Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓           '. #አይናፋሯ_ሊና '.              ✎ፀሐፊ፦ | ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_አስራ_ስምንት {⓲}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

...እንደተያያዙ ወደ ክፍል ዘለቁ  ተማሪዎቹ ያስተዋሉት እጅ ለእጅ መያያዛቸውን ነው ድምፃቸውን ከፍ አርገው ሳቁ ብዙዎቹ ነባር ተማሪዎች በመሆናቸው ሊናን ያውቋታል ሲበዛ አይናፋር ናት የሰልፍ ስነስርአት ላይ ሽልማት ልትሸለም ወደ መድረክ ስትጠራ እንኳን አቶጣም አይና አፋር ናት ከዚህ በላይ የሚያስገርመው ደግሞ በአሁኑ አመት ትምህርት ቤት ውስጥ  የገባው ወንዳወንድ ከሚባሉት ወንዶች መሀከል የሚመደበው ቆንጂዬውና የሷ ተመሣሣይ ያለው ኢብሮ ነው የሁለቱ እጅ ለእጅ መያያዝ ያሳቃቸው ለዚሁ ነበር አስተማሪው እጅ ለእጅ መያያዛቸውን አላስተዋለም ሊና አንቺም ማርፈድ ጀመርሽ ነግሬሻለሁ ዋ ሂጂ አሁን ተቀመጪ ሁለቱም የሷ ቦታ ላይ ተቀመጡ ኢብሮ የያዛት በቀኝ እጅ ነው እሷ ደግሞ በግራዋ እሱ ለመፃፍ ፈፅሞ አይመቸውም እጇን ግን ሊለቅ አልፈለገም ሊናም በቃ እንፃፍ አለችውና እጇን ከእጁ ለየችው ሁለቱም አልቧቸዋል እጃቸውን ፅፈው ጨረሱ በየመሀሉ ይተያያሉ ግን አያወሩም

የኢብሮ እናት ስልኳ  እየጠራ ነው አነሳችውና ሄለው አለች ሄለው የሚል  የወጣት ልጅ ድምፅ ተሰማ አቤት አለች እናቱ ልጅቷም እንዴት ነሽ እቴቴ ሀናን ነኝ   እንዴ እንዴ ከተቀመጠችበት ተነሳች ሀናንዬ የኔ ቆንጆ እንዴት ነሽልኝ ደህና ነኝ አንቺስ እኔም በጣም ደህና ነኝ ጥፍት አልሽ እኮ እናትሽም ውጪ ከሄደች በኋላ ብዙ አናወራም አባትሽም ያው ስራ ይበዛበታል 
አዎ እቴቴ ያው ከትምህርት በኋላም ስልጠና አለኝ እኔም ቢዚ ነኝ ለዛ ነው   ኢብሮ ሰላም ነው ቤተሰብስ?

አይ የኢብሮ እናት ፈገግ እያለች ቅድሚያ የምትጠይቂው የወደፊት ባልሽን ነዋ ሀሀ ምን ላርግ ልክ ነሽ የኔ ልጅ

እቴቴ እየመጣሁ ነው ትምህርት ቤት ለአንድ ሳምንት ትምህርት የለም እናንተ ጋር ላሳልፍ አስቤያለሁ ማሻ አላህ ልጄ እና ስንት ሰአት ትደርሻለሽ??
አይ እሱ ሰርፕራይዝ ነው
እሺ እሺ እጠብቅሻለሁ ራስሽን ጠብቂ ስልኩ ተዘጋ


ወደ ቤት የመሄጃ ሰአት ደርሷል ኢብሮ ራሱን አደፋፍሯል ክፍል ውስጥ የቀሩት እሱ እና ሊና ብቻ ናቸው

እ ሊና የሚያየው መሬት መሬት ነው አፈቅርሻለሁ በግድ ያወጣው ቃል ነበር እሷ ደነገጠች ድንዝዝ አለች እኔም ኢብሮ
እጇን ያዛትና ተጠጋት....
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ {⓳}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤