2023-10-25 02:52:50
የተወለዱት በምእራብ ሸዋ ከፊንፍኔ 62 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሆለታ እና ጊንጪ መካከል ከምትገኘው ኦሎንኮሚ በ1942 ነው። ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ።
ገና በህጻንነታቸው ወላጆቻቸው በመለያየታቸው ወላጅ እናታቸው ወ/ሮ ሞቲ አያኖ ልጆቻቸውን የማሳደጉን ሀላፊነት ብቻቸውን ተሸክመው ጠላ በመሸጥ ህይወትን ተጋተሩ።
እኩዮቹ ወደ ቄስ ትምህርት ቤት ሲሄዱ አብሬ ካልሄድኩ በማለት ቢያስቸግራቸው ወደ መምህሩ በመሄድ "እኔ ምስኪን ነኝ ለልጄ የትምህርት ቤት የወር ክፍያ የሚሆን ሶስት ብር ማግኘት አልችልምና እባካችሁ አንድ ብር አርጉልኝና ልጄ እንደ እኩዮቹ ተምሮ ይግባ" ብለው መምህሩን ጠየቁ። የእናት ልመና ምን ማለት እንደሆነ የገባቸው መምህር በጠየቁት መሰረት በወር አንድ ብር ከፍለው ልጃቸው እንዲማር ፈቀዱላቸው ። በዚህም መሰረት የዛሬው አለም አቀፋዊ ተመራማሪ ገቢሳ እጀታ ከፊደል ገበታ ጋር ተዋወቀ ። ዛሬ ለእልፍ አለም አቀፍ ሽልማቶች ባለቤት የሆነው ሰው ህይወት ኡደትም አሀዱ ማለት ጀመረች።
እስከ 7ኛ ክፍል የተማሩት እዛው ኦሎንኮሚ ሲሆን ስምንተኛ ክፍል በአካባቢያቸው ስላልነበረ 20 ኪሎሜትር በእግራቸው እየተጓዙ ተከታትለዋል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ የግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ የተከታተሉ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በእፅዋት ሳይንስ ከሃረማያ ኮሌጅ በ1965 ዓ.ም ወስደዋል። በ1968 በእፅዋት ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በ1970 በእፅዋት ማዳቀል እና ዘረ መል ምህንድስና አሜሪካ ከሚገኘው ፐርዱ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት (ሶስተኛ) ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
- ከሁለት መቶ በላይ የጥናት ጽሁፎችን ለህትመት አብቅተዋል፡፡
-አራት መፅሐፎችን የአርትኦት ስራ ሰርተዋል፡፡
-ለ28 አመታት ያህል በአሜሪካ በሚገኘው ፐርዱ ዩኒቨርስቲ ያገለገሉት የአለም ሎሬት ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ ዩኒቨርሲቲው አሉኝ ከሚላቸው ተመራማሪዎችም አንዱ ናቸው።
- ከሰባ በላይ በሚሆኑ ዓለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተቋሞች ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ሰርተዋል፡፡
-ለእነዚህ እና መሰል የምርምር ስራዎቻቸው ከ17 በላይ ዓለም አቀፍዊ ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሽልማቶችን አግኝተዋል።
-በ2009 World Food Nobel Prize የተሸለሙ ሁለተኛው አፍሪካዊ ለመሆን በቅተዋል።
-African Nationality Science Hero Award ከተሸለሙ አፍሪካዊ ሰባት ተመራማሪዎችም አንዱ ለመሆን በቅተዋል።
15.8K viewsGumaa Saaqataa, edited 23:52