Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓           '. #አይናፋሯ_ሊና '.              ✎ፀሐፊ፦ | ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
          ". #አይናፋሯ_ሊና ".
             ✎ፀሐፊ፦ ሩቂ
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
          
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
.  በ @Ethiopianislamic የቀረበ .
        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
  #ክፍል_አስራ_ዘጠኝ {⓳}
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

... እጇን ያዛትና ተጠጋት በጣም ተጠጋት ሳማት አላመነችም ደንግጣለች እሱም እራሱን  እየተጠራጠረ ነው ዛሬ ለሱ ልዩ ቀን ነው ድንዝዝ ብላ ቆማለች አይኖቾ እሱን እሱን ያያሉ ሊኑዬ እህ አቀፋት ወደራሱ ወሸቃት  ትንሽ አረጋጋትና    ከክፍል ወጡ   ሊኑ ማታ በስልክ አናወራም??

እናወራለን እሺ ማታ ጠብቂኝ እደውልልሻለሁ
ስልኬን ታውቀዋለህ
የሚስቴ ስልክ ይጠፋብኛል ኢብሮ ነበር የተወሰነ ሸኝቷት ተመለሰ

ሊና ደስታዋ ወደር አልነበረውም ሚስቴ አላት ሳማት ግን አላህን እያስከፋሁ እኮ ነው አለች ልቧ ግን አላህ ይሄን እውነተኛ ፍቅር ይረዳል ኡፍፍፍ ብላ ካለችበት ሀሳብ ወጣች

ሰፈር እንደደረሰ ረሚዝ ተቀምጧል ከመቼው መጣህ እኔ ሚስት የለኝ ማንን እሸኛለሁ

የምን ሚስት?

አይደል ኢባ አሁን እውነቱን ንገረኝ ምንሼ ግልፅ አርግልኝ

እሺ በቃ ሁሉንም ሊነግረው አሰበ በቃ እንደማፈቅራት ነገረችኝ እሷም ታፈቅረኛለች እኔም አለች   ከዛ ምን አይነት ሴጣን እንደሰፈረብኝ አላቅም ከንፈሯን ሳምኳት አቀፍኳት

ረሚዝ ምን ምን ኢብሮ ነህ ግን   "wow amazing "  ያበደ ነው ያጣፍጥልህ
በል በቃ ብሮ ልግባ  ማዘር ናፍቃኛለች ምላሿን ሳይሰማ ወደ ቤቱ ገባ ጫማውን አውልቆ ደብተሩን እንዳንጠለጠለ ከሳሎኑ ገባ
እናቱ  ተቀምጣለች  ሰላም እማ ሁሌም ሲገባ ይስማታል ጉንጯን ሳማትና ቁጭ አለ ዛሬ ደሞ ቆየህ ኢባዬ   ፈገግ እያለ ቆየው እንዴ ምን ተገኘ ፈገግታው ምንም እማ ደሞ ሰርፕራይዝ አለህ ቆይ መክሰስ ላምጣልህ

ሀናን ከተዘጋጀላት ክፍል ልብሷን ቀይራ  ወጣች ኢባዬ ሄዳ ተጠመጠመችበት   አይኑ ተቀያየረ አሰጁ ተንቀጠቀጠ እጁን በግዴታ ወደ ወገቧ ሰደደ ጉንጩን ደጋግማ ሳመችው ለምን አትደውልልኝም ግን አልናፍቅህም ፍቅር ግን ተቀይሜሀለሁ ቴክስቴንም አትመልስም እ  ቆይ ዝምተኛ ነኝ ለማለት ነው መልስ አይሰጣትም ዝም ብሎ ይሰማታል

ኢብራሂም ሲወለድ በልጅነቱ ከባድ እና አስፈር የሆነ  የልብ case አጋጥሞት ነበር ቤተሰቦቹ የተጠየቁት በርካታ ብር ነበር አቅማቸው ስለማይችል የመሞቻውን ቀን በሚጠባበቁበት እለት  ነበር  የእናቱ ጓደኛ የሀናን እናት ሰኒያ ካለችበት ከአውስትራሊያ ገንዘቡን ልካ ያሳደገችው እናቷ እና አባቷ ሚኖሩት አስራ ሁለተኛ ክፍል ነው እሷ አስረኛ ክፍል ናት የምትኖረው አክስቷ ጋር ነው ሀናን ከአንድ አመት በፊት እናቷን ለመጠየቅ አውስታራሊያ በነበረችበት ጊዜ ኢብሮን እንደምታፈቅረውና ከሱ ውጪ ማግባት እንደማትፈልግ ነግራታለች ቤተሰብም ተስማምቷል የሚጠባበቁት ትምህርታቸውን የሚጨርሱበትን ቀን ነው    ከሷ ጋር መጋባቱ የማይቀር መሆኑን ያውቃል እናቱን ማስከፋት አይፈልግም ግን አሁን ላይ የሚያፈቅራት ፍቅረኛ አለችው አንድም ቀን አፈቅራለሁ ብሎ ስለማያስብ በቃ ትልቅ ስሆን ሀናንን  ነው የማገባት ብሎ ነበር የሚያስበው አሁን ግን ፍቅር ረቶታል ሀናንም ፍቅር ነካ ነካ አረገችው እ አቤት ተቀምጠን እናውራ አልናፈቅኩህም እንዴ ኧረ  እሺ ቁጭ በል ማውራት ጀመሩ እሱ ልቡ ሊና ጋር ነው   ሰአቱ ሲመሽ ሁሉም ሊተኙ ወደ ክፍላቸው ሄዱ ሶስት ሰአት ተኩል ሆኗል ለሊና ደወለ

ሄለው ሊኑ
ማን ልበል ድምፁን አውቃዋለች ግን አውቃ ነበር

እ ባልሽ ነኛ
እ ኢብሮዬ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እየተፈራሩ ካወሩ በኋላ ሁለቱም በደንብ ማውራት ጀመሩ 

ሀናን እንቅልፍ አልወስዳት ብሏል ኢብሮ ካልተኛ አብሬው ልሁንና እመለሳለሁ ብላ አሰበች ና ሄደች በር ላይ ድምፅ ይሰማታል ዝግ ያለ ድምፅ ዘደ በሩ ተለጠፈች

ኢብሮ የተወሰነ ካወሩ በኋላ መተኛት እንዳለባት ነገረችው እሱም እሺ እወድሀለሁ በይኝ እ ፈራች በናትሽ    እ እሺ
አፈቅርሀለሁ

እኔም አፈቅርሻለሁ  ደና እደሪልኝ የኔ ሊና

እኔም አፈቅርሻለሁ የኔ ሊና የሚለው የኢብሮ ድምፅ ጆሮዋ ውስጥ ጥልቅ አለ በሩን በሀይል ደበደበች ማናት ሊና ማናት ሊና...
.
.
.
⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊⇊
╬╬═════════════╬╬
     #ክፍል_ሀያ {⓴}
           .....ይቀጥላል......
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤
        @Ethiopianislamic
        @Ethiopianislamic
╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤