2024-04-15 18:17:37
ዛሬ Ebla 15 ነው። በመላው ኦሮሞ ልብ ውስጠ ስለ እኩልነት፣ ነጻነት እና ማንነት ሲሉ ትግል ጀምረው የህይወት መስዋእትነት የከፈሉ ጀግኖቻችንን እንድንዘክርባት በሰባዎቹ መጀመሪያ የተወሰነች እለት።
አባ ጢቂ (አቦማ ምትኩ)
ይህንን ጽሁፍ የከተብኩት ከሶስት አመት በፊት ሲሆን ለዚህ ጽሁፍ ግዜያቸውን ሰውተው ሙሉ በሙሉ ትብብር ያደረጉልኝ የአቦማ አክስት ልጅ የሆኑትና በእድሜ አቻው እንዲሁም በወቅቱ በምእራብ በኩል ሲንቀሳቀስ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት ሀይል መካከል ከነበሩት፣በእስር ቤት አስር አመት ያህል ሰቆቃ የደረሰባቸው ዛሬ በአሜሪካ የሚገኙት Daniel Daffa እና የአቦማ ምትኩ የመጨረሻዋ እህቱ Giftii Wako ናቸው)
ከቀድሞው አለመያ እርሻ ኮሌጅ ከዛሬው ሀረመያ ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ተመራቂ ተብለው ከሚጠቀሱት አንዱ ናቸው የአባ ጢቂ ወላጅ አባት አቦ ምትኩ ዋቆ፡፡ የተወለደው በወለጋ ጊምቢ ከእናቱ አዴ መርጌ ሚጀና እና ከአባቱ ምትኩ ዋቆ ሲሆን ለቤተሰቡም ሀንገፋው ልጅ ተወለደ
አቦማ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው በትውልድ መንደሩ በጊምቢ የተማረ ሲሆን፣መካከለኛ ሁለተኛ ደረጃን በፊንፍኔ፣ በወቅቱ የውጭ ተወላጆች እና የገቢ ምንጫቸው ከፍ ባለ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ልጆች በሚማሩበት American Community School" ተብሎ በሚባለው ትምህርት ቤት የተማረ ሲሆን አቦማ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ትግልም በግላጭ መታየት የጀመረው በዚያን ወቅት እንደሆነ ቅርብ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ፡፡
ገና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ ከመካከላቸው አለአግባብ የተባረረን ተማሪ ወደ ትምህርቱ ለማስመለስ ትንሹ አቦማ በትምህርት ቤቱ ያሉ ተማሪዎችን ውስጥ ለውስጥ በመቀስቀስ የትምህርት ማቆም አድማ እስከ መጥራት የደረሰና ወደ ቦሀላም መሪ ተዋናይ መሆኑ ተደርሶበት ከትምህርት ቤቱ እስከ መባረር ደርሷል፡፡
፡
ቀጥሎም ለትምህርት የተጓዘው የትምህርት ጥራቱ ጠንካራ ወደሆነው
"Akaki Adventist School" ሲሆን እስከ አስረኛ ያለውን ያጠናቀ ሲሆን አስራ አንድና አስራ ሁለትን በሀገሪቱ በደረጃ የሚወጡ ተማሪዎች ተመርጠው ወደሚገቡበት በቀደምት ስሙ "ተፈሪ መኮንን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት" ካልተሳሳትኩ የዛሬው (Entoto Academic, Technical and Vocational School)ሲሆን የአቦማ ምትኩ ስለ ብሄር ብሄረሰቦች የነጻነት ጥያቄም በግልጽ መቀጣጠል የጀመረበት ሰአት ነው፡፡ በወቅቱ ያመራው እስከዛሬም በዩኒቨርሲቲው አነጋጋሪ ዉጤት ወዳመጣበት በቀድሞው አጠራር ስሙ "Haile Selassie University" ነው፡፡
አቦማ በተፈሪ መኮንን አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ የተማሪ ሊደር በነበረበት ሰአት ፋርማሲስት እየተማረ የነበረውና የአክስቱ ልጅ ግርማ ደፋ ጀሞ በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጠንካራ የነጻነት ትግል አቀንቃኝ በመሆኑ የርሱን አርአያ የተከተለ ጭምር ይመስላል፡፡
1953 "ንጉስ አይወቀስ " የተባለውን ስርአት ባለመቀበል የበሰበሰውን የዘውድ ስርአት ወንድማማቾቹ ጀነራል መንግስቱ እና ገርመሜ ንዋይ መገርሰስ እንደሚቻል በተግባር አሳይተው በማለፋቸው በየ አቅጣጫው የነጻነትን ቀንዲል ለማብራት ተማሪው ንቅናቄውን አጠንክሮታል፡፡
አቦማ ምትኩ የሶስተኛ አመት ተማሪ በነበረበት ሰአት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው የዩኒቨርስቲው ሴክሬተሪ ጀነራል ውድድር ላይ ከቀረቡት ውስጥ
መለስ ዜናዊ
ገላሳ ዲልቦ
አቦማ ምትኩ
መለስ ተክሌ (የቀድሞው ጠ/ሚ ለገሰ ዜናዊ ስማቸውን የተዋሱት በተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት ከፍተኛ ተወዳጅነት ከነበረው እና በመጨረሻም ከነ ጀነራል ታደሰ ብሩ ጋር በአንድነት ከተረሸነ የትግራይ ክልል ተወላጅ ተማሪ መሆኑ ይታወቃል)
በመጨረሻም ማጣራቱን አልፈው ለውድድር የቀረቡት የወቅቱ ለገሰ(መለስ ዜናዊ ) እና የምትኩ ዋቆ ልጅ አቦማ ነበር፡፡ በቅድሚያ የጥናት ጽሁፉን ያቀረበው አቦማ ምትኩ ሲሆን በአዳራሹ የተሰበሰበው ማህበረሰብ አፍዝ አደንዝዝ ያላቸውን እና ውስጠትን ሰርስረው ሚገቡት የአቦማ መልእክት እንደተመሰጠ ተራው የለገሰ (መለስ) ዜናዊ ተሰጠ፡፡ መለስ እዚህ ጋር ትልቅ የሆነ ብልጠትን ነበር የተጠቀመው፡፡ እርሱ ጭምር በአቦማ የጽሁፍ አቀራረብና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሰጠውን ግምት ውጤት እንደማይቀለብስ በመረዳቱ ወደ መነጋገሪያው ቀረብ በማለት እንዲህ አለ
" ለአቦማ ምትኩ ካለኝ ክብር አንጻር ውድድሩን አቋርጫለሁ"
1966 አቦማ ምትኩ የሀይለ ስላሴ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሲሆን ምክትሉ ጌታቸው በጋሻው(በአሁኑ ሰአት ፕሮፌሰር ሲሆኑ ኑሯቸውን ያደረጉት በቺካጎ ነው፡፡ ጌታቸው በወቅቱም የደርግ አባል ከነበሩትና በሚስጥር የኢህአፓ አመራር ከነበሩት መ/አ አለማየው ሀይሌ ጋር በኢህአፓ የታቀፈ ነበር)
አቦማ ምትኩ በዚህ ወቅት በቤታቸው ጭምር ከነ ባሮ ቱምሳ ጋር በኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ላይ መመካከር ከጀመረ ሰንበትበት አድርጓል፡፡ ወቅቱ ደርግ የንጉሱን ስርአት በአዝጋሚ መፈንቅለ መንግስት አሰወግዶ ራሱን ለማደላደል በሚሯሯጥበት ሰአት በድርጅት መልክ ስለ ህዝቦች ነጻነት የሚያነሳበትና ህዝቡን የማንቀሳቀስ አቅም ያለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ብቻ ነበር(እነ ኢህአፓ ጭምር በግልጽ አልወጡም) የዩኒቨርስቲው የተማሪ መማክርት ለደርግ ፈተና ሆኑበት፡፡
አይደፈሩም የተባሉትን ንጉሰ ነገስት ከቤተመንገስት ለማውጣት ከተላከው ቡድን ውስጥ ወታደሩ በፍርሀት ቆፈን ሲያቀረቅር ደፈር በማለት የደርጉን ውሳኔ በንባብ ለንጉሱ ያሰማው (በወቅቱ የፖሊስ ሰራዊት ሻለቃ ማእረግ የነበረው ደበላ dhiንሳ) ደርግ አቦማ ምትኩን እንዲለሳለስ ለማድረግ እና ከደርግ ጋር እንዲሰራ ምሽት ላይ በአቦማ ቤተሰቦች ቤት በመምጣት ብዙ ጣረ፡፡ የአቦማ አሳማኝ ክርክሮች ግን ደበላን እስከማሳመን ነበር የደረሱት፡፡
ደርግ በዩኒቨርሲቲ ተማሪው ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ፡፡ በዚህ ሰአት እነ ኤለሞ ቂልጡ ጭምር ወደ ፊንፍኔ ተጠርተው በድብቅ የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን መሰረቱ፡፡
ፊንፍኔ ላይ የተመሰረተው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የመጀመሪያዋን ግዳጅ ለአቦማ ሰጠው። በእርግጥ ለአቦማ ከባድ ሚሸን ነበር። የደርግ አባላት እየተመላለሱ አባላቸው እንዲሆን ከጠየቁት እና በወቅቱ መንግስቱ ሀይለማርያም ከመሰረተው "ሰደድ" የተባለውን ድርጅት ሽፋን ለማድረግ እንዲቀላቀል ነበር የታዘዘው፡፡ አቦማ አላመነታም፡፡በመጨረሻ አቦማ ሰደድን ሽፋን በማድረግ እንደፈለገው መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጥንስስ ሰራዊት መሳሪያ መሰብሰብ ትልቁ ተልእኮው ነበር፡፡ ይህን እያሳካ ባለበት ሰአት ግን በአንድ የኦሮሞ ጥላቻ እንደዛሬዎቹ ከሚያንዘርዝራቸው አንድ የሻለቃ ማእረግ ያለው ሰው በእነ አቦማ ቤት በድብቅ ለኦሮሞ ነጻነት ግንባር እንደሚሰራ ይጠረጥረውና ሶስት ሰዎች እርምጃ እንዲወስዱበት ትእዛዝ ወረደ፡፡ አቦማ ምትኩ ንፋስ ስልክ አከባቢ እየነዳ በነበረበት ሰአት በመኪና ተከተሉት ፍጥነቱን ጨምሮ ለማምለጥ ሞከረ። በስድስት ኪሎ አድርጎ ግብጽ ኤምባሲ አከባቢ ካለችው ኮፊ ሀውስ ፊት ለፊት ወደምትገኘው የቤተሰቦቹ ቤት ሲደርስ ሶስት ክላሽንኮፍ የታጠቁ በአቋራጭ ቀድመውት መግቢያውን ዘግተው ቆመዋል፡፡
13.2K viewsGumaa Saaqataa, 15:17