2023-06-08 18:39:48
የቀጣዩ ዓመት የመከላከያ በጀት 50 ቢሊዮን ብር ሆኖ ቀረበ
- በጦርነቱ ለወደሙ መሠረተልማቶች ግንባታ 20 ቢሊዮን ብር ተይዟል
ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት በጀት ውስጥ ለመከላከያ ሚኒስቴር 50 ቢሊዮን ብር ሲመደብ ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ ተቋማትና አገልግሎቶችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙ ተገለጸ።
በ2015 በጀት ዓመት ለመከላከያ ሚኒስቴር የተመደበው በጀት 84 ቢሊዮን ብር ሲሆን በ2014 የበጀት ዓመት 22 ቢለየን ብር ከተመደበ ከጥቂት ወራት በኋላ ከጸደቀው 122 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ውስጥ 90 ቢሊየን ብሩ በማግኘቱ በ2014 የተቋሙ በጀት ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶ ቢሊዮን ብር ባለይ ተሻግሮ ነበር።
የሰሜኑ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መፍትሔ ማግኘቱን ተከትሎ መከላከያ ሚኒስቴር ለ2016 በጀት ዓመት 50 ቢሊዮን ብር እንደተያዘለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከቀረበው የቀጣዩ ዓመት ረቂቅ በጀት ለመረዳት ተችሏል።
ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው ረቃቅ በጀት ውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የወደሙ መሠረተልማቶችን ወደነበሩበት ለመመለስ 20 ቢሊዮን ብር እንደተያዘም ሰነዱ ያመለክታል።
ለ2016 በጀት ዓመት ለክልሎች ድጎማ 214 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከሁለት ዓመታት
በላይ ከፌዴራል መንግስት የበጀት ድጎማ ያለገኘው የትግራይ ክልል ለቀጣዩ በጀት ዓመት 12.5 ቢሊዮን ብር ተመድቦለታል።
ለክልሎች ድጎማ ከተያዘው በጀት ውስጥ እንደሁልጊዜው ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት ኦሮሚያ ፣ አማራና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ሲሆኑሕዝቦች ፤ እንደቅደም ተከተላቸውም ብርዐ71.9 ቢሊዮን ፣ ብር 45.1ቢሊዮን እና ብር 26.9 ቢሊዮን ተመድቦላቸዋል።
በተጨማሪም ፣ ሶማሌ 20.8 ክልል ቢሊዮን ብር፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝች ክልል 6.4 ቢሊዮን ብር፣ ሲዳማ ክልል 8.5 ቢሊዮን ብር ተደልድሎ በረቂቅ በጀቱ ቀርቧል፡፡
በተመሳሳይ ፤ ለአፋር ክልል 6.3 ቢሊዮን ብር፣ ለቤንሻንል ክልል 3.8 ቢሊዮን ብር፣ ለጋምቤላ ህዝቦች ክልል 2.7 ቢሊዮን ብር፣ ለሃረሪ ህዝብ ክልል 1.5 ቢሊዮን ብር፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስታደዳር 5.2 ቢሊዮን ብር፣ ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር 1.8 ቢሊዮን ብር ሆኖ በረቂቁ ተደልድሏል፡፡
4.3K viewsedited 15:39