Get Mystery Box with random crypto!

ግጻዌ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የሰርጥ አድራሻ: @gitsawe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.19K
የሰርጥ መግለጫ

የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2022-07-06 09:11:40 Channel photo updated
06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 12:52:22

@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
3.2K views09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 13:14:02 +++ የጀማሪ ጠባይ +++

መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል። አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ። የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል። ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም። ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል። መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው። መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል። አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ።"

ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?" እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም። ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም። ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል። ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል። "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል። ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው። ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ። እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሰኔ 22፣ 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ቤተሰብ ይሁኑ

https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
3.8K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 10:54:11 አንዳንድ ሰዎች ግን አሉ ሁሌ ቤተ ክርስቲያን የሚጠርጉ፤ የካህናት ልብስ የሚያጥቡ፣ ካህናትን የሚመግቡ፤ ሁሌ ሰርክ ጉባዔ የማይቀሩ፣ ሥዕላትንና ንዋየ ቅድሳትን ሽቶ የሚቀቡ፣ወንበርና ሸክማ ሸክሞችን የሚሸከሙ አሉ። በረከታቸው ይደርብን!

ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ


@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
2.9K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 10:28:40 #ስንክሳር_ዘሰኔ_16


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ስድስት በዚህች ዕለት መልካም ሽምግልና ያለው ስም አጠራሩ የከበረ በገዳም የሚኖርና በገድል የተጠመደ አባት የላይኛው ግብጽ ሰው #አባ_አቡናፍር አረፈ፡፡

የዚህንም አባት ገድል የተናገረ አባ በፍኑትዮስ ነበር እርሱ ቁጥሩ ከገዳማውያን ነውና፡፡

አባ በፍኑትዮስም ወደ በረሃ ውስጥ በገባ ጊዜ አንዲት የውኃ ምንጭና አንዲት የሰሌን ዛፍ አግኝቶ በዚያ እየተጋደለ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡

በአንዲት ዕለትም አባ በፍኑትዮስ ወደርሱ ሲመጣ አባ አቡናፍርን አየው ፈርቶም ደነገጠ የሰይጣን ምትሐት የሚያይ መስሎታልና ይህም አባት አቡናፍር ልብስ አልነበረውም ጸጉሩና ጽሕሙ ሥጋውን ሁሉ ይሸፍናሉ አባ በፍኑትዮስንም በላዩ በመስቀል ምልክት አማትቦ አጽናናው በፊቱም አቡነ ዘበሰማያትን ጸለየ ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ ሆይ መምጣትህ መልካም ነው አለው ይህንንም በማለቱ ከእርሱ ፍርሃቱን አራቀለት፡፡

ከዚህ በኋላ ሁለቱም በአንድነት ጸለዩ የእግዚአብሔርንም ገናናነት እየተነጋገሩ ተቀመጡ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደዚህ በረሀ ከዓለም አወጣጡ እንዴት እንደሆነ በዚያም በረሃ አኗኗሩ እንዴት እንደሆነ ይነግረው ዘንድ አባ በፍኑትዮስ አባ አቡናፍርን ለመነው፡፡

አባ አቡናፍርም እንዲህ ብሎ መለሰለት እኔ ደጋጎች ዕውነተኞች መነኮሳት በሚኖሩበት በአንድ ገዳም እኖር ነበር የገዳማውያንን ልዕልናቸውን ሲናገሩ ሲያመሰግኑአቸውም ሰማሁ እኔም ከእናንተ የሚሻሉ አሉን አልኳቸው እነርሱም አዎን እነርሱ በበረሀ የሚኖሩ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበሩ ናቸው እኛ ለዓለም የቀረብን ስለሆን ብንተክዝና ብናዝን የሚያረጋጋን እናገኛለን ብንታመም የሚጠይቀንና የፈለግነውን ሁሉ እናገኛለን በበረሀ የሚኖሩ ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ ናቸው አሉኝ፡፡

ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልቤ እንደ እሳት ነደደ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ የፈቀደውን ይመራኝ ዘንድ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ተነሥቼ ጸለይኩ፡፡ ትንሽ እንጀራም ይዤ ተጓዝኩ አንድ ጻድቅ ሰውም አግኝቼ የገዳማውያንን ገድላቸውንና ኑሮአቸውን እያስተማረኝ በእርሱ ዘንድ ኖርኩ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደዚህ ደረስኩ እግዚአብሔርም ያዘጋጀልኝን ይቺን ሰሌን አገኘኋት በየዓመቱም ዐሥራ ሁለት ዘለላ ታፈራለች ለየወሩም የምመገበው አንዱ ዘለላ ይበቃኛል ውኃም ከዚህች ምንጭ እጠጣለሁ በዚህችም በረሀ እስከ ዛሬ ስልሳ ዓመት ኖርኩ ከቶ ያላንተ የሰው ፊት አላየሁም አለኝ፡፡

ይህንንም ሲነጋገሩ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እነርሱ ወረደ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ሰጣቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ከሰሌን ፍሬ ጥቂት ምግብ ተመገቡ፡፡

ያን ጊዜም የቅዱስ አባ አቡናፍር መልኩ ተለወጠ እንደ እሳትም ሆነ በእግዚአብሔርም ፊት ተንበርክኮ ሰገደ ለአባ በፍኑትዮስም ሰላምታ ሰጠው ያን ጊዜም ነፍሱን በጌታ እጅ ሰጠ፡፡ ቅዱስ በፍኑትዮስም በጸጉር ልብስ ገንዞ በዚያች ቦታ ቀበረው፡፡

ከዚህም በኋላ አባ በፍኑትዮስ በዚያች ቦታ ይኖር ዘንድ አሰበ በዚያን ጊዜ ያቺ የሰሌን ዛፍ ወደቀች የውኃውም ምንጭ ደረቀ፡፡

ቅዱስ አባ በፍኑትዮስ ወደ ዓለም ተመልሶ የገዳማውያንን ዜና ይልቁንም የቅዱስ አባ አቡናፍርን ዜና ይሰብክ ዘንድ ይህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ የከበሩ ገዳማውያን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን፡፡


ዳግመኛም በዚህች ዕለት የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለት ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ እስራኤል አገር እንዲመለስ አዘዘው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ስለ እናቱ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መከራና ስደት ይቅር ይበለን ለዘላለሙ አሜን፡፡





@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
4.7K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 12:46:37
ተራዳኢው መልዓክ ፈጥኖ ደራሻችን፣ ከአምላካችን የምታስታርቀን ወዳጃችን፣ አእላፍ ነፍሳትን በአማላጅነትህ ስለምታስምር "ሺህ በክንፉ ሺህ በአክናፉ" ተብለህ በቅጽል የምትጠራ፣ ለሞት የተጻፈውን ወደ ሕይወት በመቀየር አምላክህን ለምትመስል ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ በእውነት ላንተ ክብር ይገባሃል።

ለእኛም ብዙ የተጻፈብን የሞት ደብዳቤ አለና የባሕራንን ደብዳቤ እንደለወጥክ የእኛንም ወደ ሕይወት ለውጥልን። ጠላት የደገሰልን ብዙ የጥፋት ድግስ አለና ለክፋት ታስቦብን የሚሰራውን ሁሉ አንተ ለበጎ አድርገው።

እንኳን ለገናናው ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ሰኔ 12/2014 ዓ.ም
ስዕል:- በሠዓሊ ቤርሳቤህ ደረጀ

@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
4.0K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 15:55:07 #ዘቅዳሴ
#ኤፌሶን_1:13-ፍጻሜ፡
ወአንትሙሂ ሰማዕክሙ ቃለ ጽድቅ"እናንተም ልትድኑበት የተማራችሁትን የእውነት ቃል ሰምታችሁና አምናችሁ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታትማችሁ፡፡.............................
.................................................ይህችውም አካሉ ናት የሁሉም ፍጻሜው እርሱ ነው ሁሉንም በሁሉ ይፈጽማል፡፡"
#ይሁዳ_1:9-14፡ወሚካኤልኒ ሊቀ መላዕክት"የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳን ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር በተከራከረ ጊዜ የስድብ ቃልን ሊናገር አልደፈረም 'እግዚአብሔር ይገሥጽህ' አለው እንጂ፡፡.....................................................................................የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው፡፡"
#የሐዋ_ሥራ_1:10-12፡ወአስተርአይዎሙ ፪ቱ እደው ወቆሙ ኀቤሆሙ"እነርሱም ወደ ሰማይ አተኵረው ሲመለከቱ እነሆ ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው፡፡ እነርሱም 'እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየአያችሁ ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል' አሏቸው፡፡"
#ምስባክ
ሶበ ትሬእዮሙ ለጠቢባን ይመውቱ
ወከማሁ ይትሀጎሉ አብዳን እለ አልቦሙ ልብ
ወየኀድጉ ለባዕድ ብዕሎሙ፡፡
#ትርጉም
ብልሃተኞች እንዲሞቱ
ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ
ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንዲተዉ አይቶአል፡፡
#መዝ_48:10
#ወንጌል
#ማቴዎስ_25:14-31፡እስመ ከመ ብእሲ ዘይነግድ"መንገድ እንደሚሄድ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲህ ይሆናልና፡፡ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡........................................................................................ክፉውን አገልጋይ ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡፡"
#ቅዳሴ፡ያዕቆብ ዘሥሩግ፡፡(ተንሥኡ)

@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
@gitsawe
3.5K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 15:55:07 #ሰኔ_12
ቅዱስ ሚካኤል ወአፎምያ ወላሊበላ ረአዬ ምሥጢር፡፡
#ዘነግህ_ምስባክ
ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ
ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ
ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር፡፡
#ትርጉም
የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሰፍራል ያድናቸውማል
እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ እዩም፡፡
#መዝ_33:7
#ወንጌል
#ማቴዎስ_24:30-36፡ወይእተ አሚረ ያስተርኢ ተአምሪሁ"በዚያም ወራት የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል ያንጊዜም የምድር አሕዛብ ሁሉ ያለቅሳሉ የሰው ልጅንም በኀይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፡፡...................................................................................ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም፡፡"
@gitsawe @gitsawe
@gitsawe @gitsawe
3.2K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ