Get Mystery Box with random crypto!

ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianislamic — ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianislamic — ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianislamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 110.65K
የሰርጥ መግለጫ

በቅንነት ዩቲብ ቻናላችን ሰብስክራፕ ያድርጉ
https://bit.ly/4044MQR

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-11-24 20:58:25 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
   #ክፍል_ሀያ_አራት {➋➍}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷


...ያሰው ደግሞ አንተ ነህ ለልጄ ምታስፈልጋት ልጄን መዳር የምፈልገው ለአንተ ነው

ኡመር በሰማው ነገር ተደናግጧል አፉ ተሳስሮበታል ውስጡን ደስታና ፍርሀት ወሮታል ምክኒያቱም ከልቡ ነው የሚያፈቅራት   ነገር ግን ፈርቷል ደሞ እሱ የጠየቀ ቢመስላትስ ግን ፍቅረኛዋስ

ኡመሬ የት ሄድክ አለው የሊና አባት

ኧረ ጋሼ እዚሁ ነኝ አለ ኡመር የሙሀባ አምላክ ሌላ እድል የሰጠው መስሎ ታየው ማፍቀር ከባድ ነው ለመርሳት ብትሞክርም ይከብዳል አላህ ሊናን ለሱ የፃፈለት መስሎ ታየው ከሷ ጋር ተጋብቶ ልጆችን ወልዶ የሚኖርበት ቀን ቅርብ መስሎ ታየው ከሷ ጋር የሚያሳልፋቸው የፍቅር ጊዜያት  የሚያምር ወንድ ልጅ ወልዳለት ባባ እያለ ሲያጫውተው የሚወዳት ሊና ፈገግ ስትልለት እጇን በኩራት ይዟት ሲራመድ ሁሌ ለስራ ሲወጣ ስትስመው የሱ ብቻ ስትሆን ብዙ ጊዜን ከሷ ጋር ሲያሳልፍ ማሰብ ጀመረ 

ኡመሬ ላኢላሀኢለላህ ደህና ነህ ግን እንዴ ምነው አጠፋሁ እንዴ

ኡመርም ኧረ ጋሼ አላጠፋህም ግን እሷ ባትስማማስ ማለት እሺ ካላለችስ

አባቷም አይ አንተን የመሰለ ልጅማ እምቢ አትልም  በል በደንብ አስብበት

ኡመርም አፈር እያለ እ እሺ መርሀባ


የምሳ ሰአት ተደውሎ ተማሪዎች ወደየክፍሉ እየገቡ ነው ግማሾቹ ተማሪዎች

"ቆይ ምሳ ሰአት እረፍቱ ከመቼው አለቀ አሁን ደሞ ልንገባ ነው ኤጭ" ሲሉ

ከፊሎቹ ደግሞ

"ወይኔ አሳይመንት እኮ አልሰራውም!  ልቅጣው እንዴ ወይስ እንዴት ይሻላል"  ይላሉ

ኢብራሂም ደግሞ እስካሁን ክፍል ያልተመለሰችውን ላይብረሪ ያለችውን ፍቅሩን ያኮረፈችውን ሊናን ለመታረቅ ቦታዋ ላይ ተቀምጦ እየጠበቃት ነው  እስካሁን አልመጣችም

ሊና ልታጠናም ብትሞክር አልጠና ብሏታል ይኸው እንደፈጠጠች ሰአቱ አለቀ  ፍቅር የሚባል የማይረባ ነገር ውስጥ ገብታ ልቧ በመሰበሩ ከፍቷታል የምታነበው መፅሀፍ  ላይ እምባዎቿ ጠብ... ጠብ... ብለው ቅርፅ ሰሩ  በቅፅበት ወደ ገጠር ስትሄድ አያቷ ያለቻት ትዝ አላት

"ሊናዬ ፍቅር ሀያል ነገር ነው ፍቅር ማለት ራስን መስጠት ነው ፍቅር ማለት መታመን ነው የምትወደጂውን ሰው ከራስሽ በላይ መውደድ ነው ፍቅር ማለት  ይቅርባይነት ነው ፍቅር ማለት የሚያስከፋ, የሚያስኮርፍ, የሚያናድድ, የሚያስቅ ስሜት አለው ድብልቅልቅ ያለ ማዕበል ፍቅር እስከ ጀነት የሚዘልቅ ታላቅ ነገር ነው"

አያቴ ውሸቷን ነበር ማለት ታዲያ ኢብሮ ፍቅረኛ እያለው ነው የቀረበኝ አፈቅርሻለሁ የሚለኝ እ ያኔ እንደዛ ካላንቺ አልኖርም ያለኝ ውሸት ነበር ማለት ነው : : አያቴ ልክ አልነበርሽም ተነስታ መፅሀፉንም ሳትመልስ ከላይብረሪው ወጣች  ደረጃውን በቀስታ ወጥታ ክፍሏ ደረሰች ስትገባ ወንበሯ ላይ ተቀምጧል ሌላ ወንበር ላይ መቀመጥ ፈለገች ግን ሁሉም ተማሪዎች የሚቀመጡባቸው ናቸው አማራጭ ስላጣች ሄዳ ተቀመጠች አስተማሪ እስኪ መጣ ጋደም አለች

ኢብሮ ጉሮሮውን አፅድቶ ሊና እንደምትሰሚኝ አቃለሁ በጣም አፈቅርሻለሁ የእውነት ላንቺ ያለኝ ፍቅር የእውነት ነው

ኢብራሂም ነገሮች ተገልብጠውበታል እድል ፊቷን አዙራበታለች  ምንም ሳትለው ወሬውን ሳታስጨርሰው ከክፍል ወጣች...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
    #ክፍል_ሀያ_አምስት {➋➎}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
24.6K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-18 22:12:46 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
   #ክፍል_ሀያ_ሶስት {➋➌}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

አዎ ምነው ኒካህ እንሰር በቃ የምፈልገው እሱን ነው እሱን ማድረግ አልችልም በጣም ይቅርታ ኧረ ባክህ ብሎ ነገር የለም የምሄደው ሰኞ ነው ዛሬ ደግሞ እሮብ ነው እሁድ እነግራቸዋለሁ ለእነ ማማ ተረዳከኸኝ ሀናን አልተረዳውሽም ለምን ትቸኩያለሽ? አንተ የኔ መሆንህን ማረጋገጥ ስለሚኖርብኝ አሁን እንደገባህ ተስፋ አደርጋለሁ ቻው በቃ ወደክፍሌ መግባት ይኖርብኛል የምሰራው ስራ አለ


አቶ ኢብራሂም እንዴት አደርክ
እንዴት አደርሽ ሀናን
ትምህርት ቤት ልትሄድ ነው?
መሆኑ ነው ጠብቀኝ አብረን እንሄዳለን በር ድረስ ልሸኝህ
አይሆንም አርፈሽ ተቀመጪ ኡፍ አንተ ደሞ  የምትወደውን ሰማያዊ ቀሚስ በጥቁር ሂጃብ ጠምጥማ ወጣች እጅህን ልይዝህ እፈልጋለሁ የሱን ፍቃደኝነት ሳታረጋግጥ  እጁን ያዘችው መንገድ ጀመሩ

አንዳንድ ሁኔታዎች ጥሩ ነገርን ይዘው ይመጣሉ በተቃራኒው አንዳንድ ሁኔታዎች መጥፎ እድልን ያመጣሉ እጁን ይዛው ትምህርት ቤቱ በር ጋር እንደደረሱ ከሊና ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ  ታላቅ እህት ብቻ ነው እንዳለው የነገራት ከሚባለው በላይ ደንግጧል ሁሉም ነገር ጨልሞበታል ምን ማድረግ እንዳለበት አያውቅም

ሊና ፍጥጥ ብላ ቀረች ሀናንም ኧረ እናቱ አይንሽን ከባሌ ላይ ንቀይ ሌላ እዳ
ኦ...በጣም ይቅርታ ወደ ውስጥ ገባች

ኢብሮ በጣም ተናዷል ፊቱ በአንድ ጊዜ ተቀየረ አሁን ምንድን የው የሚላት መቼስ እሷንም ቲያትር እየሰራው ነው አይላት ቻው በቃ በፍጥነት ወደ ትምህርት ቤት ገባ ክፍል እንደደረሰም ሊና አንድ ጊዜ ስሚኝ በአላህ ላስረዳሽ

ኢብራሂም ለአላህ ብለህ ተወኝ ሰላሜን ስጠኝ ከዚህ በኋላ በፍፁም አጠገቤ እንዳላይህ እኔን አርሳኝ...
ቦርሳዋን ይዛ ወጣች
እሺ ወዴት ነሽ?   መልስ የለም

ሄለው ሰላሙ አለይኩም
ወአለይኩም ሰላም ጋሼ
ኡመሬ እንዴት ነህ
አልሃምዱሊላህ አንተስ?

አልሃምዱሊላህ  ፈልጌህ ነበር ተገናኝተን እናውራ?
ምነው ጋሼ ችግር አለ
ኧረ የለም አላህ ችግርን ያርቅልን ለሌላ ነገር ነው
መርሀባ ከዝሁር በኋላ ይሁን?
አዎ ልጄ  ልክ ሰባት ሰአት ተኩል  ዘይነባ ሻይ ቤት እንገናኝ
መርሀባ

ሰአቱ እንደደረሰ ቀጠሮውን አክብሮ ተገኘ የሊና አባት ዘግየት ብሎ መጣ በማርፈዱ ይቅርታን ጠይቆ ወደ ወጉ ገቡ
ምን መሰለህ ኡመርዬ አንድ ልጅ ሲኖርህ ተስፋህ ሁሉ ልጅህ ላይ ይሆናል የኔ ተስፋ ሊና ናት በጣም የምወዳት አንድ ልጄ ናት ስሜቷን  እንኳን መግለፅ አትችልም  በጣም ዝምተኛ ናት እናም የሚረዳት የሚያወራት የሚንከባከባት ሰው ያስፈልጋታል ያሰው ደግሞ አንተ ነህ...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_ሀያ_አራት {➋➍}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
20.9K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-18 21:59:37 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
   #ክፍል_ሀያ_ሁለት {➋➋}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ኡመር ነው ደነገጠች   ልክ እንዳያት ልቡ ክፍል አለ አሁንም ይወዳታል   ለዚህ ነበር መምጣት ያልፈለገው ግባ ብላ መንገድ ለቀቀችለት  ምንም ሳይላት  ገባ በጣም እየደበረው ነው ሰላም ካሉት በኋላ  ለመብላት ተቀመጡ ምግቡን ወደድከው 

አዎ በጣም አሪፍ ነው እማ በጣም ሞያ አለሽ
አታስብ ለሞያው ስታገባም ሽር አርጌ ነው የምድርህ
ነገሩን በፈገግታ ሊዘጋው አስቦ ነበር ግን የሊና አባት አልተፋታውም
ኡመሬ ግን ስራ አለህ ቤትም አለህ መኪናም አለህ  ለምን ማግባት አልፈለክም
ባባ አሁን አደለም ከሶስት ወር በኋላ ወደ ጀርመን እሄዳለሁ ከሶስት አመት በኋላ ስመጣ  ያኔ አስብበታለሁ ማሻ አላህ አላህ ያሳካልህ   ሊና አንገቷን እንደደፋች ነው እሱ በመሀል ቀጥ እያለ ያያታል



ኢብሮዬ ወክ አርገን እንመለስ መሽቷል እኮ ሀናን እና ቢመሽስ ደስ ይላል እኮ
እኔ ግን ደስ አይለኝም ይቅርታ
እሺ የምናወራው ነገር አለ
ምንደን ነው?
ያው እኔና  አንተ መጋባታችን አይቀርም እኔና አንተ ቤተሰብ ነን አይደል  ስለዚህ እኔ ኒካህ እንድናስር እፈልጋለሁ??
ምን...

.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_ሀያ_ሶስት {➋➌}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
18.0K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-23 20:43:10 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_ሀያ_አንድ {➋➊}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...ገና እንደደረሰ ክፍል  ውስጥ አገኛት

ሊኑ ብድግ አለች  ኢብሮ አይን አይኑን በስስት እያየች
ወይዬ ...
ደና አደርክ
አጠገቧ ቁጭ ብሎ   አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ  
እየጠበኩህ ነው...
 
አንድን ሰው ካፈቀርሽው ምንም ነገር ቢፈጠር ጥለሽው ትሄጃለሽ?

መልስ ሳትሰጠው አስተማሪ ገባ አብረው ተቀምጠው መማር ጀመሩ

ከመስጂድ እየወጣ ነው የሊናን አባት አገኛቸው
አሰላሙ አለይኩም ኡመርዬ
ወአለይኩም ሰላም ጋሼ እንዴት ኖት
አይ ይሄን አንቱታ ተወው ብዬህ የለ
አፍወን እንዴት ነህ ጋሼ
ደህና ነኝ አንተስ ጠፋህ እኮ...
አዎ ያው ስራም ቢዚ ስለሚያረገኝ ነው
መስጂድ ብዙ ጊዜ አይሀለሁ ግን ተገጣጥመን አናቅም ወይ ሱና ስትሰግድ  እደርሳለሁ እኔ ስሰግድ ደሞ ትወጣለህ ብቻ ብዙ ቀን አይሀለሁ ማሻ አላህ ልጄ ካንተ ብዙ እጠብቃለሁ

መርሀባ ጋሼ  

ደሞ ዛሬ እራት እኛ ጋር ነህ እንገናኛለን መሄድ አለብኝ

ኧረ ጋሼ...  ሳያስጨርሰው አቶ ጀሚል ወደ መኪናው ገባ ኡመራም መኪናውን አስነስቶ ጉዞውን ጀመረ
ልሂድ አልሂድ ኡፍ እኔ ሊናን ማግኘት አልፈልግም እሷን መርሳት ነው የምፈልገው ግን ጋሼን ማስቀየም አልፈልግም  አሁን ላይ ማንም ሰው በኔ እንዲከፋ አልፈልግም  ብቻ አላህ ያውቃል...

ሰአቱ 9:30 ሆኗል ተማሪዎች የመውጫውን በር አጣበውታል   ሁለቱ ፍቅረኛሞችም ራቅ ብለው እያወሩ ነው  አሁን ተገናኝተው አሁን ሰአቱ ያልቅባቸዋል  ብዙ መንገድን ሸኛት ወደ እቅፉ ወሸቃት ለረጅም ሰአት ተቃቀፉ ዳግም  የማይገናኙ  ነው የሚመስሉት  ቻው በቃ ተለያዩ እሱም ደስ ብሎት ነጠር ነጠር እያለ ሄደ

መግሪብ ተሰግዶ ካለቀ ሀያ ደቂቃ አልፏል ሁለት ሰአት ሊሆን ነው


ቆይ ማሚ ማነው ሚመጣው ዛሬ ይሄ ሁሉ ጥሩ ምግብ ልዩ እንግዳ ባለውለታችን የሊና እናት ነበረች ልጇ የጠየቀቻትን ጥያቄ እየመለሰች

ኢላሂ አንተ ጠብቀኝ...
ያአላህ እርዳኝ  ሊናን እንዳላያት አርግልኝ አንተ እርዳኝ
አሚን

  ኡመር ነበር


መኪናውን በቀስታ እያሽከረከረ ወደ ሊና መኖሪያ ቤት አመራ ከመኪናው ወርዶ በሩን በዝግታ አንኳኳ

ሊና በር ክፈቺ

እሺ እማዬ  እንግዳውን ለማየት ጓግታ ከፈተች ኡመር ነው ደነገጠች...
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_ሀያ_ሁለት {➋➋}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
35.9K views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-22 23:29:57 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_ሀያ {⓴}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...ሊና ማናት ሊና ማናት ከአልጋው  
  ላይ ተስፈንጥሮ ተነሳ በሩን ቶሎ ከፍቶ እባክሽ ሀኑ ተረጋጊ ሁሉንም አስረዳሻለሁ ምኑን ነው የምታስረዳኝ እ እየጮኸች ነው እንዴት እንደሚያረጋጋት አያውቅም   ሀኑ ፕሊስ የወደፊት ሚስቴ ከሆንሽ ልትረጂኝ ይገባል አሁን    ቁጭ በይና እናውራ
ጥሩ በደንብ እናውራ ሰተት  ብላ ወደክፍሉ ገባች አልጋው ላይ ቁጭ አለች ምን እንደሚላት   አያውቅም በሩን ዘግቶ ተመለሰ የሱ መኝታ ቤት ከሌሎቹ ቤተሰቦቹ ትንሽ ስለሚርቅ እንጂ ጩኸቷን ይሰሙ ነበር ገና ከመቀመጡ ሊና ማናት ምን መሰለሽ ሀናን የመጣለትን ለመናገር አሰበ  የሆነ ቲያትር እየሰራ ነው እና ልምምድ ስናረግ ነበር የምን ቲያትር በቅርቡ ነው የተጀመረው ርዕሱ ፈተና ነው አላምንህም   እህ እኔን ያላመንሽ ማንን ልታምኚ ነው  ቆይ
እሺ ማማን ልጠይቃት
እ አልነገርኳቸውም ሰርፕራይዝ ላረጋቸው ነው ያሰብኩት  እ
እምባዋ ወረደ በርግጥ ልጆች ነን ግን እኔ ስለምወድህ ነው ደረቱ ላይ ተለጠፈች         ያወራው ነገር   አልተዋጠላትም ብልጥ ናት ነገሮችን አርቃ ታስባለች ብዙ የውጪ ፊልሞችን ታያለች ፎቶ እንነሳ አለችው



አዎ እንነሳ
እሺ አማራጭ የለውም
በኔ ባንቺ?
በኔ
አንገቱን ዝቅ እና ከፍ እያረገ መስማማቱን ገለፀላት 
ስልኳን ቪዲዮ ላይ አደረገችው ሰላም የቲያትር ፍቅረኛው ሊና ይሄ ቪዲዮ ላንቺ  ነው ኢብሮ ደነገጠ ሊያወራ   ሲል ዝም እንዲል ምልክት ሰጠችው  አማራጭ የለውም የሚሻለው ዝም ቢል ነው
ሀናን ቀጠለች እና ኢብሮዬ የወደፊት ባሌ ነው እጮኛዬ በጣም ነው የምንዋደደው እንፋቀራለን አደራ ባሌን ጠብቂልኝ ደሞ   ለሰርጋችን ሚዜ ነሽ አደል ፍቅር ወደሱ ዞረች እ አዎ

በቃ አሁን ይሄን ቪዲዬ ትልክላታለህ
እ ይሄማ አይሆንም
ለምን?
እሷ ጠቅጠቅ ስልክ ነው ያላት  በተን
እ እሺ በቃ ትንሽ አውርታው ሄደች ወደ ክፍሏ

ደሞ እንዳትቆይ ትናፍቀኛለህ ግማሽ መንገድ ሸኝታው ተመለሰች ሀናን ነበረች
  ኢብሮም እሺ በቃ ቻው ወደ ትምህርት ቤት እየሄደ ነው ፍቅሩን እስኪያገኛት ቸኩላል ገና እንደደረሸ ክፍል ውስጥ አገኛት ሊኑ...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_ሀያ_አንድ {➋➊}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
29.4K views20:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-21 22:28:49 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ {⓳}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

... እጇን ያዛትና ተጠጋት በጣም ተጠጋት ሳማት አላመነችም ደንግጣለች እሱም እራሱን  እየተጠራጠረ ነው ዛሬ ለሱ ልዩ ቀን ነው ድንዝዝ ብላ ቆማለች አይኖቾ እሱን እሱን ያያሉ ሊኑዬ እህ አቀፋት ወደራሱ ወሸቃት  ትንሽ አረጋጋትና    ከክፍል ወጡ   ሊኑ ማታ በስልክ አናወራም??

እናወራለን እሺ ማታ ጠብቂኝ እደውልልሻለሁ
ስልኬን ታውቀዋለህ
የሚስቴ ስልክ ይጠፋብኛል ኢብሮ ነበር የተወሰነ ሸኝቷት ተመለሰ

ሊና ደስታዋ ወደር አልነበረውም ሚስቴ አላት ሳማት ግን አላህን እያስከፋሁ እኮ ነው አለች ልቧ ግን አላህ ይሄን እውነተኛ ፍቅር ይረዳል ኡፍፍፍ ብላ ካለችበት ሀሳብ ወጣች

ሰፈር እንደደረሰ ረሚዝ ተቀምጧል ከመቼው መጣህ እኔ ሚስት የለኝ ማንን እሸኛለሁ

የምን ሚስት?

አይደል ኢባ አሁን እውነቱን ንገረኝ ምንሼ ግልፅ አርግልኝ

እሺ በቃ ሁሉንም ሊነግረው አሰበ በቃ እንደማፈቅራት ነገረችኝ እሷም ታፈቅረኛለች እኔም አለች   ከዛ ምን አይነት ሴጣን እንደሰፈረብኝ አላቅም ከንፈሯን ሳምኳት አቀፍኳት

ረሚዝ ምን ምን ኢብሮ ነህ ግን   "wow amazing "  ያበደ ነው ያጣፍጥልህ
በል በቃ ብሮ ልግባ  ማዘር ናፍቃኛለች ምላሿን ሳይሰማ ወደ ቤቱ ገባ ጫማውን አውልቆ ደብተሩን እንዳንጠለጠለ ከሳሎኑ ገባ
እናቱ  ተቀምጣለች  ሰላም እማ ሁሌም ሲገባ ይስማታል ጉንጯን ሳማትና ቁጭ አለ ዛሬ ደሞ ቆየህ ኢባዬ   ፈገግ እያለ ቆየው እንዴ ምን ተገኘ ፈገግታው ምንም እማ ደሞ ሰርፕራይዝ አለህ ቆይ መክሰስ ላምጣልህ

ሀናን ከተዘጋጀላት ክፍል ልብሷን ቀይራ  ወጣች ኢባዬ ሄዳ ተጠመጠመችበት   አይኑ ተቀያየረ አሰጁ ተንቀጠቀጠ እጁን በግዴታ ወደ ወገቧ ሰደደ ጉንጩን ደጋግማ ሳመችው ለምን አትደውልልኝም ግን አልናፍቅህም ፍቅር ግን ተቀይሜሀለሁ ቴክስቴንም አትመልስም እ  ቆይ ዝምተኛ ነኝ ለማለት ነው መልስ አይሰጣትም ዝም ብሎ ይሰማታል

ኢብራሂም ሲወለድ በልጅነቱ ከባድ እና አስፈር የሆነ  የልብ case አጋጥሞት ነበር ቤተሰቦቹ የተጠየቁት በርካታ ብር ነበር አቅማቸው ስለማይችል የመሞቻውን ቀን በሚጠባበቁበት እለት  ነበር  የእናቱ ጓደኛ የሀናን እናት ሰኒያ ካለችበት ከአውስትራሊያ ገንዘቡን ልካ ያሳደገችው እናቷ እና አባቷ ሚኖሩት አስራ ሁለተኛ ክፍል ነው እሷ አስረኛ ክፍል ናት የምትኖረው አክስቷ ጋር ነው ሀናን ከአንድ አመት በፊት እናቷን ለመጠየቅ አውስታራሊያ በነበረችበት ጊዜ ኢብሮን እንደምታፈቅረውና ከሱ ውጪ ማግባት እንደማትፈልግ ነግራታለች ቤተሰብም ተስማምቷል የሚጠባበቁት ትምህርታቸውን የሚጨርሱበትን ቀን ነው    ከሷ ጋር መጋባቱ የማይቀር መሆኑን ያውቃል እናቱን ማስከፋት አይፈልግም ግን አሁን ላይ የሚያፈቅራት ፍቅረኛ አለችው አንድም ቀን አፈቅራለሁ ብሎ ስለማያስብ በቃ ትልቅ ስሆን ሀናንን  ነው የማገባት ብሎ ነበር የሚያስበው አሁን ግን ፍቅር ረቶታል ሀናንም ፍቅር ነካ ነካ አረገችው እ አቤት ተቀምጠን እናውራ አልናፈቅኩህም እንዴ ኧረ  እሺ ቁጭ በል ማውራት ጀመሩ እሱ ልቡ ሊና ጋር ነው   ሰአቱ ሲመሽ ሁሉም ሊተኙ ወደ ክፍላቸው ሄዱ ሶስት ሰአት ተኩል ሆኗል ለሊና ደወለ

ሄለው ሊኑ
ማን ልበል ድምፁን አውቃዋለች ግን አውቃ ነበር

እ ባልሽ ነኛ
እ ኢብሮዬ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እየተፈራሩ ካወሩ በኋላ ሁለቱም በደንብ ማውራት ጀመሩ 

ሀናን እንቅልፍ አልወስዳት ብሏል ኢብሮ ካልተኛ አብሬው ልሁንና እመለሳለሁ ብላ አሰበች ና ሄደች በር ላይ ድምፅ ይሰማታል ዝግ ያለ ድምፅ ዘደ በሩ ተለጠፈች

ኢብሮ የተወሰነ ካወሩ በኋላ መተኛት እንዳለባት ነገረችው እሱም እሺ እወድሀለሁ በይኝ እ ፈራች በናትሽ    እ እሺ
አፈቅርሀለሁ

እኔም አፈቅርሻለሁ  ደና እደሪልኝ የኔ ሊና

እኔም አፈቅርሻለሁ የኔ ሊና የሚለው የኢብሮ ድምፅ ጆሮዋ ውስጥ ጥልቅ አለ በሩን በሀይል ደበደበች ማናት ሊና ማናት ሊና...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_ሀያ {⓴}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
21.9K views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-20 19:38:19 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_አስራ_ስምንት {⓲}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...እንደተያያዙ ወደ ክፍል ዘለቁ  ተማሪዎቹ ያስተዋሉት እጅ ለእጅ መያያዛቸውን ነው ድምፃቸውን ከፍ አርገው ሳቁ ብዙዎቹ ነባር ተማሪዎች በመሆናቸው ሊናን ያውቋታል ሲበዛ አይናፋር ናት የሰልፍ ስነስርአት ላይ ሽልማት ልትሸለም ወደ መድረክ ስትጠራ እንኳን አቶጣም አይና አፋር ናት ከዚህ በላይ የሚያስገርመው ደግሞ በአሁኑ አመት ትምህርት ቤት ውስጥ  የገባው ወንዳወንድ ከሚባሉት ወንዶች መሀከል የሚመደበው ቆንጂዬውና የሷ ተመሣሣይ ያለው ኢብሮ ነው የሁለቱ እጅ ለእጅ መያያዝ ያሳቃቸው ለዚሁ ነበር አስተማሪው እጅ ለእጅ መያያዛቸውን አላስተዋለም ሊና አንቺም ማርፈድ ጀመርሽ ነግሬሻለሁ ዋ ሂጂ አሁን ተቀመጪ ሁለቱም የሷ ቦታ ላይ ተቀመጡ ኢብሮ የያዛት በቀኝ እጅ ነው እሷ ደግሞ በግራዋ እሱ ለመፃፍ ፈፅሞ አይመቸውም እጇን ግን ሊለቅ አልፈለገም ሊናም በቃ እንፃፍ አለችውና እጇን ከእጁ ለየችው ሁለቱም አልቧቸዋል እጃቸውን ፅፈው ጨረሱ በየመሀሉ ይተያያሉ ግን አያወሩም

የኢብሮ እናት ስልኳ  እየጠራ ነው አነሳችውና ሄለው አለች ሄለው የሚል  የወጣት ልጅ ድምፅ ተሰማ አቤት አለች እናቱ ልጅቷም እንዴት ነሽ እቴቴ ሀናን ነኝ   እንዴ እንዴ ከተቀመጠችበት ተነሳች ሀናንዬ የኔ ቆንጆ እንዴት ነሽልኝ ደህና ነኝ አንቺስ እኔም በጣም ደህና ነኝ ጥፍት አልሽ እኮ እናትሽም ውጪ ከሄደች በኋላ ብዙ አናወራም አባትሽም ያው ስራ ይበዛበታል 
አዎ እቴቴ ያው ከትምህርት በኋላም ስልጠና አለኝ እኔም ቢዚ ነኝ ለዛ ነው   ኢብሮ ሰላም ነው ቤተሰብስ?

አይ የኢብሮ እናት ፈገግ እያለች ቅድሚያ የምትጠይቂው የወደፊት ባልሽን ነዋ ሀሀ ምን ላርግ ልክ ነሽ የኔ ልጅ

እቴቴ እየመጣሁ ነው ትምህርት ቤት ለአንድ ሳምንት ትምህርት የለም እናንተ ጋር ላሳልፍ አስቤያለሁ ማሻ አላህ ልጄ እና ስንት ሰአት ትደርሻለሽ??
አይ እሱ ሰርፕራይዝ ነው
እሺ እሺ እጠብቅሻለሁ ራስሽን ጠብቂ ስልኩ ተዘጋ


ወደ ቤት የመሄጃ ሰአት ደርሷል ኢብሮ ራሱን አደፋፍሯል ክፍል ውስጥ የቀሩት እሱ እና ሊና ብቻ ናቸው

እ ሊና የሚያየው መሬት መሬት ነው አፈቅርሻለሁ በግድ ያወጣው ቃል ነበር እሷ ደነገጠች ድንዝዝ አለች እኔም ኢብሮ
እጇን ያዛትና ተጠጋት....
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ {⓳}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
17.5K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-17 21:33:11 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_አስራ_ሰባት {⓱}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ወሬያቸውን ለመጀመር  ተዘጋጁ  ዝም ተባብለዋል ሊና እሱ ያወራ ዘንድ  በጉጉት እየጠበቀች ነው  እሱም ቆይ አታወራም እንዴ  እጃቸውን እንደተያያዙ ነው   አልተላቀቁም አሁንም ጥብቅ አርጎ ይዟታል  ግን አያወሩም የፍርሀት አለም  


ኡመር ቤቱ ውስጥ ጋደም ብሏል ስራ አልገባም በቃ ራሱን እየወቀሰ ነው ኡመር እንዲህ አልነበርክም አላህ ይቀጣሀል አንድ ተራ ሴት ወደህ እንዲህ ትሆናለህ ሀ ማቆም አለብህ ከዚህ በኋላ ቆንጂየው ወጣቱ ጠንካራው ኡመር ይመለሳል አዎ እጆቹን አቆላለፋቸውና በሀሳብ ርቆ ሄደ 

ረሚዝ ቆይ ኢብራ የት ሄዶ ነው ዛሬ እህ ላይብረሪ ገብቶ ይሁን ቢሆንስ ሳይነግረኝ ለማንኛውም እዚሁ ልጠብቀው


ሰአቱ አለቀ ምሳ ሰአት ተደወለ ምንም ሳያወሩ እሱ እሷን ሲጠብቅ እሷም በተመሳሳይ እሱን ስትጠብቅ ሰአቱ ሄደ የደውል ጥሪው ሲያሰማቸው ተነሱ   አሁንም ዝም እንደተባባሉ ነው እጃቸውን አልተላቀቁም   የሆነ የሚያምር መድረክ ላይ  ቤተሰብ ተሰብስቦ ብዙ ሰው ኗራ ውዱ ባሏ ኢብሮ እጇን ይዟት የሙሽራ ቀሚሷን አርጋ  እያጨበጨቡላት  ስታልፍ ሊና ይሄን   እያሰበች ክፍል ደረሰች   እንደ አጋጣሚ ሆኖ  አስተማሪ ገብቷል ደሞ ፈተና ነው እየፈሩ ለመግባት ወሰኑ መያያዛቸውን ረስተውታል እንደተያያዙ ወደ ክፍል ዘለቁ
..
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
    #ክፍል_አስራ_ስምንት {⓲}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
19.0K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-17 21:28:37 ┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_አስራ_ስድስት {⓰}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...ማውራት አለብን
ስለምን?

...ስለ እኛ. ስለ እኔና ስላንቺ
ፈርታለች ልቧ እየመታ ነው ግን አብራው  መሆን ትፈልጋለች::  ግን ምናልባት እሱ አብረን መሆን አንችልም ሊለኝ ቢሆንስ
አይ :አይ ሊሆን አይችልም ግን

እኔን አቁመሺኝ የት ሄድሽ?

ጥያቃው ከሀሳቧ አነቃትና እሺ አናውራ... ፈርታለች እሱም ቢሆን ማታ ሲለማመድ ነበር ምክኒያቱም እሱም ማውራት አይደፍርም በዚያ ላይ ሴት ይፈራል
መቼ??
እኔንጃ መቼ ይሁን?? ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች

ከቻልሽ አሁን ምሳ ሰአት ስለሆነ

እ እሺ ቁርጧን ማወቅ እንዳለባት ወስናለች
በቃ እንሂድ ታች ብንወርድ ለማውራትም ጥሩ ይመቻል አይመስልሽም
ልክ ነህ እንውረድ ፈርቷል ቆመ እጇን ሊይዛት አስቦ ነበር ግን ፈራ ኧረ ተው ከራሱ ጋር ለደቂቃዎች ታግሎ እጇን ያዛት ጥብቅ አርጎ ነው የያዛት  የሆነ የምትሄድበት ወይም ከሰማይ የሆነ መልዐክ ወርዶ የሚነጥቀው ነው የሚመስለው  በትምህርት ቤቱ ውስጥ ብዙ couple አሉ እጅ ለእጅ መያያዝ የሚካበድ አይደለም ሊና እጇን ከመያዙ በላይ ጥብቅ ማድረጉ ገርሟታል እሷም ያዘችው እንደተያያዙ ከክፍል ወጡ ከክፍላቸው ፊት ለፊት ያለውን ደረጃ መውረድ ሲጀምሩ  የክፍላቸው ተማሪ የሆኑት አብረሀምና ኢዘዲን ድምፃቸውን ከፍ አርገው መሳቅ ጀመሩሀ...ሀ...ሀሀ   አብረሀም አስከትሎ በስመአብ "ድስት ግጣሙን አያጣም " ይሉሀል ይሄ ነው ዋው ግን ይደነቃል  ኢዘዲን የአብረሀምን ንግግር ሳያስጨርስ ጣልቃ በመግባት ኧረ ያምራል ማዘር ትሙት ያሳካላችሁ ውለዱ ክበዱ አለ አብረሀም በእግሩ መንገድ ዘግቶባቸዋል  አስከትሎም አይ ኢዙ የምን መውለድ  "ምንም ቢዋደዱ ቢመስሉ ጨረቃ የተማሪ ፎንቃ መጨረሻው ጭቃ" ሲባል አልሰማህም ኢብሮ ተናደደ አሳልፈኝ ሰውዬ  ባላሳልፍህስ? አሳይሀለዋ ብሎ ሲጠጋው አሳለፈው እንደተያያዙ ወረዱ ሊናና ኢብሮ የሚሰማቸው ስሜት ተመሳሳይ ነው ፍርሀት ግን ደስ የሚል ነገር...
ካሰቡት ቦታ ተቀመጡና ወሬያቸውን ለመጀመር ተዘጋጁ...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
    #ክፍል_አስራ_ሰባት {⓱}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
20.8K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-09 13:04:23
#Update

በአጠቃላይ በ2015 ከተፈተኑ ተማሪዎች ውስጥ 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡት።

ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች
29.9K viewsedited  10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ