Get Mystery Box with random crypto!

ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianislamic — ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianislamic — ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianislamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 110.65K
የሰርጥ መግለጫ

በቅንነት ዩቲብ ቻናላችን ሰብስክራፕ ያድርጉ
https://bit.ly/4044MQR

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-02-27 22:20:51 «በቃ ቀይሪ መጣሁ .... » ትቻት ወጣሁ።
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ የኢክራም እርምጃ ሲቀርበኝ ተሰማኝ። ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ዞሬ ስመለከት የፌሪ ገላ ላይ የማውቀው ልብስ የኢክራም ገላ ላይ ደምቋል። ረዥም ናት። የሰውነት ቅርጿ ውብ ነው። ፈገግ አለች። ሁለት እጆቿን እንደክንፍ ዘረጋቻቸው።  እጆቿ ሲዘረጉ ልብሱ ይበልጥ ከፍ አለ። ጭ ... ኖ .... ቿ ፍም ይመስላሉ። ቅላቷ ይንቦገቦጋል።

«እና ማን ላይ ያምራል?»
«ሁለታችሁም ላይ ጥሩ ነው።» እውነቱን ለመናገር ይኼ ልብስ ከሰውነቷ ቅላት ጋር አብሮ ሄዷል። ኢክሩ ላይ ይበልጥ አምሯል። ግን አንቺ ላይ ይበልጥ ያምራል ማለት ከባድ ክህደት መስሎ ተሰማኝ።

ከዚያም ቀረበችኝ። ከዛስ አላችሁ እንዴ? አይባልም እሺ! እንደዚህ አይነት ነገር አይጠየቅም። ግን መጥታ ታፋዬ ላይ ተቀመጠች።

«ሚስቴ ታፋዬ ላይ ነው የምትቀመጠው ያልከኝን አስታወስከው?»
«አዎ!»
«ለዛ ነው ታፋህ ላይ የተቀመጥኩት!»
«ሽቶሽ ልብሷ ላይ እንዴት ኖረ?»
«ነፋሁበታ! ጠረኗንም ገደልኩት!»
«ሞተልሽ?»
«ስለሞተ መሰለኝ የእኔን ጠረን ያሸተትከው!»
«ሽቶ ግን የእኔ ይሻላል አይደል!»
«እድሜ ለበርጊቾ! በየወሩ ከሀገር እየወጣ ያመጣልሻል!»
«እኮ! ጠረኔም በለጣት!» ደስ አላት።
ስስ ጣቶቿ ጉንጬ ላይ አረፉ። ከዚያስ አላችሁ? ተው! ከዛስ አትበሉ። ጣቷ ጉንጬ ላይ ካረፈና ኢክራም ታፋዬ ላይ ከተቀመጠች ምን ሊከሰት ይችላል? መናገሩ አግባብ አይደለም። ሁሉም ሰው ቤት ውሀ ላይኖር ይችላል። ግን ከንፈሯ ከንፈሬን ነካው። መናገሩ ልክ አይደለም እንጂ እገልፀው ነበር። ጣቶቼ ጭኗ ስር ገቡ። ተው ላጤ ሆድ ይብሰዋል ..... ባለትዳር ይጨንቀዋል አልግለፀው። አንገቴን መጠጠችው። አልበላችም እንዴ? ምግብ የለም ወይ በሀገሩ? መኝታ ክፍል መች እንደገባን አላውቅም። ባለፈው የሆነው ሆነ። አልጋ ከወዘወዙት መወዝወዙ አይቀርም። አካል ሲያመው ያቃስታል .... በብዙ ሲደሰትም እንዲያው! ተው አንናገረው! ሁሉም ሲያልቅ ፀፀት አለው። እንደከዚህ ቀደሙ ግን አይከብድም! ተቃቅፈን ፀሀይ ወጣች። በሌላ ሴት እቅፍ ውስጥ የወጣች የመጀመሪያዋ ፀሀይ ነበረች።

ይቀጥላል!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
10.5K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-27 22:20:12 የልብ ነገር
ክፍል አምስት
(ፉአድ ሙና)
***
እንደክራር ...
አቃሰተች አቅል ስታ
በፈቃዷ እጇን ሰጥታ!

ገዘገዛት
አዝማሪ ነው አለቃቃሽ፣
ለእሷ ጥፋት ራሱን ወቃሽ።

***
«ፋሚዬ .... የኔ ጌታ ...»
«ፌሪዬ .... »
«አሞሀል እንዴ?»
«አላመመኝም ኧረ .... »
«ለምንድነው ስደውል ማንሳት ያቆምከው? ፊትህም ተጨንቋል። የታለ የኔ ፋሚ? ሳቂታው .... ተጫዋቹ ፋሚ የታለ?»
«እኔንጃ ፌሪዬ!»
«ናፈቅኩህ በጣም? ትቼው ልምጣ እንዴ የኔ ጌታ?»
«በመሀል እረፍት ይሰጧችኋል እንዴ?»
«አይሰጡንም ውዴ!»
«ምን ያህል ጊዜ ቀረሽ?»
«ወደ አራት ወር ከግማሽ አካባቢ መሰለኝ።»
«እሺ በቃ።» ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።
ፌሪዬን ማናገር ይጨንቀኝ ጀምሯል። አይኔን አይታ ታውቅብኝ ከሆነ እያልኩ ፈርቻለሁ። በራስ መተማመኔ ሸሽቶኛል። በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት የመጀመሪያው ነው። አድርጋችሁ የማታውቁትን ነገር ማየት እና መስራት! መጀመሪያ ላይ ያለውን የፍርሀት ስሜት ካለፋችሁ ከዚያ በኋላ ሀጢያቱን መድገም ውሀ ከመጠጣት ይቀላል።

ከኢክራም ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ከወደቅን ወዲያ በፍፁም ይህን ስህተት ላለመድገም ከራሴ ጋር ቃል ተገባባሁ። ለአንድ ወር ያህል መፅናት ቻልኩ። ግን ራሴ ከዳኝ ወይም ራሴን ከዳሁ። ቤቷ ይመስል ቤቴ ማዘውተር ጀምራለች። ራሴን መቋቋምም ሆነ እሷን ማስቀየም ከብዶኛል።
«ፉዬ ....»
«ወዬ ....»
«ገላዬ አያምርም እንዴ?»
«ያምራል ኧረ!»
«የደበረህ ነገረ አለ እንዴ ከኔ?»
«ኧረ የለም!»
«ለምን ተውከኝ ታዲያ?»
«ማለት»
«የባለፈውን ....» ወደ መኝታ ክፍላችን በአፏ ጠቆመችኝ።
«ኢክሩዬ ....»
«ወዬ የኔ ውድ!»
«ባለትዳር እኮ ነኝ!»
«ባትሆንስ ኖሮ?»
«ባልሆንስ ኖሮ? ምን?»
«ባትሆንስ ኖሮ ታገባኝ ነበር?»
«ለምን አላገባሽም?»
ደስ አላት። ተፍነከነከች። ተጠመጠመችብኝ።
«ግን እኮ አግብቻለሁ።»
«እኔን ትወደኛለህ?»
«ፈሪሀን የበለጠ እወዳታለሁ።»
«ትታህ ውጪ ሄደች አይደል ፈሪሀ!»
«ፈቅጄላት ነው።»
«ሁለት አመት ነው አንተ የፈቀድከው!»
«ቀጣዩንም ፈቅጄላት ነው።»
«ማዘን እና መፍቀድ ይለያያል።»
«እንባዋ ጭንቀቷ አሳዝኖህ እሺ አልክ እንጂ ልብህ አልፈቀደም። እንድትመጣ ትፈልግ ነበር አንተ! አይደል?»
«አልተሳሳትሽም።» ፈገግ አለች።
«አንተ ከእኔ ጋር አንዴ ለተኛኸው ትሳቀቃለህ ሌላ ወንድ ቢሆን .... »
«ሌላ ወንድ አይደለሁም!» አቋረጥኳት።
«ለምን አታገባኝም?»
ክው አልኩ! በዚህ ወሬ መግፋት አልፈለግኩም።
«ኢክሩዬ ለምን ስለ ሙና አልነግርሽም?»
የምትወደው አርዕስት ስለተከፈተ ደስ አላት።
«በጣም ደስ ይለኛል። ለምን ፉአድ ሙና ተባልክ?»
«ፈሪሀ ሶስት እህቶች አሏት።»
«ፈሪሀ ፈሪሀ አትበልብኝ ስለ ስምህ ነው መስማት የፈለግኩት።» ስሜቷ ከደስታ ወደ ቁጣ ከመቅፅበት ተቀየረ። በቅናት ተንገበገበች።
«እንዴ ሚስቴ እኮ ናት!»
«እሱን አውቃለሁ። እንደ ዚክር አስር ቦታ አታንሳት።»
«እንዴ ከስሜ ጋር ያለውን ግንኙነት እየነገርኩሽ አይደል?»
«በቃ ከዚህ በኋላ ስለሷ ማውራት ስትፈልግ የዛች እያልክ አውራ!»
«ፈሪሀ ፌሪ ፌሪዬ ፌሮ ፈሪ ፈር..... » መሯሯጥ ጀመርን። በመጨረሻም ተሳክቶላት ወይም እንዲሁ መሸነፍ ሆኖልኝ ቆምኩላት። አፌን በለስላሳ እጇ ግጥም አድርጋ ያዘችው።
«የዛች በል!»
መሯሯጡ ደከመኝ። ሳልፈልግክ የመሻቷን ሞላሁ።
«የዛች ውብ ....»
«የዛች አይጥ በል!»
«የዛች ንግስት .... »
«የዛች አይጥ በል .... » መሯሯጡ በድጋሚ ተጀመረ። ቆምኩላት።
«ኧረ ኢክሩ .... ሚስቴ እኮ ናት!»
«አያገባኝም .... እኔ ነኝ ሚስትህ .... አጠገብህ ያለሁት!»
«አትቀልጂያ ..... »
«ሰራተኛዋን ጠርቼ እነግራታለሁ እንደውም! ከዚህ በኋላ ሚስቱ ነኝ እላታለሁ» ተነሳች።
«የዛች አይጥ ....» አልኩላት በአፌ .... ድራማ መስራት ደክሞኛል። በደስታ እየዘለለች መጥታ ተጠመጠመችብኝ።
«እ  ..... ስለስሜ ልንገርሽ ወይስ?»
ወደ ሶፋው ተመልሰን ተቀመጥን።
«የዛች እያልክ አውራ ስሟ ካለበት!» አስጠነቀቀችኝ።
«የዛች ....» በልቤ መልዓክ እላለሁ።
«የዛች ቤተሰብ ውስጥ ከእሷ በተጨማሪ ሁለት ሴቶች አሉ። የእሷን ታናሽ ያገባው ሰው ስም ከእኔ ጋር ሞክሼ ነው።»
«ከስምህ ጋር ምን አገናኘው?»
«እስኪ ልጨርስ አትጣደፊ!»
«እሺ ይቅርታ በቃ ቀጥልልኝ .... » ሙዝዝ አለች።
«እና እነሱ ቤት ፕሮግራም ሲኖር ሁለታችንም ስለምንኖር ፉአድ ቢሉ መለየት ከበዳቸውና ሁለታችንም ስም ላይ የሚስቶቻችንን የቤት ስም ጨመሩበት። እናም የዛች የቤት ስም ሙና ነው። ፉአድ ሙና ስባል ለመድኩት .... ስለምወዳትም ወደድኩት። ከዋናው ስሜ በላይ አሁን የምታወቀው በእሱ ነው።»
«ባላውቀው ይሻለኝ ነበር። ከዚህ በኋላ ተሳስቼ በዚህ ስም አልጠራህም!» ለንቦጯ ተዘረገፈ።
«ኧረ?»
«አዎ! እንደውም ፉአድ መዱ ነው የምልህ!»
«መዱ ያንቺ መሆኑ ነው?»
«አዎ! የቤት ስሜ መዲና ነው።»
ሰዓቱን ሳየው ከምሽቱ አንድ ሰዓት እየተጠጋ ነው።
«እየመሸ እኮ ነው አትሄጂም እንዴ ዛሬ?»
«ምነው እስክሄድ ቸኮልክ የምታስገባት አለች እንዴ?»
«ኧረ ለምን አታድሪም ከፈለግሽ! ማንም የለም።» እደሪ ማለቴ ሳይሆን የማስገባት አለመኖሯን ለማስረገጥ የተናገርኩት ነበር።
«ዛሬ ጉድህን አየዋለሁ። እዚህ ነው የማድረው እንደውም!»
«ተይ ከበርጊቾ ጋር አታጣይኝ!»
«ቢኖር መች እስከዚህ አረፍዳለሁ? ውጪ ሄዷል።»
«ለዛ ነዋ እንደዚህ ፈታ ያልሽው!»
«የምሬን ነው አድራለሁ ያልኩህ በነገራችን ላይ!»
እምቢ የምልበት አቅም አልነበረኝም። አልጋዬ ሰው ናፍቋል። ቤቴ የሰው ድምፅ ካስተጋባ ቆይቷል። ኢክሩ ደግሞ የጨዋታ ሰው ናት።
«እሺ ....» አልኳት። አይኗ መልስ እየጠበቀ ነበር። ደስ አላት።
«የመኝታ ልብስ አልያዝኩም .... ያቺ ትታው የሄደችው ልብስ የለም?»
«የሷን ልብስ ልትለብሺ?»
«አዎ እንደውም ማን ልብሱን ይበልጥ እንደሚያሳምረው ትዳኛለህ!»
«እሷ ሰደቃ ስለምትወድ ልብሷን ልሰድቅሽ ባይሆን!» ሳቅኩባት። ተናደደች።
«ስማ ግን አብረሀት ብዙ ስለኖርክ ለምደሀት ነው እንጂ እኮ ምኗም አያምርም! ደግሞ እስካሁን ልጅ ሳትወልድልህ አስበኸዋል? ይደብራል።»
«Brain wash እያደረግሽኝ መሆኑ ነው?» ሳቅኩ!
«እኔ ብሆን እስካሆን ሀያ ልጅ ወልጄልህ ነበር። ቤተሰቦችህም የልጅ ልጅ አይተው ይደሰቱ ነበር። በእሷ ራስ ወዳድነት ወላጆችህ ይህን መነፈጋቸው በጣም ያሳዝናል።»
«በይ ነይ ልብሱን ምረጪ!» የምታወራውን ነገር ጭንቅላቴ ውስጥ ላለማስገባት እታገላለሁ።
ተከታትለን ወደ መኝታ ክፍል ገባን። ከተከፈተ የቆየውን የፌሪን ቁምሳጥን ከፈትኩት። ፌሪዬ ትታቸው የሄደቻችው ልብሶች ተደርድረዋል። የመኝታ ልብሶቿን ጠቆምኳት። ፌሪዬ ለብሳቸው ስንት የፍቅር ትዕይንት ያስተናገዱ ልብሶቿን እያነሳች እየጣለች መምረጥ ጀመረች። በመጨረሻም ፌሪዬ ሲሸልስ በነበርን ሰዓት የገዛችውን የመኝታ ልብስ መረጠች። ደነገጥኩ። የሲሸልሱ ቆይታችን ከአይኔ ተደቀነ። ኢክራምን ሌላ ልብስ እንድትመርጥ ለመንኳት። የፌሪ ትዝታ ላይ መደረብ አልፈለግኩም። ሌላ ተመሳሳይ ልብስ መረጠች። ስስ ቀይ የውስጥ ልብስ ነበር። እያየኋት ልብሷን መቀየር ጀመረች።
.
.
12.4K views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-26 22:38:32
ረመዳንን ፆም ከሚስኪኖቻችን ጋር !

እባካችሁን ደጋግ ኢትዮጵያዊን ! እባካችሁን ሼር SHARE
እባካችሁን ደጋግ ኢትዮጵያዊን በሙሉ ይህንን ቪዲዮ ለብዙ እንዲዳረስ የበኩሎ ድጋፍ ያድርጉ ። አክማም የበጎ አድራጎት ማህበር ሚስራችው በጎ ስራ ላይ በአቅማችሁ ልክ ተሳተፍ ለሌሎችም መልዕክቱን ያዳርሱ ።
ለበለጠ መረጃ | 0917206320 | 0919444490
የቲክቶክ አካውታችሁ follow | www.tiktok.com/@akmamofficial

ታላቅነታችንን_በሚስኪኖች_እንፈልግ!
CBE ACC. 1000300715269
Zemzem Acc. 0022896120101
9.6K viewsedited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-26 22:34:35 የልብ ነገር
ክፍል አራት
(ፉአድ ሙና)
***
አንድ ሁለት ...
ለህይወት አንዱ ነው ከባዱ፣
ከዚያ ቀላል ነው መውረዱ!

እምነት ወደቀ
ቅጥ አጣ ህይወት
ተሸረሸረ ወንድነት!

አንድ ሁለት!

የቤቴ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ቁምጣ ብቻ ለብሼ ከመስታወቴ ጋር ተፋጥጫለሁ። ፌሪዬን ካገኘ ሁለት አመት ከመንፈቅ የሆነው አካሌ ከነብሴ ጋር ሙግት ገጥሟል። ስልኬን አንስቼ ወደ ክፋዬ ደወልኩ። አነሳችው።

«ሰውየው ራቁቱን ....» ሳቀች።
«ፌሪዬ ... »
«ናፈቅኩህ አይደል? ደሞ ሻወር ቤት ምን ትሰራለህ?»
ከመታጠቢያ ቤት ወጥቼ ወደ መኝታ ክፍላችን አመራሁ። አልጋዬ ላይ ተወርውሬ በጀርባዬ ተንጋለልኩ።
«ፈለግክ እንዴ?» ሳቀች። አሽሙረኛ ሳቅ አላት።
በአይኔ የአዎንታ ምልክት አሳየኋት።
«እሺ ... » ቲሸርቷን አወለቀችው። የሸኘሁት ውበት ይበልጥ ጎምርቷል። ሀገረ እንግሊዝ ተስማምቶታል።
«ፋሚዬ አለቃዬ እየደወለች ነው አንዴ!» ስልኩ ተቋረጠ። የኔም ስሜት ከስልኩ ጋር አብሮ ተቋጨ። አልቅስ አልቅስ አለኝ።
መልሳ ከደወለች ብዬ ጠበቅኳት .... አልደወለችም። 

ገላዬን ለመታጠብ ስነሳ ስልኬ ጠራ። ፌሪዬ ከሆነች ብዬ ስልኩን ተመለከትኩት። ኢክራም ነበረች።
«ሄሎ ኢክሩ ... »
«ፉዬ አሰላሙአለይኩም»
«ወአለይኩሙሰላም እንዴት ነሽ?»
«አልሀምዱሊላህ .... ድምፅህ ጎርንኗል አሁን ገና መነሳትህ ነው እንዴ?»
«እሁድ አይደል ....»
«እሱማ ለዛም ነው መደወሌ .... ስራ አለብኝ የሚል ሰበብ የማይሰራበት ቀን ስለሆነ አንድ ሰበብ ይቀንስልሀል።» ትስቃለች። ድምጿ እንደዚህ እንደሚያምር ልብ አላልኩትም ነበር። ወይም ደግሞ ዛሬ እየቆላችው ነው። ምላሷ በቋቋ የሚሄድ አይነት አቆላል! አሊያም የሚሰማት ስሜቴ ይሆናል።
«እና ምን ልታዘዝ?»
«ዛሬ ለምን አብረን አንውልም?»
«ዛሬ እንኳን ይቅር በይኝ ከቤት መውጣት በጣም ደብሮኛል።»
«ችግር የለውም በቃ እኔ ቤት እመጣለኋ!»
«ቀልደኛ!»
«የምሬን ነው። ጓደኛዬ አይደለህ እንዴ?»
«ታውቂያለሽ አይደል አንዳንዴ ድፍረትሽ በጣም እኮ ነው የሚገርመኝ!»
«አንተ ተገረም .... እኔ መጣሁ።» ስቃ ስልኩን ዘጋችው።
ገላዬን ከታጠብኩ በኋላ ተመልሼ አልጋዬ ላይ ተጋደምኩ።
ስልኬ ጠራ። ኢክራም ነበረች።
«እሺ የበርጊቾ ልጅ!»
«እሺ የሙና ልጅ? የማን ልጅ ልበልህ ግን የሙና comfort አይሰጥም!»
«አዝግ!»
«እሺ የደወልኩልህ ከቤት ስለወጣሁ ይዤልህ የምመጣው ነገር ካለ ልጠይቅህ ነው።»
በልቤ ይህቺ ልጅ አመረረች እንዴ እያልኩ እገረማለሁ።
«ምን ይዘጋሀል? ወይስ በእኔ ምርጫ ገዝቼ cook ላድርግልህ?»
«እንደሱ ይሻላል መሰለኝ  .... » ልቤ ደረቴን ሰንጥቃ ልትወጣ ምንም አልቀረኝም። ፍርሀት ወረረኝ።

ከኢክራም ጋር በጊዜ ሂደት የፈጠርነው መቀራረብ ያስፈራኛል። ፈሪሀ እኔ ወደ ሌላ ሀገር ሄጄ ከአንድ ወንድ ጋር ይህን ያህል ብትቀራረብ ምን ሊሰማኝ እንደሚችል ሳስብ ትክክል እንዳልሆንኩ ይሰማኛል። ግን ደግሞ እንደትላንቱ አይነት ጥንካሬ ውስጤ የለም። ከፈሪሀ ውጪ ሴት የሌለ የሚመስለው ፉአድ ከሁለት አመት በላይ መቋቋም የቻለ አይመስለኝም። ውስጤ ላይ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት አለ። የማላውቀው የቸልተኝነት መንፈስም እየወረረኝ ነው። ኢክራም እየመጣች እንደሆነ ነግራኝ እንኳን ለሰራተኛዋ እንግዳ እየመጣ እንደሆነ አላሳወቅኳትም። ከየት የመጣ ቸልተኝነት እንደሆነ አላውቅም። ወይም ሰራተኛዋ እንድታውቅ አልፈለግኩምም ይሆናል። አላውቅም .... እየሆነ ያለው እንኳን ለምን እንደሚሆን አላውቅም።

የውጪው በር ተከፍቶ የኢክራም መኪና ሲገባ በመስታወቱ በኩል አያለሁ። መኪናዋን ቦታ አስይዛ ወረደች። ዘበኛው ከኋላ ያለውን ፌስታል አወረደላት። ፈዝዤ አያታለሁ። ሙሉ ሰውነቷ ላይ የተለጠፈ ስስ ቀሚስ ለብሳለች። ከቀሚሱ ላይ ቤቢ ኮት ደርባለች። ቀና ስትል አየችኝ። ፈገግ አልኩላት። ትንሽ እንኳን አልተሳቀቀችም። የባሏ ቤት አሊያም የራሷ ቤት የምትገባ እንጂ ፈሪሀ የምትባል የውበት ጌታ ሚስት የሆነችበትን ደረጃ የምትወጣ አትመስልም።

«ሰውዬው ... » ጠጋ ብላ ጉንጬን ሳመችኝ።
ልቤ ታገለኝ እወጣለሁ አትወጣም ሙግት ገጠመኝ። ቤቢ ኮቷን አውልቃ የቀሚሷን እጅጌ ሰበሰበች።
«የሚጣፍጥ ቁርስ ነው የምሰራልህ!»
«ኢኩዬ ቁርስ እኮ ሰራተኛዋ ሰራችልኝ .... በላሁ።» አይኖቼ ቀሚሷ የተለጠፈበትን ጉደኛ ወገብ ላለማየት ይታገላሉ።
«እንደዛ ከሆነ በቃ በኋላ እሰራልሀለሁ።» እጅጌዋን አስተካክላ ወደ ሳሎኑ ተመለሰች። ተመልሳ ከፊቴ ስንዝር ያህል ቀረበች። በዚህ ሁኔታ እንዳለን ሰራተኛዋ መጣች።
«የምትፈልጉት ነገር አለ?»
«ሲኖር እንጠራሻለን!» ኢክራም ቀድማ መለሰች። ይኼ ነገር በሰራተኛዋ እንደሚያስጠረጥረኝ ገመትኩ። ሰራተኛችን ከፈሪሀ ጋር ቅርበት አላት።
«ወደ መኝታ ክፍል ብንገባ አይሻልም?» በፍርሀት የሰነዘርኩት ጥያቄ ነበር።
«ይሻላል? እሺ!»
ተከታትለን ወደ መኝታ ክፍል ገባን። እንደገባን በሩን ቆለፍኩት።

የኢክራም እጆች ሲንቀጠቀጡ ይታየኛል። በሩን የዘጋሁት ተመኝቻት ሳይመስላት አይቀርም። አልጋው ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ። መኝታ ክፍላችን ውስጥ ያለው ሶፋ ላይ ተቀመጠች።

«ስማማ የሙናን ነገር ፍቺውን አልነገርከኝም አይደል? አላሳዝንህም? ስንት ዘመን አለፈው ስጨቀጭቅህ!» ፍርሀቷን ለመግደል ያነሳችው ጥያቄ ነበር።
«አንቺ ደግሞ አትረሺም አይደል .... »
ተረጋጋች መሰለኝ ወደ አልጋው መጥታ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠች። ጠረኗ ይገድላል። ፍርሀት እና ድንጋጤ ሊደፋኝ ነው። ከዚህ በኋላ ሸይጧን ቀሪውን በእኔ ወጪ ሳይለን የቀረ አይመስለኝም። እንዲሁ ስንቀራረብ ይታየኛል። የፍቅር መልክ .... የውበት ተምሳሌት የሆነችው ፍቅሬ በምትተኛበት አልጋ ላይ ኢክራም ተንጋለለች። ቀሚሷ ተሸበሸበ። ባዕድ ከንፈር ነካኝ። ስልኬ ጠራ። ኢክራም አቅሏን ስታለች። ተሽቀዳድማ ዘጋችው። መሆን አይደለም መታሰብ ያልነበረበት ሆነ። የፈሪሀ ዙፋን ተደፈረ። ገላዬ በባዕድ ጦር ተወረረ። በኢክራም!

«ፉአድ!» ሰራተኛዋ ተጣራች።
አልመለስኩም።
«ከመስጂድ ዚያራ ወንዶች አሉ ወይ እያሉ ነው።» ዝም አልኩ። ወንዶች የሉም። ወንድ ብሆንማ የአመታት ፍቅሬን መቅደስ ባላስደፈርኩ ነበር። ወንዶች የሉም። አዎ! እንደዚህ ከዘቀጡ በኋላ ወንድነት ምንድነው? ፆታ ነው? ወንዶችማ የሉም!

ኢክራም ከላዬ ላይ ወደ ጎን እንደተንጋለለች ስልኬን አነሳሁት። የደወለችው ፌሪ ነበረች። የዘጋባት እጅ የሴት እንደነበር ብታውቅ ምን ይሰማት ይሆን? ማሰብ አቆምኩ። ድጋሚ ከንፈሬ ላይ የኢክራም ከንፈር አረፈ። ከዛም ብዙ ነገር ሆነ። የሆነውን ብፅፈው ጥሩ አይደለም። የላጤ ሆድ ያስብሳል። የባለትዳር ቁጣ ያስነሳል። ግን የሆነ ነገር አለ። ከመሳም ያለፈ ... የሁለት ሰው ሰውነት ከጋለ በኋላ የሚሆን ነገር ተፈጥሯል። አልጋው ድምፅ እንዲያወጣ የሚያደርግ ... አቅል የሚያስት ነገር ሆኗል። ግን ብናገረው ጥሩ አይደለም። ውሀ ተረኛ የሆነ ሰው ሆድ ይብሰዋል። ግዴለም አልናገረው። ግን የኢክራም ድምፅ ልዩ ቅላፄ አውጥቷል። ስሜ ተቆላምጦ ሲደጋገም ሰምቼዋለሁ። እንደዚህ ሁኚ ...እንደዚያ ሁንልኝ የሚሉ የትዕዛዝ ድምፆችን ተለዋውጠናል። ግን መናገሩ አስፈላጊ አይደለም። አዕምሮ ከቁጥጥር ውጪ ሲሆን ተዛዝበናል። የላብ ጠረናችንን ተሸታትተናል። ግን መናገሩ የላጤን ሆድ ያስብሳል። የመስመር አለፍክ ባዮችን ማስመሪያ ያስነሳል። ግድ የለም ልለፈው ግን ብዙ የሆነ ነገር ነበር።

@Ethiopianislamic
10.4K viewsedited  19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-23 19:33:48 ምግብ አዝዘን አስተናጋጁ ትንሽ እንደራቀን በአይኗ ማውራት ጀመረች። ከኢክራም ልዩ ባህሪ ውስጥ ከሰው ጋር በአይን መግባባት ነው። እንዴት እንደሆነ ባላውቅም በአይኗ ብቻ ማለት የፈለገችውን ታስረዳኛለች። ደግሞም በደንብ ይገባኛል። ግን ደግሞ ቢገባኝም እጠይቃታለሁ።

«ምንድነው?»
«ቢሮ ሆነን ቃል የገባህልኝን ንገረኝ!»
«ምኑን? ምን ቃል ገባሁ?»
«በአላህ አትድረቅ! ሙና ማነው ምንድነው?»
«ለምን አጓጓሽ?»
«የሚስትህ ስም ፈሪሀ ነው! እና የእናትህን ስም አውቀዋለሁ። እንዴት ሙና ልትባል እንደቻልክ ገርሞኝ ነው።»
«እኔን በማጥናት የሚሰጥ ድግሪ አለ እንዴ?»
«አትድረቅ! ለምን ፉአድ ሙና ተባልክ?»
አስተናጋጁ «ማዮኔዝ ይደረግበት አይደል?» ብሎ አቋረጠን!

ይቀጥላል!.....
.
ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
12.0K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-23 19:33:46 #የልብ_ነገር
#ክፍል_ሶስት
(ፉአድ ሙና)
***

አየሁት እንባዋን
ከመከፋቷ ውስጥ፣ ሲረግፍ እንደዝናብ
ምን ነበር ቢጠረግ፣ የመራቋ ነገር ከታሪካችን ባብ!

ሳቅ አየሁኝ ከዚህ
ሳቅ አየሁኝ ከዛ፣ የተመሳቀለ፣
አንዷ ትዝታዬን፣ እሷን የመሰለ።

***
ፌሪዬ ውጪ በሄደች በሁለተኛው ዓመት መጨረሻ ከባድ የሆነ መርዶ አረዳችኝ። የምትሰራበት ተቋም ውጪ ያለው ቢሯቸው ላይ ለሁለት ዓመት እንድትሰራ እንደጠየቋት ነገረችኝ።

ካፌ ውስጥ ተቀምጬ ነበር። ከፌሪ የተደወለልኝን የቪዲዮ ጥሪ አነሳሁ።

«እ ምን አሉሽ?» ፊቴ ላይ ቁጣዬ ይነበባል።
«አይቻልም አሉኝ!»
«ምን ማለት ነው?» ሳላስበው በጣም ጮህኩ። ቁጣዬን መቆጣጠር እየተሳነኝ ነው።
«የገባሽው ስምምነት ላይ ተካቷል .... የውል ግዴታሽን መፈፀም አለብሽ አሉ።»
«ታውቂ ነበር ፌሪ! ታውቂ ነበር! ከጅምሩ ከዚህ እንደማለቅሽ አስበሽ የዘየድሽው መላ ነው። ታውቂ ነበር! አትወጂኝም እንዴ? በግድ ነው እንዴ የተጋባነው?»
«ወላሂ አላውቅም ነበር ፋሚዬ! እንዴት እኔ ካንተ መሸሽ እፈልጋለሁ? አባቴ ደስ እንዲለው ነው እንጂ .... »  ማልቀስ ጀመረች።
«በለቅሶሽ ልታሳምኚኝ አትሞክሪ! አሁን ቲኬት ቆርጬ እልክልሻለሁ! ትመጫለሽ!» ስልኩን ጠረቀምኩባት!
ፀሀፊዬ ጋር ደውዬ ለፌሪ የመመለሻ ትኬት እንድትቆርጥ ነገርኳት። እንደ እብድ እያደረገኝ ነው። ካፌው ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ ከንፈሩን እየመጠጠ ያየኛል።

ወደ ቢሮዬ ስመለስ ፌሪ ከሳምንት በኋላ የምትመለስበት የአየር ቲኬት ተቆርጦ ጠበቀኝ። ትኬቱን ፎቶ አንስቼ ለፌሪ ላኩት። ፌሪ ደጋግማ እየደወለች ነው .... አላነሳሁላትም። ወደ ቤት ሄጄ ሶስት ቀን ሙሉ ከቤት ሳልወጣ ቆየሁ። በሶስተኛው ቀን ፌሪ የምትልካቸው የድምፅ መልዕክቶች ስላሳዘኑኝ ደወልኩላት።

«የኔ ጌታ! አለቃዬ! ፍቅሬ!» ድምጿ አንጀት ይበላል።
«ምንድነው?»
«ትኬቱን እኮ አየሁት .... »
«እና!»
«አንተ ጌታዬ ነህ .... አስተዳዳሪዬ ነህ .... የበላዬ ነህ .... በህይወቴ ሁሉ ወሳኙ አንተ ነህ ፋሚዬ ...» ማልቀስ ጀመረች። በዝምታ ጠበቅኳት። ድምጿን ሳግ እየተናነቀው ቀጠለች።
«ነይ ካልክ .... ከወሰንክ እመጣለሁ። እስከዛሬ እንቅልፍ ሳልተኛ የለፋሁለትን ማስተርሴን ትቼው እመጣለሁ።»
ድምጿ ውስጥ እውነተኝነት አለ። በጣም ሲከፋት የምታወራበትን ድምፀት አውቀዋለሁ።
«አላውቅልሽም! ትምህርቱ ገደል መግባት ይችላል!» ልቤን መረበሿ ቢሰብረውም ለመጠንከር ሞከርኩ።
«ሁለት አመት ሙሉ ታግሰሀል እኮ አባ! ለሁለት አመት በናፍቆት የተሰቃየነው ሁሉ ገደል ይግባ የኔ አለቃ .... ጌታዬ!»
«ልትጨቃጨቂኝ ነው ካልደወልክ ያልሽው?» ስልኩን ዘጋሁባት።

ደጋግማ ደወለች። ትንሽ ራሴን ካረጋጋሁ በኋላ አነሳሁት።

ፌሪዬ ከአይኗ እንባ እየተንዠቀዠቀ ነው። ፊቷ ረጥቧል። የበደልኳት ያህል ጨነቀኝ።

«እሺ የኔ ጌታ .... እመጣለሁ። ትዕዛዝህን አከብራለሁ የኔ ፍቅር! ምን ይዤልህ ልምጣ?» መንሰቅሰቅ ጀመረች።

«ምንም አልፈልግም!» ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።

ስልኩን እንደዘጋሁት ልቤ ደረቴን እንደአታሞ መደብደብ ጀመረ። ፈራሁ .... ጨነቀኝ .... በምድር ላይ የምሳሳላትን አንድ ፍጡር የበደልኳት መሰለኝ። ራሴን አረጋግቼ ውሳኔዬ ላይ ለመፅናት ሞከርኩ። ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። ለቅሶዋ አይኔ ላይ እየተደቀነ ሰላም ነሳኝ። በረራዋ ሁለት ቀን ሲቀረው ደወልኩላት። ትልቅ የገበያ ማዕከል ውስጥ ነበረች።

«የኔ ፍቅር .... የኔ ፌሪ ...» ተንተባተብኩ።
«ወዬ ፋሚዬ» ፈገግ ለማለት ሞከረች።
«ምን እየሰራሽ ነው ሞል ውስጥ?»
«አንዳንድ ነገር Shop እያደረግኩ ነው። Gift ምናምን!»
«ለማን?»
«ለቤተሰብ .... For our dads and moms ምናምን!»
ማልቀስ አማረኝ .... ልቤን አንዳች ነገር እፍን አደረገኝ።
«ፌሪዬ .... »
«ወዬ ፍቅር»
«በጣም አፈቅርሻለሁ እሺ!»
«እኔ ደግሞ ካንተ በላይ!»
«በቃ ጨርሰሽ ነይ እሺ .... ፈቅጄያለሁ።»
«ማለት?»
«በቃ እንዲከፋሽ ... በእኔ ምክንያት ልፋትሽም ገደል እንዲገባ አልፈልግም! እንግዲህ እንደምንም እችለዋለሁ። ጨርሺና ከማስተርስሽ እና ከስራ እድገትሽ ጋር ደስ እያለሽ ተመለሽ።»
ተንሰቀሰቀች .... ባለችበት ተንበርክካ ተርገፈገፈች።
«በቃ አታልቅሺ የኔ ውብ .... አታልቅሺያ!»
«እወድሀለሁ ፋሚዬ .... ወላሂ እወድሀለሁ የኔ ጌታ! እንደማትጨክንብኝ አውቅ ነበር። የኔ ንጉስ!»
«አሁን ስትስቂ ማየት ነው የምፈልገው!»
ጥርሶቿ ፈነጠቁ። ፈገግታዋ እና የአይኗ ጨረር .... ደካማ ጎኖቼ ተለቀቁ። ደረቅ መሬት ላይ የመጀመሪያዎቹ የዝናብ ጠብታዎች የሚያስነሱት አይነት አብዋራ .... ከልቤ ላይ በፈገግታዋ ተጠረገ። የመታፈኔ ስሜት ለቀቀኝ። ፌሪዬ ሳቀች። ፌሪዬን ደስ አላት። በተጨማሪ ሁለት አመታት ስቃዬ ፈገግታዋን .... ሳቋን ገዛሁላት።

***
«ፉአድ ሙና?»
«አዎ!»
«የምር ስምህ ነው? ማለቴ ሙና?»
የቢሮዬ እንግዳ መቀበያ ላይ አንድ የቋሚ ደንበኛችን ልጅ አዲስ ስለጀመረችው ቢዝነስ እያማከረችኝ ነው። ሰሞኑን በየሁለት እና ሶስት ቀኑ ትመላለሳለች።
«የሚጠጣ ምን ይምጣልሽ?»
«ኧረ ደስ አይልም ፉዬ! እንደባለፈው ልታረሳሳኝ ነው አይደል?»
«ምኑን?»
«ሙና የሚለውን ነዋ!»
«ቆይ ስሜን ልታጠኚ ነው እንዴ የምትመጪው?»
«አይደለም!»
«እኮ ስለ ስራሽ ብናወራ ይሻላላ!»
«ስራውን ብዬ አይደለም የምመጣው ጓደኛሞች እንደሆንን አስቤ ነው። ጓደኛሞች ሆነናል ተባብለን የለ እንዴ ባለፈው?»
«አዎ ልክነሽ!» እንዳለችኝም ሆነ እንዳልኳት ምንም አላስታሰውስም። ግን ላስከፋት አልፈለግኩም።
«ስለ ስራው እኮ በቃ የምፈልገውን ነግረኸኛል። ካንተ ቢዝነስ ጋር የማይገናኘውን ደግሞ አንድ ዘመዳችን አለች ከሷ ጋር አውርተናል። እንዳንተ አይነት ጓደኛ ስለፈለግኩ ነው። ባትኮራብኝ ነው የሚሻልህ!»
ቅብጠቷ ትንሽ ስላሰጋኝ ሰራተኛዎቼ እንዲሰሙን አልፈለግኩም። ወደ ቢሮዬ ይዣት ሄድኩ።
«እሺ ልጅ ኢክራም!»
«ምነው የአባቴን እና የአያቴን ተውከው?»
«ኢክራም ባርጊቾ ነስሩ!»
«ስርዓታ!»
«እሺ በቃ! ኢክሩ ጓደኛዬ .... ለምን ምሳ አልጋብዝሽም?»
ተፍለቀለቀች። በጣም ደስ እያላት ከመቀመጫዋ ተነሳች።
«ስማ ግን ምሳ እየበላን ትነግረኛለሀ? ስለ ሙና!»
«ችግር የለውም እነግርሻለሁ!»

ምሳ ለመብላት ከቢሯችን አቅራቢያ ወዳለ አንድ ታዋቂ ሆቴል ሄድን። ወደ ሆቴሉ ስንገባ ኢክራም እየሳቀች «ስማ ምሳ አበላሻለሁ ነው አይደል ያልከኝ?» አለች።
«ሬስቶራንት አላቸው ውስጥ!»
«እ እኔ ደግሞ room ብቻ መስሎኝ!» ትስቃለች።
«ተጫዋች ነሽ!»
«ተጫዋች ሰው አትወድም?»
«ኧረ እወዳለሁ።»
«ስለዚህ ትወደኛለሀ!» ትስቃለች።
«ፐ ሎጂክ!» ወንበር ስቤ አስቀመጥኳት!
«ፐ ደግሞ Romantic ነሽ!»
«ሚስት ስላለኝ አይጠፋኝም!»
«እና ለእሷ እንደምትስበው ነው የሳብክልኝ?»
«ለሷ አልስብላትም!»
«ለምን?»
«ሁሌ ታፋዬ ላይ ነው የምትቀመጠው!»
«እንደዚህ ሬስቶራንት ስትበሉም?»
«ሬስቶራንት ውስጥ አንበላም!»
«እና!»
«ቀልዴን ነው ባክሽ!» መውጫ ስታሳጣኝ መሸነፍ መረጥኩ።
«ለማንኛው አሳሳብ ላይ ጎበዝ ነህ! ከዚህ በኋላ አንተ ካልሳብክልኝ አልቀመጥም!»
«ቆመሽ ትቀሪያለሻ!»
10.9K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-19 22:15:20 #የልብ_ነገር
#ክፍል_አንድ
(ፉአድ ሙና)
***

እንደ ፀሀይ ግባት ...
ውበት ማከማቻ፣
እንባ እያፈሰሱ፣ የሚያምሩ አይኖቿ፣

አመት እንዳልበላ ...
እንደተራበ ሰው፣
እየሮጠች መጣች፣ ከንፈሬን ልትጎርሰው!

***

ልክ ከአይኗ እንደገባሁ ሻንጣዋን የመግፋት አቅም አጣች። አይኔ በእንባ ተሸፍኗል። በእንባዬ ውስጥ ፍቅሬ ስትንደረደር ይታየኛል። በእጆቼ የያዝኩትን አበባ አንጠልጥዬ እኔም ወደሷ መሮጤን ተያያዝኩት። ወንድ አልነበርኩ እንዴ? ሊያውም ቆፍጣናው ፉአድ! እንባ የአይኖቹን አጥር ያለፈቃዱ የማይነቀንቁበት ደረቅ! አልቻልኩም .... ራሴን መቆጣጠር ከበደኝ።

አጠገቧ ደረስኩ ... ከሽሽጌ ገባች። ናፍቄያታለሁ። የሸሚዜን ቁልፎች ፈትታ ገላዬን በእጆቿ ለመንካት ትሞክራለች። ትኩስ ከንፈሮቿ በትኩስ እንባዋ ተለውሰው .... አቻ ከንፈሬን ይመጠምጣሉ።

«ይኸው ሻንጣሽ የኔ እመቤት!» የአየር መንገዱ ሰራተኛ ቱታውን እንደለበሰ ሻንጣዋን ገፍቶ እኛ  ጋር መድረሱ ነበር። መሳሳማችንን ገትተን ... ኪሴን ዳብሼ፣ አመሰገንነውና ሻንጣዎቿን እየገፋሁ ወደ መኪናችን መሄድ ጀመርን። በየመሀሉ እየቆምን እንተቃቀፋለን።

ቦታው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ናፋቂ አይኖች ከናፍቆታቸው ጋር የሚገናኙበት ... አፍቃሪ ልቦች ከውዳቸው ጋር የሚለያዩበት፤ ትዕይንተ ብዙ ስፍራ! ሻንጣዎቿን መኪናው ላይ ጭነን መኪና ውስጥ እንደገባን፤ እንደ አዲስ መላቀስ ጀመርን።

የመታወቂያ ስሟ ፈሪሀ ሁሴን፤ በእኔ አንደበት የለመደችው ደግሞ ፌሪ፣ የኔዋ፣ ፌሪ ፈሪ! የዛሬ አራት አመት ነበር ዛሬ የተገናኘንበት ቦታ ቆሜ ሳላምንበት የሸኘኋት! ለሁለት ዓመት የሄደችበት የትምህርት ጉዞ ተለጥጦ አራት አመት ተቀጣሁ!

«አንተ Airport ስንሳሳም ብዙ ሰው አየን እንዴ?»
«የለም ሁሉም አይነስውር ነበሩ።»
«I was out of my mind! ካንተ ውጪ ማንም አይታየኝም ነበር።»
«It's okay የኔ አበባ! ግን UK እኮ ምግብ ያለ ነበር የሚመስለኝ!»
«ምነው? ከሳሁ እንዴ?»
«ከንፈሬን እኮ በላሽኝ!»
ሳቀች። ሳቋ ያምራል! ጥርሶቿ ሲከፈቱ በቀጥታ ልብን ይይዛሉ! በጥርሶቿና በልብ መካከል ያለው ግንኙነት ቢጠና ደስ ይለኛል። በሀገረ እንግሊዝ የተማረችበት ዩኒቨርሲቲ ይህን አለማጥናቱ ይገርመኛል።

ቤት እንደደረስን መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። ሰራተኛዋ ከመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ የደረደረቻቸውን ምግቦች ቆማ ታስተካክላለች።
«Fami ሻወር እየገባሁ ነው .... መጣሁልህ!»
«እዛው እደሪ አሉሽ ደግሞ! እነ Mom ይመጣሉ!»
«Yours? Or mine?»
«ያንቺማ ለቅሶ አለ መሰለኝ እዛ አዳማ! አልተነሱም። ተረጋግታችሁ ነገ ኑ ብያቸዋለሁ! The road is not safe!»
«Who the hell died on my arrival day? He should be jealous!» ትስቃለች።
«አንቺ ክፉ! አርፈሽ ታጠቢ እስኪ!»
«ለምን አትገባም ከእኔ ጋር? አብረን እንታጠብ ... Join me!»
«ወዳንቺ ስመጣ ነው የታጠብኩት!»
«This one is special ሀቢቢ!» ሳቋ ሲስረቀረቅ ይሰማኛል።
የሌላውን ጊዜ ፉአድ ብሆን ኖሮ ሳትጋብዘኝ እየተንደረደርኩ እንደምገባ አውቀዋለሁ። ዛሬ ግን ፈራሁ! ሙሉ ራቁቴን ፊቷ መቆም አስፈራኝ። ገላዬ አፍ አውጥቶ የሚናገርብኝ ይመስለኛል። ጨንቆኛል።

የኔ ልዕልት ... ታጥባ ጨረሰች። መኝታ ክፍል ልብሷን እየቀየረች «ሀቢቢ አንዴ ና እስኪ!» አለች።
ወደ መኝታ ክፍል ስገባ አይኔን አጥበረበረኝ። ሙሉ ብርሀን ከፊቴ ቆሟል። የማያንፀባርቅ የሰውነቷ ክፍል የለም። ፈገግ ብላ አየችኝ። የፈገግታዋን ትርጉም እኔም እሷም እናውቀዋለን።

«ድጋሚ ልትታጠቢ ነው?» ሳቄ መጣ!
«ውሀ አለ አይደል! ለምን ሺህ ጊዜ አልታጠብም!»
የፈለገችውን ብሆንላት ደስ ይለኝ ነበር። ግን ደግሞ እፈራለሁ። ገላዬን አላምነውም። ከቂያማ ቀድሞ ለማውራት የሚሽቀዳደም፤ ጉዴን የሚናገር እየመሰለኝ ነው።
«የኔ ውድ ... አራት አመት ነው የናፈቅኩሽ! ናፍቆቴን በዚህ መልኩ አይደለም መወጣት የምፈልገው! እማዬ እና አባ እየመጡ ነው። አንደኛውን ስንረጋጋ ይሻላል እሺ!»
የታችኛውን ከንፈሯን ወደፊት ለጠጠችው። አቅፌ አባበልኳትና ልብሷን መልበስ ጀመረች።

የመመለሻ ትኬቷ ከተቆረጠ ጀምሮ ውስጤ ሰላም አልነበረውም። ለእሷ ያለኝ ፍቅር ጥልቅ ነው። ከብዙ ማሰላሰል በኋላ ልጋፈጠው ወሰንኩ። ልቤ እንደማትጨክንብኝ ‘ምሎልኛል። ቢሆንም መልካም ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን መላ ቀየስኩ!

የናፈቃትን የሀገሯን ምግብ በልታ ... የናፈቋትን አግኝታ ... ያለፏትን ሀዘንና ደስታ ጠይቃ ሁለት ሳምንታት እንዳለፉ ራሴን ነፃ ለማውጣት ወሰንኩ።

«ፌሪዬ»
«ፋሚዬ»
«እወድሻለሁ»
«እኔ ደግሞ እጥፉን!»
«ዛሬ የሆነ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለሁ!»
«ምንድነው?»
«ይቅር ልትይኝ ....   ቃል ግቢልኝ!»
«ምንድነው?»
«ቃል ግቢልኝ በአላህ!»
«እሺ ቃል እገባለሁ!»
«ፌሪዬ ... »
«ፋሚዬ ...»
«ሁለተኛ ሚስት አግብቼያለሁ ... »
«ምን?» ፊቷ ፍም መሰለ።

ይቀጥላል ...
.
ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic
13.5K views19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-13 20:15:09 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
#ክፍል_ሠላሳ_ስድስትት {❸❻}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

(የመጨረሻው ክፍል)


...ምን...ሲጀመር ማነሽ አንቺ ታቂኛለሽ

<የኔ ማንነት ምን ይጠቅምሀል>
<መጣልኝ ድምፅሽ ሀናን ነሻ>
<አዎ ነኝ ስልኬን ቀይሬ ነው>
<እና ለምን ደወልሽ አረሳሽኝም እንዴ>
<ኢብሮ አሁን ብቻ ስማኝ በአላህ አምስት ደቂቃ ልለምንህ>
<አውቃለሁ በድዬሻለሁ በቃ ይቅር በይኝ ስልኩን ልዘጋው ነው>
<እሺ ይቅር እንድልህ አምስት ደቂቃ ስማኝ>
<እሺ ግን አዲሱን ስልኬን ከየት አገኘሽው>
<መሬት ላይ ወድቆ ልበልህ>
<ኡፍ የሚቀለድበትን ሰአትም  አታውቂም በይ አሁን ቀጥይ>
<ኢብሮ ከጠፋህ አራት ወር ሞላህ እናትህ እና አባትህ እህት ወንድሞችህ እኔን ጨምሮ ብቻ ብዙ ሰው ስላንተ ተጨንቋል  ኢብሮ አንተ ከጠፋህ በኋላ ሊናም አብራህ ስለጠፋች የአንተ ቤተሰቦችና የሷ ቤተሰቦች ተግባብተዋል ብንፈልጋችሁም አጣናችሁ   በድንገት ሊና መጣች ሊና መምጣቷን ስንሰማ ቶሎ እሷን ለማግኘት ሄድን አሲ እናትህ ኦያለቀሰች ልጇ ያለበትን ቦታ ስትጠይቃት ደብረ ዘይት እንደሆንክና ቦታውንም ጨምራ ነገረችን ወደዛ ስንመጣ አከራይህ  ጠዋት እንደለቀቅክ ነገረችን ስንደውል ስልክህ አይሰራም ኢብሮ ከዛም ሊና ልታገባ ነው የሚባል ወሬ ስሰማ ላረጋግጥ ሄድኩ ምን ብዬ እንደምጠይቃት ባላውቅም   ዝም ብዬ ወደ ቤቷ ስሄድ በር ላይ የሆነ ወጣት ልጅ ሲወጣ አየሁት ሰላም ካልኩት በኋላ ሊና  ልታገባ ነው ወይ ብዬ ስጠይቀው  ፈገግ እያለ  አዎ ኡመር እባላለሁ   እኔ ነኝ የማገባት አንቺ ምኗ ነሽ ሲለኝ ጓደኛዋ ብዬው ተመለስኩ ኢብሮ ከነገ ወዲያ እሁድ ሊና ታገባለች ስለዚህ ተስፋ ቁረጥ ሀቢቢ   ወደኔ ና ሀቢቢ አሁንም እኮ እወድሀለሁ>

<ሀናን  አንቺ እኛን ለማለያየት የፈጠርሽው ነገር ነው ሊና  ሁሌም የኔ ናት የኔ ፍቅር ትመጣልኛለች እማ እኮ በኔ የሚጨክን አንጀት የላትም  ትመጣለች  ከኔ ውጪ የማንም አትሆንም ደግመሽ እንዳትደውይ>   ስልኩን ጆሮዋ ላይ      ጠረቀመው  አላመንም እኔ አላምንም ሊና ጥላኝ አትሄድም   እሷ የኔ ብቻ ናት መንገድ ላይ እየለፈለፈ ይሄዳል

ሊና ለኢብራሂም ደውላ በሷ ተስፋ እንዲቆርጥ ወሰነች ቀኑን ሙሉ ስታለቅስ ስለዋለች  አይኗን አሟታል የምታፈቅረውን ኢብሮን  ማጣት ለሷም ቢሆን ከባድ ነው  ለቀናት የዘጋችውን ስልኳን ከፍታ ለኢብራሂም መደወል ጀመረች ኢብሮ ሀናን ደግማ የደወለች መስሎት ሊዘጋባት ነው ሲያየው ሊና ናት ቶሎ አንስቶ ወደ ጆሮው አስጠግቶ
 
<እማ ፍቅሬ ሀያቲ ጠፋሽብኝ እኮ እናቴ ናፈቅሽኝ እማ ሊኑዬ>

ድምፁን ስትሰማ አልቻለችም

የኔ ፍቅር አፈቅርሀለሁ እሺ  እያለቀሰች ነው ምታወራው

<እናቴ እኔም እኮ አፈቅርሻለሁ ለምን ታለቅሻለሽ>

የኔ ፍቅር  እንደከሀዲ አሰብከኛ

<የምን ከሀዲ እማ ፍቅሬ መቼ ነው የምትመጪልኝ ፍቅሬ ናፈቅሽኝ ልሞትብሽ እኮ ነው  >

አትጠብቀኝ  በጣም ባፈቅርህም ሌላ ሰው ለማግባት ተገድጃለሁ እሁድ ላገባ ነው

ለቅሶዋ ጨመረ

ከሀናን የሰማው ነገር እውን መሆኑ ገባው እምባው እንደጉድ መፍሰስ ጀመረ ጉልበቱ ተብረከረከ ባለበት ቁጭ አለ

<ሊኑ እኔን ለማን ጥለሽ እናቴ ላንቺ ስል እኮ ከሁሉም ውጭ ሆኛለሁ ፍቅር ስለማውቅ ነው አታረጊውም ይልቅ ቶሎ ነይልኝ ያላንቹ አቅቶኛል

አልችልም ኢብሮዬ ሁሌም አፈቅርሀለሁ ደህና ሁንልኝ

ስልኩን ዘግታ እሪ አለች

ኢብራሂም ራሱን አያቅም ዝም  ብሎ ይሄዳል ወዴት አንደሆነ ግን ለራሱም አላወቀውም


         ከሁለት ቀን በኋላ

የሰርጉ ቀን ደረሰ የኡመር  የደስታ ቀን ሊና ስታለቅስ በአይኗ እምባ  እየጎረፈ እእቅልፍ በአይኗሳይዞር አደረች  ጠዋት ራሷን አሳምናለች  ሰአቱ ሄዷል ሁሉም ተዘገጃጅቷል ኒካሁ ታስሯል ደስተኛ እንደሆነች እያስመሰለች ነው በትልቅ ሰርግ ተሞሸረች ቀለበት ከጣቷ አጠለቀላት እሷም አጠለበችለት  ለብዙ ሰአት አቀፋት ነሺዳው ከዘፈን ጋር ተደበላለቀ የኡመር ቤተሰቧች የሊና ቤተሰቦች ዘመድ አዝማድ ጎረቤት ተሰብስቧል  አሁን  ኡመር ሊናን ይዞበት የሚሄድበት ሰአት ደርሷል

ለሊቱን መጓዝ የጀመረው ኢብሮ አዲስ አበባ ገብቷል እነ ሊና ቤት ጋር ደረሰ የተጣለውን ትልቅ ድንኳን አየ ሀቅ ነው ማለት ነው አስችሏት አገባች  የፖል እንጨት ተደግፎ መመልከት ጀመረ ከቆይታ በኋላ ነሺዳው ቀለጠ ኡመር እጇን ይዟት መኪና ውስጥ ስትገባ አያት እየሳቀች ስለነበረ ፍፁም ደስተኛ ናት ብሎ አሰበ ሲጋራውን ወደ አፉ እየማገ  ሄደ  ዳግመኛ ላይመለስ ወደማያቀው ቦታ ጉዞ ጀመረ...
.
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
  ተ◈ፈ◈ፀ◈መ
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
16.5K viewsꫝꪖꪑꪊᦔ 亗, 17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-31 20:16:36 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
 #ክፍል_ሀያ_ስድስት {➋➏}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...ስልኩን ወደ ልቧ አስጠጋችው   እንጥፋ ነው ያለው ወይስ ተሳስቼ ይሆን   እንዴ የምን መጥፋት ነው ያመዋል ግን እኮ እውነቱን ነው አባዬ አንድ ነገር ይሆናል ካለ ይሆናል ነው ቆይ ኡመርን ላገባ ነው በርግጥ ኡመር ቆንጆ ነው ደስ የሚል አቋም ውብ ፈገግታ አለው የትኛዋም ሴት ለትዳር  የምትመኘው አይነት ወንድ ነው አውቃለሁ ግን እኮ   እኔ አላፈቅረውም የማፈቅረው ኢብሮን ነው   እኔ አልጠፋም  ብለው እኮ እሱም የግዴታ ሀናንን ያገባል  አይ ምን እያልኩ    ነው ቆይ አላህ የጀነት ቁልፍን በእናት እግር ስር አድርጓት ሳለ እናቴን  በስተርጅና ጊዜዋ እኔ ጠፍቼ ላስለቅሳት ነው  ግን እኮ ይሄ  ለፍቅር የሚከፈል ትንሽ ነገር ነው ኢብሮዬ ባይወደኝ ኖሮ እኮ ሀብታሟን ሀናንን ያገባ ነበር   ምንድን ነው የማስበው ቆይ ትምህርቴንስ ልተወው  ነው እሱስ ይሁን ግን እኮ ሀራም ውስጥ እገባለሁ አሁንም ሀራም ውስጥ ተዘፍቄያለሁ  እንተቃቀፋለን ምናምን ቆይ ሊና ምን ሆነሻል እሺ ብሞትስ ኡፍፍ ግን በዚህ እድሜዬ አግብቼ የማፈቅረውን ልጅ ማጣት አልፈልግም    ስልኳን ከፍታ እመጣለሁ  ብላ ላከችለት

ኢብራሂም ስልኩን ወዲያው የተላከለትን መልዕክት ለማየት ከፈተው ሲያየው  እመጣለሁ ይላል  ደስታ ልቡን ወረረው ሀናን ሲል ጠራት ሳሎን ቤት ሆና ስልኳን   አሰየጓረጓረች ነው
ሀኒ..

ነይማ አንዴ
መጣሁ
ስልኳን ዘግታ  ወደ ሱ ክፍል ሄደች 

ኢብሮም እንድትቀመጥ ካደረጋት በኋላ ያው ፍቅር ነገ ኒካህ ልናስር አይደል ደስ ይላል እና የኔ ማለት ያንቺ ያንቺ ማለት የኔ ነው አይደል

ሀናን  ልቧን ደስታ እየሞላው አዎ አላች ፈገግ እንዳለች

እናም ትንሽ ብር እንድትሰጪኝ ፈልጌ ነው

ስንት ብር ነው የምትፈልገው ፍቅር?

አንድ አስር ሺህ ካለሽ ነው ግን አለ ፈራ ብሎ

ቦርሳዬ   ውስጥ ስምንት ሺህ ብር አለ ስመጣ ለአንዳንድ ነገር ይሆናል ብዬ የያዝኩት    ቆይ ላምጣልህ ተነስታ ሄደች


ኢብሮ አሁን ብሩን አዘጋጅቷል ወደ ደብረ ዘይት ነው መሄድ ያሰበው ለሷ አላንስም ብሎ አስቧል የተወሰነ ልብስ አዘጋጅቷል   ቤተሰቦቹን ጥሎ መሄዱ ቢያሳስበውም   ሀናንን ግን በፍፁም ማግባት አይፈልግም   እንዲቀናው በመመኘት ተኛ

በተመሳሳይ ሊናም ልብሷን አዘጋጅታ ጨርሳለች  ቤተሰቦቿ እሷን ላለማስጨነቅ        ጊዜ እንስጣት ብለው ተኝተዋል አባቷ አንድ ልጄ አበባዬ የሚላት አጠራር ድቅን ይልባታል እምባዋ ዝም ብሎ ይፈሳል ግን ወስናለች አላህን ይቅር እንዲላት ተማፅና ወደ አልጋዋ ገባች


የለይልን ሰላት እየሰገደ ነው ኡመር ሀይማኖቱ ላይ ጠንክሯል  ሰላቱን ማገባደድ ላይ ስለ ደረሰ እጆቹን ከፍ አድርጎ
ያቃዲር  ምስጋና ላንተ ይገባ አመሰግንሀለሁ ያረቢ  አንተ ሊና ለኔ ጠቃሚ ከሆነች በሀላሉ ስጠኝ ለኔ ጠቃሚ ካልሆነች አስረሳኝ ሌሎችንም ዱአ ጨምሮ ሰለዋትን በነብያችን ላይ አውርዶ ጋደም አለ


አይነጋ የለምና ነጋ ሊና እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር   ነጋ ገና ለፈጅር አዛን ሳይል ልብሷን ይዛ ካደገችበት ቤቷ ከወላጆቿ ርቃ ለመሄድ ከቤት ወጣች  አይኗ በእምባ እንደተሞላ ከተባለችበት ቦታ ደረሰች...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
    #ክፍል_ሀያ_ሰባት {➋➐}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
25.1K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-24 21:44:20 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
 #ክፍል_ሀያ_አምስት {➋➎}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...ወሬውን ሳታስርሰው ከክፍል ወጣች  ምንም ማለት አቃተው ልክ እንደሷ ተጋደመ  ከቆይታዎች በኋላ አስተማሪ መጣ  ገብቶ ማስተማር ጀመረ አማራጭ ስለሌላት አጠገቡ ተቀመጠች አስተማሪው  የሰጠዋችሁን አሳይመንት ሰራችሁ ሲል ተማሪዎቹን ጠየቀ በጣም አስፈሪ አስተማሪ ነው የሆነ ጥፋት ካየ  ማርክ ይቀንሳል እናም ግማሽ የሚሆኑት  ከሊና ነው የገለበጡት ሁሉም ሰርተዋል ሁሉንም እየዞረ ተቀበለ ኢብራሂም ጋር ደረሰ አንተ ተነስ ተነስ ኢብሮ ብድግ አለ ይሄ ሆስፒታል ወይም መኝታ ቤት አይደለም አሁን አሳይመንትህን ስጠኝ

ኢብሮም: አልሰራሁም
አስተማሪው:ለምን? ኮስተር እያለ
ሊና የዚህን አስተማሪ ፀባይ ታቃለች ኢብሮ ላይ አስተማሪው ሲጮህ አላስቻላትም ቲቸር አሳይመንቱን እኔ ቤት ረስቼው ነው እባክህ ይቅርታ አርግለት ጭራሽ ልሰሪለት ወስደሽ ነው ና ውጣ አስወጣውና ከዚህ በኋላ  በኔ ክፍል እንዳላይህ አስራ አንድን ካላስደገምኩህ  ታያለህ ንቀት ነው ጭራሽ ስሪ ትላታለህ አስፈራርተሀት ነው

ሊና ካንቺ ይሄን አትጠብቅም እየጠቀምሽው መስሎሽ ነው እንዴ እየጎዳሽው እኮ ነው አሁን ውጣ

ኢብሮ ምንም ሳይል ወጣ ደረጃው ላይ ተቀመጠ እናቱን በጣም ነው የሚወዳት ሊያስከፋት አይፈልግም ደሞ ትምህርቱን ጨርሶ  የሚመረቅበትን እለት ሁሌ በጉጉት እንደምትጠብቅ ደጋግማ ነግራዋለች አሁን ግን  "maths " አስተማሪ incomplete  ብሎታል ምን ብሎም እንደሚያስረዳው አያውቅም በዛ ላይ ሊና ተጣልታዋለች ሀናን በዚህ ኒካህ ካላሰርን ትለዋለች በቃ አይምሮው በጣም ተወጥሯል ስድስተኛው ክፍለ ጊዜ አለቀ አስተማሪው የማስተማሪያ እቃዎቹን ሰብስቦ ወጣ ሊና ተከተለችው ቲቸር   አቤት አላት ዞር ብሎ ቲቸር አሳይመንቱን የወሰድኩት የኔ መስሎኝ በስህተት ነው እባክህ ቲቸር ይቅርታ አርግለት ነገ ይሰራል ከፈለክ ሙሉውን ያስረዳል ለተማሪዎች እባክህ

ቲቸር : ልመንሽ ሊና ለነገሩ አንቺ ጎበዝ ተማሪ ነሽ አንቺን አስከፋሁ ማለት አንድ ሀገር ተረካቢ ዜጋን አስከፋሁ ማለት ነው ይቅርታ አርጌለታለሁ

ሊና: በጣም አመሰግናለሁ ቲቸር

ዞር ብላ ኢብሮን አየችው በጣም እንደከፋው ፊቱ ላይ ያስታውቃል   አናዷታል ግን ታፈቅረዋለች ተጠጋችው ወደ ኋላም ሸሸት አለች ግን ደፍራ ሄደች አጠገቡ ቁጭ አለች ዝም አለ ሚያወራው ምንም የለም አስተማሪውን አናግሬዋለሁ ይቅርታ አርጎልሀል    ብላ ነገረችው

አመሰግናለሁ ከዛ ውጪ ቃላት አላወጣም  ፊቱ በጣም እንደከፋው ያስታውቃል እሺ አይክፋህ አጁን ያዘችው ያቃጥላል 

እንዴ ኢብሮ አሞሀል እንዴ  እጇን ወደ ግንባሩ ላከች ትኩሳት አለህ እኮ በጣም ታቃጥላለህ 

መልስ አልሰጣትም ዝም አለ

አስተማሪ ገባ ግን እሷ ግን አላስተዋለችውም ፊቱን ወደሷ አዞረች ሲከፋህ እኮ አልወድም እምባዋ ፈሰሰ

ይሄን ሲያይ ኢብሮ ሊኑ ትወጂኛለሽ?

ሊና:ከምታስበው በላይ  ግን አንተ እኮ ሚስት አለህ
ኢብሮ: ካንቺ ውጭ የምን ሚስት ወደ ደረቱ ስቦ አቀፋት ብሶቷን እልኋን ሁሉ ስቅስቅ ብላ በማልቀስ ገለፀችው  ወዲያው ግን እሺ እሷ ማናት? 
ምን እንደሚላት   ግራ ገባውና እ...እሷ....ማናት መሰለሽ

ሊና አየህ የምር ነው በቃ ወደ ክፍል መግባቷን ትታ ደረጃውን ወርዳ ታች ሄደች


    ሰአቱ ኢሻ ተሰግዶ ቆየት ብሏል  የሊና አባት ጀሚል   ሊናን አሰንድትጠራት ለሚስቱ ለሊና እናት ነግሯታል  ገብታ አንኳኳች ሊና ሊና
ሊና:አቤት እማ
እናቷ:አባትሽ ይፈልግሻል ነይ
ሊና:እሺ

የሊና ወላጆች ተመካክረዋል ስለ እሷና ስለ ኡመር ዛሬ ሊነግሯት ወስነዋል 

ሳሎን ቤታቸው ስለሚቀዘቅዝ ጃኬት ደረብ አርጋ መጥታ ተቀመጠች

አባቷም ሊናዬ መጣሽ የኔ አበባ ዛሬ ምንነግርሽ ወሳኝ ነገር ነው  ምን መሰለሽ ልጄ  የአሁን ልጆች የአላህን ደንብ ጥሰው ሸሪአን አንቋሸው ፍቅረኛ እያሉ በሀራም እየተዘፈቁ ነው ያሉት

ሊና ስለ ኢብሮ አባቷ ያወቀባት መስሏት ድንግጥ አለች ልቧ ትርክክ አለ

አባቷም እና ልጄ አሁን አሁን ሴት ልጅ አባቷ አምጥቶላት ሲድሯት ፋራ ኋላ ቀር ምናምን ይሏታል ቢገባቸው ኋላ ቀር የሆኑት እነሱ ናቸው እና ልጄ አንቺን የሚጠብቅሽ የሚንከባከብሽ አላህን የሚፈራ ሰው ልንድርሽ ነው

ሊናም እ እንዴ አባ ማለት ልጅ እኮ ነኝ ትልቅ ሰው ልትድሩኝ ነው አባ ይሄንማ አታደርግም እንዴ ትምህርቴስ አባ አላማዬስ ሀሳባቸውን እንዲቀየሩ በመለማመጥ እያየቻቸው

አባቷም የምን ትልቅ ሰው ገና ሀያ አመቱ ነው ሶስት አመት ነው የሚበልጥሽ በዛ ላይ አይነ ግቡ ነው ትምህርትሽን እንደውም እንድትማሪ ይፈልጋል ኡመር እኮ ነው ታቂው የለ

አባ ኡመር ጭራሽ ከሩጫ በማይተናነስ አካሄድ ወደ ክፍሏ ገብታ ቆለፈችው  ስልኳን አነሳች  መልዕክት ተልኮላታል ከኢብሮ ነበር ቶሎ አየችው

"ሊና አሰንዳስቀየምኩሽ አውቃለሁ ያቺ ያየሻት ልጅ ሀናን ትባላለች ልጅ እያለው ልቤን ታምሜ እናቷ ናት ብዙ ገንዘብ ከፍላ ያዳነችኝ እና ሀናን እና እኔ ስናድግ እንደምንጋባ ከተወሰነ ድፍን አምስት አመት ሞላው እኔ ስለፍቅር የምጨነቅ ሰው አልነበርኩም በቃ ሳድግ  እሷን አገባለሁ ብዬ ነበር የማስበው ሀናን ታስጠላኛለች ባህሪዋ ይቀፋል በጣም ወሬኛ ቆንጆ ነኝ ባይ ናት ሊኑ ባላሰብኩት ሰአት አፈቀርኩሽ ወላሂ በጣም ነው የምወድሽ ሀናን ኒካህ ካላሰርን እያለች እየጨቀጨቀችኝ ነው እምቢ ማለት አልችልም እማዬም አባዬም ፈርደዋል ለሷ ሊና የእውነት ካፈቀርሽኝ  እንጥፋ ነገ ከሌሊቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ  ዋናው አስፓልት ጋር እጠብቅሻለሁ ልብስሽን ያዢ ለፍቅር መስዋዕትነት ክፈይ በጣም አፈቅርሻለሁ የኔ እናት "
.
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
   #ክፍል_ሀያ_ስድስት {➋❻}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
41.1K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ