Get Mystery Box with random crypto!

ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianislamic — ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianislamic — ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianislamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 108.27K
የሰርጥ መግለጫ

በቅንነት ዩቲብ ቻናላችን ሰብስክራፕ ያድርጉ
https://bit.ly/4044MQR

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-03-10 18:29:06
የረመዳን ጨረቃ በሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ስለታየች ነገ ሰኞ መጋቢት 02, 2016 E.C. (March 11, 2024 G.C.) የረመዿን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።


አላህ የምንጠቀምበት ያድርገን!
ረመዳን ሙባረክ!
32.6K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 19:53:07 «ምንሼ?»
«ግጭት ይመስለኛል!»
«ኢክሩ በታጠፈችበት በኩል እኮ ነው!»
«የምርህን ነው?»
«አዎ .... እስኪ አየት አድርገን እንለፍ!»
ማዞሪያ ጋር ስንደርስ አዙረን ወደ ኋላ ተመለስን። ኢክሩ በታጠፈችበት በኩል የትራፊክ መዘጋጋት ተፈጥሯል። ከርቀት ሰው ከቦ ይመለከታል። ቆመጥ የያዙ ፖሊሶች ሲሮጡ ይታየናል።

ሰሚሬ አንዱን ህንፃ እያሳየ «ለምን መኪናችንን እዚህ ፓርክ አናደርግም?» አለ።
«አዎ የሚለቅ አይመስልም ጃሙ!»
መኪናችንን ህንፃው ስር ፓርክ አድርገን ከመኪናችን ወረድን! ለማንኛውም ብዬ ኢክራም ጋር መደወል ጀመርኩ!

ይቀጥላል!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
23.2K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-09 19:53:07 የልብ ነገር
ክፍል ዘጠኝ
(ፉአድ ሙና)
***

ቃ ቃ ቃ!
እንደ እቃቃ
ህይወት ሲንቃቃ!
ቃ! ቃ! ቃቃ! ቃቃቃ!

ጓ ጓ ጓ!
ልብ ሲደቅቅ
ሲሰበር ከአንጓ!
ጓ! ጓ! ጓጓ! ጓጓጓ!

***
ነገሩ የትዕግስት ጉዳይ ነው እንጂ የማይደርስ ቀን .... የማይነጋ ለሊት የለም። እነሆ ፈሪሀም ሀገሯ ገብታለች። አራት አመት ሙሉ ከናፈቋት ወዳጆችዋ ጋር በሰላም ተገናኝታለች። አባቷም የቋመጠለትን እድል አገኝቷል። ሰርግ የሚመስል ድግስ ደግሶ ምርቃቷን አክብሯል። ይህ ሁሉ ግን ለእኔ ስሜት አይሰጥም .... ምክንያቱም የቀድሞው ፉአድ አይደለሁም። ለፈሪሀ ፍቅር የተንበረከከው ፉአድ ከጉልበቱ ላይ አቧራውን አራግፎ ከተንበረከከበት ተነስቷል። ፈሪሀን ያክል ፍቅሩ ላይ ሴራ ጎንጉኗል።

ፈሪሀ አይኖቼን በትኩረት ተመለከተቻቸው።
«ቀልደኛ! .... አሁን በሁለተኛ ሚስት ይቀለዳል?»
«ቀልዴን አይደለም ፌሪ .... ሁለተኛ ሚስት አግብቻለሁ።»
«ምን እያልክ ነው?» ፊቷ ወደ ቲማቲምነት መቀየር ጀምሯል።
«እንዳልኩሽ ነው።» ግድየለሽ ሆኛለሁ።
«የኔ ውድ .... አንተ አታደርገውም። እኔ አውቅሀለሁ ፋሚ! አንተ እኔ ላይ ሌላ ሴት ማግባት ቀርቶ አታይም ውዴ! አውቅሀለሁ የኔ ጌታ አንተ አታደርገውም።» አይኖቿ በእንባ እየተሞሉ ነው።
«አዝናለሁ ፌሪ .... አግብቻለሁ።»
«በምን ልመንህ? አንተን አውቅሀለሁ። እንደዚህ አታደርግም በፍፁም! በአላህ ቀልዴን ነው በለኝ!»
«አራት አመት ከባድ ነበር ፌሪዬ .... ከሁለት አመት በላይ መታገስ አልቻልኩም።» ስልኬን ከፍቼ የእኔ እና የኢክራምን ፎቶ በሩቁ አሳየኋት። ፊቷ ላይ እሳት ተንቀለቀለ። የእንባዎቿ ዘለላዎች አፏ ውስጥ ቀድሞ በገባ ተሽቀዳደሙ። ሰውነቷ መርገፍገፍ ጀመረ።
«ፉአድ ሙና!» በሳግ በታፈነ ድምጿ ጮኸች።
«አቤት?»
«ከአጠገቤ ጥፋ!»
«እሺ!» ተነሳሁ።
«የት አባህ ነው የምትሄደው? .... ተቀመጥ!» ተንደርድራ የመኝታ ክፍሉን በር ቆለፈችው። ስትመለስ በጥፊ ወለወለችኝ። ደረቴን ትከሻዬን በእጆቿ እየደበደበች ማልቀሷን ቀጠለች። መቧጨር እንዳትጀምር በጥንቃቄ እየጠበቅኳት ነው። ልብሴን በሁለት እጆቿ እንደጨመቀች ደረቴ ላይ ተጋድማ ማልቀሷን ቀጠለች። ማልቀሱ ሲደክማት ወደ መሳደብ ተመለሰች።
«ይኼኔ ከድሮም ትማግጥብኝ ነበር!
ውሻ ነህ! ውሻ ነህ!
ምን ጎደለህ ከእኔ?
ስድ ነህ! ልክስክስ ነህ!» ማቆሚያ የሌለው ስድብ አወረደችብኝ።
«ብርጭቆ እንደሰበረ ሰው ይቅር በይኝ ትላለህ ደግሞ! ወይኔ ፈሪሀ! እኔ እዚያ ባንተ ናፍቆት እሰቃያለሁ .... አንተ እዚህ ከማንም ጋር አልጋ ለአልጋ ትንከባለላለህ! ቆሻሻ! ቆሻሻ ነህ!»
ደረቴን በስስ መዳፏ ትደበድባለች።
«የአንድ ቀን ስህተት እኮ አይደለም ይኼ! አስበህ .... ወስነህ .... ሽማግሌ ልከህ እኮ ነው ያደረግከው! ቢያንስ እንዴት አታማክረኝም? ስሜትህ አናትህ ላይ ከወጣ ተመለሽ ብትለኝ እመጣ አልነበረ ወይ? እሱን ምክንያት አድርገህ ሴሰኝነትህን ነው ያረካኸው! ሰው ሚስቱን አጥቶ ነው ብሎ ይረዳኛል ብለህ .... ሆን ብለህ ነው እድሉን የተጠቀምከው! ውሻ ነህ! ቆሻሻ ነህ!»
ዝም ብዬ የሚወርድብኝን ስድብና ድብደባ እቀበላለሁ።
«ለመሆኑ ሽማግሌ ማን ሆነልህ? አባትህ ለዚህ ሴሰኝነት እሺ ብለው ሽማግሌ ሆኑ? ወይስ መስጂድ የሰበሰብካቸው አራት ማግባት እያሉ የሚውሉ ሴሰኛ ወንዶችን ይዘህ ሄድክ? ሚስትየውስ ለራሷ ክብር የላትም ወይ? እንዴት ሰው የሰውን ትዳር ሊያፈርስ ይገባል? እንዴት ባል ያለው ወንድ ላግባ ትላለች? ወይስ ሸ ር ሙ ጣ ነው ያገባኸው?»
ለቅሶዋ ጉልበት ማጣት ድምጿም መዘጋት ጀመረ።
«እሺ ብሎ ግን ቆ መ ል ህ? አካልህ ታዘዘህ ወይ? ይኼኔ እኮ እዚህ አልጋዬ ላይም ይዘሀት መጥተህ ይሆናል! ውሻ! ልክስክስ! ልክስክስ ነህ!»
እቅፍ አደረግኳት። ጭምቅ!
«ልቀቀኝ! ልቀቀኝ አልፈልግም! ሂድና ሸ ር ሙ ጣ ህን እቀፍ! ደረትህ ይሸታል! እሷን ያቀፍክበት ይገማል!»
«ይቅርታ ....» አልኩኝ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ!
«ለምኑ ነው ይቅርታ? ልብሴ ላይ ውሀ የደፋህብኝ ነው እንዴ የመሰለህ?»
ፌሪ የመኝታ ክፍሉን ቁልፍ ይዛ ስትሰድበኝና ስትደበድበኝ ቆየች። ሁሉም ሰለቸኝ።
«ይኼ የተፈቀደልኝ ነው! መብቴን ነው ያደረግኩት! ይቅርታ የጠየቅኩሽ ስለምወድሽ ነው። ስህተት ስለሰራሁ አይደለም!»
«ትወደኝ የለ እንዴ! ድንቄም መውደድ!»
ቁልፉን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችው።
«ይኸው ውጣ! ሸርሙጣህ ጋር ሂድ! Bitch!»
ቁልፉን አንስቼ በሩን ከፈትኩ።
«ንገራት ..... እንደምገላት ንገራት እሺ! ቤቴን በትና እንደማልተዋት ንገራት! Son of a bitch!»

ከቤት እንደወጣሁ መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ኢክራም ጋር ደወልኩ።
«ኢክሩ .... »
«ወዬ ፉዬ እንዴት ሆንክ?»
«ኧረ ስሰደብ እና ስደበደብ ነው ያረፈድኩት!»
«ቤቱን ለቅቃ ሄደች ወይስ እዛው ናት?»
«ኧረ ምን ትሄዳለች .... እዛው ተቀምጣለች። እያለቀሰች ነው።»
«በቃ እኔ ጋር ና ..... ባልየው!» ሳቀች።
«የት ነሽ?»
«ቤት ነኝ እወጣለሁ .... የተለመደው ቦታ ቢሆንስ?»
«ይቻላል። ከሰሚር ጋር እመጣለሁ።»
ሰሚር ጋር ደውዬ አነሳሁትና ወደ ኢክራም ሄድን።
«ባ ሌ!» ኢክሩ በደስታ ተፍነከነከች።
«ሚስትየው!» የደረሰብኝን ድብደባ በኢክሩ እቅፍ አበረድኩ።
«በቃችሁ .... ሆድ አታስብሱኛ!» ሰሚሮ አለያየን። ከከተማችን ታዋቂ ሆቴሎች መካከል ከአንዱ ተሰይመናል።
«ምነው ግን በጠዋቱ አረዳሀት?» ሰሚሬ ይስቃል።
«መርዶ በጠዋቱ ነዋ የሚርረዳው!» ኢክሩ መለሰች።
ኢክሩዬ ነፃነቴ ሆናለች። የምላትን የምትሆን የፍላጎቴ ጥግ! ሳያት እረጋጋለሁ።
«ፉዬ ግን ምን አሰብክ? ዛሬ ማን ጋር ልታድር ነው?» ይስቃል።
«ያው ሁለተኛ ሚስቱ ጋር ነዋ! ሁለት ሳምንት አብረው አደሩ አይደል!»
«አንቺ ደግሞ ለእሷ የዋሸነውን አመንሽው እንዴ? አልተጋባችሁም እኮ ገና!»
«እጠይቅሻለሁ እያልኩ ነበር። ባባ የለም እንዴ? ወደ ቤት ከቸኮልሽ ቆየሳ!»
«ከልብ ካለቀሱ ሲባል አልሰማህም? በእህቶቼ እያሳበብኩ ነው ‘ባክህ!»

ምግቡ ቀርቦልን በልተን እንደጨረስን እቅድ ማውጣት ጀመርን።

«ለጊዜው ነገሩ እስኪለይለት ..... እስክትፈታት እሷ ጋር ሁን! ባየችህ ቁጥር ስለምትበሳጭ ፍቺው ይፈጥናል!» አለ ሰሚር!
«እስኪ እናያለና! ግን ‘ባክህ ይኼኔ እስካሁን ሻንጣዋን ጭና ቤተሰቦቿ ጋር አዳማ ደርሳ ይሆናል።»
ኢክሩ መዳፎቿን እያማታች! «ግልግል ነዋ!» አለች።
ሰሚር በግርምት እያያት «ግን ሴቶች እርስ በርስ ስትጨካከኑ ለከት የላችሁማ!» አለ።
«በምንወደው ቀልድ ስለማናውቅ ነዋ!»
ኢክራም ዛሬ ሳቅ ሳቅ ብሏታል። የለፋችበትን ሰው ..... ፉአዷን የሷ ብቻ የምታደርግበት ቀን ከፊቷ ተደቅኗል። ለከፈለችው የትዕግስት መስዋዕትነት ራሷን እያመሰገነች ይመስላል።

ለጊዜው ፈሪሀ ጋር እንድቆይ ተስማምተን ከሆቴሉ ወጣን። ቢሮ እንግዳዎች እየጠበቁኝ ስለነበር ከኢክሩ ጋር ተሰነባበትን። ሰሚር ጋቢና ተቀምጦ በሀሳብ እንደተዋጥኩ እየነዳሁ ነው። የኢክራም መኪና ከፊታችን ይታየኛል። መገንጠያው ጋር ስንደርስ የኢክራም መኪና ወደቀኝ እኛ ደግሞ ወደ ፊት ሄድን። ከመቅፅበት ከባድ የግጭት ድምፅ ሰማን። ጓ! ጓ! ጓጓ! ጓጓጓ!
19.1K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-04 22:23:57 በሀሳብ እንደተዋጥኩ ኢክሩ ከገንዳው ወጥታ ወደ እኔ መምጣት ጀመረች። የለበሰችውን ሁሉ የምታሳምር አይነት ቆንጆ ነች። ታግላ ታግዬ አሸንፋኛለች። ተቆጣጥራኛለች። እጅ ሰጥቻለሁ። መፈንቅለ ትዳሯ እየተሳካ ይመስላል። ወይኔ ፈሪሀ!

ይቀጥላል!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
15.0K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-04 22:23:57 የልብ ነገር
ክፍል ስምንት
(ፉአድ ሙና)
***

የእኔ ያልነውን
ያፈቀርነውን፣ የህይወት ማገር፣
ተቀየርንበት
እንዴት ይገርማል፣ የልብ ነገር።

ያጣመደንን
የፍቅር አምሳል፣ ቀርፆ አሳምሮ፣
ጥለነው ስንሄድ
ጆሮ ነሳነው፣ ለልቡ ‘ሮሮ።

***
የህይወት ከባድ ድሎት እምነት ነው። ፈጣሪን ማመን ... አለምን ማመን ... ራስን ማመን .... እግራችን የሚያርፍበትን እያንዳንዱን መሬት ማመን .... ከላያችን ያጠለለንን ሰማይ ማመን .... ቤተሰባችንን ማመን .... ፍቅራችንን ማመን ... ማመን ... ማመን! የሰው ልጅ ማመን ባይችል መኖር የሚችል አይመስለኝም። ያብዳል! ለዚህም ይመስለኛል መከዳት ትልቅ ህመም የሚፈጥርበት .... ህይወቱን ኦና የሚያደርግበት! መከዳት ያማል .... ያስቀመጡት ከጠበቁት ቦታ ሲንሸራተት ማየት ልብ ላይ የተሰካ አንዳች ነገር በኃይል ሲነቀል የሚሰማውን አይነት ህመም ያማል። ሰው ደግሞ ይከዳል! መክዳት ተፈጥሮው ነው። የዚህችን አለም እውነተኛ ገፅ የምንመለከተው የተከዳን ቀን ይመስለኛል። መክዳት ደግሞ መጀመሪያ ይከብዳል  .... ከዚያ ይለመዳል .... ሲልም ይወደዳል። ፈጣሪን መክዳት .... ሰውን መክዳት .... ራስን መክዳት!

ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢክራም ጋር የተነካካንበትን ቀን ሳስበው ልቤ ላይ የነበረው ፍርሀት .... ፀፀት .... ቁጭት ያስገርመኛል። በሂደት እንዲህ ሊጠፋ .... እንዲህ ልንላመድ .... ከሚስቴ በላይ ልዋሀዳት .... ይገርማል! መጀመሪያ አካሌ ብቻ ነበር ፈሪሀን የከዳው! አሁን ግን ልቤም እየተከተለው ነው። ልብ ሲከዳ መጥፎ ነው። ትናንትን ያስረሳል። አሁን የፈሪሀ ውበት በኢክራም ተውጦብኛል። በብዙ ነገር ከእሷ እንደምትሻል አሳይታኛለች። ፈሪሀን በከዳሁት ልክ ፈጣሪዬንም የከዳሁ ይመስለኛል። ቀስ እያልኩ የተንሸራተትኩ ... በወንጀሌ የተመፃደቅኩ .... ከክብር ዙፋኔ የወደቅኩ .... ብዙ በጣም ብዙ አይነት መክዳትን የከዳሁ ይመስለኛል። ፈሪሀ ልትመለስ አንድ ወር ብቻ ቀርቷታል። የቤቴ ንግስት .... የምወዳት እና የምትወደኝ ሴት .... የማፈቅራት የከዳኋት ውብ .... የምትናፍቀኝ የማልናፍቃት ፈሪሀ .... ልትመለስ ነው። በየደቂቃው ትደውላለች .... ልብስ ለመግዛት ታስመርጠኛለች .... ስሟን ስልኬ ላይ ባየሁ ቁጥር እበረግጋለሁ። የፍርሀት መበርገግ አይመስለኝም .... የጭንቀት ነው። ሳላስበው ነገሮች ከቁጥጥሬ እንዳይወጡ እፈራለሁ። ስለቤተሰቦቼ .... ስለቤተሰቦቿ እያሰብኩ እጠበባለሁ። ፈሪሀ ላይ ማገጥኩ ብል በምን አይናቸው ያዩኛል? እኔንጃ! ብፀፀት እንኳን ይቅር አይሉኝም። እነሱ ፈጣሪን አይደሉም።

ቁምጣዬን እንደለበስኩ ተጋድሜ የዋና ገንዳው ውስጥ የሚሆነውን ትዕይንት እመለከታለሁ። ኢክሩ ለሙስሊም ሴቶች የተዘጋጀ ሂጃብ እና ሱሪ ያለው የመዋኛ ልብስ ለብሳ ገንዳው ውስጥ ትንሳፈፋለች። ሰሚሬ ከተረኛ «ሚስቱ» ጋር ገንዳው ውስጥ ይሳሳቃሉ። የእርሱ እጅ ላይ ሆና ለመዋኘት ትሞክራለች። አንዳንድ ሰዎችን እውነት ....  ሌሎችን ክህደት ያዛምዳቸዋል። ምንም ከድሮም ብንተዋወቅም የእኔና የሰሚር ግንኙነት ከአህመድ ጋር ካገኘሁት ወዲያ እጅጉን ጨምሯል። የጋራ ወንጀላችን ያዛመደን ይመስለኛል። በዚህ ሰዓት ፈታ ብሎ የሚያፍታታኝ እንጂ እየጨቀጨቀ ጭንቀት የሚጨምርብኝ አይነት ሰው ማግኘት አልፈልግም። ባለኝ ትርፍ ሰዓት ሁሉ አገኘዋለሁ። ኢክራምም ተጫዋችነቱ ደስ ይላታል። ሰሚር ስጨናነቅ ሲያየኝ ከከተማ ካልወጣን ብሎኝ፤ ሀዋሳ ነን። ሀዋሳ ካሉት ውድ ሪዞርቶች በአንዱ!

ሰሚሬ ከውጪ ሆኜ ስብሰለሰል ተመልክቶኝ ይመስለኛል .... ሴቶቹን ትቶ ወደኔ መጣ። ከጎኔ ያለው አልጋ ላይ እየተጋደመ በፎጣ ራሱን ያደራርቃል።

«አለሽ? ወይስ UK ነሽ?»
«UK ነኝ!» ሳቅኩኝ።
ከሰሚር ጋር ለመግባባት ብዙ ማውራት አያስፈልግም። የሚፈጥራቸው አጫጭር ኮዶች አሉ። ልፋት ያቀላሉ።

«ስማማ ሰሚሬ ፈሪሀ እኮ አንድ ወር ብቻ ነው የቀራት ለመምጣት!»
«እና ቦታ መያዝ ያለበት ነገር አለ?»
«አዎ!»
«ሰራተኛችንን ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል። ከፈሪሀ ጋር ይቀራረባሉ። ከመጣች ምንም ብትጠይቃት አትደብቃትም። የኢክራምን ጉዳይ ደግሞ ነገሩ ሲሆን በአይኗ አትይ እንጂ በደንብ ታውቃለች። ባባራት ለመናገር ጥሩ ሰበብ ይሆንላታል ብዬ ፈራሁ!»
ሰሚሬ እግሩን ወደ መሬት አውርዶ ወደ እኔ ዞሮ ተቀመጠ።
«ፉዬ ... »
አይኔን ከፍ አደረግኩ!
«ልብህ ማንን መርጧል?»
«ማለት?»
«የእውነት ፈሪሀን ትፈልጋታለህ ወይስ ክህደት መሆኑ ነው የደበረህ?»
«እኔንጃ .... » ጭንቅ አለኝ።
«እሺ አሁን ፈሪሀ ሚስትህ አይደለችም ብለን እናስብ! ዛሬ እያየሀቸው ቢሆን .... ማንን ትመርጣለህ?»
«ኢክራምን ይመስለኛል!»
«ለምን?»
«ሴት ናት! የምር ሚስት ናት! ዓለሟ በእኔ ዙሪያ ነው። ሌላ አለም አትፈልግም! እንደዛ አይነት ሴት እወዳለሁ። የምትዋረድልኝ .... ወደሷ የምቀርባት ሳትሆን ወደ እኔ የምትቀርብልኝ ሴት!»
«በቃ በቃ ..... ያለቀለት ነው ይኼማ!»
«ስትል?»
«በቃ ፈሪሀን ፍታት እና ኢክራምን አግባ!»
«እንዲህ ቀላል ነው?»
«ኪሳራው ፈሪሀን ማጣት ነው። ፈሪሀን ደግሞ አንተ ቀድመህ ለማጣት ወስነሀል። ስለዚህ ኪሳራ የለውም። ልጅም የለህም፤ ስለዚህ አያስጨንቅም!»
«ሰው መሆን የምትችል አይመስለኝም ፌሪ!»
«አንተ አትፈታትም እኮ በራሷ ፍታኝ እንድትል እናደርጋለን። ስለዚህ ጥፋቱ የሷ ይሆናል።»
«ይኼ ደግሞ ምን የሚሉት አስማት ነው?»
«ፈሪሀ ዘመነኛ ነን እንደሚሉት አይነት ናት አይደል? ዲነኛ አይደለችማ?»
«አዎ .... ማን ገደለውና ኢማኔን?»
«አየህ እንደዛ ከሆነ ሁለተኛ ሚስት አግብቻለሁ ትላታለህ። ለኢክራም እንነግራታለን። ኢክሩ የአራዳ ልጅ ናት ትተውናለች። ያኔ ፈሪሀ ፍታኝ ትልሀለች። አለቀ! ከኢክራም ጋር ተጋብተህ ትኖራለህ።»
«ምን አይነት ጨካኝ ነህ ግን ሰሚሮ?»
«ምናባህ?»
«ፌሪ እኮ ስንት አመት አቅፌያት የተኛኋት ሚስቴ ናት!»
«እና ማንአባህ ማግጥባት አለህ? ሰሚር ማግጥባት አለህ?»
«ብቻዬን ይኼ ሁሉ አመት?»
«ማግጠሀል! አለቀ።»
«ወይም ሌላ ምርጫ ልስጥህ?»
«ምን?»
«የፈጅር ሚስት ታውቃለህ?»
«አላውቅም!»
«ኢክሩን የሆነ ቤት ተከራይተህ ታስቀምጣታለህ! ከዛ ፈጅር መስጂድ ብለህ ትወጣለህ! ሁሌ ደሞ ቂርዓት አለ ከፈጅር በኋላ!»
«የምን ቂርዓት?»
«ኢክራም ናት ኡስታዛዋ! ሁሌ ፈጅር ሰግደህ እሷ ጋር ሄደህ ታረፋፍድና .... ስራ በዛው ትሄዳለህ።»
«ሳላገባት ኢክራምን?»
«በድብቅ አይድሩልህማ!»
«አዎ እሱማ! ግን የማላገባት ከሆነማ ምን ድራማ አሰራኝ? እኔ ነፃ የሆነ .... የማልማግጥበት ህይወት ነው የፈለግኩት! በቃ መስተካከል እንደድሮው መሆን እፈልጋለሁ።»
«ፈሪሀን ፍታት እና ኢክራምን አግባ አለቀ። ፈሪሀን ካገባህ ኢክራም ጋር መሄድህ አይቀርም!»
«እስኪ አስብበታለሁ።»
«ደሞ ቆፍጠን በል እንጂ! የውሳኔ ሰው ሁን የፈለገው ይምጣ!»

አንዳንዴ በገዛ እጃችን ወደ ህይወታችን የምናመጣቸው ወንጀሎች በፈለግነው ሰዓት የሚሰናበቱን አይደሉም። ወደ ወንጀል እንደመግባት መውጣቱ አይቀልልም። ትብታቡን በጣጥሶ ለማለፍ ጥንካሬ ይፈልጋል። አሁን ወደ ክብሬ ብመለስ ደስ ይለኛል። ወደ ዙፋኔ! ቁልቁል ወደ ተምዘገዘግኩበት ከፍታ! ይገራልኝ ዘንድ ምኞቴ ነው።
15.8K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-02 23:16:54 ሰላቱ እንደተጠናቀቀ ወደምንወደው ካፌ ጎራ ብለን መጨዋወት ጀመርን።
«ስማማ ሰሚሬ .... ግን ጀመዓ ሰላትንና ሴትን እኩል ማዘውተር እንዴት ቻልክ? እኔ እኮ ሚስቴ ብቻ ሆና እንኳን አልቻልኩም።»
«አህሜ ፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄ አትጠይቀኝ ባክህ!»
«ምነው?»
«ነገ ደግሞ ይነዝንዘኝ እንዴ እሱን ይዞ!»
«ሴት እንደምታጫውት ኢማሙም እኮ ያውቃሉ!» አለ አህሜ እየሳቀ።
«በነገራችን ላይ የኢማሙን ልጅ አጫውቼያት ስመለስ በእሳቸው ሰግጃለሁ። Family reunion ነው የሆነብኝ!»
ከሚያወራው ውስጥ ግማሹ ሳክስ እንደሆነ ስለምናውቅ እንደቀልድ ልናልፈው ነበር።
«በነገራችን ላይ የኢማሙ ልጅን ምናምን ያልኳችሁ የምሬን ነው። እኔ የእሳቸው ልጅ መሆኗን ያወቅኩት በኋላ ነው።»
«ወሬ ቀይር በአላህ! ደሞ ኮንፊሰደንስህ እኮ ከወንጀል ያዳንካት ነው የሚመስለው!» አህሜ አቋረጠው።
«እዚ ሼባ ፊት ይብራብን እያልኩህ ..... አየሀ!»
«እሺ ስለ ሰላቱ ንገረኝ እንዴት ነው አብረህ የምታስኬደው?»
«የምቀጥርበትን ሰዓት ቀድሜ ነው የማመቻቸው .... ነገሩ ካለቀ በኋላ ይቀፉሀል እኮ ለተወሰነ ቀን .... በጣም ካላፈቀርካት እንደዛ ነው።»
«ስለዚህ?»
«ወዲያው ትቻቸው ወደ መስጂድ ነው የምመጣው!  ይደብሩኛል። ከዛ ተውበት አደርጋለሁ! ከዛ ደግሞ ከትንሽ ቀን በኋላ ነገሩ ሊደገም ይችላል።»
«ምን ታደርጋላችሁ አብራችሁ? ስልህ ስቴፑን ፈልጌ ነው።»
«ተው አህሜ ይጀንብብናል።» ሳቁን ለቀቀው።
«እኔ መስጂድ መምጣት ከብዶኛል። እና ያንተን ጥበብ እፈልገዋለሁ።»
«በቃ ቤትህ መጥቶ ያስተምርህ! አሁን ላወራችሁት ራሱ ኡዱ ማድረጌ ነው!» አህሜ አቋረጠን።
«አያሳስብም ደሞ ለፉዬ! ከዚህ በኋላ በወንጀል ጉዳዮች የሰላተል ጀመዓ አማካሪው ነኝ!» ሳቁን ለቀቀው።
.
ይቀጥላል ....
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
15.5K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-02 23:16:51 የልብ ነገር
ክፍል ሰባት
(ፉአድ ሙና)
***

አመመኝ አልልም
አልተነካም ጅስሜ፣
ጤነኛ አልምሰልሽ
ብታይ ስሄድ ቆሜ!

የሩሄን እህህታ
ጆሮ መቸ ሰምታ፣
ቧጥጬው ልሞት ነው
ልቤን ጠዋት ማታ!

***
አህመድ ሰሞኑን ቋሚ ፕሮጀክቱ አድርጎኛል። አላውቅም ምናልባት በሹራ ተመድቦብኝም ሊሆን ይችላል። ድንቄም ሹራ! ብሞት እንኳን የማያውቅ ጀመዓ! ከሁሉም የገረመኝ ግን ይህን ያህል ጊዜ ከመስጂድ ስርቅ ምን ሆኖ ይሆን ብሎ የጠየቀኝና ያስፈለገኝ ሰው አለመኖሩ ነው። አላህ ይስጣቸውና የተብሊግ ጀመዓዎች ብቻ ቤት የምሆንባቸውን ጊዜያት እየጠበቁ ሊዘይሩኝ ይመጣሉ። መጀመሪያ ሰሞን ሀያዕ እያደረግኩ አብሬያቸው ወደ መስጂድ እሄድ ነበር። ትንሽ ሲቆይ ግን አንኳኩተው «ወንዶች አሉ?» ሲሉ ዝም ማለት ጀመርን። ሰራተኛዋ ዝም ካልኩ መውጣት እንዳልፈለግኩ ስለምትረዳ፤ የለም ብላ ታሰናብታቸዋለች። ፌሪ በነበረችባቸው ጊዜያት ቀድማኝ «የሉም በያቸው!» ትላለች። በዕረፍት ቀናችን ትቻት ከቤት እንድወጣ አትፈልግም።

ባላወራውም ሁሌ በልቤ የታዘብኩት ግን ከትልቁ መስጂድ ሰዎች ውስጥ ከአህመድ በቀር የዘየረኝ አለመኖሩ ነው። አህመድም የግል ጓደኛዬ ስለሆነ እንጂ ባይሆን የሚዘይረኝ አይመስለኝም። ትልቁ መስጂድ ላይ በጣም ከሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ግንባር ቀደም ነበርኩ። ከመስጂድ ስጠፋ ግን የፈለገኝ አልነበረም። እንደውም በተገላቢጦሹ የትንሹ መስጂድ ተብሊግ ጀመዓ የለም እየተባሉና በር እየተዘጋባቸው እንኳን እኔን ከመፈለግ አልቦዘኑም። ትልቁ መስጂድ ሰለፍይ ነን የሚሉ ጅሎች የሞሉት ነው። ጅሎች ያልኳቸው ስላልፈለጉኝ ነው። ምንም አይነት ሰዋዊ ግንኙነት የሌለው ማሽን የሚመስል ስብስብ ነው። ሰላት መስገድ እና ቂርዓት መቀመጥ እንጂ ከዚህ የዘለለ ሰዋዊ መስተጋብር የለውም። አሊሞቻቸውን እንኳን የሚያውቋቸው ሲሞቱ ነው። ሰላት እንደተሰገደ ሰው ትከሻ ላይ እየዘለሉ መሮጥ የሚወዱ ሰርከሰኞች የሞሉበት ነው። አሁን ወደ ትልቁ መስጂድ ብሄድ «የት ጠፍተህ ነበር?» ብሎ የሚያዋክበኝ ብዛቱ! ልሙት ልኑር ሳያጣሩ ስመለስ ማዋከብ ምን የሚሉት ነው? ከትልቁ መስጂድ ስልክ ከተደወለ ቃል የገባሁት ብር አለ ማለት ነው። ገንዘብ ሲፈልጉ ብቻ ይፈልጉኛል። አሁን የዛን መስጂድ አዛን መስማት ራሱ ያስጠላኛል። የፊርቃ ሰው አይደለሁም እንጂ ብሆን ኖሮ በእነሱ እልህ አዲስ ፊርቃ እመሰርት ነበር። አብዛኛውን ሰው ፊርቃ የሚያስቀይረው እልህ ይመስለኛል።

እሁድ ከሰዓት ነው። አህመዴ የአስር ሰላትን ትልቁ መስጂድ እንድንሰግድ ቃል አስገብቶኛል። ቃሌን ለመጠበቅ ሰዓቴን በተደጋጋሚ ተመለከትኩት።
«ምነው? ደረሰ እንዴ?» አለች ደረቴ ላይ እንደተጋደመች።
ኢክሩ ቤቴ ቤቷ ከሆነ ሰንብቷል።
«አይ አንድ ሰዓት ይቀረዋል ነገር መሰለኝ።»
«ሻወር እስክንወስድ ምናምን ጊዜ ስለምንፈጅ አሁን እንነሳ!» ከደረቴ ላይ ተነስታ ፀጉሯን ማስተካከል ጀመረች።
ስልኬ ጠራ። አህሜ መስሎኝ ነበር። ስመለከተው ፌሪ ናት።
«ማነው?» አለች ኢክሩ እየተጠጋችኝ!
«ፌሪ ናት .... እንደተለመደው እሺ!»
«አያሳስብም!»
ከኢክራም ጋር በጣም ከመላመዳችን የተነሳ ፌሪ ስትደውል ሚናችንን በአግባቡ እንወጣለን። ፌሪ አሳየኝ የምትለው ነገር ካለ ኢክሩ ኮተቷ ካሜራ ውስጥ እንዳይገባ በማድረግ ታግዘኛለች። እሷም ከካሜራው ጀርባ ሆና ትከተለኛለች።
ስልኩን አንስቼ ከፌሪ ጋር አወራን። ለመመለስ ሁለት ወራት ብቻ እንደቀሯት አበሰረችኝ። ብስራት ነው ግን? ምንም ደስታ አልሰማ አለኝ። እንደውም ጭንቀት ጭንቀት አለኝ። በራቀ በራቀ የሚል ስሜት ይወረኛል።
ስልኩን አናግሬ እንደጨረስኩ አንድ ላይ ወደ ሻወር ገባን። ምን ልትሰሩ የሚል የዋህ ካለ ልንታጠብ በሉልኝ። «ታጥበን» እንደጨረስን የምለብሰውን ልብስ ኢክሩ መምረጥ ጀመረች።
«ዛሬ ሼኪ ነው ‘ማስመስልህ!»
ጀለቢያዎቼን እያነሳች ትጥላለች። አንድ ወደ ጥቁረት የሚያደላ ጀለቢያ አነሳችና ወደኔ ይዛው መጣች። በቅርቡ ለኢድ የገዛሁት ነበር።
«ይኼ አብሮ ይሄዳል። ጁሙዓ ቢሆን ነጭ እናደርገው ነበር። እሁድ ስለሆነ ....  ስለምትንቀሳቀሱም ይሄ የበለጠ አብሮ ይሄዳል።»
«ጀለቢያ ይሻላል አልሽ?»
«አዎ ባክህ! እና ጥምጣም ደግሞ .... »
«ኧረ በአላህ በቃ እንዴ! መስጂድ ከሄድኩ ስንት ጊዜዬ ነው .... አይን ውስጥ አታስገቢኝ!»
«ማን ምን ያመጣል? ንፁህ ነው እንዴ የሚመስሉህ?»
«ይኼ ኮንፊደንስሽ እኮ ነው ደስ የሚለኝ!» ፈገግ አልኩላት።
የግቢያችን በር ሲከፈት ሰማንና፤ ተከታትለን ወደ መስታወቱ ሄድን። የአህመድ መኪና እየገባች ነው። ሳቅኩኝ።
«ይኼ ልጅ የምቀጣው መስሎት ከቤት ሊያግተኝ መጣ አይደል?»
«ጀለስህ ነው?»
«አዎ! ልበሺ ወደ ላይ ከመጣ ዘመዴ ናት እለዋለሁ።»
«እሺ አባያ አለኝ መኪናዬ ውስጥ! ሰራተኛዋ ይዛልኝ ትምጣ አንተ ታች አቆየው!»
ቀድሜ ወደታች ወረድኩ። ሰራተኛዋ አባያውን ወሰደችላት።

«አንተ! ይህን ያህል አታምነኝም?»
«እሱ እንኳን አላምንህም .... ግን በዚሁ ሰሚር አንሳኝ ብሎኝ እሱን አንስቼ መምጣቴ ነው።»
«እንዴ ሰሚሬ! እሱ ልጅ አለ በአላህ?»
«መኪና ውስጥ ተቀምጧል። ከገባ እንዳንቆይ ብዬ ተቀመጥ አልኩት።»
ኢክራም አባያዋን ለብሳ መጣች። አምሮባታል። የቤት እመቤት መስላለች።
«አሰላሙአለይኩም!» ፈገግ ብላ ተቀላቀለችን።
ለምን ወደ ታች እንደወረደች ግራ ተጋብቻለሁ። እንድትሰተር የፈለግኩት ወደ ላይ ካልወጣሁ ብሎ ካስቸገረኝ ብዬ ነበር።
«ወአለይኩሙሰላም!» አህሜ መለሰ። መጥታ ከአጠገቤ ተቀመጠች።
አህሜ በመገረም ይመለከተኛል።
በልቤ ምናባቷ ብላ እንደምትተዋወቅ እየሰጋሁ «ተዋወቁ ....» አልኩኝ።
«አህመድ እባላለሁ የባልሽ ጓደኛ ነኝ ....» ሳቀ። እኛም ሳቅን። መንገድ እየመራት እንደሆነ ገብቶኛል። ልጅት ግን የዋዛ አልነበረችም።
«ኢክራም እባላለሁ። ባሌ እንኳን አይደለም። ቤተሰብ ነን።»
ሌላ ምርመራ እንዳይጀምር ስለሰጋሁ «እንውጣ አይደል?» አልኩ እየተነሳሁ!
«አዎ አዎ! ሰሚሬም ይደብረዋል።»
ኢክራሜን ተሰናብተን ወደ መኪናው ሄድን።

ሰሚር ማለት የጀመዓችን ቀልደኛ እና ተጫዋች ነው። ከተጫዋችነቱ በተጨማሪ ደግሞ በሴት አጫዋችነቱ የ ISO የጥራት ማረጋገጫ የተሰጠው ወዳጃችን ነው። እሱ ካለ ስለሴት ማውራት ግዴታ ነው። ከግቢው ወጥተን ወደ መስጂድ መሄድ ጀመርን። አህመድ አላስቻለውም።
«ስማማ ፉአዴ!»
«እሺ!»
«ዝምድናችሁ የምንድነው ከልጅቷ ጋር?»
«ከኢክራም ጋር?»
«አዎ! ማለቴ ጋብቻ የሚከለክል ነው?»
«አይደለም!»
«ስትር ማለቷ እንዴት ደስ ይላል! ኧረ አትፍዘዝ!»
«ምን ላድርጋት?»
«አግባታ!»
«አይ አህሜ! ፈሪሀን የምትበቀልበት አጋጣሚ አገኘሀ!» ሳቅን።
«ባክህ አግባባት ስርዓት ትይዛለች ያቺም!»
«ቀልደኛ!»
«ካልሆነ ወደኔ ላከው .... አስተናግድልሀለሁ!» ሰሚሬ ተቀላቀለን።

መስጂድ ስንደርስ ጠያቂ እንደ ንብ መንጋ ሰፈረብኝ። የት ነበርክ? ከሀገር ወጥተህ ነው? ሰፈር ቀየርክ እንዴ? ምናምን! በልቤ «መች ፈለጋችሁኝ?» እያልኩ እገረማለሁ። የመጀመሪያ ጀመዓ አምልጦን ስለነበር ሁለተኛ ጀመዓ ቆምን። እኔን እንዳሰግድ ጋበዙኝ። እምቢ አልኩ።
«አንተ እያለህማ እኛ አንገባም!»
በግድ ገባሁ። ከደቂቃዎች በፊት ከኢክራም ጋር የነበርኩበት ሁኔታ እና አሁን የቆምኩበት ቦታ ተምታቱብኝ። ቆዳችን አይጮህም። እጆቻችን አያወሩም። ሀፍረታችን አይናገርም። ልብስ ብዙ ነገር ይሸፍናል! እጅግ ብዙ! ለዚህ ፀጋው ከማመስገን ውጪ ምን እላለሁ? ምንም!
19.0K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-19 22:15:20 #የልብ_ነገር
#ክፍል_አንድ
(ፉአድ ሙና)
***

እንደ ፀሀይ ግባት ...
ውበት ማከማቻ፣
እንባ እያፈሰሱ፣ የሚያምሩ አይኖቿ፣

አመት እንዳልበላ ...
እንደተራበ ሰው፣
እየሮጠች መጣች፣ ከንፈሬን ልትጎርሰው!

***

ልክ ከአይኗ እንደገባሁ ሻንጣዋን የመግፋት አቅም አጣች። አይኔ በእንባ ተሸፍኗል። በእንባዬ ውስጥ ፍቅሬ ስትንደረደር ይታየኛል። በእጆቼ የያዝኩትን አበባ አንጠልጥዬ እኔም ወደሷ መሮጤን ተያያዝኩት። ወንድ አልነበርኩ እንዴ? ሊያውም ቆፍጣናው ፉአድ! እንባ የአይኖቹን አጥር ያለፈቃዱ የማይነቀንቁበት ደረቅ! አልቻልኩም .... ራሴን መቆጣጠር ከበደኝ።

አጠገቧ ደረስኩ ... ከሽሽጌ ገባች። ናፍቄያታለሁ። የሸሚዜን ቁልፎች ፈትታ ገላዬን በእጆቿ ለመንካት ትሞክራለች። ትኩስ ከንፈሮቿ በትኩስ እንባዋ ተለውሰው .... አቻ ከንፈሬን ይመጠምጣሉ።

«ይኸው ሻንጣሽ የኔ እመቤት!» የአየር መንገዱ ሰራተኛ ቱታውን እንደለበሰ ሻንጣዋን ገፍቶ እኛ  ጋር መድረሱ ነበር። መሳሳማችንን ገትተን ... ኪሴን ዳብሼ፣ አመሰገንነውና ሻንጣዎቿን እየገፋሁ ወደ መኪናችን መሄድ ጀመርን። በየመሀሉ እየቆምን እንተቃቀፋለን።

ቦታው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ናፋቂ አይኖች ከናፍቆታቸው ጋር የሚገናኙበት ... አፍቃሪ ልቦች ከውዳቸው ጋር የሚለያዩበት፤ ትዕይንተ ብዙ ስፍራ! ሻንጣዎቿን መኪናው ላይ ጭነን መኪና ውስጥ እንደገባን፤ እንደ አዲስ መላቀስ ጀመርን።

የመታወቂያ ስሟ ፈሪሀ ሁሴን፤ በእኔ አንደበት የለመደችው ደግሞ ፌሪ፣ የኔዋ፣ ፌሪ ፈሪ! የዛሬ አራት አመት ነበር ዛሬ የተገናኘንበት ቦታ ቆሜ ሳላምንበት የሸኘኋት! ለሁለት ዓመት የሄደችበት የትምህርት ጉዞ ተለጥጦ አራት አመት ተቀጣሁ!

«አንተ Airport ስንሳሳም ብዙ ሰው አየን እንዴ?»
«የለም ሁሉም አይነስውር ነበሩ።»
«I was out of my mind! ካንተ ውጪ ማንም አይታየኝም ነበር።»
«It's okay የኔ አበባ! ግን UK እኮ ምግብ ያለ ነበር የሚመስለኝ!»
«ምነው? ከሳሁ እንዴ?»
«ከንፈሬን እኮ በላሽኝ!»
ሳቀች። ሳቋ ያምራል! ጥርሶቿ ሲከፈቱ በቀጥታ ልብን ይይዛሉ! በጥርሶቿና በልብ መካከል ያለው ግንኙነት ቢጠና ደስ ይለኛል። በሀገረ እንግሊዝ የተማረችበት ዩኒቨርሲቲ ይህን አለማጥናቱ ይገርመኛል።

ቤት እንደደረስን መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። ሰራተኛዋ ከመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ የደረደረቻቸውን ምግቦች ቆማ ታስተካክላለች።
«Fami ሻወር እየገባሁ ነው .... መጣሁልህ!»
«እዛው እደሪ አሉሽ ደግሞ! እነ Mom ይመጣሉ!»
«Yours? Or mine?»
«ያንቺማ ለቅሶ አለ መሰለኝ እዛ አዳማ! አልተነሱም። ተረጋግታችሁ ነገ ኑ ብያቸዋለሁ! The road is not safe!»
«Who the hell died on my arrival day? He should be jealous!» ትስቃለች።
«አንቺ ክፉ! አርፈሽ ታጠቢ እስኪ!»
«ለምን አትገባም ከእኔ ጋር? አብረን እንታጠብ ... Join me!»
«ወዳንቺ ስመጣ ነው የታጠብኩት!»
«This one is special ሀቢቢ!» ሳቋ ሲስረቀረቅ ይሰማኛል።
የሌላውን ጊዜ ፉአድ ብሆን ኖሮ ሳትጋብዘኝ እየተንደረደርኩ እንደምገባ አውቀዋለሁ። ዛሬ ግን ፈራሁ! ሙሉ ራቁቴን ፊቷ መቆም አስፈራኝ። ገላዬ አፍ አውጥቶ የሚናገርብኝ ይመስለኛል። ጨንቆኛል።

የኔ ልዕልት ... ታጥባ ጨረሰች። መኝታ ክፍል ልብሷን እየቀየረች «ሀቢቢ አንዴ ና እስኪ!» አለች።
ወደ መኝታ ክፍል ስገባ አይኔን አጥበረበረኝ። ሙሉ ብርሀን ከፊቴ ቆሟል። የማያንፀባርቅ የሰውነቷ ክፍል የለም። ፈገግ ብላ አየችኝ። የፈገግታዋን ትርጉም እኔም እሷም እናውቀዋለን።

«ድጋሚ ልትታጠቢ ነው?» ሳቄ መጣ!
«ውሀ አለ አይደል! ለምን ሺህ ጊዜ አልታጠብም!»
የፈለገችውን ብሆንላት ደስ ይለኝ ነበር። ግን ደግሞ እፈራለሁ። ገላዬን አላምነውም። ከቂያማ ቀድሞ ለማውራት የሚሽቀዳደም፤ ጉዴን የሚናገር እየመሰለኝ ነው።
«የኔ ውድ ... አራት አመት ነው የናፈቅኩሽ! ናፍቆቴን በዚህ መልኩ አይደለም መወጣት የምፈልገው! እማዬ እና አባ እየመጡ ነው። አንደኛውን ስንረጋጋ ይሻላል እሺ!»
የታችኛውን ከንፈሯን ወደፊት ለጠጠችው። አቅፌ አባበልኳትና ልብሷን መልበስ ጀመረች።

የመመለሻ ትኬቷ ከተቆረጠ ጀምሮ ውስጤ ሰላም አልነበረውም። ለእሷ ያለኝ ፍቅር ጥልቅ ነው። ከብዙ ማሰላሰል በኋላ ልጋፈጠው ወሰንኩ። ልቤ እንደማትጨክንብኝ ‘ምሎልኛል። ቢሆንም መልካም ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን መላ ቀየስኩ!

የናፈቃትን የሀገሯን ምግብ በልታ ... የናፈቋትን አግኝታ ... ያለፏትን ሀዘንና ደስታ ጠይቃ ሁለት ሳምንታት እንዳለፉ ራሴን ነፃ ለማውጣት ወሰንኩ።

«ፌሪዬ»
«ፋሚዬ»
«እወድሻለሁ»
«እኔ ደግሞ እጥፉን!»
«ዛሬ የሆነ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለሁ!»
«ምንድነው?»
«ይቅር ልትይኝ ....   ቃል ግቢልኝ!»
«ምንድነው?»
«ቃል ግቢልኝ በአላህ!»
«እሺ ቃል እገባለሁ!»
«ፌሪዬ ... »
«ፋሚዬ ...»
«ሁለተኛ ሚስት አግብቼያለሁ ... »
«ምን?» ፊቷ ፍም መሰለ።

ይቀጥላል ...
.
ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
12.8K views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-13 20:15:09 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ሠላሳ_ስድስትት {❸❻}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

(የመጨረሻው ክፍል)


...ምን...ሲጀመር ማነሽ አንቺ ታቂኛለሽ

<የኔ ማንነት ምን ይጠቅምሀል>
<መጣልኝ ድምፅሽ ሀናን ነሻ>
<አዎ ነኝ ስልኬን ቀይሬ ነው>
<እና ለምን ደወልሽ አረሳሽኝም እንዴ>
<ኢብሮ አሁን ብቻ ስማኝ በአላህ አምስት ደቂቃ ልለምንህ>
<አውቃለሁ በድዬሻለሁ በቃ ይቅር በይኝ ስልኩን ልዘጋው ነው>
<እሺ ይቅር እንድልህ አምስት ደቂቃ ስማኝ>
<እሺ ግን አዲሱን ስልኬን ከየት አገኘሽው>
<መሬት ላይ ወድቆ ልበልህ>
<ኡፍ የሚቀለድበትን ሰአትም  አታውቂም በይ አሁን ቀጥይ>
<ኢብሮ ከጠፋህ አራት ወር ሞላህ እናትህ እና አባትህ እህት ወንድሞችህ እኔን ጨምሮ ብቻ ብዙ ሰው ስላንተ ተጨንቋል  ኢብሮ አንተ ከጠፋህ በኋላ ሊናም አብራህ ስለጠፋች የአንተ ቤተሰቦችና የሷ ቤተሰቦች ተግባብተዋል ብንፈልጋችሁም አጣናችሁ   በድንገት ሊና መጣች ሊና መምጣቷን ስንሰማ ቶሎ እሷን ለማግኘት ሄድን አሲ እናትህ ኦያለቀሰች ልጇ ያለበትን ቦታ ስትጠይቃት ደብረ ዘይት እንደሆንክና ቦታውንም ጨምራ ነገረችን ወደዛ ስንመጣ አከራይህ  ጠዋት እንደለቀቅክ ነገረችን ስንደውል ስልክህ አይሰራም ኢብሮ ከዛም ሊና ልታገባ ነው የሚባል ወሬ ስሰማ ላረጋግጥ ሄድኩ ምን ብዬ እንደምጠይቃት ባላውቅም   ዝም ብዬ ወደ ቤቷ ስሄድ በር ላይ የሆነ ወጣት ልጅ ሲወጣ አየሁት ሰላም ካልኩት በኋላ ሊና  ልታገባ ነው ወይ ብዬ ስጠይቀው  ፈገግ እያለ  አዎ ኡመር እባላለሁ   እኔ ነኝ የማገባት አንቺ ምኗ ነሽ ሲለኝ ጓደኛዋ ብዬው ተመለስኩ ኢብሮ ከነገ ወዲያ እሁድ ሊና ታገባለች ስለዚህ ተስፋ ቁረጥ ሀቢቢ   ወደኔ ና ሀቢቢ አሁንም እኮ እወድሀለሁ>

<ሀናን  አንቺ እኛን ለማለያየት የፈጠርሽው ነገር ነው ሊና  ሁሌም የኔ ናት የኔ ፍቅር ትመጣልኛለች እማ እኮ በኔ የሚጨክን አንጀት የላትም  ትመጣለች  ከኔ ውጪ የማንም አትሆንም ደግመሽ እንዳትደውይ>   ስልኩን ጆሮዋ ላይ      ጠረቀመው  አላመንም እኔ አላምንም ሊና ጥላኝ አትሄድም   እሷ የኔ ብቻ ናት መንገድ ላይ እየለፈለፈ ይሄዳል

ሊና ለኢብራሂም ደውላ በሷ ተስፋ እንዲቆርጥ ወሰነች ቀኑን ሙሉ ስታለቅስ ስለዋለች  አይኗን አሟታል የምታፈቅረውን ኢብሮን  ማጣት ለሷም ቢሆን ከባድ ነው  ለቀናት የዘጋችውን ስልኳን ከፍታ ለኢብራሂም መደወል ጀመረች ኢብሮ ሀናን ደግማ የደወለች መስሎት ሊዘጋባት ነው ሲያየው ሊና ናት ቶሎ አንስቶ ወደ ጆሮው አስጠግቶ
 
<እማ ፍቅሬ ሀያቲ ጠፋሽብኝ እኮ እናቴ ናፈቅሽኝ እማ ሊኑዬ>

ድምፁን ስትሰማ አልቻለችም

የኔ ፍቅር አፈቅርሀለሁ እሺ  እያለቀሰች ነው ምታወራው

<እናቴ እኔም እኮ አፈቅርሻለሁ ለምን ታለቅሻለሽ>

የኔ ፍቅር  እንደከሀዲ አሰብከኛ

<የምን ከሀዲ እማ ፍቅሬ መቼ ነው የምትመጪልኝ ፍቅሬ ናፈቅሽኝ ልሞትብሽ እኮ ነው  >

አትጠብቀኝ  በጣም ባፈቅርህም ሌላ ሰው ለማግባት ተገድጃለሁ እሁድ ላገባ ነው

ለቅሶዋ ጨመረ

ከሀናን የሰማው ነገር እውን መሆኑ ገባው እምባው እንደጉድ መፍሰስ ጀመረ ጉልበቱ ተብረከረከ ባለበት ቁጭ አለ

<ሊኑ እኔን ለማን ጥለሽ እናቴ ላንቺ ስል እኮ ከሁሉም ውጭ ሆኛለሁ ፍቅር ስለማውቅ ነው አታረጊውም ይልቅ ቶሎ ነይልኝ ያላንቹ አቅቶኛል

አልችልም ኢብሮዬ ሁሌም አፈቅርሀለሁ ደህና ሁንልኝ

ስልኩን ዘግታ እሪ አለች

ኢብራሂም ራሱን አያቅም ዝም  ብሎ ይሄዳል ወዴት አንደሆነ ግን ለራሱም አላወቀውም


         ከሁለት ቀን በኋላ

የሰርጉ ቀን ደረሰ የኡመር  የደስታ ቀን ሊና ስታለቅስ በአይኗ እምባ  እየጎረፈ እእቅልፍ በአይኗሳይዞር አደረች  ጠዋት ራሷን አሳምናለች  ሰአቱ ሄዷል ሁሉም ተዘገጃጅቷል ኒካሁ ታስሯል ደስተኛ እንደሆነች እያስመሰለች ነው በትልቅ ሰርግ ተሞሸረች ቀለበት ከጣቷ አጠለቀላት እሷም አጠለበችለት  ለብዙ ሰአት አቀፋት ነሺዳው ከዘፈን ጋር ተደበላለቀ የኡመር ቤተሰቧች የሊና ቤተሰቦች ዘመድ አዝማድ ጎረቤት ተሰብስቧል  አሁን  ኡመር ሊናን ይዞበት የሚሄድበት ሰአት ደርሷል

ለሊቱን መጓዝ የጀመረው ኢብሮ አዲስ አበባ ገብቷል እነ ሊና ቤት ጋር ደረሰ የተጣለውን ትልቅ ድንኳን አየ ሀቅ ነው ማለት ነው አስችሏት አገባች  የፖል እንጨት ተደግፎ መመልከት ጀመረ ከቆይታ በኋላ ነሺዳው ቀለጠ ኡመር እጇን ይዟት መኪና ውስጥ ስትገባ አያት እየሳቀች ስለነበረ ፍፁም ደስተኛ ናት ብሎ አሰበ ሲጋራውን ወደ አፉ እየማገ  ሄደ  ዳግመኛ ላይመለስ ወደማያቀው ቦታ ጉዞ ጀመረ...
.
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
  ተ◈ፈ◈ፀ◈መ
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
14.9K viewsꫝꪖꪑꪊᦔ 亗, 17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-31 20:16:36 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
 #ክፍል_ሀያ_ስድስት {➋➏}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...ስልኩን ወደ ልቧ አስጠጋችው   እንጥፋ ነው ያለው ወይስ ተሳስቼ ይሆን   እንዴ የምን መጥፋት ነው ያመዋል ግን እኮ እውነቱን ነው አባዬ አንድ ነገር ይሆናል ካለ ይሆናል ነው ቆይ ኡመርን ላገባ ነው በርግጥ ኡመር ቆንጆ ነው ደስ የሚል አቋም ውብ ፈገግታ አለው የትኛዋም ሴት ለትዳር  የምትመኘው አይነት ወንድ ነው አውቃለሁ ግን እኮ   እኔ አላፈቅረውም የማፈቅረው ኢብሮን ነው   እኔ አልጠፋም  ብለው እኮ እሱም የግዴታ ሀናንን ያገባል  አይ ምን እያልኩ    ነው ቆይ አላህ የጀነት ቁልፍን በእናት እግር ስር አድርጓት ሳለ እናቴን  በስተርጅና ጊዜዋ እኔ ጠፍቼ ላስለቅሳት ነው  ግን እኮ ይሄ  ለፍቅር የሚከፈል ትንሽ ነገር ነው ኢብሮዬ ባይወደኝ ኖሮ እኮ ሀብታሟን ሀናንን ያገባ ነበር   ምንድን ነው የማስበው ቆይ ትምህርቴንስ ልተወው  ነው እሱስ ይሁን ግን እኮ ሀራም ውስጥ እገባለሁ አሁንም ሀራም ውስጥ ተዘፍቄያለሁ  እንተቃቀፋለን ምናምን ቆይ ሊና ምን ሆነሻል እሺ ብሞትስ ኡፍፍ ግን በዚህ እድሜዬ አግብቼ የማፈቅረውን ልጅ ማጣት አልፈልግም    ስልኳን ከፍታ እመጣለሁ  ብላ ላከችለት

ኢብራሂም ስልኩን ወዲያው የተላከለትን መልዕክት ለማየት ከፈተው ሲያየው  እመጣለሁ ይላል  ደስታ ልቡን ወረረው ሀናን ሲል ጠራት ሳሎን ቤት ሆና ስልኳን   አሰየጓረጓረች ነው
ሀኒ..

ነይማ አንዴ
መጣሁ
ስልኳን ዘግታ  ወደ ሱ ክፍል ሄደች 

ኢብሮም እንድትቀመጥ ካደረጋት በኋላ ያው ፍቅር ነገ ኒካህ ልናስር አይደል ደስ ይላል እና የኔ ማለት ያንቺ ያንቺ ማለት የኔ ነው አይደል

ሀናን  ልቧን ደስታ እየሞላው አዎ አላች ፈገግ እንዳለች

እናም ትንሽ ብር እንድትሰጪኝ ፈልጌ ነው

ስንት ብር ነው የምትፈልገው ፍቅር?

አንድ አስር ሺህ ካለሽ ነው ግን አለ ፈራ ብሎ

ቦርሳዬ   ውስጥ ስምንት ሺህ ብር አለ ስመጣ ለአንዳንድ ነገር ይሆናል ብዬ የያዝኩት    ቆይ ላምጣልህ ተነስታ ሄደች


ኢብሮ አሁን ብሩን አዘጋጅቷል ወደ ደብረ ዘይት ነው መሄድ ያሰበው ለሷ አላንስም ብሎ አስቧል የተወሰነ ልብስ አዘጋጅቷል   ቤተሰቦቹን ጥሎ መሄዱ ቢያሳስበውም   ሀናንን ግን በፍፁም ማግባት አይፈልግም   እንዲቀናው በመመኘት ተኛ

በተመሳሳይ ሊናም ልብሷን አዘጋጅታ ጨርሳለች  ቤተሰቦቿ እሷን ላለማስጨነቅ        ጊዜ እንስጣት ብለው ተኝተዋል አባቷ አንድ ልጄ አበባዬ የሚላት አጠራር ድቅን ይልባታል እምባዋ ዝም ብሎ ይፈሳል ግን ወስናለች አላህን ይቅር እንዲላት ተማፅና ወደ አልጋዋ ገባች


የለይልን ሰላት እየሰገደ ነው ኡመር ሀይማኖቱ ላይ ጠንክሯል  ሰላቱን ማገባደድ ላይ ስለ ደረሰ እጆቹን ከፍ አድርጎ
ያቃዲር  ምስጋና ላንተ ይገባ አመሰግንሀለሁ ያረቢ  አንተ ሊና ለኔ ጠቃሚ ከሆነች በሀላሉ ስጠኝ ለኔ ጠቃሚ ካልሆነች አስረሳኝ ሌሎችንም ዱአ ጨምሮ ሰለዋትን በነብያችን ላይ አውርዶ ጋደም አለ


አይነጋ የለምና ነጋ ሊና እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር   ነጋ ገና ለፈጅር አዛን ሳይል ልብሷን ይዛ ካደገችበት ቤቷ ከወላጆቿ ርቃ ለመሄድ ከቤት ወጣች  አይኗ በእምባ እንደተሞላ ከተባለችበት ቦታ ደረሰች...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
    #ክፍል_ሀያ_ሰባት {➋➐}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
25.1K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ