Get Mystery Box with random crypto!

#የልብ_ነገር #ክፍል_አንድ (ፉአድ ሙና) *** እንደ ፀሀይ ግባት ... ውበት ማከማቻ፣ እንባ | ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

#የልብ_ነገር
#ክፍል_አንድ
(ፉአድ ሙና)
***

እንደ ፀሀይ ግባት ...
ውበት ማከማቻ፣
እንባ እያፈሰሱ፣ የሚያምሩ አይኖቿ፣

አመት እንዳልበላ ...
እንደተራበ ሰው፣
እየሮጠች መጣች፣ ከንፈሬን ልትጎርሰው!

***

ልክ ከአይኗ እንደገባሁ ሻንጣዋን የመግፋት አቅም አጣች። አይኔ በእንባ ተሸፍኗል። በእንባዬ ውስጥ ፍቅሬ ስትንደረደር ይታየኛል። በእጆቼ የያዝኩትን አበባ አንጠልጥዬ እኔም ወደሷ መሮጤን ተያያዝኩት። ወንድ አልነበርኩ እንዴ? ሊያውም ቆፍጣናው ፉአድ! እንባ የአይኖቹን አጥር ያለፈቃዱ የማይነቀንቁበት ደረቅ! አልቻልኩም .... ራሴን መቆጣጠር ከበደኝ።

አጠገቧ ደረስኩ ... ከሽሽጌ ገባች። ናፍቄያታለሁ። የሸሚዜን ቁልፎች ፈትታ ገላዬን በእጆቿ ለመንካት ትሞክራለች። ትኩስ ከንፈሮቿ በትኩስ እንባዋ ተለውሰው .... አቻ ከንፈሬን ይመጠምጣሉ።

«ይኸው ሻንጣሽ የኔ እመቤት!» የአየር መንገዱ ሰራተኛ ቱታውን እንደለበሰ ሻንጣዋን ገፍቶ እኛ  ጋር መድረሱ ነበር። መሳሳማችንን ገትተን ... ኪሴን ዳብሼ፣ አመሰገንነውና ሻንጣዎቿን እየገፋሁ ወደ መኪናችን መሄድ ጀመርን። በየመሀሉ እየቆምን እንተቃቀፋለን።

ቦታው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ነው። ናፋቂ አይኖች ከናፍቆታቸው ጋር የሚገናኙበት ... አፍቃሪ ልቦች ከውዳቸው ጋር የሚለያዩበት፤ ትዕይንተ ብዙ ስፍራ! ሻንጣዎቿን መኪናው ላይ ጭነን መኪና ውስጥ እንደገባን፤ እንደ አዲስ መላቀስ ጀመርን።

የመታወቂያ ስሟ ፈሪሀ ሁሴን፤ በእኔ አንደበት የለመደችው ደግሞ ፌሪ፣ የኔዋ፣ ፌሪ ፈሪ! የዛሬ አራት አመት ነበር ዛሬ የተገናኘንበት ቦታ ቆሜ ሳላምንበት የሸኘኋት! ለሁለት ዓመት የሄደችበት የትምህርት ጉዞ ተለጥጦ አራት አመት ተቀጣሁ!

«አንተ Airport ስንሳሳም ብዙ ሰው አየን እንዴ?»
«የለም ሁሉም አይነስውር ነበሩ።»
«I was out of my mind! ካንተ ውጪ ማንም አይታየኝም ነበር።»
«It's okay የኔ አበባ! ግን UK እኮ ምግብ ያለ ነበር የሚመስለኝ!»
«ምነው? ከሳሁ እንዴ?»
«ከንፈሬን እኮ በላሽኝ!»
ሳቀች። ሳቋ ያምራል! ጥርሶቿ ሲከፈቱ በቀጥታ ልብን ይይዛሉ! በጥርሶቿና በልብ መካከል ያለው ግንኙነት ቢጠና ደስ ይለኛል። በሀገረ እንግሊዝ የተማረችበት ዩኒቨርሲቲ ይህን አለማጥናቱ ይገርመኛል።

ቤት እንደደረስን መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። ሰራተኛዋ ከመመገቢያ ጠረጴዛው ላይ የደረደረቻቸውን ምግቦች ቆማ ታስተካክላለች።
«Fami ሻወር እየገባሁ ነው .... መጣሁልህ!»
«እዛው እደሪ አሉሽ ደግሞ! እነ Mom ይመጣሉ!»
«Yours? Or mine?»
«ያንቺማ ለቅሶ አለ መሰለኝ እዛ አዳማ! አልተነሱም። ተረጋግታችሁ ነገ ኑ ብያቸዋለሁ! The road is not safe!»
«Who the hell died on my arrival day? He should be jealous!» ትስቃለች።
«አንቺ ክፉ! አርፈሽ ታጠቢ እስኪ!»
«ለምን አትገባም ከእኔ ጋር? አብረን እንታጠብ ... Join me!»
«ወዳንቺ ስመጣ ነው የታጠብኩት!»
«This one is special ሀቢቢ!» ሳቋ ሲስረቀረቅ ይሰማኛል።
የሌላውን ጊዜ ፉአድ ብሆን ኖሮ ሳትጋብዘኝ እየተንደረደርኩ እንደምገባ አውቀዋለሁ። ዛሬ ግን ፈራሁ! ሙሉ ራቁቴን ፊቷ መቆም አስፈራኝ። ገላዬ አፍ አውጥቶ የሚናገርብኝ ይመስለኛል። ጨንቆኛል።

የኔ ልዕልት ... ታጥባ ጨረሰች። መኝታ ክፍል ልብሷን እየቀየረች «ሀቢቢ አንዴ ና እስኪ!» አለች።
ወደ መኝታ ክፍል ስገባ አይኔን አጥበረበረኝ። ሙሉ ብርሀን ከፊቴ ቆሟል። የማያንፀባርቅ የሰውነቷ ክፍል የለም። ፈገግ ብላ አየችኝ። የፈገግታዋን ትርጉም እኔም እሷም እናውቀዋለን።

«ድጋሚ ልትታጠቢ ነው?» ሳቄ መጣ!
«ውሀ አለ አይደል! ለምን ሺህ ጊዜ አልታጠብም!»
የፈለገችውን ብሆንላት ደስ ይለኝ ነበር። ግን ደግሞ እፈራለሁ። ገላዬን አላምነውም። ከቂያማ ቀድሞ ለማውራት የሚሽቀዳደም፤ ጉዴን የሚናገር እየመሰለኝ ነው።
«የኔ ውድ ... አራት አመት ነው የናፈቅኩሽ! ናፍቆቴን በዚህ መልኩ አይደለም መወጣት የምፈልገው! እማዬ እና አባ እየመጡ ነው። አንደኛውን ስንረጋጋ ይሻላል እሺ!»
የታችኛውን ከንፈሯን ወደፊት ለጠጠችው። አቅፌ አባበልኳትና ልብሷን መልበስ ጀመረች።

የመመለሻ ትኬቷ ከተቆረጠ ጀምሮ ውስጤ ሰላም አልነበረውም። ለእሷ ያለኝ ፍቅር ጥልቅ ነው። ከብዙ ማሰላሰል በኋላ ልጋፈጠው ወሰንኩ። ልቤ እንደማትጨክንብኝ ‘ምሎልኛል። ቢሆንም መልካም ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን መላ ቀየስኩ!

የናፈቃትን የሀገሯን ምግብ በልታ ... የናፈቋትን አግኝታ ... ያለፏትን ሀዘንና ደስታ ጠይቃ ሁለት ሳምንታት እንዳለፉ ራሴን ነፃ ለማውጣት ወሰንኩ።

«ፌሪዬ»
«ፋሚዬ»
«እወድሻለሁ»
«እኔ ደግሞ እጥፉን!»
«ዛሬ የሆነ ነገር ልነግርሽ እፈልጋለሁ!»
«ምንድነው?»
«ይቅር ልትይኝ ....   ቃል ግቢልኝ!»
«ምንድነው?»
«ቃል ግቢልኝ በአላህ!»
«እሺ ቃል እገባለሁ!»
«ፌሪዬ ... »
«ፋሚዬ ...»
«ሁለተኛ ሚስት አግብቼያለሁ ... »
«ምን?» ፊቷ ፍም መሰለ።

ይቀጥላል ...
.
ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic