Get Mystery Box with random crypto!

ሰላቱ እንደተጠናቀቀ ወደምንወደው ካፌ ጎራ ብለን መጨዋወት ጀመርን። «ስማማ ሰሚሬ .... ግን ጀ | ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

ሰላቱ እንደተጠናቀቀ ወደምንወደው ካፌ ጎራ ብለን መጨዋወት ጀመርን።
«ስማማ ሰሚሬ .... ግን ጀመዓ ሰላትንና ሴትን እኩል ማዘውተር እንዴት ቻልክ? እኔ እኮ ሚስቴ ብቻ ሆና እንኳን አልቻልኩም።»
«አህሜ ፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄ አትጠይቀኝ ባክህ!»
«ምነው?»
«ነገ ደግሞ ይነዝንዘኝ እንዴ እሱን ይዞ!»
«ሴት እንደምታጫውት ኢማሙም እኮ ያውቃሉ!» አለ አህሜ እየሳቀ።
«በነገራችን ላይ የኢማሙን ልጅ አጫውቼያት ስመለስ በእሳቸው ሰግጃለሁ። Family reunion ነው የሆነብኝ!»
ከሚያወራው ውስጥ ግማሹ ሳክስ እንደሆነ ስለምናውቅ እንደቀልድ ልናልፈው ነበር።
«በነገራችን ላይ የኢማሙ ልጅን ምናምን ያልኳችሁ የምሬን ነው። እኔ የእሳቸው ልጅ መሆኗን ያወቅኩት በኋላ ነው።»
«ወሬ ቀይር በአላህ! ደሞ ኮንፊሰደንስህ እኮ ከወንጀል ያዳንካት ነው የሚመስለው!» አህሜ አቋረጠው።
«እዚ ሼባ ፊት ይብራብን እያልኩህ ..... አየሀ!»
«እሺ ስለ ሰላቱ ንገረኝ እንዴት ነው አብረህ የምታስኬደው?»
«የምቀጥርበትን ሰዓት ቀድሜ ነው የማመቻቸው .... ነገሩ ካለቀ በኋላ ይቀፉሀል እኮ ለተወሰነ ቀን .... በጣም ካላፈቀርካት እንደዛ ነው።»
«ስለዚህ?»
«ወዲያው ትቻቸው ወደ መስጂድ ነው የምመጣው!  ይደብሩኛል። ከዛ ተውበት አደርጋለሁ! ከዛ ደግሞ ከትንሽ ቀን በኋላ ነገሩ ሊደገም ይችላል።»
«ምን ታደርጋላችሁ አብራችሁ? ስልህ ስቴፑን ፈልጌ ነው።»
«ተው አህሜ ይጀንብብናል።» ሳቁን ለቀቀው።
«እኔ መስጂድ መምጣት ከብዶኛል። እና ያንተን ጥበብ እፈልገዋለሁ።»
«በቃ ቤትህ መጥቶ ያስተምርህ! አሁን ላወራችሁት ራሱ ኡዱ ማድረጌ ነው!» አህሜ አቋረጠን።
«አያሳስብም ደሞ ለፉዬ! ከዚህ በኋላ በወንጀል ጉዳዮች የሰላተል ጀመዓ አማካሪው ነኝ!» ሳቁን ለቀቀው።
.
ይቀጥላል ....
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic