Get Mystery Box with random crypto!

ያተረፍኩት የወንድም እህቶቼን ስቃይ እየሰማሁ ማልቀስን ብቻ ነው፡፡ አልደርስላችሁ ነገር እኔም ከሰ | ሀላል ትዳር👫💍

ያተረፍኩት የወንድም እህቶቼን ስቃይ እየሰማሁ ማልቀስን ብቻ ነው፡፡ አልደርስላችሁ ነገር እኔም ከሰጋጁ ተለምኖ ወር መዝለቂያ የሚሰፈርልኝ ደሀ ነኝ፡፡ ሰጋጁን ደግሞ አንድ ሁለት ቀን ገንዘብ ጠይቀነው በሶስተኛው ቀን ከደገምን ይሰለችብናል፡፡ ሁሉም ነፍሴ ነፍሴ እንጂ ወንድሜን እህቴን አይልም፡፡ በዚህ ጊዜ ኢማም ከመሆን በላይ ትልቅ መዓት የለም፡፡ አሁን እኔም የማላክመውን ህመም በመስማት ልቤ ከሚቆስል ኢማምነቴን ትቼ እብስ ማለት ይሻለኛል፡፡›› ነበር ያሉኝ! ክብሬን የማተርፍበት ጭላንጭል ተስፋ የነበረኝ እዚህ ነበር፡፡ ዛሬ እንደማይሆን አረጋገጥኩ፡፡ ያሉኝን ቢሉኝ …… ያደረጉትን ቢያደርጉ ችዬ መስራት እንዳለብኝ አመንኩ፡፡ አዎን የገሀዱን አለም እውነታ መቀበል አለብኝ፡፡ አማኝ ነኝ የሚለው ህዝብ ሂጃቧ ተገለጠ …… ገላዋ ታየ እያለ በቻለው መጠን ከፈጣሪ ጋር የማጠቋቆር ስራ ከመስራት በዘለለ ሌላ አይፈይድህም! ብትቸገር አይረዱህም! …… የተሳሳትክ ሲመስላቸው ግን በቻሉት መጠን አንተን ከፈጣሪ ጋር ለማጠቋቆር ይጣደፋሉ፡፡ ቢመርም እውነታው ይኼ ነው፡፡››
አይኖቼ በእንባ እንደራሱ በሌላ ቀን የተፃፈውን ማንበብ ጀመርኩ፡፡ በሁለቱ ፅሁፎች መሀከል ረዘም ያለ የጊዜ ልዩነት ነበረው፡፡
‹‹ኢቦዬ …… በጣም ተናድጃለሁ፡፡ ያ ቆሻሻ ሰውዬ እኮ እንደሳመኝ ለአባዬ ሰው ልኮ አስነገረው፡፡ ልጅህን ሳምኳት ብሎ አንገቱን ሊያስደፋው ሞከረ፡፡ ሰውዬው ለአባቴ ጓደኛ እንደነበር ነበር ያሰብኩት! ግን በአባቴ በጣም ይቀና እንደነበር ተረዳሁ፡፡ ሰው እንዴት ሙት ገድሎ ይፎክራል? አባዬ ረጋ ብሎ ሁሉንም ነገር ማወቁን ከነገረኝ በኋላ ድጋሚ እዮስያስ የሚባል የሰው ሰይጣን ጋር እንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፡፡ ሀኪም ቤት የሚባል ላይሄድ …… መድሀኒትም ላይወስድ ምሏል፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ እኔን ትተሽ ለወንድምሽ እና ለእናትሽ በአቅምሽ የምትችይውን አድርጊ፤ እሱን ማድረግሽ ለእኔ ከበቂም በላይ ነው፡፡›› አለኝ፡፡ ሌላ ምን አደራ እንዳለኝ ታውቃለህ? ‹‹ጓደኛ ስትይዢ መልካም ሰው ምረጪ! እኔ በመታመሜ በገዛ ጓደኞቼ ብዙ ገንዘቤን ተክጃለሁ፡፡›› አለኝ፡፡ አሁን አባዬን አይኔ እያየ ሲሞት ከማየት ውጪ አማራጭ የለኝም፡፡ ለመንኩት ለመንኩት ግን ሊሳካልኝ አልቻለም፡፡ አሁን በሁሉም ነገር ተስፋ እየቆረጥኩ ነው፡፡ ሩጫውም ከአቅሜ በላይ እየሆነ ነው፡፡››
ገለጥኩት፡፡ ስለአባዬ መሞት የፃፈችውን አገኘሁ፡፡ የማውቀውን ማንበብ ስላልፈለግኩ ገለጥ ገለጥ እያደረግኩ ከለቅሶው ከሁለት ወር በኋላ የፃፈችውን ማንበብ ጀመርኩ፡፡
‹‹ኢቦዬ …… ለአንተ ብዬ ባልኖር ህይወት ትቀፋለች፡፡ አንዳንዴ የሰዎች መገልገያ ከመሆን የዘለለ ዋጋ እንደሌለኝ ይሰማኛል፡፡ አሰሪዬ ሲለው እያሳሳቀ …… ሲለውም በፈጣጣው ደስ ያለውን የሰውነቴን ክፍል ይነካካል፡፡ አናቱ ላይ የወጣበት ቀን ደግሞ ሙሉ ወጪሽን ሸፍኜ ካላስቀመጥኩሽ ይለኛል፡፡ ይኼ ለሽርሙጥና የተሰጠው አዲሱ ስያሜ ይመስለኛል፡፡ በባለትዳር ነጋዴዎች ዘንድ ደግሞ በጣም እየተለመደ ነው፡፡ ከትዳራቸው ውጪ ወጣት ሴቶችን በቅምጥነት መያዝ ማለት ነው፡፡ ቤት ይከራዩላቸዋል …… ሙሉ ወጪያቸውን ይሸፍኑላቸዋል …… ሲያምራቸው ብቅ እያሉ ደግሞ ይተኟቸዋል፡፡ እኔንም እንደዛው እንድሆን ብዙ ሰው ይጠይቀኛል፡፡ ግን እናንተን ላልጠቅምበት ራሴን ማጣት አልፈለግኩም፡፡ አሰሪዬን ድንገት ተናድጄ እንኳን ሰውነቴን እንዳይነካኝ ብናገረው ከስራ ያባረኛል፡፡ ያለ ተያዥ መቅጠሩን እንደትልቅ ውለታ ይዘከዝክልኛል፡፡ ያለኝ አማራጭ ልቤ እያረረ ጥርሴን ማግጠጥ ነው፡፡ በሳቅ እያባበሉ ነገሮችን ማለፍ! እስከመች እንደሆነ አላውቅም! …… ግን ህይወት ከብዳኛለች፡፡››
ቻርጅ እያደረገች የነበረችው ስልኬ ተንጫረረች፡፡ ደብተሩን ዘግቼ ቦታው መለስኩና እንባዬን እያበስኩ ወደ ስልኬ ሄድኩ፡፡ ማህሌት ነበረች፡፡ አነሳሁት፡፡
እየተፍለቀለቀች ‹‹hey አብርሽ …… እንዴት ነህ?›› አለች፡፡
‹‹አለሁ ሰላም ነሽ?››
‹‹አለሁ እደውላለሁ ብዬ ጠፋኋ?! Sorry በጣም!››
‹‹ኧረ ችግር የለውም!››
‹‹ደሞ ላይብረሪም ጠፋህ!››
‹‹ኧረ አለሁ አለመገጣጠም ነው፡፡››
‹‹So let me come to the point ምን መሰለህ hike ማድረግ አስበን ነበር ያው ነቃ ለማለትም ትንሽ መዝናናት አሪፍ ነው፡፡ እና ቅርብ የምታውቀው ተራራ አለ እንዴ?››
ጥያቄዋ አስገርሞኛል፡፡ እኛ ህይወት ተራራ ሆናብን ተራራ ተጠግተን እንኖራለን፤ እነርሱ ለመዝናናት ተራራ ይፈልጋሉ፡፡
‹‹ማለት? ተራራ ስትወጡ ትዝናናላችሁ? ማለቴ …… እሱን ነው ነቃ እንዲያደርገን ያልሽው?›› ሳቋን ለቀቀችው፡፡
‹‹stop joking …… ባይሆን የምታውቀው ካለ ንገረኝ!››
‹‹አለ የእኛ ቤት ራሱ ተራራ ላይ ነው፡፡ የኛን ሰፈር ተራራ ትወጣላችኋ በቃ!››
‹‹ደስ ይላል በቃ this Sunday እንወጣለና! የሚያስፈልጉ ነገሮችን ላይብረሪ ስትመጣ ደውልልኝና እናወራለን፡፡››
የማህሌት ጉዳይ እያስገረመኝ ስልኬን ቻርጅ ሰክቼ ስዞር ኢንቱ ከጀርባዬ ቆማ እየተመለከተችኝ ነበር፡፡ በዚህ ሰሞን ለምን እንደሆነ ባላውቅም ቶሎ ከስራ ትመለሳለች፡፡ ከማህሌት ጋር ያወራነውን ሰምታለች መሰለኝ በስለላ አይን ቃኘችኝ፡፡ ተነስቼ ሳምኳት፡፡ ኮስተር ብላ ‹‹ማናት?›› አለችኝ፡፡ አስረዳኋት፡፡ ፈገግ አለች፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ፈገግታዋ ጥንካሬዬ ነው፡፡
እያነበብኩ እራት ሰዓት ሲደርስ ኢንቱ ምግብ አቀራረበች፡፡ እማዬ ሰፈር ጓደኞቿ ቤት አምሽታ መምጣቷ ነበር፡፡ ምግቡ እንደበፊቱ ለሶስት የሚበቃ አልነበረም፡፡
ኢንቱ አቀራርባ ስትጨርስ ‹‹እኔ በልቻለሁ እናንተ ብሉ!›› አለች፡፡
በልቻለሁ ማለቷ ገርሞኝ ‹‹እንዴ መች ነው የበላሽው ቅድም አይደል እንዴ የመጣሽው?›› አልኩ፡፡
‹‹አይ ቅድም ስራ ቦታ ምግብ መጥቶ በልተናል፡፡ ደሞ ጣፋጭ ስለነበር …… የሌለ ነው የዘጋኝ!››
እማዬም ትንሽ በልታ በቃኝ አለች፡፡ ኢንቱዬ በግድ አንድ ጎረሰችልኝ፡፡ ደስ አለኝ፡፡
መኝታችንን አነጣጥፈን ጋደም እንዳልን ስለ ኢንቱዬ ህይወት ማሰብ ጀመርኩ፡፡ በዚሁ ከቀጠልኩ ገና ሰባት አመታትን ከጫንቃዋ ላይ ላልወርድ መሆኑን ሳስብ አንገፈገፈኝ፡፡ አብዱኬ በሚለኝ መንገድ ተጉዤ እሷን ባላሳርፋት እንኳን ልደግፋት ወሰንኩ፡፡
.
ይቀጥላል