2022-08-28 10:54:44
ውስጥ?››
ፈገግ አለችና ‹‹አቤላ ከፈቀደልን ካንተ ጋር የሆነ ቦታ ደርሰን እንድንመጣ ፈልጌ ነበር!›› አለች፡፡
አቤል እየሳቀ ‹‹ምን ጣጣ አለው …… ብቻ እንደትናንትናው ብዙ በር ያለበት ቤት አስገብተሽው እንዳይጠፋ!›› አለ፡፡
አቤላን ተሰናብተን መኪናዋ ውስጥ ገባን፡፡ መኪናው ውስጥ ያለው ጠረን ደስ ይላል፡፡
‹‹እሺ …… ወዴት ነን?›› አልኳት ቀበቶዋን የምታስረውን ማህሌትን እየተመለከትኩ!
‹‹you will see it! …… አንድ ቦታ እወስድሀለሁ …… unfortunetly ለዛሬ ጥናት ያልፍሀል፡፡ I hope you won’t get mad! yeah?››
‹‹እሺ ግን ይኼን ያህል ጊዜ የሚወስደው ምን ቢሆን ነው?››
‹‹please be patient!›› ሳቀች፡፡
መኪናዋን በአርባ ሜትሩ በኩል እያካለበች ጦርሀይሎችን አልፋ …. ቶታልን ዞራ …. ሞቢል ጋር የሚገኘው ካልዲስ ኮፊ ግቢ ውስጥ ቆመች፡፡
አስተናጋጁ ሲመጣ ለእኔም ለእሷም አዘዘች፡፡ ምን እንደምፈልግ አልጠየቀችኝም፡፡ የመኪናውን መስታወቶች ዘጋቻቸው፡፡
‹‹አብርሽዬ …… እስኪ just tell me ምን የጎደለኝ ይመስልሀል?››
‹‹እኮ አንቺ?››
‹‹yeah እኔ!››
‹‹አትቀልጂ ባክሽ! ምንም ነዋ! ምንም ነው የጎደለሽ!›› ሳቅ አለች፡፡
‹‹I was የአምስት አመት ህፃን ምናምን ነገር when my mom dies! Dad single parent ሆኖ ነው ያሳደገኝ!››
‹‹እናትሽ ሞታለች እንዴ? ይቅርታ አላወቅኩም ነበር!››
‹‹Its okay! Its okay! Feel free!››
‹‹ወንድምም ሆነ እህት የለኝም፡፡ I am the only one! …… Dad is በጣም busy! ስራውን ቤት ሳይቀር ነው የሚሰራው! Somedays በጣም ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር፡፡ ለኔ ብሎ ድጋሚ አላገባም! He is married to his work! የኛን ቤት ስታይ ይህን ገምተሀል?››
‹‹በፍፁም! በፍፁም አልገመትኩም!››
‹‹So እኔም እንዳንተ ፈጣሪ ከኔ ጋር መልካም ግንኙነት የለውም ማለት እችላለሁ አይደል?›› ሳቀች፡፡
‹‹የኛ እኮ በሁሉም ነው! አንቺ እኮ በአንዱ ብትከፊ ሌላ መፅናኛ አለሽ!››
‹‹ሀብታም ነን I know! ሰው ግን የለኝም! Even በእሱም ቢሆን አላማርርም!››
አስተናጋጁ ምግቡን ይዞ መጣ፡፡ ፒዛ ነበር፡፡ እየበላን ማውራት ጀመርን፡፡
‹‹Okay let’s play a game እስኪ አይንህን ጨፍንና ስለእኔ ጥሩ ጥሩ ጎኔን ንገረኝ!››
አይኔን ጨፍኜ ስለማህሌት አሰብኩ፡፡
‹‹ማህሌት …… ቀላ ያለች፣ አይኖቿ ትላልቅ፣ ፀጉሯ ረዥም፣ ሁሌ ቀሚስ የምትለብስ ……››
‹‹No! No! Come on! ግለፀኝ አይደለም ያልኩህ! ፈጣሪ ለእኔ የሰጠኝን መልካም ፀጋ ቁጠርልኝ!››
‹‹እሺ …… ማህሌት ቅን ነች! ደግ ነች! በጣም ቆንጆ ናት! ጎበዝ ተማሪ ናት! አባት አላት! የምግብ ችግር የለባትም ማለቴ የሀብታም ልጅ ናት! ጥሩ ጓደኞች አሏት! በቃ!››
‹‹Okay open your eyes. አንተ ስለኔ ሰባት ጥሩ ነገር ቆጥረሀል፡፡ አሁን የኔ ተራ ነው፡፡›› አይኖቿን ጨፈነች፡፡ አይኗን ስትጨፍን የበለጠ ታምራለች፡፡ ከንፈሮቿ ያሳሳሉ፡፡
‹‹አብርሽ …… በራሱ ይተማመናል! በጣም Genius ነው፡፡ በጣም የምታምር Smart እህት አለችው፡፡ እናቱ በህይወት አሉ፡፡ በጣም ቆንጆ ነው፡፡ amazing friends’ አሉት! በጣም ግልፅ ነው! ጥሩ ስነ-ምግባር አለው! ጤነኛ ነው!›› አይኗን ከፈተች፡፡
‹‹So እኔ ዘጠኝ ቆጠርኩ! አሸነፍኩህ ማለት ነው!››
ዘጠኝ መልካም ነገር አለኝ? አስቤው አላውቅም ነበር፡፡
ክላክስ እያደረገች ‹‹ፈጣሪን ምን አድርግልኝ ብለኸው ታውቃለህ?›› አለችኝ፡፡
‹‹አባቴን አትርፍልኝ ብዬው አውቃለሁ …… ገደለው! እህቴ ላይ መከራ አታብዛባት አልኩት …… ደራረበባት! እማዬን አሽልልኝ አልኩት …… ህመሟን ጨመረው! በጠየቅኩት ቁጥር ተቃራኒው እየሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ተውኩት! አትድረስብኝ አልደርስብህም ብዬ ማለት ነው!››
‹‹ጎበዝ አድርገኝ አላልከውም …… ጎበዝ አደረገህ! ጤናዬን አደራ አላልከውም …… ጤነኛ አደረገህ! Why don’t you see መልካም መልካሙን?››
አስተናጋጁ ትኩስ ነገር ይዞልን መጣ፡፡
‹‹የቆምኩበት ቦታ ከባድ ነው ሚቾ!››
‹‹what you just call me? ሚቾ! Wow! ወድጄዋለሁ! ሁሌ እንደሱ ጥራኝ!›› አለችና ማኪያቶዋን እየማገች ስለ ተስፋ፣ ስለ ፈጣሪና ስለህይወት ያላትን አመለካከት ታስረዳኝ ጀመረች፡፡
አብራርታ ስትጨርስ ‹‹እስኪ ያንተን ንገረኝ!›› አለች፡፡
‹‹እኔ ስለ ረሀብ ነው የማስበው! ገና ስለምግብ ነው የምጨነቀው! በባዶ ሆዴ ደግሞ አንቺ ያልሽው አይነት ተስፋም፣ ህይወትም፣ ፈጣሪም …… ሊያፈላስፉኝ አይችሉም፡፡ ፍልስፍናዬ ረሀብ ነው፡፡ ፍልስፍናዬ የእህቴ ስቃይ፣ የእናቴ ህመም ነው፡፡›› አይኔ እንባ ሞላ፡፡
ብርጭቆዋን ዳሽ ቦርዱ ላይ አስቀምጣ ጭምቅ አድርጋ አቀፈችኝ፡፡ አንገቴን ደረቷ ስር ቀብሬ አነባሁ፡፡ ስረጋጋ ሂሳብ ከፈለችና መኪናዋን አስነሳች፡፡ ጨልሞ ነበር፡፡ ወደ ሰፈር እየተመለስን ‹‹ሚቾ …… ሐዋርያት ማለት ግን ምን ማለት ነው?›› አልኳት፡፡
ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ አልኩኝ፡፡
‹‹Okay …… ሐዋርያት የእምነቱ ተከታዮች የምንጠራበት ስያሜ ነው፡፡ ቤተክርስትያናችን ደግሞ ሐዋርያዊት ነው የምትባለው!››
‹‹እሺ ሐዋርያዊት ማለት ምን ማለት ነው? ጥያቄዬ እሱ ነበር! ማለቴ ስለእምነቱ!››
‹‹ሐዋርያዊት is a religion በአንድ አምላክ የሚያምን …… በእየሱስ ስም ጥምቀት የሚያምን …… ሐይማኖታዊ ስርዓቱ የሚከበርበት or የሚተገበር እምነት ነው!››
‹‹ምንድነው ለየት የሚያደርገው?››
‹‹ያው እኛ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ ናቸው ብለን እናምለን፡፡ like ስላሴ አንድም ሶስትም በሚባለው አናምንም! አብ፣ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አንድ አካል ብለን እናምናለን፡፡ ሌላው ደግሞ ቀን መርጠን የምናከብረው በዓልም የለም፡፡ plus ስናገባ ቀለበት አናደርግም! እንደምታየው አንገቴና እጄ ላይም ምንም አይነት ጌጣ ጌጥ የለም፡፡ ጆሮዬም አልተበሳም!››
‹‹ኦው ይገርማል ›› አንገቴን በግርምት እየነቀነቅኩ ጆሮዋንና አንገቷን ተመለከትኩ፡፡ ጆሮዋም አልተበሳም፡፡ እጇም ሆነ አንገቷ ላይ ጌጥ የለም፡፡
ወደ ቤተ-መፅሀፍቱ ስንደርስ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ በሩ ጋር አውርዳኝ ተሰናብታኝ ሄደች፡፡ ወደ ቤተ-መፅሀፍቱ ስገባ አቤላ እየሳቀ ያየኛል፡፡ አንገቴን ሰብሬ ከፊትለፊቱ ተቀመጥኩ፡፡ ትንሽ ማንበብ ፈልጌያለሁ፡፡ መፅሀፌን ከፍቼ ንባቤ ላይ ሰመጥኩ፡፡ አቤላ በየመሀሉ እየሳቀ ይመለከተኛል፡፡ ሶስት ሰዓት ተኩል ሊሆን ሲል አብዱኬ መጣ፡፡ ከቤተ-መፅሀፍቱ እየወጣን አቤላ የአብዱኬን ትከሻ እየነቀነቀ ‹‹አባቴ ኢቦ ማህሌትን አፈፍ አድርጎልሻል!›› አለው፡፡
‹‹አቤላ ደሞ ምንሼ ነው? ነገር አብርድ እንጂ! ሰላማዊ ግንኙነት ነው ያለን!››
‹‹እሱ ጦርነት ነው አላለ!›› አብዱኬ ጣልቃ ገባ፡፡
‹‹ታውቂያለሽ አብዱኬ ሲዞሩ አምሽተው አሁን ነው ላይብረሪ የገባው! የት እንደነበሩ እንኳን ምንም አልነገረኝም!››
‹‹ላይብረሪ ስለነበርን ነዋ! ካፌ ነበርን በቃ ስናወራ ምናምን! ምንም አዲስ ነገር የለውም!››
‹‹ለምን አቤላን ትታችሁት ሄዳችሁ?››
መመለስ አልቻልኩም፡፡ ዝም ስል ሁለቱም ጮክ ብለው ሳቁ፡፡
ከአቤላ ጋር ተለያይተን ወደ ቤት ሄድን፡፡ ኢንቱዬና እማዬ መምጣታችንን በጉጉት ሲጠብቁ ነበር፡፡ ከሌላ ጊዜው ትንሽ አርፍደናል፡፡
የቀረበው እ
966 views07:54