Get Mystery Box with random crypto!

Gumaa Saaqqataa

የሰርጥ አድራሻ: @gumaaoro
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.17K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-02-20 19:45:13
ARSENAL አስመላሽ ኮሚቴ Loading....
19.4K viewsGumaa Saaqataa, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-20 14:48:35
ሀብታሙ አያሌው ይህን ከለጠፈ ቦሀላ ከደቂቃዎች በፊት አጥፍቶታል
20.2K viewsGumaa Saaqataa, 11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-19 21:26:33
ከምንም በላይ የሚያጠነክረን ለኦሮሞ ያላቹ ጥልቅ የሆነ ጥላቻ
19.5K viewsGumaa Saaqataa, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-19 20:00:55
ኧረ ቢያንስ አቅጣጫው እንኳ እየተነገረን እንጂ
19.9K viewsGumaa Saaqataa, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 22:31:59
gareen Gammachuu Kumsaan durfamu barsiistuu Caaltuuf badhaasa jajjabinaaf ta’a jedhee amanu laateeraaf.

Barsiistuu Caaltuun dhalattuu Finfinneeti. Abbaan ishee sababa Oromummaan mana hidhaa keessatti miidhaan irra gahee du’e.
Caaltuun Ijoollee Oromoo eenyummaa isaan beekanii akka guddataniif xiiqii cimaa nama qabdu dha.
GALATOMAA
17.3K viewsGumaa Saaqataa, 19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-05 18:07:57 ........ሆርዶፋ ጨንገሬ .....

ወቅቱ የሞሶሎኒ ሀይል ሀገራችንን ለሁለተኛ ግዜ የወረረበት ወቅት ነው። ንጉሱ የቅርብ መኳንንቶቻቸውን አስከትለው በባቡር ጂቡቲ ደርሰው የእንግሊዝን ተዋጊ መርከብ ተሳፍረው ወደ እንግሊዝ ሸሽተዋል። ከቀሩት ራስ ደጃዝማች፣ፊታውራሪ ቀኛዝማች ከፊሎቹ ህሊናቸውን ለኢጣልያ ሊሬ ሸቅጠዋል። በዚህ ወቅት ከነበሩት ራሶች መካከል አንዱ ራስ ሀይሉ ፊንፍኔ ላይ ከኢጣልያ መኮንኖች ጋር አንድ ክርክር ውስጥ ይገባሉ። ይኸውም፣
"በፈረስ ጉግስ እና የፈረስ ላይ ውግያ እኛ እንበልጣለን" የሚል እሰጥ አገባ ።

ጣልያኖቹ በራሳቸው በኩል በፈረስ ውግያ ጎበዝ የተባለው ተመርጦ አቀረቡ። ራስ ሀይሉም ፍለጋቸውን ከጎጃም ጀመሩ። የተባለውን ሰው ግን ማግኘት አልቻሉም፣በመቀጠልም ወደ ጎንደር እና መንዝ ዙሪያ ደጃዝማቾቻቸውን አሰማርተው "ጠንካራ በፈረስ ላይ ውግያ" የሚታወቅ ጀግና ፍለጋ ብዙ ማሰኑ። ፍለጋቸው ግን ሊሳካ አልቻለም። በቁጥር ሶስት ያህል ያገኟቸውም ፍልሚያው እንደማንኛውም ጉግስ በዱልዱም ልምጭ የሚወረወር ሳይሆን ተመሳሳይ መጠን ባላቸው ስል ጦሮች ሲሆን ህይወትን እስከማጣት እንደሚደርስ ሲሰሙ ድምጻቸውን አጥፍተው ተሸሸጉ።

የቀጠሮው እለት በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ብቻ እየቀሩት ነው። ራስ ሀይሉ በአሳዳሪዎቻቸው የኢጣልያ ሹማምንት መሳቂያ ሊሆኑ ሆነ።

በመጨረሻ የራስ ሀይሉ የቅርብ አማካሪዎች ፈራ ተባ እያሉ አንድ ነገር አማከሯቸው
"ለምን ሩቅ ሳንሄድ በዚሁ አከባቢ ካሉ ፈረሰኞች ውስጥ አንፈልግም" ሲሏቸው
ራሱ በማናናቅ "እስቲ ሞክሩ" በማለት ፈቀዱላቸው።

ደጃዝማቾቹ እሩቅ መሄድ አላስፈለጋቸውም
ወደ ሆለታ በማቅናት የሚፈልጉትን አይነት ሰው በአከባቢው ላሉ ተወላጆች ሲገልጹላቸው ማንን ከማን እንደሚመርጡ ተቸገሩ።

ከብዙ ክርክሮች በኋላ ሁለት ሰዎች በፈረስ ተዋጊነታቸው የላቁ እንደሆነ ሁሉም ተስማማባቸው።
ገረሱ dhuኪ እና ሆርዶፋ ጨንገሬ።
ገረሱን ግን በወቅቱ ሊያገኙት የሚቻል አይነት አይደለም። ገረሱ dhuኪ የኢጣልያንን ሰራዊት እንቅልፍ ከሚነሷቸው አርበኛ በመሆኑ ያለው ጫካ ነው። ስለዚህ የሁሉም ምርጫ ሆርዶፋ ጨንገሬ የተባለ እድሜው በአስራዎቹ መገባደጃ ላይ የሚገኝ ወጣት ሆነ።

መልእክተኞቹ በቀጥታ ወደ ሆርዶፋ ጨንገሬ በማምራት የመጡበትን ሲነግሩት ወጣቱ ሆርዶፋ አንዳች አላንገራገረም።
......
ፍልሚያ የሚደረግበት ስፍራ የኢጣልያ ጀነራሎች ከፍ ተደርጎ በተሰራላቸው መድረክ ላይ ከፊት ተደርድረዋል።ከኋቸው የኢትዮጵያ ራስ እና ደጃዝማቾች እንደየ ማእረጋቸው ተቀምጠዋል።

ከኢጣልያ በኩል የተመረጠው ተዋጊ መኮንን ግዙፍ ፈረሱ ላይ እንደሆነ ብቅ ሲል ከየአቅጣጫው የድጋፍ ፉጨትና ጭብጨባ ጎረፈለት።

ብዙም ሳይቆይ በኦሮሞ ፈረሸኞች የታጀበው ትንሹ ሆርዶፋም በሌላው አቅጣጫ አንደ ገመገም በሚሰማ የአጃቢዎቹ ዘፈን ፈረሱን እያስገሰለ በቦታው ደረሰ።

ዳኞች ሁለቱን ተፋላሚዎች ነጥለው ወደ መካከል በመውሰድ የፍልሚያውን ህግጋት እየገለጹላቸው ነው...

"በቅድሚያ አባራሪውን ለማወቅ እጣ ይጣልና እጣው የደረሰው ሰው አባራሪ ይሆንና ለሁለቱም በታደላቸው ተመሳሳይ ጦር የፍልሚያ መጨረሻ መስመር ድረስ ባለው ውስጥ አባርሮ ይወጋዋል።
ተባራሪውም ከፊት ሆኖ እየጋለበ በተሰጣቸው ተመሳሳይ ጋሻ ከአጥቂው እስከተሰመረላቸው መጨረሻ ድረስ ይከላከላል።

ተባራሪው በአባራሪው ጦር ሳይወጋ እራሱን ተከላክሎ መጨረሻው መስመር ላይ ከደረሰ በቀጣይ እርሱ አባራሪ ሆኖ ከሁዋላ አጥቂ ይሆናል"

ሁለቱ ተወዳዳሪዎች እና ዳኞች ባሉበት እጣው ተጣለ።
ሆርዶፋ ጨንገሬ እድለኛ አልነበረም። እድል ለኢጣልያዊው መኮንን ደረሰች።
ሆርዶፋ ጨንገሬ ተባራሪ ሊሆን ነው።

እድል የዞረችበት የሜታው ወጣት ፊቱ ላይ አንዳች ለውጥ አይታይም።የፈረሱን ልጓም ለቀቅ በማድረግ በተዘጋጀለት መስመር ላይ እንደቆመ አባራሪው ከሁዋላው የሚያብረቀርቅ ጦሩን በሆርዶፋ ጨንገሬ ጀርባ ላይ ወድሮ እንደያዘ "ጀምር" የሚለው የጥይት ተኩስ ተተኮሰ።
ራሱን የሚከላከልበትን ጋሻ በአባራሪው አቅጣጫ በግራ ክንዱ ያሳሳመው የጨንገሬ ደቦል አይኖቹን አባራሪው ላይ እንዳደረገ ወደ ፊት መጋለብ ጀመረ።

የኢጣልያዊው መኮንን ጦሩን እንደሰበቀ ግዙፍ ፈረሱን በሆርዶፋ አቅጣጫ ሽምጥ አስጋለበው።
ተመልካቹ በጠቅላላ ከመቀመጫው ተነስቶ በሰከንዶች ውስጥ ሊከሰት የሚችለው ትንፋሽ አሳጥቷቸው እየተጠባበቁ ነው።

ኢጣልያዊው ፈረሰኛኛ ወደ ሆርዶፋ እየቀረበ ነው። የሚያብረቀርቀውን ጦር በሆርዶፋ ላይ ሊቀበቅበው ይበልጥ ተጠጋው ። የሆርዶፋ አይኖች አጥቂው ላይ እንደተተከሉ ወደ መጨረሻው ሊቃረቡ በተጠጉ ቅጽበት ኢጣልያዊው መኮንን ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ከኮርቻው ቀና በማለት አልሞ በሜትሮች ቅርበት ውስጥ እንዳለ ጦሩን ሲወረወረው ሆርዶፋ ጨንገሬ በአይን ቅጽበት ተሽከርክሮ ከፈረሱ ሆድ ስር ገብቷል። የተወረወረው ጦር በፈረሱ አናት ላይ በማለፍ መሬቱ ላይ ተሰነቀረ።
በቦታው የነበረው ህዝብ ያየውን ለማመን ተቸግሮ ባለበት ሆርዶፋ ጨንገሬ ተመልሶ ከፈረሱ ኮርቻ ላይ እንደተቀመጠ የመጨረሻው መስመርን እየጋለበ ጨረሰ።

የኢጣልያ ሹማምንት በንዴት ኮፍያቸውን አሽቀነጠሩ።

.....
ተራው ሆርዶፋ ጨንገሬ አባራሪ የሚሆንበት ነው። በላብ የተጠመቀው ኢጣልያዊው መኮንን ከሆርዶፋ ፊት በመሆን
መከላከያ ጋሻውን እንደ ወደረ" ጀምሩ" የሚለው ተኩስ እኩል ሸመጠጠ።

ኢልመ ጨንገሬ በእልህ የፈጠጡ አይኖቹን በኢጣልያዊው ላይ እንደተከለ ተከተለው። ኢጣልያዊው መርበትበት ይታይበታል። ከቅምጡ ቀና እንዳለ ፈረሱን ወደ ኢጣልያዊው ለማስጠጋት ልጓሙን ዘወር በማድረግ ለቀቀው። ጦሩን አጥብቆ እንደያዘ እጁን ከፍ ሲያደርግ ኢጣልያዊው ሆርዶፋ የሰራውን የማምለጥ ስልት ለመሞከር እና ከሚወረወርበት ጦር ለማምለጥ ሞከረ።
ግና አልተሳካለትም። ሆርዶፋ ጨንገሬ የወረወረው ጦር መኮንኑን ከፈረሱ ግላስ ጋር እንደሰፋው ራሱን መቆጣጠር ሳይችል ቀረ ። በኢጣልያዊው ሽንጥ የተቀበቀበው ጦር የወጣው ህይወቱ ካለፈች ቦሀላ ነበር።

ሆርዶፋ ጨንገሬን ያጀበው የሜታ ፈረሰኛ ወደ ሰፈሩ ሲመለስ እንዲህ በማለት እየጨፈረ ነበር
Ordofaa Cangaree ሆርዶፋ ጨንገሬ
Diimaa akka barbaree ቀዩ እንደበርበሬ
Xaaliyaanii qabee ጣልያኑን ይዞ
Ganyaatti danqaree! በሽንጡ ቀበቀበው
.

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው የካሳ ተሰማ የመጀመሪያው የሸክላ ዘፈኑ ላይ እንዲህ በማለት አስታውሶታል
.
.
ሆርዶፋ ጨንገሬ እንደገራው ፈረስ
ጡቷ ደንገላሳ ይላል መለስ ቀለስ።
13.5K viewsGumaa Saaqataa, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-04 19:51:42
Witness the bravery of Oromo horsemen, known for their fearless riding skills and strong bond with their horses.
12.7K viewsGumaa Saaqataa, 16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-30 20:32:53
12.7K viewsGumaa Saaqataa, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-30 19:23:48
ሰርግ ላይ በባረቀ ጥይት 4 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ
አማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ልዩ ቦታው ከተማ አገር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ባሳለፍነው እሁድ(19/05/2016) ሠርግ ላይ የ 4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

መንስኤውም ሰርጉ ላይ የነበረ አንድ ሚኒሻ ጥይት ባርቆበት የተፈጠረ ነው ተብሏል።
12.6K viewsGumaa Saaqataa, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-30 17:42:56
ፈረሰኛው
እንጅባራው...
AGEW
12.7K viewsGumaa Saaqataa, 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ