Get Mystery Box with random crypto!

ግጻዌ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የሰርጥ አድራሻ: @gitsawe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.19K
የሰርጥ መግለጫ

የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-06 00:48:25
ጥቁር መልበስም አትችሉም!!
.................................
የጅማ ዩንቨርሲቲ ተማሪ ነኝ። ሰይጣን ክርስቲያኖችን ላይ እየጨፈርኩባቸው ነው ብሎ የሚያስብበት ግቢ ነው። ይገርማችኋል ነገ ጾመ ነነዌ ሲገባ የግቢው ካፌ በሬ አርዶ ሥጋ ለእራት ያቀርባል። ተማሪው ጾሙን ላለመግደፍ በበሶ እና በቆሎ በልቶ ያሳልፋል።

በግቢው ሂጃብ እስከ ጥግ መልበስ በደምብ የሚቻል ሲሆን ነጠላ ግን አጣጥፈን በትከሻችን መያዝ እንኳን አንችልም። ይሄ ማለት እግዚአብሔር ፈቅዶላቸው ሥጋ ወደሙን የሚቀበሉ ተማሪዎች ወደ ግቢ አይገቡም ማለት ነው። እንደው ከዕለታት በአንድ ቀን ድንገት ደስ ብሎን የሀገር ባህል እንልበስ ካልን እንኳን ልብሱ ላይ የመስቀል ምልክት ካለ ወደ ግቢ መግባት አንችልም።

ይኸው በግቢያችን መጾምም፣ መደሰትም፣ ማዘንም አትችሉም ተብለናል። ነጭ ነጠላም ጥቁር ልብስም ከለበሳችሁ ነገ አስራችኋለሁ እያለ ነው። አሁን ኦርቶዶክስ ላይ የተጀመረው ዘመቻ በግልጽ በጦር ነው፤ ግን እዚህ ላይ የደረስነው ለብዙ ዓመታት በጭንቅላታችን ላይ (Subconciously) ካዳከሙን በኋላ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም።

ከጾመ ነነዌ በኋላ ግን እግዚአብሔር ያነባነውን ዕንባ ተቀብሎ ሲፈርድ፣ የእኛን መጥፋት ሲተነብዩ የነበሩ ደቂቀ ሰይጣናት ሲያፍሩ ለማየት ግን ቸኩያለሁ!


"ለእመ እግዚአብሔር ምስሌነ መኑ ይክለነ?"
"እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይችለናል?"
ሮሜ 8፥31
...............................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ

#share ካደረጋችሁስ ይህንንም አድርጉልን!!
ቅዱስ ሲኖዶስም ጥቁር ልብስ ከገበያ እንዲጠፋ ብቻም ሳይሆን መከልከልም እንደተጀመረ ለብጹዓን አባቶቻችን አድርሱልን!
#onepatriarch #onesynod
https://t.me/dnJohannes
1.1K views21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 16:57:58
271ሺ ደርሰናል
ግማሽ ሚልየን መድረስ አለብን

በመንግስት መገናኛ ብዙኅን ድምጿ እንዳይሰማ የታፈነችውን ቤተክርስቲያናችን ድምጽ እናጉላ
ላልሰሙት አሰሙ!

የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel
442 views13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 01:46:08
900 views22:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 01:46:08 ፭. ለቤተ ክርስቲያን ተሰጠ ስለተባለው ይዞታና ስለ ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን የተሰጠውን ማብራሪያ በተመለከተ፣ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ከአምልኮ ሥፍራ የመሬት ይዞታ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት አራት ዓመታት ከሌሎች ቤተ እምነቶች በተሻለ መልኩ ከአንድ አንድ ሚሊዬን አርባ አምስት ሺህ ካሜ ይዞታ በላይ እንደተሰጣትና ይህም የይዞታ ስፋት ለሌሎች ቤተ እምነቶች በድምሩ ከተሰጠው በሦስት እጥፍ እንደሚበልጥ እና አዲስ ይዞታ እንደተሰጠ ተደርጎ በማስመሰል የተሰጠው ማብራሪያ ፍጹም ስህተት እና ሕዝብን የሚያሳስት በመሆኑ ሊታረም ይገባል፡፡ ይኼውም ለቤተ ክርስቲያን ተሰጠ የተባለው ይዞታ ቤተ ክርስቲያን ቀድሞውን በእጂ አድርጋ ለዘመናት ስትጠቀምበት የነበረውን ሕጋዊ ይዞታዋ እና ይሄው በካርታ ተረጋግጦ እንዲሰጥ ስትጠይቅ የቆየች ንብረቷ እንጂ እንደ አዲስ በሊዝ አዋጁ መሠረት በምደባ ያገኘችው አይደለም፡፡
ምንም እንኳን በተገለጸው ልክ አልተሰጣትም እንጂ ቢሰጣት እንኳን ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ውስጥ ከ75% በላይ የሚሆነውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ እንደመሆኑ መጠን ከሌሎች ቤተ እምነቶች በተሻለ የሰፋ ይዞታ ማግኘቷ እንደልዩ ጥቅም የሚያስቆጥር አይደለም፡፡

የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ መሆኑ እየታወቀ፣ የውጪ መንግሥታት በዕርዳታ ለመሥራት ፈቃዳቸውን መስጠታቸው በራሳቸው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደበት የተገለጸ ሆኖ እያለ፣ መንግሥት ቋሚ የገቢ ምንጭ የሚያገኝበት የቱሪስት መዳረሻ መሆኑ እየታወቀ የቤተ ክርስቲያን ሀብት ብቻ ተደርጎ ከፈረንሣይ መንግሥት የተገኘውን ድጋፍ ለቤተ ክርስቲያን እንደተሰጠ ልዩ ጥቅም በማድረግ ማቅረብ አግባብነት የለውም፡፡

፮ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልል ትግራይ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ለሚኖሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች በወቅቱ ሰጥተውን የነበረውን መግለጫ አንድም ተቃውሞ ሳይቀርብበት አሁን በኦሮምያ ለተከሰተው ይህን ያህል ተቃውሞ አግባብ አይደለም በማለት የሰጡትን ማብራሪያ በተመለከተ፡- በመጀመሪያ ደረጃ በክልል ትግራይ የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ከሰጡት መግለጫ መረዳት እንደሚቻለው እና መላው ሕዝበ ክርስቲያን እንደሚያውቀው የቤተ ክርስቲያኒቷን ሕጎችና ቀኖናዎች ጥሰው ሕገወጥ ሲኖዶስ አልመሠረቱም፤ ጳጳሳትንም አልሾሙም፣ እውነታው ይህ ሆኖ እያለ አሁን የተፈጸመውን ሕገወጥ ሹመትና መፈንቅለ ሲኖዶስ ሕጋዊ ሽፋን እንዲኖረው ለማድረግ በሚያስመስል ሁኔታ ሁለቱ የማይገናኙ ድርጊቶችን በንጽጽር የተሰጠው ማብራሪያ እርምት እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም መንግሥታችን በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልና፣ በሕግ የተሰጣትን መብትና ጥቅም በማስከበር ሕገወጡን ድርጊት ተገቢውን እርምት በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ እያሳሰበ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ጭምር የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ በደላችንን ለዓለም ሕዝብ ችግሩ ተፈቶ የቤተ ክርስቲያኒቱ መብት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ እስከ ሕይወት መስዋዕትን ድረስ በመክፈል የምናሳውቅ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶሱ ይገልጻል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

#አንዲት_ቤተ_ክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriarch
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox

"ሐዋርያት በሰበሰቡአት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን" ጸሎተ ሃይማኖት

በተረፈ ይህ ሁሉ ፈተና ስለ በደላችን የመጣ ነውና ንስሓ እንግባ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምም እንጸልይ::

Oortodooksotaa fi jiraachuun walii galaa mana kiristaanaa kan isin yaachisu hundumaaf , duula miidiyaa hawwaasaa kanan dhiyeessa.

Gara Qulqulluu Sinoodoosii dhaabachuu keenya agarsiisuuf , hundumti keenya piroofaayila keenya suuraa Eebbifamoo fi Qulqulluu Abuna Maatiyaasiin jijjiirreetu , haashtaagota kana gaditti jiranis waliin akka poostii goonuufan gaafa dha.

#Mana_Kiristaanaa_Tokkittii
#Sinoodoosii_Tokkicha
#Patiraarikii_Tokkicha

#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriarch
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox

"Duuka bu'oonni kan walitti qaban tokkittiif qulqulleettii Mana kiristaanaatti ni amanna" Hundee Amantaa

ንኦርቶዶክሳዊያንን ንሃላወ ቤተክርስቲያን ዘተሓሳስበኩም ኩልኹም ነዚ ወፍሪ ናይ ማሕበራዊ ሚዲያ ጻውዒት ይገብረልኩም ኣለኹ፡፡

ኣብ ጎኒ ቅዱስ ሲኖዶሰ ምህላውና ንኽነመልክት ኩልና ነቲ ፕሮፋይልና በዚ ናይ ብጹዕ ወቅዱስ ኣቡነ ማትያስ ስእሊ ክንቅይሮን ነዚ ኣብ ታሕቲ ዘሎ ሃሽታጋት ሓቢርና ፖስት ክንገብሮን ይሓትት፡፡

#ሓንቲ_ቤተ_ ክርስቲያን
#ሓደ_ሲኖዶስ
#ሓደ_ፓትርያርክ
#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriach
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox

ብዝተረፈ እዚ ኹሉ ፈተናስ ብበደልና ዝመጸ ኢዩሞ ንስሓ ንእቶ ብዛዕባ ሰላም ቤተክርስትያንና ንጸሊ፡፡

I make this call to everyone who is of a great concern for the EOTChurch, to be part this social media challenge.

To show that we are standing by the Holy Synod, I request that we all change our profile with this photo of His Holiness Abune Mathias and post the hashtags below together.

#eotc_one_holy_synod
#one_church
#one_patriarch
#his_holiness_abune_mathias
#oriental_orthodox

"We believe in one Holy Apostolic church"
~ Prayer of faith

All this temptation came because of our sins, so let us all repent and also pray for the peace of our church.
843 views22:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 01:46:08 በሕገ መንግሥቱ መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸው በግልጽ የተደነገገ እንደመሆኑ መጠን መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ላይ እጁን ማስገባት እንደሌለበት የምናምንበት ሐቅ ሲሆን ከዚህ ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ውጭ በሆነ መንገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የተፈጸመውን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ጥሰትን እንደተራ ግጭት እና የግለሰቦች አለመግባባት በመቁጠር ትንታኔ ለመስጠት የተሄደበት ርቀት ሲታይ በአሁኑ ሰዓት ሕጋውያን የሆኑትን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ተልዕኳቸውን ከኤርፖርት ታግተውና ለሃይማኖታዊ አምልኮ የተሰበሰበውን ሕዝበ ክርስቲያን አዝኖ እንዲበተን በማድረግ ለአንድ አንጋፋና የሀገር ባለውለታ ሊቀጳጳስ የማይመጥን እንግልትና ማዋከብ መደረጉ ሳያንስ ይባስ ብሎ ለሕገወጡ የቡድን አባላት ለአብነትም ያህል በምዕራብ ወለጋ፤ በምሥራቅ ወለጋ፣ በቄለም ወለጋና ሆሮጉድሩ ዞኖች በኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የልዩ ኃይል አባላት ልዩ የፓትሮል እጀባና እንክብካቤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ ተቋማት በሕገወጥ መንገድ ተደፍረው እንዲገቡ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአምልኮና የአስተዳደር ተቋማት ተሰብረው በሕገወጥ ቡድኖች እንዲወረሩ መደረጋቸው፤ ይህን ሕገወጥ አድራጎት የተቃወሙትን የቤተ ክርስቲያኒቱን የሃይማኖት አባቶችና የአስተዳደር ሠራተኞች ለእስር እንዲዳረጉ መደረጉ፣ ሕጋዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ተሽከርካሪ መኪኖች ለማንኛውም
አገልግሎት እንዳይንቀሳቀሱ፣ በክልሉ መንግሥት አመራር ተሰጥቷል በሚል እገታ መከናወኑ ሲታይ መንግሥታችን ሕገመንግሥታዊ ጥስት በመፈጸም በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱንና በእርሱም ይሁንታ መፈንቀለ ሲኖዶስ እየተከናወነ እንዳለ እምነት የሚያሳድር በመሆኑ ይህ አድራጎት እንዲታረምና መንግሥት ኃላፊነቱን በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልናና መብት እንዲያስከብር ንብረቶቿ በሕገወጥ ቡድኖች ከመወረር እንዲጠብቅ፣ በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት የቤተ ክርስቲያኒቱ ብፁዓን ሊቃነጳጳሳትና የሥራ ኃላፊዎች ያለምንም እንግልትና የደህንነት ስጋት ተመድበው ሲሠሩባቸው በቆዩበት አህጉረ ስብከት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃና የሕይወት ዋስትና እንዲያረጋግጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

፪. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቀደምት ሥርዓተ መንግሥታትን በዋቢነት አሁናዊው የብልጽግና መንግሥት በውጭ የነበረውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቅዱስ ሲኖዶስ በእርቅ አንድ ማድረጋቸውን ሲገልጹ በሀገር ውስጥ ሁለት መንበርና ሁለት የፕትርክና መሪነት እንደነበረ የሰጡትን ማብራሪያ በተመለከተ፡- በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር በወቅቱ በነበረው ፖለቲካዊ ሁኔታ የተከሰተውን ልዩነትና የሲኖዶስ መከፈል በእርቀ ሰላም ማለቁ የማይካድ ሐቅ ቢሆንም በተፈጸመው የእርቅ ስምምነት ውሳኔ መሠረት በግልጽ እንደሰፈረው ሁለት ፓትርያርክ በአንድ መንበር ላይ የነበረ ሳይሆን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ክብራቸው ተጠብቆ በጸሎትና ቡራኬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በአባትነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ የመሪነት ሥራን በአባትነት እንዲመሩ በግልጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወስኖ በውሳኔው መሠረት ተግባራዊ የሆነና በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር የሚታወቀውን እውነታ በሚንድ መልኩ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአንድ መንበር ሁለት ፓትርያርክ ሲመራ ቆይቷል ተብሎ የተገለጸበት አካሄድ በእውነታ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን

በአሁኑ ሰዓት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ አሠራር በመጣስ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈጸመውን "ሢመተ ጵጵስናና መፈንቅለ ሲኖዶስ ሕጋዊ ሽፋን ለመስጠት የተደረገ ከመሆኑም በተጨማሪ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተወግከው የተለዩት ግለሰቦች ቀድሞውንም ሹመቱን ፈጽመን በዕርቅ እና በድርድር አንድ እንሆናለን : በሚል ሲገልጹት የነበረውን ሀሳብ የሚያረጋግጥና አሁንም በድርድር ሃይማኖታዊ መመሪያችሁን ጥሳችሁ ቀኖናዊ ሥርዓታችሁን አፍርሳችሁ፤ አስተዳደራዊ መዋቅራችሁን ንዳችሁ ተቀብሏቸው እንደማለት የሚያስቆጥር ማብራሪያ አዘል መመሪያ እርምት እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

፫ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተፈጸመው የእርቀ ሰላም ሂደት ወቅት በውጭ ሀገር የነበሩት አባቶች ሹመታቸው ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ሀገር ሊገቡ የቻሉት በየደረጃው አገልግሎት ሲሰጡ በመቆየታቸው ነው በማለት የሰጡትን በተመለከተ፡- በውጭ የነበሩ ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት በእርቀ ሰላሙ ወደሀገር ተመልሰው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሊሆኑ የቻሉትና ተቀባይነት ያገኙት ሹመታቸው የተከናወነው በቀኖና ጥሰት ሳይኖን በሕጋዊ ፓትርያርክ የተፈጸመ ሲመት ከመሆኑም በላይ በስደት ሊቆዩም የቻሉት በወቅቱ በተፈጠረው የፖለቲካ ጫና እየታወቀና ከአሁኑ ሕገወጥ፣ ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መሠረት የሌለው ሹመት ጋር ግንኙነት የሌለው ሆኖ እያለ ሕጋዊውን ከሕገወጡ ጋር በማቀላቀልና በማነጻጸር የተሰጠው ማብራሪያ እርምት እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያሳስባል።

0 ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው በቋንቋ የመገልገል መብትን መንግሥት ማፈን አይችልም በማለት የተሰጠው ማብራሪያ በተመለከተ፡- እናት ቤተ ክርስቲያን ዘመን ተሻጋሪ ታሪኳ እንደሚያረጋግጠው የቋንቋ አገልግሎትን በሕጎቿ እውቅና የሰጠች፣ ከዚህም አልፎ በተለይም ግለሰቦች በተደጋጋሚ በሚጠቅሱት በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ለሚኖሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የእምነት ተከታዮች የቋንቋ አገልግሎት ስትሰጥ የቆየች በመሆኑ በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን

የአምልኮና የሥርዓት መጻሕፍቶች በኦሮምኛ ቋንቋ በማስተርጎም ለአገልግሎት ያበረከተች፣ ሕገወጥ ሹመቱን ከፈጸሙት ሦስቱ የተሻሩት ሊቃነጳጳሳት ጨምሮ በርካታ የቋንቋው ተናጋሪ ብፁዓን ሊቃነጳጳሳትን በክልሉ ባሉ አህጉረ ስብከት መድባ አገልግሎት እየሰጠች የክልሉን ተወላጆች በቋንቋቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን እውቀት ቀስመው ለአገልግሎት ብቁ እንዲሆነ መንፈሳዊ ኮሌጆችን በመክፈት፤ በሁሉም አህጉረ ስብከት የካህናት ማሠልጠኛ ተቋማትን አደራጅታ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አገልጋይ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ እና _ ሰባክያነ ወንጌል አስተምራ ለአገልግሎት አሰማርታ እያለች የቋንቋ አገልግሎትን እንደተቃወመችና ለአገልግሎቱም በሯን እንደዘጋች በሚያስቆጥር ሁኔታ የተሰጠው ማብራሪያ ከእውነታቸው የራቀና የሕገወጥ ሥልጣን ፈላጊዎችን ሕገወጥ አካሄድና መግለጫ እውቅና የሚሰጥ አድራጎት በመሆኑ እርምት እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያሳስባል።
588 views22:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 01:46:08 ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለሚኒስትሮችና ለካቢኒ አባላት በሰጡት የወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ አስመልክቶ ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ።
ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም.
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ
መግለጫ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ምልዓተ ጉባኤ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ደሙ ወረዳ ሀሮ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ የሃይማኖት፣ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰት አስመልክቶ በሰፊው ተወያይቶ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት ልዩ ልዩ ሕግጋት ውጭ ጳጳስ ሾመናል ባሉ አካላት እና ተሹመናል በሚሉት አካላት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግጋት በሚፈቅድለት መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ የለያቸው ሲሆን፣ በዕለቱ ይኸው ውግዘት በመላው ዓለም ለሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምዕመናን ውግዘቱን እንዲያውቁት መንግሥትም በዚህ ጉዳይ የሚፈጠር ችግር እንዳይኖር ሰላም እንዲያስከብር ዓለም በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መረጃ ኖሮት ቤተ ክርስቲያን ለወሰነችውም ውሳኔ ግንዛቤ እንዲወስድ በመግለጫ ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡

በዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ የሆኑ አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን በመላው ዓለም የሚገኙት ደስታቸውን በመግለጥ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ሳይሸራረፍ እንደሚያስፈጽመ በልዩ ልዩ መንገድ እየገለጹ ይገኛል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የልዩ ልዩ ሃይማኖት ተቋማትና ሲቪክ ማኅበራት የተፈጸመውን ድርጊት በመቃወም እና ቤተ ክርስቲያኒቱ የወሰነችውን ውሳኔ በመደገፍ ከጎናችን እንደሆነ እና አብረውን እንደሚሰሩ በልዩ ልዩ መንገድ እየገለጹልን ይገኛል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያናችን ከጎናችን ለቆሙትና ድጋፋቸውን ለገለፁልን ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ የሃይማኖት እና የሲቪክ ተቋማት ምስጋናዋን አቅርባለች።

እነዚህ በሕገ ወጥ መንገድ ተሹመናል የሚሉት አካላትም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከማዕከላዊ መዋቅር ውጭ ተወግዘው ተለይተው እያለ በሌላቸው ሥልጣን ወዳልተፈቀደላቸው የአገልግሎት በታዎች በመግባት በሚያደርጉት ግብ ግብ በዕምነቱ ተከታዮች፣ በማህበረ ካህናትና ምዕመናን ላይ ሁከት እየተፈጠረ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቤተ ክርስቲያናችን ለመንግሥት ያቀረበችው ሕግን የማስከበር እና የዜጎችን ሰላም የማስፈን ሥራ ጥሪ ተቀብሎ በሕገወጦች ላይ የወሰደው ምንም ዓይነት እርምጃ እየታየ አለመሆኑም ታውቋል፡፡

ይህ ሁሉ ድርጊት ሲፈፀም መንግሥት ሰምቶ እንዳልሰማ በዝምታያለፈውን ጉዳይ በጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሚኒስትሮችና ለካቢኔዎቻቸው በሰጡት የወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተከሰተውን ወቅታዊ ችግር በማንሳት ልዩ ልዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡

ይኸውም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅዱስ ሲኖዶሱ እና ውጭ ባሉ አባቶች መካከል ሲካሄድ የነበረውን የዕርቅ ሒደት እልባት እንዲያገኝ ማድረጋቸው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታዎችና ሕንጻዎች መካከል 4ኪሎ የሚገኙትን ሁለቱን ቀደምት ሕንጻዎች ለቤተ ክርስቲያን መመለሳቸው፣ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ሀገረ ስብከት ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ መሥሪያ ቦታ ማድረጋቸው! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገር መሆኗን መግለጻቸው፣ የቤተ ክርስቲያኗ መዳከም ጉዳቱ ለቤተ ክርስቲያኗ ብቻ ሳይሆን ለሀገረ መንግሥቱም ጭምር መሆኑን መግለጻቸው፣ አግባብነት ያለውና ለዚህም : አድራጎታቸው ቤተ ክርስቲያናችን በወቅቱ በእውቅና ሽልማት አጅባ አመሰግናለች፡፡

ሆኖም ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም በተለያዩ የመንግሥት ሚዲያዎች በተላለፈው 36 ደቂቃ በሚፈጀው በሰላምና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚኒስትሮች ካቢኔ አባላት የሰጡትን ማብራሪያ ቤተ ክርስቲያናችን በአጽንዖት ተመልክታዋለች፡፡

በመሆኑም በቀረበው ማብራሪያ ላይ ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን አቋም እንደሚከተለው

በዝርዝር እንገልጻለን፡፡

፩. መንግስት በቤተ ክርስተያናችን የተፈጠረውን ሃይማኖታዊ እና ቀኖናው ጥሰትን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሲኖዶሳዊ ውሳኔ ሊያመጣ የሚችለውን ውጤት አቅልለው በአሁኑ ወቅት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ጉዳይ በጣም ቀላል ነው” በማለት ያዩበት መንገድ፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ ጉዳዩ ቀላል እና በንግግር የሚፈታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ይህ አገላለጽ በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ውስጥ ጣልቃ እንደመግባት እና ቤተ ክርስቲያን የምታስተላልፋቸውን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ውሳኔዎች ያላቸውን ውጤት ወደ ጎን የተወ መሆኑን ቤተ ክርስቲያን ታምናለች፡፡ ከዚህም አልፎ ሁለቱም ወገን ውስጥ እውነት አለ፣ ሁለቱም አባቶቻችን ናቸው፣ ለማንም አንወግንም፤ ማንም የካቢኔ አባል እዚህ ውስጥ እጁን እንዳያስገባ፣ የሚሉት አገላለጾች በሕግ እውቅና የተሰጣትን ቤተ ክርስቲያን እና በሕጋዊቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ በሕገ ወጥ መንገድ የተነሱትን ሕገ ወጥ ቡድኖች በአቻ እይታ ተመልክተው ሊወያዩ ይገባል በማለት የስጡት ማብራሪያ ሕገ ወጥነትን የሚያበረታታ፣ ለሕጋዊ ተቋማት መንግሥት ያለበትን የመጠበቅና ዋስትና የመስጠት ኃላፊነቱን ወደ ጎን ያደረገ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ተቋማት በሕገ ወጥ ቡድኖች እንዲታመሱና እንዲተራመሱ ይሁንታ የሚሰጥ፣ ሕግንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንታዊ ታሪክና የሀገር ባለውለታነትዋን ያላገናዘበ፣ ማብራሪያ በመሆኑ ሊታረም የሚገባ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያሳስባል።

ከዚህም በተጨማሪ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትኛውም ካቢኔ በዚህ ጉዳይ እጁን እንዳያስገባ በማለት የሰጡት የሥራ መመሪያ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ ሰውነት አክብረው እና የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ያሉትን በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን ኃላፊነታቸውን እንዳይወጡ የሚያደርግና በሕገመንግሥቱ ለአስፈጻሚው አካል የተሰጠውን ሥልጣን የሚሽር፤ ሥርዓተ አልበኝነትን የሚያበረታታ፤ የሕግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል አድራጎት በመሆኑ ይህ አድራጎት እንዲታረምና መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን የሕግ የበላይነትና የተቋማትን ደህንነት የማረጋገጥ ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያሳስባል፡፡
730 views22:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 01:31:57
አንድ ፓትርያርክ
አንድ ሲኖዶስ
አንዲት ቤተ ክርስቲያን!!!!!
.
.
ከአንዱ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ነን!..... ሁለት ሲኖዶስ የለንም። አንድ መንፈስ ቅዱስ የሚመራው አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ!!.

ከጥንት ጀምሮ ያልተለየን የአባቶቻችን አምላክ አሁንም እንደ ቸርነቱ ተመልክቶ ረድኤቱን አያርቅብን!!
2.0K views22:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 05:23:13 + እኛ ያላወቅነው +
..............................................................
    እመቤታችን ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በሥላሴ ኅሊና ታስባ ስትኖር ሥራዋ በጎደለው መሙላት ነበር። እርሷ ከፍጥረት ሁሉ በንጽሕና የተሟላች ስለሆነች ዘወትር እኛ ባጎደልነው ትሞላለች። በአምላክ ኅሊና የታሰበችውም በኃጢአት የምንጎድለው እኛን ለሟሟላት ነበር። ዕድሜያቸው የገፋና ልጅ በማጣታቸው በኃዘን የጎደሉትን ቅዱሳን አባትና እናቷን በደስታ የሞላች እመቤታችን ናት። በሶስት ዓመቷ አባትና እናቷ በስስት ዓይናቸው የሚያዩዋት ልጃቸውን ወደ ቤተ መቅደስ ሲወስዷት አሁንም ቤተ መቅደሱን አሟላችው። እርሷ ከመግባቷ በፊት ገነት ሊያስገባ የማይችል መሥዋዕት ሲሰዋ የነበረበትን አማናዊ የክርስቶስ ሥጋና ደም እንዲሰዋበት በማድረግ የዘለዓለም ሕይወት የሚያሰጥ ቤተ መቅደስ አድርጋዋለችና።

   እመቤታችን ሰርግ ስትጠራ እንኳን ይህን የሟሟላት ሥራዋን አልዘነጋችም። በቃና ዘገሊላ ዕለት ከልጇ ጋር የተገኘችበት ሰርግ ለእኛ ምን መልዕክት ያስተላልፍ ይሆን? እርሷ ወይኑን የሞላችው ተፈልጋ ሳይሆን እርሷ ራሱ እንደጎደለ አውቃ ነው። የትህትና እናት የሆነች፤ እንደርሷና ልጇ በዚያ ሰርግ ውስጥ የከበረ ተጋባዥ ባይኖርም ከሰርጉ ግርግርና ድግስ ይልቅ ያለውን ጉድለት ለሟሟላት ዓይኗን ከአስተናጋጆቹ ጋር አደረገች። ወይን እንደጎደለ ሳይነግሯት በፍጥነት የሟሟላት ሥራዋን ጀመረች። ሙሽራው እንኳን ያላወቀውን ጉድለት ቶሎ በአማላጅነቷ ሞላችው።

    ልክ እንደ ሙሽራው እኛስ ስንት ያላወቅነው ጉድለት ይኖር ይሆን? ማርያም ሆይ ከሀብት ጥግ፣ ከዕውቀት ጥግ የደረስን ሲመስለን፣ "ሁሉ ነገር ሙሉ ነው" ብለን የቆምን ሲመስለን ስንቴ "ወይን እኮ የላቸውም" ብለሽልን ይሆን? ልጅሽስ ስንቴ "አንቺ ሴት ካንቺ ጋር ምን አለኝ?" ብሎ ያልሽውን ሁሉ ፈጽሞልሽ ይሆን? ስንቴ እኛ ሳንጠይቅሽ ወደ ልጅሽ አማልደሽን ይሆን?

   ወላዲተ አምላክ ሆይ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ሙሽራው ለሁሉም ይበቃል ብሎ ያሰበውን ወይን በአቅሙ አዘጋጅቷል። ሳያስበው ግን ወይኑ አለቀ። አንቺ ግን በዚያ ስለተገኘሽ በአማላጅነትሽ ሞላሽለት። እምአምላክ እናታችን አንቺ ያለሽበት ጓዳ፣ አንቺ ያለሽበት ሰርግ፣ አንቺ ያለሽበት ሀገር ሁሌም የተሟላ ነው። እምዬ እባክሽን ዘወትር ከእኛ አትለይን። እኛ በቻልነው እንሰራለን፣ በቻልነው እንማራለን፣ በቻልነው አምላክን እናገለግላለን። አንቺ ግን ሙሽራው ያላወቀውን ጉድለት እንደሞላሽ እኛም ያላየነውና ያላወቅነው እልፍ ጉድለት አለና አንቺ ሙይልን። እመቤታችን እኛም እንደ ብልህ ሰርገኛ እንጠራሻለን። ከነልጅሽ በሥራችን፣ በትዳራችን፣ በትምህርታችን፣ በሕይወታችን ሁሉ ታደሚልን። ቢርበንም ያንቺን ስም ስንጠራ ከበላው በላይ እንጠግባለን። ብናለቅስም ያንቺን ስም ስንሰማ ዕንባችን ይታበሳል። ዘወትር ኃጢአት በማሰብ የሚኖጉደው ሀሳባችን አንቺን ስናስብ ግን ዕረፍትን ያገኛል። እምዬ ማርያም ዘወትር በኃጢአት ውኃ የምንሞላውን ሰውነታችንን ልጅሽ ወደ ጽድቅ ወይን እንዲለውጥልን ለምኝልን።
.............//........//.........//....................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ጥር 12/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ

  @dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
2.1K views02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 10:42:56 + ዝክረ ቅዱስ ዮሐንስ +
.............................................................
አምላካችን ክርስቶስ ፍጥረቱን ሁሉ ይወዳል። ከፍጥረታቱ ሁሉ ደግሞ አስበልጦ ሰውን ይወዳል። ከሰውም ሁሉ ደግሞ ድንግል ማርያምን ይወዳታል፤ ምክንያቱም አማናዊት መቅደሱ፣ ማሕጸኗን ዙፋኑ አድርጎ ከእርሷ ተወልዶ እናቴ ሊላት ወዷልና። ከእናቱ ቀጥሎ ደግሞ እሷን አደራ ብሎ የሰጠውን ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስን ይወዳል። አሃ? እንዴት ነው ታዲያ እግዚአብሔር ሲወድ ያዳላል ማለት ነው? አያዳላም!

አባቶቻችን ሲያስተምሩ የእግዚአብሔር ፍቅር ልክ እንደ ጸሐይ ብርሐን ነው ይላሉ። ጸሐይ ስትወጣ እኩል ለሁሉም ብርሃኗን እንደምትሰጥ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅርም ለሁሉም እኩል ነው። ነገር ግን የምናገኘው የጸሐይ ብርሃን የሚወሰነው የቤታችንን መስኮት በከፈትነው ልክ ነው። ሙሉ ለሙሉ ከዘጋነውና ከቤት አንወጣም ብለን ቁጭ ካልን የጸሐይ ብርሃንን ጭራሽ ላናይ እንችላለን። የእግዚአብሔር ፍቅርም የልባችንን መስኮት በከፈትነው ልክ ይገባል። ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስም ለእግዚአብሔር ፍቅር የልቡን በር አንዳች ሳያስቀር ብርግድ አድርጎ የከፈተ ንዑድ ሐዋርያ ነው። ለዚህም በጻፈው ወንጌል ላይ በተለያዩ ቦታዎች "ኢየሱስ ይወደው የነበረው ሐዋርያ" እያሉ ራሱን ሲገልጽ እናየዋለን።

አንድ ሰው ሲሞት እጅግ የሚወደው ዘመድ ወይም ሀብት ካለው አደራ ብሎ የሚሰጠው ከልቡ ለሚያፈቅረውና ለሚያምንበት ሰው እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም በመስቀል ሆኖ ብቸኛ ቤቱም፣ መቅደሱም፣ ዘመዱም፣ ፍጥረቱ ሆና እናትም የሆነችውን ለሚወደውና ለሚያምንበት ዮሐንስ አስረከባት። እኛም እናታችን እንድንላት በዮሐንስ በኩል ተሰጠችን። "ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው" እንዲል ሰው ሆኖ በመስቀል ላይ ለእኛ ሲል መሞቱ የፍቅሩን ጥግ ለእኛ ያሳየበት የመጀመሪያው ነገር ነው። ከዚያ ቀጥሎ ግን ክርስቶስ ለሰው ልጅ ያለውን ታላቅ ፍቅሩን ያየነው እናቱን እንኳን ሳይሰስት "እናንተም እንደእኔ እናቴ በሏት" ብሎ በዮሐንስ በኩል ሲሰጠን ነው። ታዲያ ለዚህ ክቡር ድንግል ሐዋርያ ምን ያህል ውለታ ይኖርብን ይሆን?

ቅዱስ ዮሐንስ "ኢየሱስ ይወደው የነበረ ሐዋርያ" ብቻም ሳይሆን እርሱም አምላኩን ከልቡ የሚወድ ነበር። ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ወንድሞቹ ሐዋርያት ሲሸሹ ፍቅር ፍርሐትን አውጥታ ትጥላለችና እስከ መስቀል ስር ድረስ በፍቅሩ ጽንዓት ምክንያት የተከተለ ነበር። ጌታ የተቀበለውን መከራም ካየ በኋላ "ቁጹረ ገጽ .. ፊቱ የተቋጠረ" ተብሎ ስም እስኪወጣለት ድረስ ሕማሙን እያሰበ በኃዘንና በለቅሶ የኖረ ጻድቅ ሐዋርያ ነበር።

"ተውህቦ መራኁት ለአቡነ ጴጥሮስ፣ ወድንግልና ለዮሐንስ፣ ወመልዕክት ለአቡነ ጳውሎስ እስመ ውእቱ ብርሃና ለቤተ ክርስቲያን" ብለን በቅዳሴያችን እንደምናዜመው ለቅዱስ ዮሐንስ ድንግልና ተሰጥቶታል። የጌታን መታጠቂያ በአንድ ቀን ታጥቆ ፍትወቱ ከእርሱ ፍጹም ተወግዶለታል። (በነገራችን ላይ ወንጌለ ዮሐንስን የሚጸልይ ወይም የሚደግም ሰው የዝሙት ፈተና ይወገድለታል ይላሉ አባቶቻችን) ሕይወቱን ሙሉ በንጽሕና፣ በድንግልና የኖረ ጻድቅ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

ከሶስቱ የምሥጢር ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሊቁ ዮሐንስ የፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን ፍቅሩን እንደሞቀው ሁሉ ብርሃኑን ደግሞ በደብረ ታቦር አይቷል። ጌታ በአንድ ወቅት ሐዋርያቱን "ሰዎች ማን ይሉኛል" ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ ሲመሰክር ክርስቶስ መልሶ " በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህም" ብሎት ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም ይህን ሲሰማ የሥላሴን ነገር የሚገልጠው አብ እንደሆነ በዚህ ተረድቶ ከጌታ ደረት ተጠግቶ የወልድ ልቡ ከሚሆን ከአብ የሥላሴን ምሥጢር በቅጽበት ሰምቶ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" ብሎ ወንጌሉን መጻፍ ጀመረ።

ይህ ምሥጢረኛ ሊቅ ከጌታ ደረት መጠጋቱ ሳያንስ ሠላሳ ዓመት ሙሉ ከልጇ ስትማር ከነበረችው ልህቅተ ሊቃውንት የምሥጢር መዝገብ እመቤታችን ጋርም አሥራ አምስት ዓመት እንደ ልጇ እየታዘዛት ሲማር ኖሯል። ታዲያ የዚህን ንዑድ ክቡር ሐዋርያ ክብር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? ክብሩ ከመላዕክት ጋር ስለተካከለ ለመልዓክ እንኳን ሊሰግድ ሲሞክር መልዓኩ ልክ እንደ አባቶቻችን "ኧረ አይገባም" ብሎ በክብር ያስቆመውን አባት ማክበርስ በጌታ ዘንድ ምን ያህል ያስከብር ይሆን? ይህን "ኢየሱስ ይወደው የነበረው ሐዋርያን" መዘከርስ በኢየሱስ ዘንድ ምን ያህል ያስወድድ ይሆን?

እንግዲህ ምን እንላለን? እንደ ውዱ አባታችን ለክርስቶስ ፍቅር ልባችንን ውልል አድርገን የምንከፍትበት ብርታት፣ እስከ መስቀል ሥር የምንከተልበት ፍቅርና ጽንዓት፣ ተከትለንም ክብርት እናቱን የምንረከብበት ንጽሕና ለሁላችን ያድለን። የንዑድ ክቡር ቅዱስ ዮሐንስም ረድኤቱ፣ በረከቱ፣ ጸሎቱ፣ ፍቅሩ ሁላችንን ትርዳን። አሜን!
.....................................
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ጥቅምት 5/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
.
.
እንኳን ለቅዱስ ዮሐንስ ተዝካረ ፍልሰት (የተሰወረበት ዕለት) በሰላም አደረሳችሁ!!

  @dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
254 views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-05 09:31:58

436 views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ