Get Mystery Box with random crypto!

ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianreporteramharic — ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianreporteramharic — ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianreporteramharic
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.55K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 28

2022-08-27 15:37:32
[አበይት ዜና] ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ




--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
2.6K viewsedited  12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 14:40:18
የሲዳማ ክልል የዞን አደረጃጀት ፀደቀ።


የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የዞን አስተዳደር እና አደረጃጀትን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ተቀብሎ ክልሉ በ4 ዞኖች እና በ1 ከተማ አስተዳደር እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል።

የክልሉ ምክር ቤት ውሳኔውን ያሳለፈው እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ነው።

የዞኖቹ ስያሜዎች ሰሜን ሲዳማ ዞን፣ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን፣ ደቡብ ሲዳማ ዞን እና ምስራቅ ሲዳማ ዞን በሚል እንደሚጠራ ተገልጿል።

--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
2.7K viewsedited  11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:43:51
ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት ተቀበሉ

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ነሐሤ 21/2014 በተለያዮ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያሰመረቀ ሲሆን በዕለቱም ሲጠበቅ በነበረው ፕሮግራም ለብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ እና ለአትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት አበርክቷል::

ብጹዕ አቡነ ኤርሚያስ በሃይማኖት አባትነታቸው የተማሩትንና ያስተማሩትን በተግባር እየኖሩ ያሉ አርአያ ሰብ በመሆናቸው እንዲሁም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በስፖርቱ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ፋና ወጊ አትሌት በመሆን እና ለህብረተሰብ ፍቅርና አንድነት መጎልበት እየተጋች ያለች ተምሳሌት በመሆኗ ነው ብሏል ዮኒቨርሲቲው::

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ ሶስተኛ ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ እንዲሁም በማሪታይም ሙያ ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው በዛሬው ዕለት ያስመረቀው

--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
2.9K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:42:40
መንግሥት በትግራይ የሚኖሩ ወገኖች የህወሃት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው ቦታዎች እንዲርቁ አሳሰበ


መንግሥት ይህን ያለው ለህወሃት ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ በገለፀበት ወቅት ነው፡፡
መንግሥት እስከ አሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ህዉሃት ጥቃቱን ቀጥሎበታል ያለው የመንግስት መግጫ ፣ የፌዴራል መንግሥት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለህዉሃት ፀረ ሰላም ዕብሪት ምንጭ የሆኑ የተመረጡ ወታደራዊ ዐቅሞችን ዒላማ ያደረገ እርምጃ እደሚወስድ አስታውቋል።

"ስለሆነም በትግራይ የምትኖሩ ወገኖቻችን በተለይም የህወሃት ወታደራዊ መሣሪያዎች እና
ማሠልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ይመከራል" ሲል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን በመግለጫው አሳስቧል፡፡

--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
3.8K viewsedited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:24:11
በኦጋዴን ቤዚን ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ [አበይት ዜና]



--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
3.3K viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:35:54
በኦጋዴን ቤዚን ሰባት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት መኖሩ ተረጋገጠ


በኢትዮጵያ ደቡብ ምስራቅ ክፍል ኦጋዴን ቤዚን ያለው የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት ሰባት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ጫማ መሆኑ በጥናት መረጋገጡን የማዕድን ሚኒስቴር ኢንጅነር ታከለ ኡማ አስታወቁ፡፡

በኦጋዴን ቤዚን ያለውን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ክምችትና የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት ለማድረግ መጋቢት 2014 ዓ.ም. ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ውል የገባው የአሜሪካው ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሲሼየትስ ኢንክ ኩባንያ የጥናቱን ሰነድ ዛሬ አርብ ነሐሴ 20፣ 2014 ዓ.ም. ለሚኒስቴሩ አስረክቧል፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው በተባለለት በዚህ ጥናት ከዚህ ቀደም ከሁለት እስከ ሶስት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ እንደሆነ ሲገመት የነበረው የኦጋዴን ቤዚን የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት በሁለትና ሶስት እጥፍ የጨመረ ሆኖ መገኘቱን ኢንጅነር ታከለ ተናግረዋል፡፡

“ከዚህ ቀደም የነበሩ ኩባንዎች ምን ያህል ክምችት እንዳለ አይነግሩንም ነበር” ያሉት ሚኒስትሩ አሁን የተጠናው ጥናት ግን ለክምችቱ መጠን ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ስለክምችቱ የነበሩ ጥናቶች የኩባንያዎች እንደሆኑ አሁን በአሜሪካው ኩባንያ የተደረገው ጥናት ግን የመንግስት መሆኑን ኢንጅነር ታከለ አክለዋል፡፡

በሪፖርተር ( አማኑኤል ይልቃል )
--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
3.7K viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:29:52
በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ለቀጣይ ስድስት ወራት መጨመር አይቻልም ተባለ፡፡

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ፡፡
የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡
ይህንን ክልከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በ 9977 አጭር ቁጥር ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ አስታዉቋል፡፡

--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
3.5K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:18:01
ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት እንዲረጋጋ እና የተጀመረው የሰላም ሂደት እንዲቀጥል ተጠየቀ



ይህን የጠየቀው የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ነው፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤቱ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል መልሶ ያገረሸው የትጥቅ ግጭት በእጅጉ እንደሚያሳስበዉ አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በፊት የተፈጠረው የትጥቅ ግጭት ተነግሮ የማያልቅ የሰው ልጅ ስቃይ እና ከፍተኛ መሰረተ ልማቶች መውደም ምክንያት መሆኑንም ምክር ቤቱ ገልጿል፡፡
በመሆኑም አሁን ዳግም የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት እንዲረጋጋና ግጭቱ እንዳይባባስ አስፈላጊው ሁሉ እንዲደረግ ምክር ቤቱ አጥብቆ ያሳስባል ሲል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫው አስታዉቋል።

በተጨማሪም አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁሙ መከበር ለሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦት ቀጣይነት እና ለሰላም ሂደቱ ስኬታማነት ወሳኝ እንደሆነ እንደሚያምን ተናግሯል።
ምክርቤቱ አለመግባባቶች በፖለቲካዊ ውይይት መፈታት እንዳለባቸው በጥብቅ እንደሚያምንና ለዚህም የሰላም ማስፈን ሂደቱ በአስቸኳይ እንዲቀጥልና ሀገሪቱን ከተጨርማሪ ጥፋት ለመታደግ የሰላም ሂደቱ በቅን ልቦና እንዲካሄድ ጠይቋል።

--------------------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
3.9K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 16:21:59
ህወሓት ነዳጅ ዘረፈ መባሉና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምላሽ | አሜሪካ በኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መጀመሩ አሳስቦኛል አለች




የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3namddM
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
3.9K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 21:11:03
ትግራይ ክልል ሊገባ የነበረ የጦር መሳሪያ የጫነ አዉሮፕላን መመታት


4.5K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ