2024-01-29 18:36:31
( ኢትዮጵያ የክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤልን እና ደጃ/ች ባልቻ ሳፎን ትመስላለች)
ጀግናን ገድላ ባንዳን የምትሸልም ክፉ ሀገር......
ኢትዮጵያ
.
ባልቻ ሳፎ በአገምጃ ሶዶ(ወሊሶ) በሚባል ቦታ በነሀሴ ወር 1854 ዓ.ም ነው የተወለዱት።
የምኒልክ ጦር የኦሮሞ ቀዬዎችን በወረረበት ግዜ ባልቻ ሳፎና ቁሴ ዲነግዴ በእድሜ ተቀራራቢ እና ከ15 አመት በታች ነበሩ። በዚህ እድሜያቸዉ ወረራውን ለመመከት በጦርነት ዉስጥ ተሳተፉ። በወቅቱ የኦሮሞ ጦር፥ በጦር መሳርያ ተበልጦ ስለነበር የማታ-ማታ ትናንሾቹ ልጆች ባልቻና ቁሴ ዲነግዴ ለምርኮ ተዳረጉ።
.
ባልቻ የተማረከዉ በበቾ ግንባር ቆራ በሚባል ቦታ ሲሆን፥ ማራኪዉ በጎበና ዳጬ አመራር ስር በነበሩ እና ራሳቸውን "አማራ" በማለት በጠሩ ቡድኖች ነበር።
ባልቻን የማረከው ወታደር ለግላጋዉን ወጣት ባልቻን የግሉ ምርኮ በማድረግ ወደ ቤቱ ወስዶ ሰለበዉ።
.
ቁሴ ዲነግዴ (ሀብተጊዮርጊስ) የተማረከዉ በመጫ (Dandii Bishaanii) ዳንዲ ቢሻኒ በሚባል ቦታ ሲሆን፥ ማራኪዉ ደግሞ የኦሮሞ ጎሳ ስብስብ ውስጥ ከሆነዉ የጎበና ዳጬ ወታደር ነዉ። ማራኪውም እንደ ግል ምርኮ ወስዶ እቤቱ ኣስቀመጠው። በኋላ ላይ ቁሴ ብልጥና አስተዋይ መሆኑን በመገንዘብ ወስዶ ለሚኒልክ ቤተመንግስት አስረከበው። በኦሮሞ በመማረኩም ከመሰለብ አመለጠ።
.
የዘር ፍሬ እንዳይኖረው የተደረገው ለግላጋው ባልቻ ገና በ22 አመቱ ወደ አድዋ በመዝመት በጠላቶች ጭምር አስደማሚ ጀብድ ሰርቷል፡፡
የመቀሌውን ምሽግ ሰብሮ በመግባት በጠላት ምሽግ ላይ ባንዲራ የተከለው የአገምጃው የሳፎ ልጅ ባልቻ ነበር(በወቅቱ የነበረችው ባንዲራ ከላይ ቀይ መሀል
ቢጫ ከስር አረንጓዴ ሲሆን ባንዲራው ወጥ ሳይሆን ሹካ ቅርጽ ሆኖ የተሸነሸነ ነበር)
.
፡
ከአድዋ ድል አርባ አመት ቦሀላ....
ኢጣልያ ዳግም በወረረችን ሰአት ንጉሱ ሀገር ጥለው
ሲፈረጥጡ ስንቱ ራስና ደጃዝማች ለኢጣልያ አድሮ ፓስታ ሲያጣጥም በሀይለስላሴ ትእዛዝ ደቡብ ላይ የቁም እስረኛ ሆኖ እንዲኖር የተበየነበት እና በወቅቱ እድሜው ወደ እርጅና ያመራው የአድዋው የድል ፈርጥ ባልቻ ዝም አላለም።ጥቂት ተከታዮቹን አስከትሎ በትውልድ መንደሩ በመሸፈት እንቢኝ ብሎ ኢጣልያንን መተግተ ጀመረ፡፡
፡
እድሜ ለባንዳ ከቀናቶች በአንዱ ያ ፍሬ እንዳያገኝ የተደረገው ፣ በሁለቱም የኢጣልያ ጦርነቶች ከተሳተፉት በጣት ከሚቆጠሩት አንዱ የሆነው ባልቻ በጠላት ተከበበ ፡፡ ውግያው ተፋፋመ፡፡
አዛውንቱ ባልቻ አርባ አመት ያልተለየው መትረየሱ እንደ እድሜው ጥይቱን አገባዶ ነበር፡፡
፡
የጠላት ድምጾች ከባልቻ አቅራቢያ ደርሰዋል
"እጅህን ስጥ.፣ እጅህን ስጥ........"
እድሜ ያልበገረው የሳፎ ልጅ እጁን ለጠላቱ ከማንሳት ይልቅ ወገቡ ላይ ሻጥ ካደረጋት ሽጉጡ ሲያውል ባንዳና ጠላት በህይወት ሊይዘው..ምርኮ አድርጎ ዳግም ሊሸልል ተሽቀዳደመ፡፡
ባልቻ አሸነፈ።በተወለደባት እናት ምድሩ ላይ በድን ገላው አረፈ፡፡
፡
ይህ በሆነ ማግስት መሀል ፊንፍኔ አንድ ጎረምሳ ባንዳ ፣ህዝቡን በዙርያው ሰብስቦ በድምጽ ማጉያ
"..ባልቻ የተባለ ስልብ ሽፍታ ዛሬ በጀግናው የጣልያን ሰራዊት ተድምስሷል"
እያለ ሲለፍፍ ዋለ፡፡
፡
ያ ጎረምሳ ባንዳ ማነው ለምትሉ
ለኢጣልያ ጋዜጠኛ በመሆን ያገለገለ፣ኢትዮጵያ የክቡር ዶክተር በማለት የሾመችው፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ቴምብር ጭምር ያሰራለት አንቱ ተብሎ እድሜውን ኖሮ በእኛ ዘመን የሀገር መሪን በመሰለ ክብር የተቀበረው ደራሲ ከበደ
ሚካኤል ነበር::
፡
ምንጬ ደራሲ ግርማቸው ተክለሀዋርያት ባልታተመው ግለ ታሪኩ የባልቻን አሟሟት የገለጸበት ጽሁፍ ሲሆን በንጉሱ ዘመን የነበሩት አምባሳደር ብርሀኑ በጻፉት መጽሀፍ መጨረሻ ገጽ ላይ ባልቻ ሳፎ በመጨረሻዋ ሰአት ከኢጣልያ ወራሪዎች ጋር ያደረጉትን ፍልሚያ አንድ በአንድ ጠቅሰውታል
14.6K viewsGumaa Saaqataa, 15:36