Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2022-09-02 14:11:15
እጅግ ያሳዝናል!

እነዚህ ህፃናት በጦርነቱ የተማረኩ ናቸው። ትህነግ ጠዋት ጠዋት ሻይ ጋር ቀላቅሎ አደንዛዥ እፅ ይሰጣቸዋል። ጦርነት መሃል "እጅ ስጥ" እያሉ ይመጣሉ። ተማርከው የከበባቸውን ሰራዊት ሁሉ እጅ ስጥ ይሉታል። እነዚህ እድለኛ ሆነው ተማርከዋል።

ህፃናትን ለጦርነት መጠቀም ወንጀል ነው። ትህነግ ግን ጭራሹን በአደንዛዥ እፅ አደንዝዞ ነው ወደ ጦርነት እየማገዳቸው ያለው።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.5K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 12:27:00
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለጥቅምት 10 ተቀጠረ በሌላኛው ችሎት ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱም ለጥቅምት 14 ተቀጥረዋል::

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.5K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 11:33:07
"ወልቃይትን ለአሸባሪው ሀይል ድጋሜ አሳልፈን ሰጥተን፣ የምንለምን ቂሎች አይደለንም። በትግላችን ክብራችንን እናስጠብቃለን። ዳግም የወልቃይት ህዝብ በባርነት ከሚወድቅ፣ እኛ አልቀን አጥንታችን መሬት ተከስክሶ ቢቀር እንመርጣለን።" -

ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.3K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 10:45:23 የሀዘን መግለጫ

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ከምሽቱ 3:00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ተፈፅሞበት ህይወቱ እንዳለፈ ከስፍራው ተሰምቷል።

አቶ ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ   አባት ነበሩ ።

አቶ ውብሸት ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በስራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዮ ተቋማት በባለሙያነትና በስራ ኃላፊነት ህዝብን በለጋ የወጣትነት ጊዜያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር እና እንደ ተወላጅ ከተማዋ የሚገባትን እድገትና ማዕረግ እንድታገኝ እንዲሁም ነዋሪዎቿ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ ወጣት አመራር ነበሩ ።

የደረሰብን ሀዘን እጅግ መራርና አስደንጋጭ ነው ፤ ይህም መስዋእትነት ለህዝብ ዘላቂ ሰላም ፣ ልማትና አንድነት የተከፈለ ዋጋ ነው ።

ቀብሩ በሸዋሮቢት ከተማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የስርአተ ቀብራቸው ይፈጸማል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.3K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:30:48 ወልድያ የባንክ አገልግሎት ጀምሯል። የህወሃት ታጣቂዎች ማታ በጎብዬ በኩል ወደ አላውሃ ለመግባት ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካም።
@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.0K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:59:52 መረጃ

በአበርገሌ ግንባር በህውሃት ወራሪ ትንኮሳ ደርሶበት የአፀፋ ምላሽ መስጠት የጀመረው ጥምር ጦር ምሽጎችን ደረማምሶ እየጨረሰ መሆኑ ተሰምቷል።
ከአበርገሌ ወደ መቀሌ በቀጣይ የምንጠብቀው ነው (wasu)

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.0K views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:59:17
።።።።የተወደዳችሁ ቤተሰቦቼ ።።።።
መርጌታ   ብርሀኔ የባህል መድህኒት 
09 13 46 29 34
1.ለሀብት
2.ለገበያ ብዙ ደንበኛ እንዲኖረን
3.ለመስተፋቅር
4.ለማንኛውም በሽታ

የምንሰራው ጥበብ
============

5.ሰውን ለማፍዘዝ ለማደንገዝ
6. ለሰላቢ በሌላ አማርኛ ነገሮችን ለመሰወር
7.ለግርማ ሞገስ
8.ለትምህርት ዘኢያገድፍ
9.ለዐቃቤ ርዕስ ለመከላከያ
10.ሰው እንዲወደን ማድረግያ
11.ብልት ማሳደጊያ ዕፀ አብይ
12.ለስንፈተ ወሲብ
13.ለዐደበተ ርቱዕ ጥሩ ተናጋሪ እንድንሆን
14.ለቁመት መጨመርያ ዕፀ (ኤግኤል)
15.በግለ ወሲብ ለምትሰቃዩ ወይም በሴጋ
16.ለመልክ ውበት እንዲኖረን ማድረጊያ
17. ስራ እንድንቀጠር ማድረግያ
18.ፈተና አሪፍ ውጤት እንድናመጣ ማድረግያ
19.ለሴቶች ትልቅ ዳሌ እንዲኖረን ማድረግያ በዕፀዋት ብቻ
20.ፀጉር እንዲረዝም ማድረጊያ ..... ወዘተ
21.ለውፍረት
22.ለቅጥነት
23.ለስልጣን መጨመርያ
24.ለጥላ ወጊ
25.ለህዝብ ፍቅር
26.ብር እንዳይባክን ማድረግያ
27.ለመንድግ
28.ለቁማር
29.ደፋር ለመሆን
30. ህልም ሌሊት/ዛር ለተዋረሰው/
31. ትዳር ላይ ማትስማሙ እድትስማሙ ሚያደርግ
32.ለመካን
33 ለበረከት
34 ለመፍትሔ ስራይ
ስ.ቁ 09 13 46 29 34
      09 13 46 29 34 ይደውሉልን።
8.0K views05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:21:33 መረጃ

በደባርቅ ከተማ 16 ሰርጎ ገቦች ተያዙ።

የደባርቅ ከተማ አሥተዳደር በምሽት የኬላ ጥበቃ 16 የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድን አባላት የኾኑ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድንን እኩይ ዓላማ ለማስፈፀም በተለያየ ምክንያት ወደ ከተማዋ ገብተው እየተንቀሳቀሱ የመረጃ ማቀበል ሥራ የሚሠሩ 16 ተጠርጣሪ ሰርጎ ገቦች እና ሶስት ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የደባርቅ ከተማ ከንቲባ ብርሃን ፀጋየ ገልፀዋል።የአሸባሪውና ተስፋፊው ትህነግ ወራሪ ቡድንን ዳግም ወረራ ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ የመጀመሪያው ተግባር የከተማችን ከሰርጎ_ገብ መጠበቅ እና የደጀንነት ሚና መወጣት ዋነኛና ቁልፍ ተግባር መሆኑ ታውቆ በአደረጃጀት ስምሪት ተሰጥቶ ወደ እየተሠራ መኾኑን ከንቲባው ተናግረዋል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.0K views04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:04:45 በሆሮ ጉዱሩው ጥቃት ከ55 ሰዎች በላይ ተገደሉ

የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በቦምብ ጥቃት ጋይቷል


በኦሮሚያ ክልል ሆሮጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማ የታጠቁ አካላት በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ ሲሉ የአይን እማኞች ተናገሩ፡፡የአከባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ለአንድ ዓመት ያህል አስከፊ የተባለ የፀጥታ ችግር ውስጥ በነበረበት በዚህ አከባቢ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በመደበኛነት ተመድበው የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብሩ ነበር፡፡ ይሁንና ባለፈው እሁድ ነሃሴ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. የአከባቢውን ፀጥታ ሲያስከብር የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ከከተማዋ መነሳታቸውን ተከትሎ የተለያዩ ስያሜ ያላቸው ታጣቂዎች በከተማዋ ባለፉት ቀናት መታየታቸውን ነው የአይን እማኞች የገለጹት፡፡

አቶ ንጉሴ ባንጃ የተባሉ የአይን እማኝ “እሁድ ማታ የኦሮምያ ልዩ ኃይል ለሌላ ግዳጅ ትፈለጋላችሁ ተብለው ከተማዋን ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ መንግስት ‘ሸነ’ ያላቸው “የኦሮሞ ነጻነት ጦር” ሰኞ ጠዋቱን ገብተው ከተማዋን ተቆጣጠሩዋት፡፡”ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። የአይን እማኙ «ታጣቂዎቹ በከተማዋ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ወደ 59 የጦር መሣሪያ ከማህበረሰቡ አስፈትተው በዚያው ሰኞ ቀን ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል፡፡»ብለዋል

አቶ ንጉሴ አክለው በሰጡን አስተያየታቸው፤ “ ፋኖ ነን ያሉ የታጠቁ አካላት ወደ ከተማዋ ገብተው ከኦነግ ጋር አብራችኋል በሚል በመደዳው ከተማዋ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው ከ15 ሺህ የማያንሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል” ነው ያሉት፡፡ ጥቃቱን ተከትሎ ከትናንት ማታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብቻ የ55 ሲቪል ዜጎች አስከሬን መቅበራቸውን የሚናገሩት እኚው አስተያየት ሰጪ “ ከማህበረሰቡ በአጠቃላይ የ87 ሰዎች ሕይወት የጠፉ በመሆኑ የ32 ሰዎች አስከሬን በየጫካውና በየገደሉ እየፈለግን ነው” ሲሉም የችግሩን ስፋት አስረድተዋል፡፡

አስተያየት ሰጪው እንደሚሉት ታጣቂዎቹ ከኪረሙ ወረዳ ሃሮ ቀበሌ የመጡ ናቸው፡፡ በትናንትናው የአገምሳ ከተማ ጥቃት ከጠፋው የሰው ህይወት በተጨማሪ በከተማዋ የሚገኝ የአዋሽ ባንክ በቦምብ ሲጋይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክን ጨምሮ በበርካታ የከተማዋ ተቋማት ላይ ዘረፋ ተፈጽሟል ብለዋል,።

አስተያየት ሰጪው ለፀጥታ ችግሩ መከሰት የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች አከባቢውን ለቀው የመውጣት ውሳኔን ተጠያቂ ያደርጋሉ። አስቀድሞም ከአንድ ዓመት በላይ በአከባቢው በቆየው የፀጥታ ችግር በርካታ ሰው በከተማዋ ተጠልለው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው በመግለጽም፤ አሁን ላይ ግን በከተማዋ ላይ ባነጣጠረው ጥቃት ነዋሪዎች ወደየጫካው ነፍሳቸውን ለማዳን መሸሻቸው ነው የተብራራው፡፡

ሌላው አስተያየታቸውን ያጋሩን የከተማዋ ነዋሪና በመምህርነት ሙያ የተሰማሩት ቢቂላ ዓለሙ፤ በጸጥታ ችግር ምክኒያት ከየገጠር ቀበሌያት የተፈናቀሉ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት በዚሁ “የፋኖ ታጣቂዎች” ባሏቸው በተፈጸመው ጥቃት ከተማዋን ለቀው ተሰደዋል፡፡

ኒሞና ዴሬሳ የተባሉ አስተያየታቸውን የቀጠሉ ሌላው በመምህርነት ሙያ የሚተዳደሩ ነዋሪ እንዳሉት 20 አስከሬኖችን በአይናቸው አይተው ስማቸውንም መመዝገባቸውን አስረድተዋል፡፡ የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ መሆኑንም በመግለጽ፡፡

እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ከ40 በላይ ቁስለኞች መታከሚያ ቦታ እንኳ አጥተው ‘አስከፊ’ ያሉት ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የነዋሪዎች ንብረት የሆኑ ከብቶችን ጨምሮ በርካታ ሃብት መዘረፋቸውንም አንስተዋል።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የአሙሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፋንታሁን ታዬ ስለሁኔታው ማብራሪያቸውን እንዲሰጡ ከዶይቼ ቬለ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ ሳይሰጡ፤ ከህበረተሰቡ ጋር በውይይት ላይ መሆናቸውንና ነገ መልስ እንደሚሰጡ አስረዱ፡፡

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
8.5K views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 23:15:08 እንኳን ደስ አላችሁ የምስራች
የድል ዜናዎች ከግንባር ተሰሙ
ወ/ሮ ኪሪያት ኢብራሂም ላይ ጥብቅ ትዕዛዝ ወጣ
ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዝምታቸውን ሰበሩ
ሰበር መረጃዎች ሙሉ መረጃው




9.1K views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ