Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ - ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬም  በቆቦና ዙሪያው በከባድ ውጊያ | 🇪🇹 E.Z መረጃ 🇪🇹

መረጃ

- ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የህወሓት ታጣቂዎች ዛሬም  በቆቦና ዙሪያው በከባድ ውጊያ ላይ መሆናቸውን  ወልዲያ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ተናገሩ፣ የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች በስፋት ከተማዋን እየለቀቁ ወደ ወልዲያና አካባቢው ከተሞች መድረሳቸውንም እየተናገሩ ነው።  በሌላ በኩል በትግራይ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ቤተ እምነቶች ዳግም የተቀሰቀሰዉ የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት እንዲቆም፤ ኢትዮጵያዉያን ለሰላም እንዲሰብኩ ጥሪ አቀርበዋል።

በሌላ በኩል

--የአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት መቀሌ በሚገኝ የህጻናት መጫዋቻ ማዕከል ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙን አወገዘ። በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረዉ የመቀሌዉ የአየር ድብደባ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በሰላም ድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ያለው ቁርጠኝነት ላይ አስፈሪ ጥላ የጣለ ነዉ ሲል ገልፆታል።(DW)

@Ezmerejaet
@Ezmerejaet