Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ ezmerejaet — 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @ezmerejaet
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4
የሰርጥ መግለጫ

እንዴት አደርሽ ኢትዮጵያዬ ! 🇪🇹

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 41

2022-08-29 21:17:08 ሰበር መረጃ

ኦነግ ሸኔ በወላጋ አማራዎችን ለጭፍጨፋ እንደወጣ ከአማራዎቹ ያልተጠበቀ ምላሽ ጠብቆታል
የኢትዮጵያ እግር ኮስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ግልፅ የወጣ ማጭበርበር ተጋለጠ
ሰበር የግንባር መረጃዎች



11.1K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:51:02 መረጃ

- ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬም  በቆቦና ዙሪያው በከባድ ውጊያ ላይ መሆናቸውን  ወልዲያ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ፣ የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች በስፋት ከተማዋን እየለቀቁ ወደ ወልዲያና አካባቢው ከተሞች መድረሳቸውንም እየተናገሩ ነው።  በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ቤተ እምነቶች ዳግም የተቀሰቀሰዉ የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት እንዲቆም፤ ኢትዮጵያዉያን ለሰላም እንዲሰብኩ ጥሪ አቀርበዋል።

በሌላ በኩል

--የአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት መቀሌ በሚገኝ የህጻናት መጫዋቻ ማዕከል ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙን አወገዘ። በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረዉ የመቀሌዉ የአየር ድብደባ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰላም ድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ያለው ቁርጠኝነት ላይ አስፈሪ ጥላ የጣለ ነዉ ሲል ገልፆታል።(DW)

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
10.9K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:31:29 ከአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

መዘናጋት ሳይኖርብን የመጣብንን በጋራ እንመክት
የአማራ ህዝብ አሁን እየደረሱበት ያሉትን  ችግሮች እያሳለፈ ያለው ለስልጣን ማራዘሚያ ጨቋኝ ነው፣ገዢ መደብ ነው፣ ታሪክ እምነት አጥባቂ ነው በሚል ስም በሰጡት ምዕራባውያን እና በስራ አስፈፃሚያቸው በአሸባሪው  ትህነግ ወያኔ ነው። ህውሀት የአማራን ህዝብ ታሪካዊ ጥላት በማድረግ እምነቱ፣ባህሉ፣ታሪኩ እንዲጠፋ የማድረግ ስራ በስልጣን በቆየባቸው ጊዜም ሰርቷል። በ1992 ዓ.ም በተቆጠረው የህዝብ ቆጠራ እስታቲክስ ተሰርቶ 2.5 ሚሊየን ህዝብ ከምድረ ገፅ አጥፍቶ በአለም የሰበአዊ መብት ድርጅት  ሲጠየቅ በመሪው በአቶ መለስ ዜናዊ በኤች አይ ቪ የሞቱ ናቸው የሚል ቀልድ እንደተቀለደ የሚታወቅ ነው በታሪክ ማህደር የሌለ ተረት ተረት በመፋጠር በህዝቦች መካከል የጥላቻ ዘር ሲዘራ የነበረ አንድን ትምክተኛ ሌላውን ጠባብ እራሱን ቅድስ አድርጎ የሚቆጥር ሲሆን የግፍ ቀንበሩ በዝቶ በኢትዮጵያውያን የጋራ ትግል ከስልጣን ቢወርድም እኔ የማላስተዳድራት ሀገር አትኖርም በማለት ከአራት ኪሎ ከወጣ በኋላም ትግራይ መሽጎ ለሀገር ሉዓላዊነት ዳር ድንበር የሚጠብቅ፣አዛውንቶችን የሚያግዝ አጋዥ የሌላቸውን ህፃናት የሚረዳ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ላይ የሀገር ከሃዲነቱን በትር ሰነዘረ ነገር ግን በጀግናው መከላከያ በአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ ተደምስሶ "የንስሀ ጊዜ ቢሰጠውም" የአማራ ህዝብ ላይ የምናወራርደው ሒሳብ አለ በማለት አማራ ህዝብ ላይ የጥላቻውን ነጋሪት በድጋሜ ይጎስም ጀመረ በብዙ መስዕዋትነት ድጋሜ ወደመጣበት ሸኝቶ ይቅር ባዩ ህዝባችን የተራቡትን አጠጥቶ የቆሰሉትን አክሞ በህዝቦቹ መካከል ምንም አይነት ችግር እንደሌለ እና አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ይቅር አለው።ነገር ግን" እፀድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች"! እንደሚባለው ህዝባችንን በጠላትነት ፈርጆ ለሶስተኛ ጊዜ ጥቃቱን ፈፅሟል። ስለዚህ ይህን አሸባሪ ቡድን ለማጥፋት የአማራ ህዝብ በአንድነት መረባረብ ይኖርበታል።

  ከዚህ በፊት ይህ አሸባሪ ቡድን የፈፀማቸውን ጥቃቶች ግፎች የምናውቃቸው ናቸው። የአማራን ህዝብ ተደራጅ የሚሉ የነቁ የምንላቸውን የአማራ ልጆች የአፄውን ስርዓት ናፋቂ፣ ትምክተኛ ነፍጠኛ እያለ የማሸማቀቅ ስራ ሲሰራ ሲያስር ሲገል የኖረ አሸባሪ ቡድን ነው። የመጣው ሁሉ አማራን ጥላት በማድረግ የመከራ ዶፍ እየወረደበት የሚገኘው በተዘራው የህውሀት የአረም ዘር መሆኑን እየገለፅን ይህን ሁሉ መከራ፣ ስቃይ፣ ሞት፣ መፈናቀል፣ሀብት ንብረቱ መውደሙ እየደረሰበት ያለው፦ ጎጃም፣ጎንደር፣ወሎ፣ሸዋ ብሎ ሳይሆን አማራ በሚለው የዘር ግንድ በመሆኑ መረዳት ይኖርብናል።

ስለዚህ ሁሉም አማራ  በሀገር ውስጥ ይሁን ከሀገር ውጪ በአንድነት በጋራ መቆም የመጣውን ወራሪ መመከት ወደ መጣበት መመለስ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ምንም አይነት ችግር አልነበረበትም አይኖርበትም፤ ይልቁንም ተመጋጋቢ የሆኑ በርካታ እሴቶች ያላቸው ህዝቦች ናቸው። ነገር ግን የአማራን መጥፋት የሚፈልገውን ህውሃት በህዝባችን ህልውና ላይ የመጣ በመሆኑ ማህበራችን የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ ከፋኖ፣ ሚኒሻ፣ ከአማራ ልዩ ሃይል እና ከሀገር አለኝታው መከላከያ ጎን ማንኛውም የኢትጵያ ህዝብ እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን።

"ውርደት ለመሸከም የሚችል ትካሻ የለኝም"! የሚሉት የእምዬ ልጆች፣ቤተሰብ ከሀገር አይበልጥም የሚለው የበላይ ዘለቀ ልጆች፣የአንድነት ፈር ቀዳጅ የወንዶቹ ቁና የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ ልጆች መካሪ አስታራቂ የሆኑት የሺህ ሁሴን የንጉስ ሚካኤል ልጆች የበረሃው መብረቅ የኡመር ሰመትር ልጆች የአባጅፋር ልጆች  የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ እና ሀገርን በእጅ አዙር ለምዕራባውያን የማስገዛት አላማን እምቢ ብለን በጋራ እንመክት ማለት እንወዳለን።  በዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ለወደፊት ተፅፎ የአንድ ሀገር ዜጎች ወንድማማቾች እርስ በእርሳቸው ተጠፋፍተው ነበር በመባል ታሪካችን እንዳይፃፍ በማወቅም ባለማወቅም የዚህ ቡድን ተባባሪ የሆኑትን ህፃናት፣አዛውንቶች የተማረኩ ወታደሮች በኢትዮጵያዊነት ለዛ እንደ አባታችን ዳግማዊ ምኒልክ በይቅር ባይነት ልንይዛቸው ይገባል።የአባታችን ልብ ለጣሊያን ራርቶ ምርኮኛን ተንከባክቦ ሸኝቶ ነበርና።

በመጨረሻም የትግራይ ተወላጆች በሀገር ውስጥ ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ከእውነት ጎን በመቆም በህዝባችሁ፣ በወገናችሁ እና በሀገር ላይ የሚደርሰውን ጥፋት የዛሬ 20 ዓመት ወደኋላ ቀርተው የሚያስቡ ከራሳቸው ውጭ ለህዝብ ደንታ ለሌላቸው የአሸባሪው ቡድን አባላት መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ታሪካዊ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ በማለት ማሳሰብ እንወዳለን።
የአማራ ወጣቶች ማህበር በሸዋ!
        ድል ለእኩልነት
       ድል ለነፃነት
       ድል ለፍትህ
    ጉዞ ምኒልክን ይዞ !
                       ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም
ደ/ብረሃን ኢትዮጵያ

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
10.7K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:55:23 ሰበር መረጃ

ኦነግ ሸኔ እና አማራ በወለጋ ጦርነት ገጠሙ/ የእግር ኳሱ ፌዴሬሽን እውነታና ሚስጥር ተጋለጠ/
ሰበር የግንባር መረጃዎች



10.4K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:29:57 ሰበር መረጃ

ኦነግ ሸኔ እና አማራ በወለጋ ጦርነት ገጠሙ/ የእግር ኳሱ ፌዴሬሽን እውነታና ሚስጥር ተጋለጠ/
ሰበር የግንባር መረጃዎች



1.8K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:32:07
መረጃ ቆቦ

የህወሓት ታጣቂዎች በቆቦ ከተማ ንጹሃንን መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!

ቆቦ ከተማን የተቆጣጠሩት የህወሓት ታጣቂዎች ንጹሃንን መግደላቸውን የራያ ቆቦ ወረዳ ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ገለጹ።መንግስት የሕዝብን ከፍተኛ ፍጅት ለማስወገድ ሲባል የመከላከያ ኃይል የቆቦ ከተማን መልቀቁን መግለጹን ተከትሎ የህወሃት ታጣቂዎች በራያ ቆቦ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል።

ለደህንነታቸውን ሲባል ድምጻቸውን ቀንሰው በስልክ ያነጋገሩን ግለሰብ፤ በከተማዋ ወጣቶች መገደላቸውን ተናግረዋል።በቆቦ ከተማ ስልክ ይዞ መገኘት እንደሚስገድል የተናገሩት አስተያየት ሰጭዋ፤ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን አሁንም አለመነሳቱን ተናግረዋል።አሁን ላይ በቆቦ ከተማ በተለያዩ መንገዶች ላይ የተገደሉ ወጣቶች አስክሬን እንዳለ የተናገሩት ደግሞ ሌላ አስተያየት ሰጭ ናቸው። አሁን ባለው ሁኔታ አስክሬን ማንሳት እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን አሁንም ውጊያ እንዳለ ተናግረዋል።

ወጣቶቹ እና አርሶ አደሮቹ “ፋኖ ናችሁ፤ የብልጽግና አባል ናችሁ፤ ሚሊሻ ናችሁ” በሚል ግድያ እየተፈጸመ እንደሆነ ገልጸዋል።በሮቢት ከተማ ብቻ ሁለት ወጣቶች መገደላቸውን ከስፍራው ወደ ወልዲያ የመጣ አንድ አስተያየት ሰጭ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
4.6K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:46:04 የግንባር ዜና የሚቀርብበት ቻናል ልጠቁማችሁ


@Addis_News
@Addis_News
5.3K viewsedited  10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:44:32 መረጃ
ዛሬ ሮቢት ላይ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት እና የምስራቅ አማራ ፋኖ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ነው።ቆቦ ሙሉ ለሙሉ አትታይም ከትግራይ ክልል እራበን ጠማን ብሎ ተፈናቃሎ በካምፕ የነበረ በሙሉ ገብቶ ሲጨፍር አድሯል
መታወቂያ ይጠይቃሉ ፤ በተጨማሪም መሃል ከተማ ላይ ኔትወርክ እንደማይሰራ ፤  እናም አሁን የደወልንላችሁ ተራራ ላይ ሁነን ነው በስልክ ያገኘንው መረጃ  ።

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
5.3K views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 13:10:11 ቆቦ ከተማ
ቆቦ በወራሪው ሀይል ቁጥጥር ስር መሆኗን አሁን አረጋግጠናል
የቆቦ ማህበረሰብ ህዝባችን ነው ወደ ቀድመው ሰላሙን ተመልሶ ንሮውን በሰላም እንዲያካናውን እንዲሁም በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲመለስ የናንተ ግዴታነውና ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል!!
በቆቦ አሁንም ውጊያው ቀጥሏል በርካታ ታንኮች ተማርከዋል
አዲስ ነገር ይዘን እንመለሳለን ጠብቁን
@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
14.4K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:53:52 ሀይቅ

ሀይቅ በዛ ባለ ቁጥር ተፈናቅለው ወዲያ ወዲህ በሚሉ ሰዎች ውስጥ እንደሆነች እንዲሁም ትልቅ የሆነ ሰልፍ ባንኮች ላይ እንዳለ በስልክ አረጋግጠናል ወልድያም ደግሞ የከባድ መሳሪያ ድምፅ እየተሰማ እንደሆነ እና ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳለ ለማወቅ ችለናል
ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳን

ምንጭ :- አዲስ ነገር መረጃ

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet
6.5K views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ