Get Mystery Box with random crypto!

ግጻዌ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የሰርጥ አድራሻ: @gitsawe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.19K
የሰርጥ መግለጫ

የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-10-11 20:21:50 ጥቅምት 2
ተዝካረ ተአምሪሁ ወስደቱ ለሳዊሮስ ሊቀ ጳጳሳት ወቴክላ ሰማዕት ወሕርያቆስ፡፡
የቅዳሴ
2ኛ ቆሮ 4:7-ፍጻሜ፡ወብነ ዝንቱ መዝገብ ውስተ ንዋየ ልሕኩት"ነገር ግን ከእኛ ያይደለ ከእግዚአብሔር የተገኘ ታላቅ ኀይል.....................................................................................................የሚታየው ኀላፊ ነውና የማይታየው ግን ለዘለዓለም የሚኖር ነው፡፡"
1ኛ ጴጥሮስ 5:5-12፡ወከማሁ አንትሙሂ ወራዙት"እንዲሁ እናንተ ጎልማሶች ሆይ..............................
........................................................ለእርሱ ክብርና ኀይል እስከ ዘለዓለም ይሁን አሜን፡፡"
የሐዋ ሥራ 20:1-7፡ወእምድኅረ ኀልቀ ሐከክ"ክርክሩም ከተፈጸመ በኋላ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን ጠራና አጽናናቸው.........................
.........................................................በአምስት ቀን ወደ ጢሮአስ ደረስን በዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን፡፡"
ምስባክ
በእግዚአብሔር ተወከልኩ እፎ ትብልዋ ለነፍስየ
አዐይል ውስተ አድባር ከመ ዖፍ
እስመ ናሁ ኃጥኣን ወሰቁ ቀስቶሙ፡፡
ትርጉም
በእግዚአብሔር ታመንሁ
ነፍሴን እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሏታላችሁ
ኀጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፡፡መዝ 10:1
ወንጌል
ማቴዎስ 5:10-17፡ብፁዓን እለ ይሰደዱ በእንተ ጽድቅ"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁአን ናቸው..............
........................................................መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን ያመሰግኑት ዘንድ እንዲሁ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡"
ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዐ)
413 views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 15:58:07 ጥቅምት 1
አንስጣስያ ቅድስት ወተዝካሮን ለቅዱሳት ሕርጣን ወሶስና፡፡
የቅዳሴ
1ኛ ቆሮ 7:32-ፍጻሜ፡አንሰ እፈቅድ ለክሙ"እኔስ ያለ አሳብ ልትኖሩ እወዳለሁ...............................................................................................በምክሬ ጸንታ እንዲሁ ብትኖር ግን ብፅዕት ናት የእግዚአብሔርም መንፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡"
1ኛ ጴጥሮስ 3:1-5፡ወከማሁ አንትንሂ አንስት"እንዲሁ እናንተ ሚስቶች ሆይ................................
........................................................የማይጠፋና የተሰወረ የልብ ሰውነት ይሁንላችሁ፡፡"
የሐዋ ሥራ 17:10-13፡ወቢጾሙሰ
"ወንድሞች ግን ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሸኙአቸው...............................................................................................ከአረማውያን ወገን የሆኑ ብዙ ደጋግ ሴቶችም ነበሩ ወንዶችም ብዙዎች ነበሩ"
ምስባክ
ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ
ሰብእሰ ከመ ሣዕር መዋዕሊሁ
ወከመ ጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ
መዝ 12:14
ወንጌል
ማቴዎስ 6:25-ፍጻሜ፡ወበእንተዝ እብለክሙ"ስለዚህም እላችኋለሁ...
........................................................ለነገ አትጨነቁ ነገ ለራስዋ ታስባለችና ለቀኒቱ ክፋቷ ይበቃታል፡፡"
ቅዳሴ፡ዘወልደ ነጎድጓድ፡፡(ኀቤከ)

@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
400 views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-09 23:55:23 መስከረም 30
ተዝካረ ተአምር ዘገብረ እግዚእነ ለአትናቴዎስ ወአባ ሢሉሲ ወጽዋኤሆሙ ለያዕቆብ ወዮሐንስ ደቂቀ ዘብዴዎስ፡፡
የቅዳሴ
1ኛ ቆሮ 9:20-ፍጻሜ፡ወኮንክዎሙ ለአይሁድ"አይሁድን እጠቅማቸው ዘንድ ለአይሁድ.............................
........................................................ነገር ግን ለሌላ ሳስተምር እኔ ለራሴ የተናቅሁ እንዳልሆን ሰውነቴን አስጨንቃታለሁ ሥጋዬንም አስገዛዋለሁ፡፡"
1ኛ ዮሐንስ 1:8-ፍጻሜ፡ዑቁ ርእሰክሙ"ኀጢአት የለብንም ብንል ግን ራሳችንን እናስታለን........
........................................................አልበደልንም ብንል ግን እርሱን ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ዘንድ የለም፡፡"
የሐዋ ሥራ 20:28-31፡ወይእዜኒ ዐቀቡ"አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት....................
.........................................................እኔ ሁላችሁንም ሳስተምር ሦስት ዓመት ሙሉ ሌትም ቀንም እንባዬ እንዳልተገታ ዐስቡ፡፡"
ምስባክ
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም
ሶበ ይሄልዉ አኀው ኅቡረ
ከመ ዕፍረት ዘይውኅዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ፡፡
ትርጉም
ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ
እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው
ከራስ እስከ ጽሕም እንደሚፈስ
መዝ 132:1
ወንጌል
ማርቆስ 1:16-23፡ወእንዘ የኃልፍ"በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍም .....................................
........................................................ትምህርቱንም አደነቁ እንደ ጻፎቻቸው ያይደለ እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና፡፡"
ቅዳሴ፡ዘእግዝእትነ፡፡(ጎሥዐ)

@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
119 views20:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 16:08:08
Periodt!

@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
555 views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 23:34:59 ቃል በገባሁት መሰረት ቅዱስነታቸው ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ሳድሳዊ (የግብጽ ፓትርያርክ የነበሩ) የደረሱት ተማሪዎች ከፈተና በፊት የሚጸልዩት ጸሎት እነሆ:-

++++++++++++++++++++++++++++++++++

<< ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

++++++++++++++++++++++++++++++++++

ውድ ተፈታኞች! አሁን የሙከራችንን ( ቃና ዘገሊላ principle) ውጤቱን የምናይበት ጊዜ ተቃርቧል። እግዚአብሔር አምላክ ያዘጋጃችሁትን ወይን ባርኮ እንደሚያጣፍጠው በፍጹም ልብ በማመን ወደ ፈተናው ግቡ። የላካችሁትን መጥሪያ እናትና ልጇ ከቶ አይንቁምና ወደ ፈተና ክፍሉ ስትገቡ ከጎናችሁ እንደተቀመጡ አትርሱት። እግዚአብሔር አምላክ በነገር ሁሉ ይርዳችሁ። ድንግል ማርያም ያላወቃችሁትን ጉድለት ትሙላላችሁ!

መልካም ፈተና!!!!


@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
102 views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 16:55:01
"ሰላም ለአእጋርኪ እለ ጻመዋ በረዊጽ እምቤተልሔም ዘይሁዳ እስከ ምድረ ግብጽ...."

"የይሁዳ ክፍለ ሀገር ከምትሆን ከቤተልሔም እስከ ምድረ ግብጽ ድረስ፤ በሩጫ ለደከሙ እግሮችሽ ሰላምታ ይገባል።"

~ መልክዓ ማርያም ~
.
.
እንኳን ለዘመነ ጽጌ አደረሳችሁ። በኃጢአታችን ምክንያት ከክርስቶስ ተለይተን የተሰደድነውን በተቀደሰው ስደቷ ትመልሰን!!
.
.


@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
440 views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 13:37:29 ለብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የተሰጠ ትምህርት

'በችግርህ ቀን ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ'

ቃና ዘገሊላ principle

ሰኞ ጥቅምት 15/2014 ዓ.ም.

በዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ

በካቴድራል፣ ቅ/ማርያምና ላዛሪስት ት/ቤት ተማሪዎች ጊቢ ጉባኤ ለ2013/2014ዓ.ም. ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በተዘጋጀ የጸሎት መርሐግብር ላይ የተሰጠ ትምህርት

@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
501 views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 21:01:43 #የሲና_ሐመልማል
የሲና ሐመልማል የሙሴ ጽላት/2/
የሲሎንዲስ ጥበብ ዕፀ መድኃኒት/2/
አሁን በምን በምን እንመስልሻለን
ዕጹብ ድንቅ ብለን እናወድስሻለን
ያረጁ ፍጥረታት የታደሱብሽ/2/
የሕይወት መሰላል ማርያም አንቺ ነሽ/2/
አሁን በምን በምን.............
የነቢያት ትንቢት የልባችን ተስፋ/2/
ባንቺ መመኪያነት እምነታችን ይስፋ ኦርቶዶክስ(ተዋህዶ) ይስፋፋ/2/
አሁን በምን በምን.......
++++++++++++++++++++++++

እንኳን ለእመቤታችን ለብዙኃን ማርያም እና ግማደ መስቀሉ በመስቀለኛ ቦታዋ በግሸን ደብረ ከርቤ ላረፈበት ታላቅ በዓል አደረሳችሁ!!

#ዘማሪ:- ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
መስከረም 21/2015 ዓ.ም
https://t.me/dnJohannes


@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
622 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ