Get Mystery Box with random crypto!

ግጻዌ

የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የቴሌግራም ቻናል አርማ gitsawe — ግጻዌ
የሰርጥ አድራሻ: @gitsawe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.19K
የሰርጥ መግለጫ

የየዕለቱን ግጻዌ የቅዳሴ ጊዜ ምንባባትና ምስባክ በዚህ ቻናል ያገኛሉ።

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-01-01 12:39:40 " ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ "
#ዮሐ_21 ፥ 3
.
.
በዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
.........................................
በጅማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ትምህርት
..........................................
ታኅሣሥ 22 / 2015 ዓ.ም
..........................................

  @dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
464 views09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 00:23:55


https://t.me/DnEstifanosGirma
23 views21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:04:11 ጥያቄ :- ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ እስከ ቀራንዮ ጌታን ተከትሎት እንደነበር እናውቃለን እና ለምን መስቀሉን አላገዘውም? ወይም ሙከራ አላደረገም? እግዚአብሔር ይስጥልኝ Thanks in advance

መልስ:- በማቴዎስ 20 ፥ 20 ላይ "በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች። እርሱም ምን ትፈልጊያለሽ አላት። እርሷም:- እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱንም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ አለችው። ኢየሱስ ግን መልሶ:- የምትለምኑትን አታውቁም :- እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን አለ። እንችላለን አሉት። እርሱም:- ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ በቀኝና ግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም አላቸው።"

ስለዚህ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መሠረት መስቀሉን ተሸክሞ ማገዝም ለስምዖን ቀሬናዊ የተሰጠ ወይም የተዘጋጀ ዕድል ነው። ማን ያውቃል ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ ከፍቅሩ አንጻር ተሸክሞ የማገዝ ሃሳብ መጥቶለት ሊሆንም ይችላል። ግን ደግሞ በራሱ ፈቃድ ማገዝ ማለት ዮሐንስን ከባድ አደጋ ላይ የሚጥል ጉዳይ ነው። ስምዖን ቀሬናዊም ቢሆን መስቀሉን ያገዘው እርሱ ፈልጎ ሳይሆን አይሁድ ክርስቶስን የግድ ሰቅለውና አዋርደው መግደል ስለፈለጉ በመንገድ ላይ እንዳይሞትና ዓላማቸው ሳይሳካ እንዳይቀር በመፍራት መንገድ ላይ አግኝተውት እንዲሸከም ስላስገደዱት ነው። ሳያስበውም ቢሆን ግን ከታላቅ በረከት ተካፋይ ሆነ። የክርስቶስን የመስቀል ክብደት ሊናገር የሚችል ብቸኛው ሰው ለመሆን በቃ!

ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ኅዳር 29/2015 ዓ.ም

ለጥያቄ :- ngl.link/yohannesdn

  @dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
483 views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 10:21:30 ኅዳር 19
ቅዳሴ ቤቱ ለሚናስ ወባኮስ ወበርተሎሜዎስ ሐዋርያ 1እም 12 ቴዎፍሎስ ወብእሲቱ ወወልዳ ዘ5 አውራኀ ዘድኀኑ እምእሳት ወተገድፉ ለአናብስት፡፡
የቅዳሴ
1ኛ ቆሮ 12:28-ፍጻሜ፡ወለእለሰ ሤሞሙ እግዚአብሔር"እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሾማቸው አስቀድሞ ሐዋርያትን ....................................
........................................................ነገር ግን ለምትበልጠው ጸጋ ቅኑ ደግሞም የምትሻለውን መንገድ አስተምራችኋለሁ፡፡"
ይሁዳ 1:20-ፍጻሜ፡ወአንትሙሰ አኃዊነ ሕንጹ ርእሰክሙ"ወንድሞቻችን ሆይ እናንተ ግን በተቀደሰች ሃይማኖት ራሳችሁን እነጹ..............................
.........................................................አሁንም እስከ ዘለዓለም ድረስ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፡፡አሜን፡፡"
የሐዋ ሥራ 4:29-37፡ወይእዜኒ እግዚኦ ርኢ ትምክሕቶሙ"አሁንም አቤቱ ትምክህታቸውን ተመልከት...
........................................................በሐዋርያትም ዘንድ ትርጓሜው የመጽናናት ልጅ የሚሆን በርናባስ የተባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚሉት አንድ የቆጵሮስ ሰው ነበር፡፡"
ምስባክ
ሕጉ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ
ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ
ኩነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ፡፡
ትርጉም
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነፍስን ይመልሳል
የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል
የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ልብንም ደስ ያሰኛል፡፡
መዝ 18:7-8
ወንጌል
ማቴ 10:1-17፡ወጸውዖሙ ለ12 አርዳኢሁ"ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ጠርቶ ያወጡአቸው ዘንድ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ በርኩሳን መናፍስት ላይ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡..............
........................................................እንገዲህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ፡፡"
ቅዳሴ፡ዘወልደ ነጎድጓድ፡፡(ኀቤከ)
https://telegram.me/gitsawe
488 views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 22:39:39
እመቤቴ ሆይ ዛሬ ከተሰደድሽበት ከግብጽ ወደ ሀገርሽ ገሊላ እንደተመለሽ ነገሩኝ። እናቴ ሆይ ወደ ልቤ የምትመለሽውስ መቼ ይሆን? ልቤ በአንቺና በልጅሽ ፍቅር የሚነደው መቼ ይሆን? ኃጢአተኛው ልቤ ሄሮድስ ሆኖ አንቺን ካሳደደ ቆይቷል። ለአንቺና ለልጅሽ ማረፊያ የሚሆን ንጹሕ ልቡና ስላጣው ከእኔ ልብ ከተሰደድሽ ቆይተሻል። ሊቃውንቱ "እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ ሀገርኪ ገሊላ እትዊ / እስከ መቼ ድረስ እመቤቴ በስደት ሀገር ትኖሪያለሽ? ሀገርሽ ገሊላ ተመለሽ" እያሉ ሲዘምሩ ነበር። እናቴ ሆይ እኔም እልሻለሁ :- እስከ መቼ ድረስ ፍቅርሽ ሳይገባኝ ልጅሽን በኃጢአቴ እያሳደድኩ እንድኖር ትፈቅጂያለሽ? ልቤ ለአንቺ ዙፋንነት የተገባ ባይሆንም ወደ ልቤ ተመለሽ! ኃጢአቴ ሁሉ አንጽተሽ በልቤ እደሪ። በጥላቻና በኃጢአት አንቺንና የተወደደው ልጅሽን ማሳደድ ላቁም። እመብርሃን ሆይ የልቤ ብርሃን የሚሆን ልጅሽን እንደታቀፍሽ ወደ ልቤ ተመለሽ!

ተመየጢ ሱላማጢስ ኀበ ልብየ
.
.
ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
ኅዳር 6/2015 ዓ.ም
ስዕሉ:- በሰዓሊ ቤርሳቤህ ደረጀ ተሳለ

  @dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
751 views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 15:01:14 ለአምላክ ማደሪያ
............................................
ለአምላክ ማደሪያ ለጌታችን ቤት
እንስገድ ሁላችን የጸጋ ስግደት
እንደተፃፈልን በንጉሥ ዳዊት(2)
ሰሎሞን ያነጻት ያኔ በኦሪት
በኋላም በጴጥሮስ ደግሞ ያጸናት
የገሃነም ደጆች ከቶ ማይችሏት(2)
የትንሣኤው ብርሃን የተገለጸብሽ
አንቺ ቤተ ክርስቲያን የሁሉ እናት ነሽ
የአምላክን ልጅነት ያገኘነብሽ(2)
የታቦር ተራራ አንቺ የኖኅ መርከብ
የሚፈተትብሽ የአምላክ ሥጋና ደም
በሰማያት ያለሽ ኑሪ እስከ ዘላለም(2)
..........................

@dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
671 views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 21:34:32 + ዝክረ ቅዱስ ዮሐንስ +
................................................................
አምላካችን ክርስቶስ ፍጥረቱን ሁሉ ይወዳል። ከፍጥረታቱ ሁሉ ደግሞ አስበልጦ ሰውን ይወዳል። ከሰውም ሁሉ ደግሞ ድንግል ማርያምን ይወዳታል፤ ምክንያቱም አማናዊት መቅደሱ፣ ማሕጸኗን ዙፋኑ አድርጎ ከእርሷ ተወልዶ እናቴ ሊላት ወዷልና። ከእናቱ ቀጥሎ ደግሞ እሷን አደራ ብሎ የሰጠውን ደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ዮሐንስን ይወዳል። አሃ? እንዴት ነው ታዲያ እግዚአብሔር ሲወድ ያዳላል ማለት ነው? አያዳላም!

አባቶቻችን ሲያስተምሩ የእግዚአብሔር ፍቅር ልክ እንደ ጸሐይ ብርሐን ነው ይላሉ። ጸሐይ ስትወጣ እኩል ለሁሉም ብርሃኗን እንደምትሰጥ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅርም ለሁሉም እኩል ነው። ነገር ግን የምናገኘው የጸሐይ ብርሃን የሚወሰነው የቤታችንን መስኮት በከፈትነው ልክ ነው። ሙሉ ለሙሉ ከዘጋነውና ከቤት አንወጣም ብለን ቁጭ ካልን የጸሐይ ብርሃንን ጭራሽ ላናይ እንችላለን። የእግዚአብሔር ፍቅርም የልባችንን መስኮት በከፈትነው ልክ ይገባል። ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስም ለእግዚአብሔር ፍቅር የልቡን በር አንዳች ሳያስቀር ብርግድ አድርጎ የከፈተ ንዑድ ሐዋርያ ነው። ለዚህም በጻፈው ወንጌል ላይ በተለያዩ ቦታዎች "ኢየሱስ ይወደው የነበረው ሐዋርያ" እያሉ ራሱን ሲገልጽ እናየዋለን።

አንድ ሰው ሲሞት እጅግ የሚወደው ዘመድ ወይም ሀብት ካለው አደራ ብሎ የሚሰጠው ከልቡ ለሚያፈቅረውና ለሚያምንበት ሰው እንደሆነ ሁሉ ጌታችንም በመስቀል ሆኖ ብቸኛ ቤቱም፣ መቅደሱም፣ ዘመዱም፣ ፍጥረቱ ሆና እናትም የሆነችውን ለሚወደውና ለሚያምንበት ዮሐንስ አስረከባት። እኛም እናታችን እንድንላት በዮሐንስ በኩል ተሰጠችን። "ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው" እንዲል ሰው ሆኖ በመስቀል ላይ ለእኛ ሲል መሞቱ የፍቅሩን ጥግ ለእኛ ያሳየበት የመጀመሪያው ነገር ነው። ከዚያ ቀጥሎ ግን ክርስቶስ ለሰው ልጅ ያለውን ታላቅ ፍቅሩን ያየነው እናቱን እንኳን ሳይሰስት "እናንተም እንደእኔ እናቴ በሏት" ብሎ በዮሐንስ በኩል ሲሰጠን ነው። ታዲያ ለዚህ ክቡር ድንግል ሐዋርያ ምን ያህል ውለታ ይኖርብን ይሆን?

ቅዱስ ዮሐንስ "ኢየሱስ ይወደው የነበረ ሐዋርያ" ብቻም ሳይሆን እርሱም አምላኩን ከልቡ የሚወድ ነበር። ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ወንድሞቹ ሐዋርያት ሲሸሹ ፍቅር ፍርሐትን አውጥታ ትጥላለችና እስከ መስቀል ስር ድረስ በፍቅሩ ጽንዓት ምክንያት የተከተለ ነበር። ጌታ የተቀበለውን መከራም ካየ በኋላ "ቁጹረ ገጽ .. ፊቱ የተቋጠረ" ተብሎ ስም እስኪወጣለት ድረስ ሕማሙን እያሰበ በኃዘንና በለቅሶ የኖረ ጻድቅ ሐዋርያ ነበር።

"ተውህቦ መራኁት ለአቡነ ጴጥሮስ፣ ወድንግልና ለዮሐንስ፣ ወመልዕክት ለአቡነ ጳውሎስ እስመ ውእቱ ብርሃና ለቤተ ክርስቲያን" ብለን በቅዳሴያችን እንደምናዜመው ለቅዱስ ዮሐንስ ድንግልና ተሰጥቶታል። የጌታን መታጠቂያ በአንድ ቀን ታጥቆ ፍትወቱ ከእርሱ ፍጹም ተወግዶለታል። (በነገራችን ላይ ወንጌለ ዮሐንስን የሚጸልይ ወይም የሚደግም ሰው የዝሙት ፈተና ይወገድለታል ይላሉ አባቶቻችን) ሕይወቱን ሙሉ በንጽሕና፣ በድንግልና የኖረ ጻድቅ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

ከሶስቱ የምሥጢር ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሊቁ ዮሐንስ የፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን ፍቅሩን እንደሞቀው ሁሉ ብርሃኑን ደግሞ በደብረ ታቦር አይቷል። ጌታ በአንድ ወቅት ሐዋርያቱን "ሰዎች ማን ይሉኛል" ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ ሲመሰክር ክርስቶስ መልሶ " በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህም" ብሎት ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም ይህን ሲሰማ የሥላሴን ነገር የሚገልጠው አብ እንደሆነ በዚህ ተረድቶ ከጌታ ደረት ተጠግቶ የወልድ ልቡ ከሚሆን ከአብ የሥላሴን ምሥጢር በቅጽበት ሰምቶ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" ብሎ ወንጌሉን መጻፍ ጀመረ።

ይህ ምሥጢረኛ ሊቅ ከጌታ ደረት መጠጋቱ ሳያንስ ሠላሳ ዓመት ሙሉ ከልጇ ስትማር ከነበረችው ልህቅተ ሊቃውንት የምሥጢር መዝገብ እመቤታችን ጋርም አሥራ አምስት ዓመት እንደ ልጇ እየታዘዛት ሲማር ኖሯል። ታዲያ የዚህን ንዑድ ክቡር ሐዋርያ ክብር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? ክብሩ ከመላዕክት ጋር ስለተካከለ ለመልዓክ እንኳን ሊሰግድ ሲሞክር መልዓኩ ልክ እንደ አባቶቻችን "ኧረ አይገባም" ብሎ በክብር ያስቆመውን አባት ማክበርስ በጌታ ዘንድ ምን ያህል ያስከብር ይሆን? ይህን "ኢየሱስ ይወደው የነበረው ሐዋርያን" መዘከርስ በኢየሱስ ዘንድ ምን ያህል ያስወድድ ይሆን?

እንግዲህ ምን እንላለን? እንደ ውዱ አባታችን ለክርስቶስ ፍቅር ልባችንን ውልል አድርገን የምንከፍትበት ብርታት፣ እስከ መስቀል ሥር የምንከተልበት ፍቅርና ጽንዓት፣ ተከትለንም ክብርት እናቱን የምንረከብበት ንጽሕና ለሁላችን ያድለን። የንዑድ ክቡር ቅዱስ ዮሐንስም ረድኤቱ፣ በረከቱ፣ ጸሎቱ፣ ፍቅሩ ሁላችንን ትርዳን። አሜን!

ዲያቆን ዮሐንስ ደረጀ
2015 ዓ.ም ጥቅምት አቦ ማህሌት ላይ ተጻፈ
አዲስ አበባ
https://t.me/dnJohannes

@dnJohannes
@dnJohannes 
@dnJohannes 
@dnJohannes 
1.8K views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 15:45:48

@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
@dnJohannes
1.6K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 07:05:07 ጥቅምት 4
አብርሃ ወአጽብሐ ነገሥተ ኢትዮጽያ ወባኮስ ቢጹ ለሰርጊስ ወገብረ ክርስቶስ ወሐናንያ አሐዱ እመ 72 አርድእት፡፡
የቅዳሴ
1ኛ ቆሮ 7:29-ፍጻሜ፡ወባሕቱ ከመዝ ይረትዕ አኃዊነ"ነገር ግን ወንድሞቻችን ............................
........................................................የእግዚአብሔርም መንፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመስለኛል፡፡"
1ኛ ጴጥሮስ 2:16-ፍጻሜ፡ወኩኑ ከመ አግኣዝያን"ነጻነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባርያዎች ሁኑ.
........................................................እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና አሁንም ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመለሱ፡፡"
የሐዋ ሥራ 9:10-20፡ወሀሎ አሐዱ ብእሲ"በደማስቆም ስሙን ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበር...............................
........................................................እህልም በላ በረታም ጥቂት ቀንም ከደቀ መዛሙርት ጋር በደማስቆ ሰነበተ፡፡"
ምስባክ
ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር
ነገሥተ ምድር ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር
ወዘምሩ ለአምላክነ፡፡
ትርጉም
ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የምድር ነገሥታት ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለጌታም ዘምሩ፡፡ መዝ 67:31
ወንጌል
ሉቃስ 10:17-25፡ዘቄርሎስ አው ባስልዮስ አው"እነዚያም ሰባው ደስ ብሎአቸው ተመለሱና...................
........................................................ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ተመኙ አላዩምም እናንተ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኙ አልሰሙም፡፡"
ቅዳሴ፡ዘወልደ ነጎድጓድ፡፡(ኀቤከ)
2.1K views04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ