Get Mystery Box with random crypto!

ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianreporteramharic — ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianreporteramharic — ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianreporteramharic
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.55K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-18 12:19:55
ደሞዝ መክፈል ላቃታቸው ክልሎች ብድር ተሰጠ


4.6K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 18:35:54
ኦነግ ሸኔ በወለንጪቲ በከፈተው ጥቃት ጉዳት ደረሰ


5.0K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:10:36
ህወሓት በምርጫ ቦርድ ላይ ያቀረበው ተቃውሞ


5.2K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 11:25:50
ዘወትር ረቡዕ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ አሁን በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።
--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
--------------------
የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ www.EthiopianReporterJobs.com
4.7K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 23:28:39 ሕወሓት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረበ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ስለ ሕወሓት የሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ሕወሓት፣ወሳኔው በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረበ።

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወ.ሓ.ት) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም ያስተላለፈውን ውሳኔ ዳግም በማጤን፣ የሕወሓት ህጋዊ ሰውነት ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ፣ ድርጅቱና ኃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንዲችሉ፣ የተወረሱ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች እንዲመለሱ ጥያቄ ማቅረቡን ትናንት ምሽት ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውሷል።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ያስተላለፈው ዉሳኔ በኤለክትሮኒክስ ሚድያ የተገለፀ ቢሆንም ለድርጅቱ የተሰጠበት ቀን ግን ግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ጠቁሟል።

በቦርዱ የተሰጠው ውሳኔ ቅቡልነት የሌለው፣ በፕሪቶርያ የተደረሰውን ስምምነትና ህግን መሰረት ያላደረገ መሆኑ መገንዘቡንም በመግለጫው ጠቁሟል።

ሕ.ወ.ሓ.ት በአገሪቱ ተንሰራፍቶ የቆየውን አፋኝ ስርዓት በመገርሰስ በኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ፣ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸው በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ፣ በቋንቋቸው እንዲዳኙ፣ በማንነታቸው እንዲኮሩና ታሪካቸው እንዲያሳድጉ የሚያስችል ሕገ-መንግስታዊ ዋስትና እንዲረጋገጥ በማድረግ በኩል ደማቅ ኣሻራ ያለው ኣንጋፋ ድርጅት መሆኑ ጠቁሞ፣ከቅርብ ኣመታት ወዲህ ግን የፖለቲካ ልዩነቶችን በሰላማዊ ፣ዲሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ መንገድ መፈታት ባለመቻሉ በ2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል ደም አፋሳሽ ግጭት ተፈጥሮ እስከያዝነው ዓመት መጀመሪያ ወራቶች ድረስ መዝለቁን አብራርቷል።

ይህን ደም አፋሳሽ እልቂት በተቻለ መልኩ ለማስቆም የተለያዩ ጥረቶችን ሲደረግ ቆይቶ በአፍሪካ ህብረት፣ በኢጋድ እና በአሜሪካን መንግስት አሸማጋይነት እንዲሁም በደቡብ አፍሪካና በኬንያ መንግስታት አመቻችነት ከፌደራል መንግስቱ ጋር ድርድር ተደርጎ እአአ ሕዳር 23 ቀን 2022 በፕሪቶሪያ ከተማ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈረም መቻሉን አስታውሷል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት በመሰረታዊነት ማዕከል ያደረገው : ሰላም፣ ሰብዓዊ መብት፣ ዲሞክራሲ፣ ተጠያቂነት እና ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት መመለስ ነው። ከስምምነቱ መፈረም ጀምሮም ሕወ.ሓ.ትና ኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት በጋራና በተናጠል የገቡትን ግዴታና የስምምነቱን ዓላማዎች እየፈፀሙ ይገኛሉ።

ለዚህም አበረታች የሚባል ውጤትና ለቀጣይ ስራዎች ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ እየተፈጠረ በመምጣቱ ስምምነቱ ዓለም አቀፍዊ እና አገራዊ እውቅና ተሰጥቶታል። የአፍሪካ ህብረት፣ ኢጋድ፣ የተባበሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የተለያዩ አገራት መንግስታት እውቅና እና ድጋፋቸውን ሰጥተውታል።

በሌላ በኩል የፌደራሉ መንግስት ህግ አውጪ አካል የሆነው የህዝብ ተወካዮች ምክር-ቤት፣ የሚኒስትሮች ምክር-ቤት፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. : ጠቅላይ ኣቃቢ ሕግ፣ የክልል መንግስታት እና የከተማ አስተዳደሮች ለስምምነቱ እውቅናና ድጋፍ የሰጡ ህገ-መንግስታዊ አካላት ናቸው ብሏል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር-ቤት ድርጅቱን ከአሸባሪነት ስያሜ የመሰረዝ ውሳኔ አስተላልፏል። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ የክልሉ ጊዜያዊ ኣስተዳደር እንዲመሰረት በፕሪቶርያው ስምምነቱ አንቀፅ 10(1) በተገደነገገው መሰረት የትግራይ ኣካታች ጊዜያዊ ኣስተዳደር በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ተመስርቷል" የፕሪቶሪያው ስምምነት ዓላማ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ ክልሉን እና የክልሉን ህዝብ ወደ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ መመለስ ነው።

በዚህም መሰረት የስምምነቱ ይዘት ተፈፃሚ እንዲሆን የትግራይ ህዝብና ድርጅታችን ህወሓት እንዲሁም ሃላፊነት ያላቸው የፌደራል መንግስት አካላት ግዴታቸውን ሊወጡ የሚገባ ቢሆንም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን የድርጅታችን ህጋዊ ሰውነት የመሰረዝ ውሳኔ እንዲነሳ የቀረበለትን ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የተሰረዘ የፖለቲካ ፓርቲ ተመልሶ ህጋዊ ሰውነት የሚያገኝበት ድንጋጌ ስለሌለ የድርጅታችን ህጋዊ ሰውነት ሊመለስ እንደማይቻል ከፕሪቶርያ ስምምነት ውጪ በሆነ መንገድ ውሳኔውን እንዳሳወቀው ሕወሓት በመግለጫው ተናግሯል።

በቦርዱ የተላለለፈውን ውሳኔ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት የማይቀበል፣ እየተጠናከረ በመሄድ ላይ ያለውን የሰላም ስምምነት ትግበራ ባለቤት አልባ የሚያደርግ፣ ከጦርነቱ ወደ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ለሚገቡ ሃይሎች መደገፍ እና ማበረታታት ሲገባ ድርጅቶችን በማፍረስ ቀጣይ ሰላም እንዳይረጋገጥ የሚያደርግ መሆኑ፣ ለህዝቦቻችን የማይመች እና ለሌሎች ሃይሎችም ተስፋ የማይሰጥ ነው ብሎ ሕወሓት እንደሚያምን አስታውቋል።

በኣጠቃላይ ሕወሓት ውሳኔውን እንደማይቀበለው እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚወያይበት ፣ምርጫ ቦርድ ውሳኔውን እንደገና በማየት የፕሪቶርያ ስምምነትና ሌሎች የፌደራል ተቋማት ያስተላለፉትን ውሳኔዎች መነሻ በማድረግ እንዲያስተካክል ይጠይቋል፡፡

"የሰላም ስምምነቱ ባለቤት የሆናችሁ መላው የድርጅታችን ኣባላት፣ የትግራይ ህዝብና ሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ይህንን ውሳኔ የሰላም ሂደቱ ኣደጋ ውስጥ የሚከት መሆኑ ተገንዝባችሁ የበኩላችሁን ጥረት እንድታደርጉ ድርጅታችን ህ.ወ.ሓ.ት ጥሪውን ያቀርብላችኋል" ብሏል።

የፌደራል መንግስትም ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠው ውሳኔ በተጀመሩት አወንታዊ የሰላም እና የመደጋገፍ ጥረቶች ላይ ሊያሳድረው የሚችል አላስፈላጊ ጫና እንዲሁም የፌደራል መንግስቲ ህጋዊ ውሳኔዎችንና ሓርነት ትግራይ ስምምነቶች በሁሉም የመንግስት ተቋማት እና አካላት እንዲከበሩ የማድረግ ሀላፊቱን ግምት ውስጥ በማስገባት፣ የቦርዱ ውሳኔ እንደገና ታይቶ ከሕ.ወ.ሓ.ት ህጋዊ ሰውነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ያሉትን ህጋዊና ፖለቲካዊ አማራጮች ተጠቅሞ ነገሮች ቅድመ-ጦርነት ወደ ነበሩበት ሁኔታ እንዲመለሱ በማያደርግ ቀና አካሄድ እንዲፈቱ፣ የፕሪቶርያ ስምምነት በተሟላ መንገድ ተግባራዊ እንዲደረግ እና የተጀመረውን የሰላም ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

የፕሪቶርያ ስምምነት እንዲሳካ "ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ የነበራችሁ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአጠቃላይ የአፍሪካ ህብረት፣ በተለይ ሂደቱን የሚያደናቅፍ እና አደጋ ውስጥ የሚከት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶርያ ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል የድርሻችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን" ብሏል።
4.1K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 23:28:37
3.5K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 17:53:59
ህገመንግስቱ መሻሻል አለበት የሚል ምክረ ሀሳብ ቀረበ


3.8K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 15:14:55
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ለንግድ ባንክ የቦርድ አባላትን ሰየመ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሦስት የቦርድ አባላትን ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓም መሰየሙ ታወቀ።

የንግድ ባንክ ቦርድ አባል ሆነው የተሰየሙት፣ የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ|ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንድም አገኝ ነገራና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር(ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግት ሀምድ ናቸው።
6.0K views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 12:08:37
በሲዳማ 136 ሰዎች በሙስና ተጠየቁ/በአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ ጨረታ


4.0K views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:44:56 የመሬት ሊዝ ጨረታ ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጣ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአራት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ አወጣ ። ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች መነሻ ዋጋ ከፍተኛው 2,213 ብር መሆኑ ታውቋል።

የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓም ይፋ እንዳደረገው፣ በከተማዋ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች 297 ይዞታዎችን ለተጠቃሚዎች በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ ውጥቷል።

በሊዝ ጨረታ እንዲተላለፉ የተዘጋጁት 297 ይዞታዎች አጠቃላይ ካሬ ሜትር 143 ሺህ (14 ነጥብ 3 ሄክታር) ሲሆኑ፣ ይዞታዎቹ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው ብሏል።

ለጨረታ ከሚቀርቡ ቦታዎች መካከልም ከዚህ ቀደም በምደባና በጨረታ ወስደው ያላለሙና እርምጃ የተወሰዳባቸው፣ በተለያዩ ጊዜያት በህገ ወጥ መንገድ የተወረሩና ወደ መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች እንደሚገኙበት አስታውቋል።

ለጨረታ የቀረቡት ይዞታዎች ዝቅተኛው የጨረታ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 960.21ብር ሲሆን፣ ከፍተኛ የተባለው መነሻ ዋጋ 2,213. 25 ብር መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ከግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ከግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መሳተፍ እንደሚችሉ ገልጿል።

ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ይዞታ የተቀመጠውን መነሻ ዋጋ መሠረት በማድረግ ከአጠቃላይ ዋጋው 20 በመቶውን ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።

በዚህ ጨረታ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ግለሰቦች ፣ የንግድ ማኅበራት ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በአንድ የጨረታ ሰነድ ከአንድ ሰው በላይ ሆኖ መወዳደር እንደሚቻል አመልክቷል።

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አዳራሽ እንደሚከፈት አስታወቋል።
4.9K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ