየን የሰጠኝን የስጦታ ፌስታል እስከምፈታዉ እየተጣደፍኩኝ ወደቤቴ ገባሁ፡፡ ስጦታዉን እናቴ እንዳታየዉ ጥንቃቄ በማረግ ሳስብ እናቴ ሳሎን መቅሪብ ሶላት እየሰገደች ነበር ....ለኔም ጥሩ ሆነ እናቴ ፌስታሉ ምንድንነዉ ? ብላ አጠይቀኝም እየሰገደች ስለሆነ ቀጥታ መኝታ ክፍሌ ገባሁ ፡፡ መኝታ ክፍሉን ቆልፌ ቶሎ ብየ ፌስታሉን ፈትቼ ሳየዉ የእኔ እጅ መሆኑን የሚያስንቅ የእጅ ሰአት ..የወርቅ ቀለበት ..ከኔ ዉበት ጋር የሚሄድ አብረን መርጠን የገዛነዉ የሚመስል የሚያምር ፋሽን ልብስ ..... በወረቀት የተጠቀለም አለ ፡፡ ወረቀቱን የተጠቀለለዉን ስፈታዉ ሂኩ ቀለበቱን ተቀበይኝ እወድሻለሁ አንቺን ማጣት አልፈልግም ለአንዳንድ ወጭ እንዲሆንሽ አብሮ ወረቀቱ ጋር የተጠቀለለ 10,000(አስር ሺ ብር) አለ የምፈልጊዉን አድርጊ እንደዉለታ እንዳቆጥሪዉ ሂኩ እወድሻለሁ ብሎ ፁሁፍ ያበቃል፡፡
እኔም ደብዳቤዉን እየደጋገምኩ እያነበብኩ የደስታ እምባ አለቀስኩ፡፡ ሳላስበዉ እናቴ መኝታ ክፍሉን ቆረቆረች እኔም ደንግጬ ብሩን እና ስጦታ እቃዉን ከአልጋዉ ዉስጥ ደበኩት ቶሎ ብየ የደስታ እምባየን ጠርጌ የክላሴን በር ከፈኩኝ ፡፡ እናቴም መቅሪብን አሰግጅም እንዴ አለችኝ፡፡ እኔም አረ እስገዳለሁ ደከም ብሎኝ ነዉ አሁን ልብሴን ቀይሬ መጣሁ ማሚ አልኳት
....እናቴም እሺ ብላ ከመኝታ ክፍሌ ወጣች ከዛም የስጦታ እቃዎቹን እና ብሩን የራሴ ቁምሳጥን ዉስጥ አስገብቼ ቆለፍኩኝ፡፡ ከዛ የለበስኩትን ልብስ ቀይሬ ሂጃብ ለብሼ መቅሪብን ሰግጄ ዳታየን አብርቼ ቀጥታ telegram ስገባ online አገኘሁት በጣም አመሰግናለሁ አላህ ይስጥልኝ ብየ አመሰገንኩት
......እሱም ቆጣ ብሎ ይሄ ለአንቺ ሲያንስሽ ነዉ የኔ ፎቅር እንደዉለታ እንዳትይዢዉ ስለዚህ ወሬ እንዳትደግሚ ብሎ ነገረኝ ...እኔም እሺ ብየ ሌላ ወሬዎች ማዉራት ጀመርን

ተገናኝተን በአካል ከተዋወቅን ቡሀላ ማን ፈቅዶ እንደሰጠው ወይም እንደሰጠኝ ባይታወቅም "የኔ የኔ" እየተባባልን ማውራት ጀመርን፤ የፍቅር ቃላቶችን መለዋወጥ ጀምረናል፡፡ ሂኩ በዲኔ ጎበዝ የነበርኩት ኢማኔ በአንዴ ወረደ ፡፡ ትምህርቴንም ተዳከምኩ ጓደኞቼን አልነገርኳቸዉ ሰርፕራይዝ ላረጋቸዉ አስቤ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ሚዜ ሁኑኝ ልላቸዉ አሰብኩ፡፡ ከትምህርት ስመለስ ከጓጀኞቼ ጋር መሄድ አቆምኩ ብቻየን እሆናለሁ ይደዉልልኛል እያወራሁ ወደ ቤቴ እሄዳለሁ፡፡ ግን ሁሌ ማታ ማታ ስደዉልለት አያነሳም ነበር፡፡ እሱም ማታ ማታ አደዉይ ቤተሰብ ጋር ስለምሆን ለማንሳት አይመችም ይለኛል፡፡ ግን ሁሌም ማታ ማታ በtelegram በሚያምር የፍቅር አገላለፅ እየገለፀልኝ ፡፡ የፍቅር ግጥም ሲገጥምልኝ እራሴዉ ጋር እያመሳሰልኩ እደሰት ነበር በጣም ደስ እያለኝ አወራለሁኝ፡፡
የፍቅር ግጥም ሲልክልኝ ገጣሚ ነህ እንዴ ስለዉ አረ ግጥም ፅፌ አላቅም ግን የአንቺ ዉበት ጌጥም ፀሀፊ አረገኝ ይለኝ ነበር፡፡
አንዴ እያወራን ሳላስበዉ ያልጠበኩት ጥያቄ ጠየቀኝ እንዳፈቀርኩት ሲያውቅ ተገላልጠሽ ያለክሪም ፎቶ ላኪልኝ ማለት ጀመረ፡፡
.....አኔም "ኒካህኮ የለንም እንዴት ተገላልጨ እልካለሁ!?" አልኩት
........" ውዴ ትንሽ ወራት ብቻ ስጭኝ ከዛ በኃላ አብረን እንኖራለን እስከዛ ግን ራሴን ላዘጋጅ፤ አንች መተሽ እንድትቸገሪብኝ አልፈልግም ንግስት አድርጌ ነው የማኖርሽ እስከዛ ግን የምፈልገውን አትከልክይኝ እባክሽ ወይስ አታምኝም እኔን፤ በፍቅራችን እምነት ይኑርሽ ከአንቺ የምፈልገዉ ተጋብተን 10 ልጆች ነው የምንወልደው" አለኝ፡፡ " .......አምንሀለሁ ደግሞው ስለወደድኩህ እንጅ ማንንም እንዳንተ ቀርቤም አውርቸም አላውቅም!!" አልኩት
......" በቃ ቃል እንግባ ሁለታችንም ላንለያይ አንች ከኔ ውጭ እኔም ካንች ውጭ ላላይ" ሲለኝ " በአላህ ስም ምየ ቃል ገባሁለት ላልለየው እሱም ቃል ገባልኝ፡፡
...." እሽ ከተስማማን የምንፈልገውን ሁሉ እናደርጋለን" ሲለኝ ልቤ ለሁለት ተከፈለ፡፡ አንዱ ልቤ "እንዴት አላህ የከለከለውን ነገር ታደርጊያለሽ አላህን አታስቆጭ ይለኛል" በአንዱ ደግሞ " ይሄኮ በአንች አልተጀመረም ደግሞ ቃል ገብቶልሻል አለባበሱ አወራሩ አደቡ የምፈልገዉ የምመኘዉ አይነት ሰዉ ነዉ ..ሙስሊም ነው አላህን ይፈራል አይጓዳሽም" ይለኛል፡፡ የቀራሁትን ቁርአን እና ሀዲስ ረስቸ የሸይጧንን ጥሪ እየተከተልኩ ይመስለኛል፡፡ አሁን እሱ ጋር የፍቅር ግንጁነት ልጀምር አልጀምር ?? እያልኩ ሁለት ልብ ሁኛለሁ

ሂክማ የፍቅር ሂወት ትጀምር ይሆን በቀጣዩ ክፍል➎ እናያለን
፡፡

@hayu_abdi
1.5K viewsedited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 17:21:02 እዉነተኛ ታሪክ

#Part

" ብቻየን ክላሴን ተቀመጥኩኝ፤ የምወዳትን እናቴን እንኩዋን እንደወትሮው ላስቃት ላጫውታት አቅም አጣሁ! የደስታየን ቁልፍ ተነጥቄ አሁን አልቅሸ ላስለቅሳት እንጅ ስቄ ላስቃት ባለመቻሌ ራሴ ላይ ቆልፌ ተገለልኩ እኔ በማላወቀው ሰው ፍቅር መውደቄ ሳያንስ ቅጡ በጠፍው ለወሬ በማይመች ጉዳይ ኡሚ ለምን ታልቅስብኝ!!? ጥበቃው አልሰለቸኝም ፀሀይ ለጨረቃ ቦታዋን ለቃለች፡፡ ግን አሁንም የለም፡፡ የሴትነት ክብር ኩራቴንም ትቸ ጧት እሱን ፍለጋ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩኝ ግን ወደ የት ሂጄ እፈልገዋለሁ ??
ግን telegram አይገባም ብየ ተስፋ ቆርጨ ልወጣ ስል አረንጓዴ አበራ፡፡ ልቤ በደስታ ብዛት ዘለለች አይኖቸ በእንባ በሞሉ! እጆቸን ከኪቦርድ ጋር ለማገናኘት ብሞክር እንባየ ጭጋግ ሆኖ እንዳላይ ከለከለኝ እጆቸም ሰነፉ አልፈጥንልኝ አለኝ፡፡ በዚህ መሀል ከኔ የሱ መልእክት ቀድሞ ደረሰኝ፡፡
...."
አሰላሙአለይኩም ሂክማ እንዴት ነሽ በቃ ስጠፋ እንዲህ ትረሽኛለሽ ማለት ነው!? እኔ ግን በችግር በውጥረት ውስጥ ሆኘም አስብሻለሁ ግን ምን ላድርግ ስልክሽ የለኝም" ብሎ የሱን ስልክ ቁጥር ላከልኝ ከዚህ በኃላ መግደርደርም ሆነ ስሜቴን መደበቅ አልችልም በጠፋበት ጊዜ ምን ያህል እንደተጨነኩ እንደናፈቀኝም ጭምር በድፍረት ነገርኩት፡፡ ከዚህ ንግግራችን በኃላ ስልክ ቁጥር ተለዋወጥን፡፡ በስልክ ቀን ላይ ስንጨዋወት በስልክ እሱ ደዉሎ ከትምህርት ስመለስ ስናወራ ዋልን፡፡
.....እኔም ደፍሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ እምቢ እንደማትለኝ እርግጠኛ ነኝ አልኩት
......እሱም ጠይቂኝ እምቢ አልልሽም አለኝ፡፡
..........ፎቶህን እኮ አላክልኝም እኔን ግን በፊት profile ሳረግ ታቀኛለህ በአካልም አቅሻለሁ ብለህኛል ....ዛሬ በፎቶ ባቅህ በጣም ደስተኛ ነኝ አልኩት
........ እሺ ምን አሸሽ አሁን telegram ግቢ እልክልሻለሁ አለኝ ፡፡
እኔም ስልኩን ዘግቼ telegram ዳታየን አበራሁ እሱም ገብቶ የእሱን ፎቶ ላከልኝ፡፡
እኔም ጀዛከሏህ ብየ ፎቶዉን ማየት ጀመርኩ
....ያረቢ የአላህ ቁንጅና ከጠበኩት በላይ ፂሙ አለባበሱ የሚያምር እድሜዉ በእኔ እኩያ የሚሆን መልከ መልካም ቅንጆ ከአሰብኩት በላይ ሁኖ አገኘሁት፡፡ የእኔ እና እሱን ዉበት ማወዳደር ጀመርኩ እኔም ቆንጆ ነኝ ሀይደርን ለትዳር እመጥነዋለሁ ብየ አሰብኩኝ፡፡ አዳሬን በደስታ የእሱን ፎቶ እያየሁ እያደነኩ ደስ የሚል እንቅልፍ ወስዶኝ አደረ፡፡

ጧት ከእንቅልፌም ስነሳ በደስታ እየተፍለቀለኩ ነበር፡፡ ኡሚ ሁኔታየ ግርምትን ፈጥሮባት " ዛሬ በጧት ምን ተገኘ!?" ብላ ጠየቀችኝ፤ እኔም ደስ የሚል ህልም አይቸ ነው ብየ ጥያቄውን አለባብሸ አለፍኩት፡፡ ከትምህርት እንደወጣሁ ደወለልኝ ተቻኩየ ስልኩን አነሳሁት፡፡ በስልክ ስናወራ በደስታ ብዛት የልብ ምቴ ፈጠነ፡፡ " ድምፅሽን በመስማቴ ደስ ብሎኛል!!" አለኝ፡፡ እኔም ደስተኛ መሆኔን ገለፅኩለት፡፡ በልቤ ያዳፈንኩትን ፍቅሩን እንዲቀጣጠል የሚያደርገውን ቃላት በጥያቄ መልክ ተነፈሰ " ሂኩ እኔ አንችን በአካል እስከማገኝሽ ቸኩያለሁ ትምህርት ቤት ስትሄጂ አይሻለሁ ሁሌ እከታተልሻለሁ ግን አንቺን በአካል ለማዉራት ፈራሁ ....መቼ ነዉ የምንገናኘዉ ????አለኝ
......እኔም ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ እሁድ ሀያአራት ሰፈር አካባቢ የሚጀኘዉ ዞላ ሆቴል አስር ሰአት ላይ እንገናኛለን ተባባልን እሁድ እስከሚደርስ በጣም ቸኮልኩ፡፡
እንደምንም ብሎ እሁድ ደረሰ የምለብሰዉ ልብስ ለመልበስ አንዱን ሳማርጥ ይሄ ያምራል ይሄ አያምርም እያልኩ በስንት ከራሴ ጋር ጭቅጭቅ አንዱን ልብስ መርጬ ለበስኩኝ በቀጠሮ ሰአት ቀድሜ እኔ ዘጠኝ ተኩል ሲል ደረስኩኝ ፡፡ ሀይደርም አስርጉደይ ለአስር ሲል ዞላ ሆቴል ደረሰ እሱ ከቀጠሮዉ አስርደቂቃ ቀድሞ ሲደርስ እኔ ግን ከቀጠሮዉ ሰላሳ ደቂቃ ቀድሜ ነበር የገባሁት የሀበሻ ቀጠሮ የሚባለዉ ነገር እኛ ጋር አይሰራም ያስብላል፡፡
.... .....ሀይደር ሲመጣ የሚያምር ዶልፊን የቤት መኪና ይዞ ነበር የመጣዉ፡፡ ግን እኔ መኪና ይኑረዉ አይኑረዉ የማቀዉ ነገር የለም....ለምን በtelegram እና በስልክ ስናወራ ስለአለዉ ንብረት የተነጋገርነዉ ነገር የለም ነበር፡፡ መኪናዉ ለኔ ምንም አልመሰለኝ ብቻ በአካል ሳየው አለባበሱ በሱና ነው አነጋገሩ በእርጋታ ነው በአጠቃላይ የሙስሊም አዳብ አለው፡፡ እንዳሰብኩት ሆኖ ሳገኘው በጣም ተደሰትኩ! ንግግሩ ቀልብን ይስባል፡፡ እኔ ከማወራ ለጆሮ ልስልስ ብሎ የሚሰማውን ንግግሩን መስማት መረጥኩ፡፡
አሰላሙ አለይኩም ሂኩ አለኝ
.....ወአለይኩም ሰላም እንዴት ነክ ሀይደር
........ በአካል መቼም አታቂኝም አለኝ.. አዲስ አበባ የዘጠኝ ብሔረሰብ መኖሪያ ነች የሰዉ ብዛት እንኳን ሀይደርን ላቀዉ ጎረቤቶቼንን እንኳ የማናቅ ብዙ ነን ሰዉ ጠዋት ለስራ ይወጣል ማታ ይገባል ስለሆነም እሱ ቢያቀኝም እኔ ግን በአካል ሳየዉ ለመጀመሪያየ ጊዜ ነበር ፡፡ የሚበላ እና የሚጠጣ ከአዘዝን ቡሀላ እስከሚመጣ ሀይደር ሂኩ ተጫወቺ አለኝ፡፡እኔም እሺ አልኩኝ
"ሂኩ ግን አንድ የደበኩሽ ነገር ግን አለ እባክሽ እንዳትቀየሚ!" አለኝ እንደመደንገጥ ብየ የደበቀኝን ለማወቅ እየጓጓሁ "እእ ምንድነው የደበከኝ!?" አልኩት፡፡

#Part ይቀጥላል
629 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:56:49
1.0K views20:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 20:28:34 እዉነተኛ ታሪክ
#Part

እኔም በመደንገጥ እንዴ ከአሁን በፊት ታቀኛለህ እንዴ ????? አልኩት
እሱም........ አዎ አደበኛ እንደሆንሽ ስነስርአት እንዳለሽ ነበር የማቀዉ እኔ ሰፈሬ ታክሲ ተራ አካባቢ ነዉ ትምህርት ስትሄጄ ስትመጪ አይሻለሁ፡፡ በስነስርአትሽ በደንብ አቅሻለሁ group ላይ እንደአጋጣሚ profile ሳይ የአንቺ acount መሆኑን ሳይ በጣም ነዉ የደነገጥኩት ለምን የማቅሽ ወንድ ጋር ስትሄጅ ስትጃጃይ አላይሽም ደስ ትይኝ ነበር profile ፎቶ መሆኑን ሳይ ከፋኝ አለኝ፡፡
...እኔም ጓደኞቼ አድርጊዉ ያምራል ስለሚሉኝ ነዉ እንጂ ወንዶችን ለማማለል ለመጀናጀን አይደለም
......... ስሜ ሀይደር ይባላል፡፡ የአንቺስ በአካል እና በፎቶ እንጂ ስምሽን አላቀዉም አለኝ፡፡
...........ሂክማ እባላለሁ ብየ መለስኩለት እኔ ስለእኔ ስለሚያቅ በወሬ ወሬ ስለእሱ ሁኔታ ጠየኩት እሱም መርካቶ ቤተሰቦቹ ሱቅ ከፍተዉለት ልብስ እንደሚያከፋፍል ነገረኝ፡፡

አሁን ስለ ግል ሁኔታችን ማዉራት ጀመርን ከአሁን በፊት ማንም ጋር አዉርቼ አላቅም ግን ሀይደር ጋር በአጋጣሚ በtelegram ተዋዉቀን ጊዜን ጊዜ በተካ ቁጥር እየተግባባን እየተላመድን መጣን፡፡
,,,,,ስለኔ ግል ሂወት መጠየቅ ጀመረ፤ እኔም ለጥያቄው ትክክለኛ መልስ ነበር የምሰጠዉ ከነ ቤተሰቦቼ ስራ ...የእሱ አባት ነጋዴ ነዉ መርካት ከአስረኛ ክፍል እንደወደቀ ሱቅ ከፍቶለት እንደሆነ ብዙ ነገሮችን አወራን፡፡ በሒደት የወንድ ጓደኛ አለሽ አለኝ ??
....አረ የለኝም አልኩት
........እሱም የወንድ ጓደኛማ ሀራም ነዉ መቼም እንዳትይዢ አለኝ እኔም በቃ እንደወንድምሽ እይኝ አለኝ፡፡
....እኔ ወንድም የለኝ እህት የለኝ ሀይደርን ግን በአጋጣሚ የሰጠኝ የሚመክረኝ ጥሩ ጓደኛ ወንድም ነዉ ብየ አሰብኩ ለሀይደር ከሌሎች ወንዶች ለየት ያለ ስሜት አደረብኝ፡፡
አልፎ አልፎ የአንቺ የትዳር ምርጫ ምንድን ነዉ ብሎ ይጠይቀኛል መቼም እኛ ሴቶች ስንጠየቅ ሌላዉን በሆዳችን ይዘን በአፋችን ኢማን ያለዉ ለኔ ፍቅር የሚሰጠኝ እኔ በብር አላምንም በፍቅር እንጂ ብለን ነዉ የምንመልሰዉ፡፡ እኔም እደዚሁ ብየ መለስኩለት፡፡
.......እሱን ስጠይቀዉ ትዳር እንደሌለውና የሱ የሆነችውን ሀዋ እየጠበቀ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ በቅጡ ልለየው የማልችለው የተዘበራረቀ ስሜት ተሰማኝ፡፡

ከዛ ጊዜ በኃላ ከበፊቱ በበለጠ በጣም ተቀራርበን ማውራት ጀመርን፡፡ ብቻ ከሱ ጋር ማውራት on line ባገኘሁት ቁጥር እሱ ጋር ማዉራቱ እያስደሰተኝ መጣ፡፡ ሁሌም ሲያወራኝ ንግግሩ በቁርአን እና ሀዲስ ታጅቦ ነው፡፡ ይሄን ባህሪ ደግሞ ከቀን ወደ ቀን እየለመድኩትና እየወደድኩት መጣሁ፡፡ telegram የምገባው እሱን በመናፈቅ ሆነ ናፍቂው ሆንኩኝ፡፡

የሆነ ሰአት ላይ እዚህ ነኝ ሳይል ከTelegram ላይ ጠፋብኝ፡፡ ጨነቀኝ የት ብየ ልፈልገው ስልኩን እንኩዋን አላውቅም በምን ላስፈልገው!? ሙሉ ቀን ዳታየን አብርቸ ከአሁን ከአሁን ይገባል ብየ ብጠብቀው የውሀ ሽታ ሆኖ ጠፍብኝ፡፡ አልቅሽ አልቅሽ አለኝ! ለካ ሳላውቀው ወድጀዋለሁ ሲርቀኝ እንደወደድኩት ገባኝ፡፡ የአላህን ቃል ሰባኪ የረሱልን ሱና ተግባሪ በሆነ ሰው በፍቅር መውደቅ ምንድነው ነውሩ!? ማንም ሊያመልጠኝ የማይፈልገው እድል ነውኮ ይሄ! እናማ በእሱ ፍቅር መውደቄ ጥፍተኛ አያሰኘኝም! አወ አያሰኘኝም! ብቻየን በናፍቆት እሱን መጠባበቅ ስራየ አደረኩ፤ ግን ሙሉ ቀን ምሽቱንም ጨምሮ አልገባም፤ ምን ሆኖ ይሆን!? ማንን ልጠይቅ? የትስ ልፈልግህ!?
ጧት ትምህርት ስሄድ በፎቶ እንኳ የማላቀዉን ልጅ ወደ ትምህርት ስገባ እኔን ያየኝ ወንድ ሁሉ እሱን እየመሰለኝ አያለሁ ግን ያየሁት ወንድ ሁሉ ሂክማ ሀይደር ነኝ የሚል ድምፅ አጣሁ ....በግድ ተምሬ መምህሮቹ ምን ሁነሽ ነዉ እያሉኝ በግድ የትምህርት ክፍለ ጊዜዉ አለቀ፡፡ እቤቴም ሂጄ ዳታየን ባበራ ሀይደር የለም፡፡
ነግቶም ወደ ትምህርት ስሄድ በፎቶ እንኳ የማላቀዉ ሀይደር ሂክማ ይለኛል ብየ በተስፋ ሂጄ መንገድ ለመንገድ ብጠብቅ የለም.....ጥበቃየን ቀጠልኩ ግን አሁንም የለም ከፋኝ ደስታ ከኔ እራቀ፡፡

#part ይቀጥላል
1.2K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 10:32:23 እዉነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ ነው አብቡት

#Part 1

ሂክማ እባላለሁ ተወልጀ ያደኩት በመዲናችን አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ በሚባለዉ ሰፈር ሲሆን ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ሴት ልጃቸው ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ለኔ ያላቸው ፍቅርና ስስት በቃል የሚገለፅ አይደለም! ፍላጎቴ ሳይዛነፍ አቀማጥለው ነው ያሳደጉኝ፡፡ በጥሩ ስነምግባር በኢስላም ተርብያ ዲኔን እያስተማሩ የአንድ ብቁ እና ንቁ እሆንላቸው ዘንድ ተንከባክበው አሳደጉኝ፡፡ የኔም የዋዛ አልነበርኩም በትምህርቴም ሆነ በቂርአቴ ስለጉብዝናየ ኡስታዞቼ እና መምህራኖቼ ምስክር ናቸው፡፡ ቦሌ መድሀኒያለም preparatory school የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡ ጓደኞቼ ስለኔ መልካምነት አውርተው አይጠግቡም፡፡
መምህራኖቼ ገና በዛ የአፍላነት እድሜ 1 ብሎ በሚጀምርበት fire age ተብሎ በሚጠራው እድሜ ክልል ውሰጥ ሆኜ የባህሪ ለውጥ ያለማሳየቴ ለመምህሮቸ ትንግርት ሆኖባቸውም ነበር፡፡ ከዛም በኃላ ለኔ ያላቸው ውዴታም ክብርም ከፍ ያለ ነው! እንደ ትልቅ ሰው ጓደኛቸው አርገው ያዩኛል፡፡
አባቴ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን ሸዋሮቢት በምትባለዉ ከተማ ነበር የሚሰራው ብዙ ጊዜ ፊልድ ስለሚበዛበት ከሸዋሮቤትም ወደ ሌላ ሀገር ይሄድ ነበር እቤትም እማ ብዙ ጊዜዋን ከኔ ጋር ታሳልፍለች፡፡ አሁን ላይ ሰወች ለሚወዱት ማንነቴ ግንባታ ኡሚ ከፍተኛውን ድርሻ ትወስዳለች! ወደ መልካም ነገር የምታመላክተኝ መንገድ መሪየ ኡሚ ናት፡፡ አባቢ ለእማ ልዩ ፍቅርና ክብር አለው መልካምነቷና ብልህነቷን ያደንቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአይኑ ማረፊያ የሆነችውን አንድ ልጅን ዲኗን እንድታውቅ መንገድ መሪ ሆናት ልጅም በሰወች ዘንድ ተወዳጅ እንድትሆንለት ከፍተኛውን ድርሻ ለወሰደቾው እናቴ አድናቆቱ ከልብ ነው፡፡

እኔም "አላህ ኸይርን ሽቶልኝ ዲኔን አስገንዝቦኛል! አንድ ስህተት እንዳለኝ አቀዋለሁ የሰዉ ልጅ ነኝ እና መሳሳቴ አይቀርም ጓደኞቼ ሁሉም profile pictur የራሳቸዉን ፎቶ ስለሚያረጉ በጓደኞቼ ግፊት እኔም profile የራሴን ማረግ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ፡፡ ፎቶ መነሳቱ ሀራም መሆኑን እያወኩ ግን ጓደኞቼ ጋር ሰርግ በሚኖረን ሰአት ትምህርት ስንሄድ የማስታወሻ ፎቶ እየተባለ እየተነሳን profile ለማረግ እንቸኩል ነበር፡፡
በዛም ላይ የማላቀዉን ለማወቅ በተለያዩ social media ላይ የዳእዋ ጥሪ የሚያረጉ ግሩፓች ላይ ተሳታፊ ሆንኩኝ፡፡ whatsap እና telegram የኔ የዳእዋ ጥሪ መገልገያ ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ብዙ group ላይ እኔን add ያረጉኛልበትምህርት ቤት የሚከፈቱ የሰፈር ልጆች የሚከፍቱት group ላይ ብዙ group ገብቻለሁ አገለግላለሁ፡፡ በቦሌ priparatory scholl አንዱ ልጅ group ከፍቶ በጣም ብዙ ተከታታይ ያለዉ ኢስላሚክ group ሁኖ ነበር ከዛም ዉጭ ሌላ group ነበሩኝ፡፡ ፎቶየን እቀያይር ነበር የትዳረ ጥያቄ በቤተሰቦቼ እየመጣ ትምህርቴን ልጨርስ እያልኩኝ አሳልፊያለሁ፡፡
እናቴም ግን የዩኒቨርስቲ ዉጤት ቢመጣልሽ አትማርም ወደ ትዳር ነዉ የምገቢዉ ልጅ ወልደሽ ማየት እፈልጋለሁ እንጂ ዩኒቨርስቲ ገብተሽ ጊዜ እንድፈጂ አልፈልግም ብቻ ትምህርት እንደጨረሽ ከተቻለ አንቺ ያመጣሽዉን ባል እቀበላለሁ ግን ኢማን የሌለዉ ከሆነ እኔ የጠየቁኝ ያዘጋጀሁልሽ ትምህርቷን ትጨርስ ብየ የመለስኳቸዉ ስላለ እኔ የወደድኩትን እንደምወጂ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ፡፡
...እናት ወልይ ናት አይደል የሚባለዉ እኔም እሺ ማሚ ነበር መልሴ፡፡እኔም ተፈትኜ ዉጤት ቢመጣም ዩኒቨርስቲ ላልገባ ወስኛለሁ፡፡
ብዙ የሚያወሩኝ የማላቃቸዉ ልጆች ቁጥሬን ከየት አገኛችሁ ብየ ስጠይቅ ከGroup አድራሻሽ ነዉ ቁጠርሽ የለንም ይሉኝ ነበር ከዛ በblock አሰናብት ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነገር አጋጠመኝ፡፡ ከማላውቀው ሰው በእኔ በtelegram ቁጥር የድምፅ መልእክት ተልኮልኝ አየሁ፡፡ መልእክቱን ስሰማ ቀጥታ ወደ ፕሮፍይሉ በመሄድ ስለሱ ማንነት ለማወቅ እንዲረዳኝ ማየት ጀመርኩኝ በጠቅላላ ኢስላማዊ ፎቶወች እና ዱአ ይበዛበታል፡፡፡ እኔም ለማጣራት ያህል ነበር ፕሮፍይሉን የፈተሽኩት፡ የድምፅ መልእክቱ ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ሲሆን profile ባረኩት ፎቶ አላህን እንድፈራ ፎቶ ሀራም መሆኑን የካተተ record ነበር አነጋገሩ በጣም አስተማሪ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ነበር ተይ ያለኝ የማላቀዉ ቁጥሮች profile እያዩ ቆንጂት ሀይ የማይለኝ የለም telegram ስገባ የማላቀዉ ቁጥር ይበዛብኝ ነበር እኔ ግን አጂ ነብይ ጋር አላወራም ብየ ማንንም አላወራም ግን ምን ዋጋ አለዉ profile ከgroup እያዩት መሆኑን የተረዳሁት ዘንግቼ ነበር፡፡

በፁሁፍም ከሀዲስ ከቁርአን ማስረጃ እያቀረበ ብዙ ትምህርቶችን ላከልኝ እኔም ጀዛ ከሏህ ብየ ፎቶየን profile ያረኩትን እንዳለ አጠፋሁ፡፡
ከዛም ግን ጎበዝ ዲነኛ እንደሆንሽ አቃለሁ profile ፎቶዉ የአንቺ መሆኑን ሳይ በጣም ነዉ የገረመኝ ሂክማ መቼ ጀምራ እንደዚህ ሁነች ብየ ግራ ገብቶኝ ነዉ አለኝ
....እኔም በመደንገጥ እንዴ ከአሁን በፊት ታቀኛለህ እንዴ ????? አልኩት
እሱም........

#part ይቀጥላል
1.4K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:35:54 ልብ ወለድ ይጀመር ምትሉ
633 views18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ